#update የርብ ግድብ ምረቃ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ በርብ ያደረጉት ንግግር፦

• ዛሬ ጠዋት ከጣና ጀምረን ደንቢያ አካባቢና ሊቦከምከም አካባቢ እምቦጭ የሚባል ብቻየን ካልኖርኩ የሚል ጠላት ጎብኝተናል፡፡ የገባኝ ሚስጥር እንደ ጣልያን ርብ ላይ እንደሚሸነፍ ተረድቻለሁ፡፡

• ጠላቶቻችን በዚህች ቅድስት ሀገር ላይ ጦርነት ቢያውጁም አሸንፈው አያውቁም፡፡ እምቦጭንም እናሸንፈዋለን፡፡

• ኢትዮጰያ የአፍሪካ ውኃ ማማ ካስባሏት አካባቢዎች አንዱ ይህ አካባቢ ነው፡፡ ነገር ግን ውኃ፣ ጉልበትና መሬት እያለ አቀናጅተን አልተጠቀምንም፡፡

• እርሻን እንደ ቅርስ ባለማዘመን ከሚተቹ ሀገራት አንዷ ነች፡፡ እያሻሻልን መሄድ ሲገባን ዛሬም አርሶ አደሮች ብዙ ጉልበት እያፈሰሱ ትንሽ ምርት የሚያገኙ ናቸው፡፡

• ይህንን የእልህ የሆነ ዝናብ፣ ፀሐይ፣ እምቦጭ በጋራ እንደምናሸንፍ እንድንችል በጋራ እንድንቆም ይገባል፡፡ አሁን ለኢትዮጵያ የሚያዋጣው መደመር ብቻ ነው፡፡ እንደ እምቦጭ ሁሉም ለእኔ ከሆነ ተያይዞ መጥፋት ነው፡፡

• በግድቡ አገዳ፣ ፍራፍሬ ፣ አትክልት አሳ፣ እያመረቱ መጠቀም ይገባል፡፡ይህንን ግድብ እውን ለማድረግ ሕይወት ጭምር የከፈላችሁ ናችሁና በአግባቡ መጠቀም ይችላል፡፡ የጎንደርን ውብ አካባቢ ቱሪስቶች እንዲጎበኙ ለማድረግ ሁላችንም እንሥራ፡፡

• ስትፈጠርም የዳቦ ቅርጫት የሆነች ኢትዮጵያን ሀብቷን አቀናጅተን እንሥራ፡፡መስኖ ከሀገራዊ ኢኮኖሚው አራት በመቶ ብቻ ነው የሸፈነው፤ ስለዚህ ይህንን ማሻሻል አለብን፡፡ አሁን ተቋቋመው የመስኖ ኮሚሽን ግድብ ጀምረው የሚጨርሱ ተቋራጮችም ስላሉ ድርሻውን ይወጣል፡፡

• የአካባቢው አርሶ አደሮች የሚያስፈልጋችሁን የቴክኖሎጂና የሙያ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

• በእምቦጭ ላይ በምናደርገው ዘመቻ በድጋሜ እንገናኛለን፤ እመቦጭ መሆን አያስፈልግም፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
ፎቶ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia