ኦነግ‼️

የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦነግ አመራሮች ያደረጉትን #ስምምነት መሰረት በማድረግ ወደ ሃገር ገብተው ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 1 ሺ154
የኦነግ ጦር አባላት እንደ #የፍላጎታቸው ወደ ስራ ሊሰማሩ ነው።

የኦሮሚያ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ እንዳሳወቀው፤ ስልጠና ሲወስዱ ከነበሩት የኦነግ ጦር አባላት ውስጥ 700ዎቹ በራሳቸው ፍላጎት የኦሮሚያን ፖሊስ እንቀላቀላለን በማለታቸው ግንዛቤ እንዲያገኙ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ እንዲገቡ ተድርገዋል።

የአጭር ጊዜ ስልጠና በመውሰድም የኦሮሚያን ፖሊስ የሚቀላቀሉ ይሆናል። የቀሩትም እንደየፍላጎታቸው በግል ስራ፣ በመንግስት ስራ እና የኦነግ ፖለቲካ አባል በመሆን ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia