#update አብዲ ኢሌ⬇️

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋና ሌሎች ዞኖች በጅምላ ጭፍጨፋ፣ የብሄርና ሀይማኖት ግጭት ቅስቀሳ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ ሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር #አብዲ_መሀመድን ጨምሮ 4 ግለሰቦች ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት ለተጨማሪ ምርመራ የ10 ቀን #ፈቀደ፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን አብዲ መሀመድ፣ ወ/ሮ ረሂማ መሀመድ፣ አብዱረዛቅ ሳኒ እና ኮሚሽነር ፈረሃን ባሂር ላይ ፍርዱ ቤቱ በፈቀደው 14 ቀን የምርመራ ጊዜ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አስታውቋል፡፡

በዚሁ ወቅት የ41 ምስክሮች ቃል መቀበሉንና የተዘረፈውን ንብረት ግምት እንዱሁም #በሄጎ እና በልዩ ሀይሉ የተጨፈጨፉ ሰዎች አስክሬን
ምርመራ ውጤት መሰብሰቡም ፖሊስ ገልጿል፡፡

የፍርድ ቤት ማዘዣ የወጣባቸውን ግብራበሮች መያዝ፣ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ የተቀበሩ ሰዎች ማንነትን መለየት፣ የአስገድዶ መድፈር የተፈጸመባቸውን ሴቶች መለየት፣ የሕክምና መስረጃ ማሰባሰብ፣ የተደበቀ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ማሰባሰብ፣ የምስክር ቃል ለመቀበል 14 ቀን እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በራሳቸውና አማካኝነት ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ምርመራ ጊዜ ተገቢነት የለውም፣ የፖሊስ አቀራረብ በዝርዝር አይደለም፣ ተገቢውን ህክምና እያገኘን አይደለም፣ በአያያዝም በኩል ችግር በመኖሩ ፍ/ቤቱ የምርመራ መዝገቡ ሊለያይ ይገባል የሚሉ ሁኔታዎችን አንስተዋል᎓᎓

መርማሪ ፖሊሰ ምርመራው በዝርዝር ነው የቀረበው ተጠርጣሪዎች በክልሉ በነበረው የብሔርና የሃይማኖት ግጭት ጅምላ ጭፍጨፋ የዜጎች መፈናቀልና የንብረት ውድመት በቅንጅት ነው የሰሩት ብሏል᎓᎓ምርመራው ተነጣጥሎ ሊታይ አይገባውም᎓᎓

ለምሳሌ የሴቶችና የህፃናት ጉዳዮች ሃላፊ ወይዘሮ #ራሂማ_መሃመድና የዲያስፖራ ቢሮ ሃላፊው #አብዱልራዛቅ_ሳኒ ግጭቱን በፌስ ቡክ ሲቀሰቅሱ ነበር ብሏል መርማሪ ቡድኑ᎓᎓

የፖሊስ ኮሚሽነር የነበረው ፈሪሃን ጣሂር ሂጎዎችን በራሱ ጊዜ መሳሪያ አስታጥቆ ሰው ያስጨረሰ ልዩ ሃይሎችንም ለጥፋት ሲያነሳሳ ግጭቱን በመኪና እየዞረ ያጠናከረ ብሎም በርካታ ታራሚዎችን ከማረሚያ አስወጥቶ ያስረሸነ ነው ብሏል ቡድኑ᎓᎓ ምርመራው ሰፊ በመሆኑ ዋስትናውን ተቃውሟል᎓᎓

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia