#update አርቲስት አለምፀሀይ⬇️

አርቲስት አለምጸሐይ ወዳጆን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ የተቋቋመው ኮሚቴ ዝግጅቱን አጠናክሮ እየሰራ እንደሆነ ተሰምቷል።

ከ27 አመታት በኋላ ወደ አገሯ የምትመለሰው አለምጸሐይ ወዳጆ #ማክሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ማለዳ 1፡00 ሰአት አዲስ አበባ ስትገባ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ቤተሰቦቿ፣ የሙያ አጋሮቿ እና የመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች በተገኙበት በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

አዘጋጅ ኮሚቴው ባወጣው መርሀግብር መሰረት ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከሚደረግ ደማቅ በኋላ ለአመታት ወዳገለገለችበት ብሔራዊ ቴአትር በመምጣት ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ለተጋባዦች በማቅረብ እንኳን ደህና መጣሽ ለዝግጅት በመደረግ ላይ ይገኛል ተብሏል።

ከእንኳን ደህና መጣሽ መርሀግብሩ በተጨማሪም በብሄራዊ ቴአትር ከአድናቂዎቿ ጋ የምትገናኝበት ልዩ ዝግጅት እየተሰናዳ ሲሆን የዝግጅቱ ቀንም በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ተሰምቷል።

©ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ
@tsegabwolde @tikvahethiopia