ለሚመለከታቹ‼️

(ከፂዮን ግርማ)

ለመምከር አይደለም-የተሰማችኝን ለማካፈል ነው። ዕድሜ ብዙ ነገር ያስተምራል። በዕድሜያችን ላይ የሚጨምረው ሰዓትና የተጓዝንበት ሂደት ለሚቀጥለው ጊዜ #ስህተት እንዳንሠራ ሊታደገን ይገባል።

ጤናማ ባልሆነ ውድድርና #በብሽሽቅ ውስጥ፤ ከተወዳዳሪውና ከተበሻሻቂው ውጪ በማያውቀው ነገር በፅኑ #የሚጎዳ አካል (ሕዝብ) አለ።

ከችግርና ችጋር ጋር እየታገለ ምንም በማያውቀው ነገር ድንገት መከራ የሚወርድበትን አካል ለመታደግ የምታስፈልገው ነገር “ትንሽ” ናት "ጨዋ" #ቃላትን መጠቀም።

ስድብ፣ ማዋረድና ማንቋሸሽ ከታከለበት ውድድርና በብሽሽቅ ወጥቶ በሐሳብና በጉዳይ ላይ ብቻ ያተኮረ አስተያየት መስጠት። #በጨዋ ቋንቋ እየታገዙ የሐሳብ ድርና ማግን መሸመን ከልካይ አይኖረውም።

አንደበታችን ለበጎ፣ ጣቶቻችንን ደግሞ #ለመልካም ሥራ እናውላቸው። ተመልሰን #ለማንመጣባት ምድር መጥፎ ነገር ጥለን አንለፍ። #ጤናማ የአደባባይ ላይ ክርክርና የውይይት ባህልን እናዳብር፣ #ቴክኖሎጂን ከመጥፎ ነገር ይልቅ ለጥሩ ነገር እንጠቀም። እጆቻችንን #ለስድብ አናታትራቸው።

#ሼር - በፌስቡክ ገፃቹ ላይ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia