#update ኦብነግ🤝የሱማሌ ክልል⬆️

የሱማሌ ክልል መንግስትና የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) #ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል።

ስምምነቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጉዳዮች የሚያካትት ነው፦

▪️ኦብነግ በክልሉ በነፃነት እንዲንቀሳቀስ የክልሉ መንግስት #ድጋፍ ያደርጋል።

▪️የክልሉ መንግስት የኦብነግ ወታደሮች ድጋፍ የሚያገኙበትን እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉበትን ሁኔታ ያመቻቻል።

▪️የሱማሌ ክልል ሆነ ኦብነግ ከትንኮሳ እና ከጠብ አጫሪነት ድርጊት ይቆጠባሉ።

▪️ለክልሉ ሰላም በጋራ ይሰራሉ።

▪️ኦብነግ ከፌድራል መንግስት ጋር እንዲወያይ የክልሉ መንግስት የድጋፍና የማስተባበር ስራ ይሰራል።

▪️የክልሉ መንግስት ኦብነግ እንደድርጅት በክልሉ ውስጥ ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲንቀሳቅስ እገዛ ያደርጋል።

▪️የክልሉ መንግስት ከሁለት አመት በኋላ ምርጫ እንዲደረግ በቁርጠኝነት ይሰራል።

📌ከላይ በተደረሱት ስምምነቶች መሰረት የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር(ኦብነግ) ለአዲሱ የክልሉ አስተዳደር በይፋ እውቅና እንደሚሰጥ እና አብሮም እንደሚሰራ አስታውቋል።

ŠRAJO
@tsegabwolde @tikvahethiopia