TIKVAH-MAGAZINE
198K subscribers
18.1K photos
274 videos
70 files
2.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
Download Telegram
ፎቶ: የመስቀል በዓል አከባበር በርእሰ አድባራት ወ ገዳማት አክሱም ፅዮን
(መስከረም 17/2017)

@tikvahethmagazine
ፎቶ: የመስቀል በዓል አከባበር ዓዲግራት ከተማ
(መስከረም 17/2017)

@tikvahethmagazine
ደመራ ለምን በሁለት የተለያየ ቀን ይበራል?

የደመራ የማብራት ሥነ-ስርዓት በትላንትናው ዕለት በተለያዩ አከባቢዎች የተከናወነ ሲሆን በሌሎች አከባቢዎች ደግሞ በትላንትናው ዕለት ዋዜማው ተከብሮ ዛሬ ጠዋት ደመራውን የመለኮስ ሥርዓት ተከናውኗል።

ለምን እንደየ አከባቢው ተለያየ ለሚለው ጥያቄ መምህረ መምህራን የኔታ በጽሐ ዓለሙ የሰጡት ማብራሪያ ይህ ነው፦

"በድሮው የመስቀል ደመራ የሚለኮሰው ሌሊት ነው። እዮሐ መብራት እያልን ችቦ እያበራን ሌሊት ተነስተን ነው የምንለኩስ ይሄ መደበኛው ቱባው ሌሊት ተነስቶ መለኮስ ነው።

ዳመራው እና እጣኑ የሚዘጋጀው በዋዜማው በ16 ነው። ሌሊቱን አንዳንዶቹ ወደ ዋዜማው አምጥተን እናከብረዋለን፤ ሌሎቻችን ደግሞ ወደ ፊት አምጥተን በ16 እናከብረዋለን።

ዋናው ባህል ግን ሌሊት ነው። እሌኒም ደመራውን ያስለኮሰችው ሌሊት ነው። ከዚያ ሌሊት የተለኮሰው መስቀሉ ላይ ሄዶ ሰግዶ ቁፋሮ የተጀመረው በ17 ጠዋት ነው።

ደመራው የተደመረበት በ16 ነው፤ ቁፋሮ የተጀመረበት ደግሞ በ17 ነው። ደመራው የተለኮሰው ደግሞ ሌሊት ነው። ለከተሜው ሌሊት በጋራ ለማክበር አይመችም።

ዋዜማ ከሆነ ወደ ማታ፤ በነጋታው ከሆነ ጠዋቱን መሰረት አድርጎ ይከበራል በሁለቱም በጥሩ ሁኔታ ይከበራል"


@tikvahethmagazine
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራትም:በብራንድም:በባትሪ ቆይታም  አስተማማኝ  የሆኑ የተለያዩ  ሞዴል ያላቸዉ  በፈለጉት ስክሬን መጠን : ኮር እና ጀነሬሽን   አሉን።

ላፕቶፕ  ከመገዛቶ በፌት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች   እናስረዳለን።
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን ።
በላፕፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!
!
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
ቤይሩት እንዴት አደረች?

በርካታ ኢትዮጵያዊያን ይኖርባታል ከሚባሉት የሊባኖስ ግዛቶች አንዷ ነች ቤይሩት። ሆኖም ከሰሞኑ እስራኤል በሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን ላይ ጀመርኩት ባለችው ዘመቻ ከትላንት ጀምሮ ከፍተኛ ፍንዳታ እያስተናገደች ትገኛለች።

እስራኤል ደቡባዊ የቤይሩት ክፍልን በአየር ጥቃት ኢላማ ያደረገችው ትላንት አርብ የተፈጸመ ሲሆን ከፍተኛ የሂዝቦላ አመራሮችንና የጦር ካንፖችን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነው ስትል እስራኤል ገልጻለች።

እንደ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘገባ እስራኤል በዚህ ጥቃት ያነጣጠረችው የሂዝቦላው መሪ ሀሰን ነርሰላ ላይ ነው ያሉ ሲሆን ይህ መሪ በዚህ ጥቃት ስለመገደሉ ግን ማረጋገጫ አልተሰጠም።

አርብ ዕለት በነበረው ከፍተኛ ጥቃት የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር 6 ሰዎች መሞታቸውን እና 91 ሰዎች መጎዳታቸውን ይፋ አድርጓል። በአጠቃላይ እስራኤል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በፈጸመችው ጥቃት 800 የሚጠጉ ሰዎች ህይወት አልፏል።

ኒውዮርክ ታይምስ ከቪዲዮዎች፣ ፎቶዎች እና የሳተላይት ምስሎችን በመተንተን በደቡባዊ ቤይሩትን ክፍል በአንድ ጎዳና ላይ ቢያንስ አራት የመኖሪያ ሕንፃዎች በጥቃቱ መውደማቸውን ገልጿል። (ምስሉ ተያይዟል)

የእስራኤል ጦር ነዋሪዎች በደቡባዊ ቤይሩትን ክፍል ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ እየሰጠ ይገኛል።

@tikvahethmagazine
በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን እንዴት እየመሩ ነው?

አል-ዐይን አማርኛ በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን እንዴት እየመሩ ይሆን ሲል የሀገሪቱ መዲና በሆነችው ቤሩትን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ጠይቋል፡፡

ለደህንነቷ በመስጋት ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች አንድ ኢትዮጵያዊ እንደገለጸችው፦

ነበለት በሚባለው ቦታ ትኖር እንደነበር፤ በአካባቢው ተከታታይ የእስራኤል የአየር ላይ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ ወደ ቤሩት ከአሰሪዎቿ ጋር በመሆን ከተሰደደች አራተኛ ቀኗ መሆኑን ትናገራለች፡፡

“ራሴን እና ቤተሰቦቼን ለመርዳት ወደ ሊባኖስ ከመጣሁ ስምንት ዓመት ሆኖኛል፣ ከስድስት ቀን በፊት የጎረቤታችን ቤት በአየር ሲመታ ሁላችንም ፈርተን ወደ ቤሩት መጣን”

ቤሩት ሰላም መስሎን ነበር የመጣነው ሆቴል ውስጥ ነው ከአሰሪዎቼ ጋር ተጠልለን ያለነው፣ አሰሪዎቼ ሆቴል ውስጥ ለረጅም ቀን የሚያቆየን ገንዘብ የለም ሲሉ ሰምቻለሁ ቀጥሎ ምን እንደምንሆን አላውቅም” ስትልም ነግራናለች፡፡

#ጥያቄ(አል-ዐይን): ምን አይነት ድጋፍ ትፈልጊያለሽ?

“ቤሩት ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተመዝገቡ ማለቱን ሰምቻለሁ፣ ስንደውል ስልክ አያነሱም፣ ከዚህ በፊት ችግር ገጥሟቸው የተመዘገቡትም ሲረዱ አላየሁም፣ ወደ ሀገሬ መመለሱንም አልፈልግም“

በቤሩት በአሰሪዎቿ ቤት እየኖረች መሆኗን የገለጸች ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ፦

“ያለሁት በቤሩት ባለ አንድ የመኖሪያ መንደር ውስጥ ነው፣ በህንጻው ላይ ማን እንዳለ አይታወቅም፣ እስራኤሎቹ ታጣቂዎች አሉ ብለው ካመኑ ሙሉ ህንጻውን ይመቱታል፣ ያለው ነገር አስፈሪ ነው

ጦርነቱ ካለባቸው ደቡባዊ ሊባኖስ አካባቢ ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ቤሩት መጥተዋል፣ ህጋዊ ሆነን እየሰራን ያለነው የቻልነውን ያህል ገንዘብ እያዋጠን እየተረዳዳን ነው ግን ቀጥሎ ምን እንደሚፈጠር አናውቅም” ብላለች፡፡

በቤሩት ባለ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልላ እየኖረች ያለች ኢትዮጵያዊት አስተያየት ፦

ከአሰሪዎቿ ጋር ሳይዳ ከሚባለው ቦታ ተፈናቅላ በቤሩት ባለ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልላ እየኖረች መሆኗን ገልጻ የሊባኖስ መንግስት ሳያዳላ ለሁላችንም ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ተናግራለች፡፡

ይሁንና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ህጋዊ ሆነው እየሰሩ ባለመሆኑ ጎዳና ላይ የወደቁ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ እና የሚረዳቸው እንዳጡም አክላለች፡፡

#ጥያቄ (አል-ዐይን): የኢትዮጵያ መንግስት ቤሩት ባለው ቆንስላ ጸህፈት ቤት በኩል በቀጣይ ሊደረጉ ለሚችሉ ድጋፎች ተመዝገቡ የሚል ማስታወቂያ ማውጣቱን ሰምታችኋል?

"ይህን ማስታወቂያ ያልሰማ ሰው የለም ግን ተመዝገቡ የሚባለው የይስሙላ እንጂ የእውነት ለመርዳት አይመስለኝም፡፡

ከዚህ በፊት ለዓመታት በአሰሪዎቻቸው ገንዘባቸው ያልተከፈላቸው ኢትዮጵያዊያን ተመዝገቡ ተብለው ተመዝግበው መጠለያም ተሰጥቷቸው ነበር አሁን ድረስ እየተንገላቱ ነው።

የሚሻለው ኢትዮጵያዊያን በጸሎታቸው ቢያግዙን እንጂ መንግስት ይረዳናል እሚል ተስፋ የለኝም”
ብላለች፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቤሩት ቆንስላ ጽህፈት ቤት ከሶስት ቀናት በፊት በተለይም በደቡባዊ እና ምስራቃዊ ሊባኖስ ያለው የደህንት ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ገልጾ ኢትዮጵያዊያን ራሳቸውን ከአደጋ እንዲጠብቁ ማሳሰቡ ይታወሳል።

Credit : Al-Ain Amharic

@tikvahethmagazine
#Breaking

የሂዝቦላው መሪ ሀሰን ነስረላህ በትላንትናው ዕለት በቤሩት እስራኤል በከፈተችው የአየር ጥቃት ህይወቱ ማለፉን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። መረጃውን ግን በሂዝቦላ ወገን ማጣራት አልተቻለም።

በ ጦሩ በይፋዊ የ "X " ገጹ ላይ ባጋራው መግለጫ "ሀሰን ነስረላህ ከአሁን በኋላ ዓለምን ማሸበር አይችልም" የሚል ጹሑፍ አስቀምጧል።

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በጥቃቱ ከሀሰን ነርሰላ በተጨማሪ ልጁን ጨምሮ ሌሎች የሂዝቦላ የጦር አዛዦችም በጥቃቱ እንደተገደሉ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
#Update: ሂዝቦላህ መሪው ሀሰን ነስረላህ መሞቱን አረጋግጧል

ሂዝቦላህ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በለቀቀው መግለጫ መሪው ሀሰን ነስረላህ መሞቱን አስታውቋል።

ቀደም ሲል የእስራኤል ጦር በኢራን የሚደገፈውን የሂዝቦላ ታጣበቂ ቡድን መሪ በትላንትናው ዕለት በቤሩት በፈጸመው ጥቃት መግደሉን መግለጹ ይታወሳል።

@tikvahethmagazine
አጫጭር

#1

በዛሬው ዕለት በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ እና በመካከለኛው ሸበሌ በምትገኝ አንዲት ከተማ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ 6 ሰዎች ሲሞቱ 10 ቆስለዋል።

በዋና ከተማዋ የተፈጸመው ፍንዳታ ከፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ሥፍራ በቆመ መኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ የተከሰተ ነው።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሶማሊያ የደረሰውን የሽብር ጥቃት በማውገዝ መግለጫ ያወጣ ሲሆን ኢትዮጵያ ፀረ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ ከሶማሊያ ህዝብ ጋር አጋርነቷን ትቀጥላለች ብሏል።

#2

እስራኤል በዛሬው ዕለት በደቡባዊ ሊባኖስ እየፈጸመችው ያለው ጥቃት ቀጥሎ ዛሬ ላይ በ120 የተለዩ ቦታዎች በፈጸመችው ጥቃት ከ20 በላይ የሂዝቦላ አመራሮችን ገድያለሁ ስትል የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር በበኩሉ በዚህ ጥቃት እስካሁን 50 ሰዎች መሞታቸውንና 17ቱ ከአንድ ቤተሰብ መሆናቸውን ገልጿል።

በሌላ መረጃ እስራኤል ሌላኛውን ጥቃት በየመን በሚገኘውና በኢራን ይደገፋል በሚባለው የሁቲ ታጣቂ ቡድን ላይ መፈጸሟ ተገልጿል። በዚህም የኃይል ማመንጫን ጨምሮ ሁለት የተለዩ ቦታዎችን ላይ የአየር ጥቃት ፈጽማለች።

የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ነርሰራላህ አርብ ዕለት በከፈተ ጥቃት መገደሉ፥ በመካከለኛው ምስራቅ ኢራንን ጨምሮ ሌሎች ታጣቂ ቡድኖችን ያሳተፈ ሁሉን አቀፍ ቀጠናዊ ጦርነት የመከሰት ስጋቱን ጨምሯል።

@tikvahethmagazine