#update ወቅታዊ የሶማሌ ክልል ዳሰሳ⬇️

በአሁን ሰዓት በሶማሌ ክልል የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው። ሰዎች እየተንቀሳቀሱ መገበያየት፤ በሰላም መውጣት እና መግባት ይችላሉ። ነገር ግን ይህ ሰላም ዘላቂና አስተማማኝ እንዲሆን መንግስት በክልሉ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ ሰው ገልፆልኛል።

የሱማሌ ክልል ልዩ ሀይል የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ እና የፌደራል ፖሊስ ቦታውን እንዲለቅለት የመፈለግ አዝማሚያ አሳይቶ ነበር። የሀገር መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ ቦታውን መልቀቅ አካባቢውን እንዲረጋጋ እንደማያደርገው እና ቦታውን መልቀቁም ለአካባቢው ሰላም ዋስትና ስለማይሆን የሀገር መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ በክልሉ የሰላም ማስከበር እንደሚቀጥል ከስምምነት ተደርሶ በትብብር እየተሰራ ይገኛል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያለው የቻናላችን ቤተሰብ እንዳጫወተኝ መንግስት የሱማሌ ክልልን በአግባቡ እንዲቆጣጠር የተለያዩ ስራዎችን መሰራት አለበት።

የሱማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት የ4 ወር ያልተከፈላቸው ደሞዝ አላቸው። ያ ክፍያ በአግባቡ ሊከፈላቸው እንደሚገባም ነው የተጠቆመው። የተወሰኑ ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረጉም የልዩ ፖሊስ አባላት አሉ እነኚህም ምንም አይነት ነገር አንዳልተደረገላቸውና በዚህም ምክንያት ወደ ጫካ መግባታቸውን ነው የተሰማው።

ጫካ ውስጥ ገብተዋል ተብለው የሚታመኑት ቡድኖችም እርስ በእርሳቸው የተከፋፈሉ ናቸው። ግማሹ ትክክለኛ ደሞዛችን ተከፍሎን ወደ ስራ እንግባ፤ ሰላም እንፈልጋለን የሚሉት ሲሆኑ ሌላኛው ቡድን ደግሞ "አብዲ ኢሌ" የቀድሞው ፕሬዘዳንት ከእስር ይፈቱልን ቦታውን እኛ እንቆጣጠር የሚሉት ናቸው። ወ ደ ጫካ ገብተዋል ተብለው ከሚታመኑት አብዛኛዎቹ የአብዲ ኢሌ ደጋፊ እንደሆኑ ይነገራል።

በሶማሌ ክልል ያለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ በልዩ ጥንቃቄ ነው የሰላም ማስከበር ስራውን እየሰራ የሚገኘው።

በነገራችን ላይ የሱማሌ ክልል ልዩ ሀይል ከባባድ መሳሪዎችን ነው በእጁ ላይ ያሉት። ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በሶማሌ ክልል ጉዳይ ቁርጠኛ እና ዘላቂ ምፍትሄ ላይ መድረስ አለባቸው። ከክልሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረግ አለበት። ልዩ ሀይል ከተባለው ሰራዊትም ጋር ውይይት ሊደረግ ይገባል። ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው ነው የሚናገሩት። የሚበሉት እንደሌላቸውና ገንዘብን ከጨረሱ እንደቆዩ ነው የሚናገሩት። ምን አይነት ችግር በልዩ ሀይል ውስጥ እንዳለ ሊሰማና ውይይት ሊደረግ ይገባል።

ይኸን መረጃ ያደረሰኝ ወዳጄ ጨምሮ እንደነገረኝ አንዳንድ የልዩ ሀይል አባላት ካለባቸው #ችግር የተነሳ ሳይወዱ በግድ ወደ ጫካ እየገቡ እንደሆነና ከተቃዋሚ ሀይሎች ጋር ለመቀላቀል እየተገደዱ እንደሆነ ገልፆልኛል።

ዶክተር አብይ በቅርቡ ከሆነው ሁኔታ አንፃር ዝርዝር መግልጫ ባለመስጠታቸው ብዙሀኑን ህዝብ ግርታ ውስጥ ከቶ ነበር። በአሁን ሰዓት በክልሉ የሰላም ማስከበር ስራ ላይ የተሰማሩት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የየከተማው ፖሊስ እና ልዩ ሀይሉ ናቸው።

በሌላ በኩል...⬇️

ህዝቡ የተዘረፈበት ንብረት እንዲመለስልት፤ እንዲሁም በቂ የምግብ አቅርቦት እንዲሟላ እየጠየቀ ይገኛል።

# በሱማሌ ክልል የሰላም ምስከበር ሁኔታ ላይ ቅርበት ያለው የቻናላችን ቤተሰብ አካል የሆነው ሰው ይህን መረጃ ሊሰጠኝ የፈለገው በክልሉ ዘላቂ መፍትሄ እንዲኖር ከተፈለገ ጥልቅ ውይይት ሊደረግ እንደሚገባው እና የዶክተር አብይ መንግስት በዚህ ላይ በስፋት እንዲሰራ ለመጠቆም ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia