#update ራያ አላማጣ⬇️


በራያ አላማጣ የማንነት ጥያቄ አንስተው አደባባይ ከወጡ ሰዎች መሀከል ሶስቱ #መሞታቸው ተሰማ፡፡

የራያ አላማጣ የከተማው አስተዳደር አስተዳዳሪ አቶ ሀብቶም ወረታ ዛሬ ለሸገር FM 102.1 እንደተናገሩት፣ የማንነት ጥያቄን መሰረት በማድረግ በተነሳው ተቃውሞ በፀጥታ ሀይሉና በነዋሪው መሀል #ግጭት መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

ትናንትና እሁድ የማንነት ጥያቄ እና የመልካም አስተዳደር ጎድሏል ያሉ የራያ አላማጣ ወጣቶች በከተማዋ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

ለወራት የዘለቀው የራያ የማንነት ጥያቄ ጉዳይን በቅጡ ለመፍታት ለምን ከሚመለከታቸው ጋር አልተወያያችሁምና አልፈታችሁም ያልናቸው የከተማው አስተዳዳሪ ጥያቄው የጥቂቶች ነው ብለዋል፡፡

የራያ አላማጣ የማንነት ጥያቄ ላለፉት ወራት በሰፊው ከመደመጥ አንስቶ `የራያን ህዝብ እናድን” የሚሉ ዘመቻዎችና ሰልፈኞች በርክተዋል፡፡

በትናንትናው እለት በራያ አላማጣ ከተማ ለሰልፍ የወጡ ወጣቶች የሞቱት ከክልሉ ልዩ ሀይል ጋር በተፈጠረው ግጭት መሆኑንም አቶ ሀብቶም ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia