ወቅታዊ መግለጫ‼️

‹‹ወደ አማራ ክልል የሚመጡ የየትኛውም አካባቢ ተማሪዎች የአማራ #ልጆች ናቸው፡፡››

‹‹የግለሰቦችን ችግር #በግለሰብ ደረጃ መጨረስ ሲገባ ለጋ ወጣቶችን #መጠቀሚያ ማድረግ ተቀባይነት የለውም፡፡›› ርዕሰ መስተዳድር አቶ
ገዱ አንዳርጋቸው
.
.
.
ሃገራችን በለውጥ እንቅስቃሴ በምትገኝበት በዚህ ወቅት አልፎ አልፎ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተፈጠረው ችግር ተማሪዎች የህይዎት እና የአካል ጎዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚህም የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን የገለፁት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የግለሰቦች ግጭት ወደ ቡድን ወይም አካባቢ ወስዶ በተደራጀ አግባብ ዕርስ በዕርስ ተማሪዎችን #ማጋጨት በምንም መንገድ #ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል፡፡

ችግሩ የተለየ የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው እና አሁን እየተፈጠረ ያለው አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ያላስደሰታቸው አካላት በታቀደ መንገድ የሚያራምዱት የግጭት ሴራ ነው ያሉት አቶ ገዱ ተማሪዎችም #ስሜታዊ በመሆን የሌሎች አጀንዳ ፈፃሚዎች ሳይሆኑ ችግር ፈጣሪዎችን
አጋልጠው እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

ከመላ ሃገሪቱ የሚመጡ ተማሪዎችና ልጆቻቸውን አምነው የሚልኩ ወላጆች ዓላማቸው ግልፅ ነው፤ እሱም ተምሮ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ፡፡ ይህንን የተማሪዎችና የወላጆች ዓላማ ስኬታማ ለማድረግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የእውቀት እንጅ የግጭት ማዕከል መሆን ስለሌለባቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዘላቂ ሰላም በጋራ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ወደ አማራ ክልል የሚመጡ የየትኛውም አካባቢ ተማሪዎች የአማራ ልጆች ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የአካባቢው ማህበረሰብ ተማሪዎቹን ሲቀበል ያሳየውን ጨዋነት እና እንግዳ ተቀባይነት እስከመጨረሻው ማሳየት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ግጭት በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ካሉ የዩኒቨርሲቲ #አመራር አካላት፣ የክልል መስተዳድሮችና ከፊዴራል መንግስት ጋር በተማሪዎቹ #ደህንነት ዙሪያ እየተነጋገርን ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia