TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... የት እንኳን እንዳለ አላውቅም። #መገደሉን በተመለከተም ገድዬዋለሁ ያለውን መጠየቅ ነው የሚሻለው " - አባ ገዳ ጎበና ሆላ

የቱልማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) አባል የሆነ ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ተናገሩ።

ከ1 ሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል ፣ የምዕራብ አርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን የ ‘ ሸኔ ’ ቡድን አባል ነው የተባለውን የአባ ገዳ ጎበና ልጅ " ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል " ብሎ ነበር።

ኮሚኒኬሽኑ " የኦሮሞ ልጆችን ሕይወት ሲቀጥፍ የነበረው የአባ ገዳ ጎበና ሆላ ልጅ (ፎሌ ጎበና) ላይ በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ ውስጥ የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት ለመቅጠፍ ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል  " ነው ብሎ የነበረው።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

አባ ገዳ ጎበና ሆላ ምን አሉ ?

- የልጃቸውን የመገደል ዜና የሰሙት በማህበራዊ ሚዲያ እንደሆነ እና እስካሁን ምንም ማረጋገጫ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

- የልጃቸውን ሞት ባያረጋግጡም በእርግጥ ልጃቸው መንግሥት ኦነግ-ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን አባል መሆኑን #አረጋግጠዋል

- ልጃቸው ፎሌ ጎበና ዕድሜው ወደ 33 ዓመት እየተጠጋ መሆኑን እና ከልጃቸው ጋር ከተያዩ 6 ዓመታት ማለፉን ገልጸዋል።

- " ከ6 ዓመታት በኋላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀናት በፊት ፎቶ ግራፉን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የተመለከትኩት " ብለዋል።

- " የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) ውስጥ እንዳለ አውቃለሁ ፤ ነገር ግን ምንም ግንኙነት የለንም። የት እንዳለም አላውቅም። መገደሉን በተመለከተም ገድዬዋለሁ ያለውን መጠየቅ ነው የሚሻለው " ብለዋል።

- ልጃቸው ሰላማዊ ሰዎች እየዞረ እንደሚገድል በመንግሥት የቀረበበትን ክስ በተመለከተ ፥ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል።

- " እኔ አባ ገዳ ነኝ አልዋሽም ፤ ከልጄ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም። ስልክ አንደዋወልም። ከ6 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፎቶግራፉን እንኳ የተመለከትኩት " ብለዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው እና የአባ ገዳው 7ኛ ልጃቸው የሆነው ፎሌ ጎበና ከቤት የወጣው የ26 ዓመት ወጣት ሳለ እንደነበረ አባቱ ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አባ ገዳ ጎበና ልጃቸው ወደ ትጥቅ እንቅስቃሴ መግባቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በተደጋጋሚ መኖሪያ ቤታቸው ላይ ብርበራ ማድረጋቸውን ሲናገሩ ነበር።

ከጥቂት ወራት በፊት አባ ገዳ ጎበና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤታቸው ላይ ብርበራ በተደረገበት ወቅት ከወላጅ አባታቸው የወረሱት የጦር መሳሪያ መወሰዱን እና ክስተቱን ተከትሎ በቤተሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩን ተናግረው ነበር።

መረጃው የቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ባንኮች

የአገሪቱ ባንኮች ከአሠራር ጋር በተያያዙ ክፍተቶች በተለያዩ ሥልቶች ለሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ፣ ይህ ሁኔታም በቀጣይ የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ውስጥ የበለጠ እንደሚጨምር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ጤናማነትን በመገምገም አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ ምን ይላል ?

➡️ የአገሪቱ ባንኮች በበይነ መረብ ማጭበርበርያ ሥልቶች፣ ከባንኮች የውስጥ ሠራተኞችና ከሦስተኛ ወገን በሚደርሱባቸው የምዝበራ ድርጊቶች በከፍተኛ ደረጃ እየተጋለጡ ናቸው።

➡️ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ማለትም እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በሐሰተኛ ሰነዶችና በሌሎች የማጭበርበር ድርጊቶች ባንኮች 1 ቢሊዮን ብር አጥተዋል። የተመዘበሩት የገንዘብ መጠንም ከቀዳሚው ዓመት በእጥፍ ጨምሯል።

➡️ የባንክ ማጭበርበሮች በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ወደ 1 ቢሊዮን ብር ሲደርሱ፣ ከአምናው በእጥፍ አድጓል። እነዚህ ጉዳዮች የተከሰቱት በዋናነት ፦
° ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችንና ቼኮችን በመጠቀም ገንዘብ በማጭበርበር፣
° ያልተፈቀደ የባንክ ዋስትና በማቅረብ፣
° የተሰረቁ የኤቲኤም ካርዶችን በመጠቀም ገንዘብ በማውጣት ድርጊት
° በሐሰተኛ የስልክ ጥሪዎችና አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን በመጠቀም ነው። በተጠቀሱት የማጭበርበሪያ ሥልቶችም 20 ባንኮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በሰኔ ወር 2015 መጨረሻ ላይ 3 ባንኮች 200 ሚሊዮን ብር ተዘርፈዋል።

➡️ ባንኮች አዳዲስ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ሲተዋወቁ በአሠራር ክፍተቶች ሳቢያ በከፍተኛ ደረጃ ለአደጋ እየተጋለጡ ናቸው።

➡️ ባንኮች ከአሠራር ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመከላከልና የመጭበርበር ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ፣ ውጤታማ የቁጥጥር ሥልቶችንና አሠራርችን በመተግበር ላይ ሊያተኩሩ ይገባል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የ #ሪፖርተርጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ባንኮች የአገሪቱ ባንኮች ከአሠራር ጋር በተያያዙ ክፍተቶች በተለያዩ ሥልቶች ለሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ፣ ይህ ሁኔታም በቀጣይ የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ውስጥ የበለጠ እንደሚጨምር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ጤናማነትን በመገምገም አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ ምን ይላል ? ➡️
ባለፈው ማክሰኞ ሚያዚያ 8 ቀሲስ በላይ መኮንን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ቀሲስ በላይ መኮንን በ ' አፍሪካ ኅብረት ' ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብና ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሳላዊ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ከአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ (367 ሚሊዮን ብር) ለማዘዋወር ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት።

የቀረበውን ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ የተጠራጠሩት የባንኩ ሠራተኞች ለአፍሪካ ኅብረት የሥራ ኃላፊዎች ስልክ በመደወል ለባንኩ ስለቀረቡት የክፍያ ሰነዶች እና #እንዲከፈል ስለተጠየቀው የገንዘብ መጠን በማሳወቅ የክፍያ ትዕዛዙን ትክክለኛነት እንደጠየቁ ለማወቅ ተችሏል።

የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ኃላፊዎች የተጠቀሰውን የክፍያ ሰነድ ምንም እንደማያውቁትና ኅብረቱም የተባለውን የክፍያ ትዕዛዝ እንዳልሰጠ አሳውቀዋል።

ይህን ተከትሎ የክፍያ ሰነዱን ይዘው ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለማዘዋወር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት ቅርንጫፍ በአካል የተገኙት ቀሲስ በላይ፣ የኅብረቱ የፀጥታ ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ካዋሉዋቸው በኋላ ለፌዴራል ፖሊስ አስረክበዋቸዋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪውን ቀሲስ በላይ ሐሙስ ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቅርቧቸዋል።

ፌደራል ፖሊስ ለፍርድ ቤት ምን አለ ?

- ቀሲስ በላይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል እንደቀረቡ ገልጿል።

- ለ3 ግለሰቦችና ለ1 የግል ድርጅት የባንክ ሒሳቦች በድምሩ 6 ሚሊዮን 50 ሺሕ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ኅብረት የፀጥታ ሠራተኞች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው እንደሰጡ ተናግሯል።

- የተጠረጠሩበትን የወንጀል ድርጊት ለችሎቱ በማስረዳት ተጨማሪ ምርመራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ ምን አሉ ?

የተባለውን ድርጊት እንደፈጸሙ ያመኑ ቢሆንም ፣ በወንጀል ድርጊት እንዳልተሳተፉ በመግለጽ ችሎቱ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤት ምን አለ ?

የግራ ቀኝ ክርክር ካዳመጠ በኋላ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ፣ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AU #Fraud #CBE

ቀሲስ በላይ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሳላዊ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ #ከ6_ሚሊዮን_ዶላር_በላይ (367 ሚሊዮን ብር) ለማዘዋወር ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ፍድር ቤት ቀርበውም ለፖሊስ ተጨማሪ ቀን ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ምን አሉ ?

" በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካለው የአፍሪካ ህብረት ሒሳብ የወጣ ገንዘብ የለም።

አንድ ሰው ሀሰተኛ ሰነዶችን ተጠቅሞ ለማውጣት ቢሞክርም እዛው በቦታው ላይ ተይዟል።

የማጭበርበር ሃሳብና ገንዘብ ለመውሰድ ጥረት ቢደረግም ማክሸፍ ችለናል። ይህንን የሞከሩት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ናቸው። እኔ የማውቀው ይህን ብቻ ነው።

በመሰረቱ ጥሬ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ሊሰጥ አይችልም። አጭበርባሪው መጥቶ  ሲጠይቅ ይህን እንኳን አያውቅም ነበር።

ሰውዬው እዚህ ሀገር የዶላር አካውንት ከሌለው ገንዘቡ ቢተላለፍም የትም ውስጥ ሊገባ አይችልም።

አጭበርባሪዎች በየቀኑ ነው ወደ ባንካችን የሚመጡት ፤ ባንክ ስለምንሰራ ይህ የተለመደ ነው። ነገር ን ሁሌም የማጭበርበር ድርጊቶቹ ከመሳካታቸው በፊት እንደርስባቸዋለን። ለፍርድም እናቀርባቸዋለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፥ የደንበኞቹን ሒሳቦች የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ያንን እያደረግን ነው። የአፍሪካ ህብረት እስካሁን ድረስ በይፋ ቅሬታ አላቀረበብንም። "

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአፍሪካ ኅብረት ምንጭ ምን አሉ ?

"የእኛ ሒሳብ ላይ መሰል ማጭበርበር ሲያጋጥም ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

አሁን ላይ ማጭበርበሩ #በተከበሩ_ሰዎች አማካኝነት እየተሞከረ ነው። ይህ ደግሞ በጣም አስጨንቆናል። አንድ ቀን ባለስልጣናት ተመሳሳይ ነገር ላለማድረጋቸው ምንም አይነት ዋስትና የለንም።

እምነት እያጣን ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ለደሞዝ አነስተኛ መጠን ያለው ፎሬክስ (የውጭ ምንዛሬ) ለመያዝ ወስነናል።

ይህን መሰሉ ሁኔታ የድርጅቱን ገንዘብ በውጭ ማቆየት እንድናስብ እያስገደደን ነው። "

https://telegra.ph/The-Reporter-04-21 #ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#ቀነኒሳ_በቀለ👏

አንጋፋው የኢትዮጵያ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ41 ዓመቱ ዛሬ በለንደን የተካሄደ የማራቶን ውድድርን በ2ኛነት አጠናቋል።

በርካቶች ለአትሌቱን ትጋት ፣ ጥንካሬና ቁርጠኝነት አድናቆት እያጎረፉ ይገኛሉ።

አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የለንደን ማራቶን ውድድርን 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ነው ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው።

የዓለም አትሌቲክስም አትሌቱ ላሳየው ድንቅ ብቃት አድናቆቱን ችሯል።

የዛሬው ማራቶን የገባበት ሰዓት ከ2019 ወዲህ ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ዘንድ የተመዘገበ የመጀመሪያው እንደሆነም ጠቁሟል።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
🔥ከባድ ትንቅንቅ የማያጣው የየኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ተመልሰዋል🔥

Coventry vs Manchester United እሁድ ሚያዚያ 13 ከሰዓት 11፡30 ይፋለማሉ!

🔥 ማን ዩናይትድ ወደ  ፍፃሜ መቀጥል ይችላል?

👉 ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#FACupAllOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#ATTENTION🚨

" አንዳንድ ወጣት ሴቶች ከቫይረሱ በላይ #እርግዝናን_ይፈራሉ "

ስለኤች አይቪ/ኤድስ ስርጭት የሚሰጠው የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ከጊዜ ወደጊዜ እየተቀዛቀዘ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ገልጿል።

ችግሮች ከመባባሳቸው በፊት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ አሳስቧል።

ቫይረሱ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ በተሰራው እንቅስቃሴ ብዙ ለውጦች መመዝገባቸውን አስታውሷል።

ይሁን እንጂ የተመዘገቡት ለውጦች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን መዘናጋት እንደፈጠሩ ፤ የሚዲያዎች ተሳትፎም መቀዛቀዙን ጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት ኤች አይ ቪ ቫይረስን በተመለከተ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ትኩረት የሚሹና በይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ ብቻ ትኩረት ያደረጉ ናቸው ብሏል።

እነዚህም ፦
- ሴተኛ አዳሪዎች፣
- አደንዛዥ እፅ የሚጠቀሙ ሰዎች፣
- የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣
- አፍላ ወጣቶች በተለይ (ከማኅበራዊ ሚዲያ ጋር በተያያዘ)፣
- የቀን ሠራተኞች፣
- ከማኅበራዊ ችግሮች ጋር ተያይዞ ተጋላጭ የሆኑት እንደሆኑ አመልክቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በላይ ቢሆንም ከቦታ ቦታ በፆታ፣ በኅብረተሰብ ክፍል፣ በገጠርና በከተማ ከፍተኛ ልዩነት አለው ብሏል።

በከተሞች ያለው ስርጭት በገጠር ካለው በሰባት እጥፍ እንደሚበልጥም ጠቁሟል።

ይህንን ልዩነት መሠረት ያደረገ አጠቃላይ ማኅበረሰቡን ተደራሽ የሚያደርግ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየተከናወነ አይደለም ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፦
° የመጠጥ ቤቶች ፣
° የጫት ቤቶች
° በሺሻ ቤቶች መስፋፋት ሌላ ተግዳሮቶች እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጿል።

" አንዳንድ ወጣት ሴቶች ከቫይረሱ በላይ እርግዝናን ይፈራሉ። የወጣቶች አዲስ የመያዝ ምጣኔ ጨመረ ባይባልም እየቀነሰ አይደለም፤ ይህ በራሱ ችግር ለመኖሩ አመላካች ነው "ም ብሏል።

በተለይ በወጣቶች በኩል ሁሉን አቀፍ ሥራ ባለመሠራቱ እንደ ሀገር ዋጋ ሊያስከፍሉ የሚችሉ አጋላጭ ባሕሪያት እየተስተዋሉ መሆኑን አመልክቷል።

የኤች አይ ቪ ቫይረስን በተመለከተ ጠንካራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እንደሀገር ማከናወን እንደሚጠበቅ አሳስቧል። #ኢፕድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

' ቲክቶክ ' አሜሪካ ውስጥ ከታገድኩኝ " የ170 ሚሊዮን አሜሪካውያን የመናገርና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይረገጣል " አለ።

ይህን ያለው የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት መተግበሪያው ከቻይና ካልተፋታ እንዲታገድ ረቂቅ ህግ ካጸደቁ በኃላ ነው።

የ 'ቲክቶክ' ቃል አቀባይ መተገበሪያው እንዲታገድ የሚለውን ረቂቅ ህግ አውግዘዋል።

" ከታገደ ፦
- የ170 ሚሊዮን አሜሪካውያንን የመናገር መብት ይረግጣል፣
- 7 ሚሊዮን ንግዶች እንዲጠፉ ይሆናል፣
- ለአሜሪካ ኢኮኖሚ በዓመት የሚገባውን 24 ቢሊዮን ዶላር ያሳጣል " ብለዋል።

አክለው ፤ " ባይትዳንስ የቻይና ወይም የሌላ አገር ወኪል አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።  " የቻይና ኩባንያ እንዳልሆነም በተደጋጋሚ ተናግረናል " ሲሉ አክለዋል።

ጉዳዩን የሚከታተሉ አካላት ግን ' ቲክቶክ ' ከቻይና ተፋቶ ድርሻው ለአሜሪካ ሰዎች ካልተሸጠ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ #የመታገዱ ነገር አይቀሬ ነው ብለዋል።

ትላንት የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ' ቲክቶክ ' በመላው ሀገሪቱ እንዲታገድ የሚያደርግ ረቂቅ ህግ አጽድቋል።

@tikvahethiopia
🍲 " የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል " 🍲

ሰሞኑን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪ የምግብ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ፤ " የምግብ በጀት እጥረት ገጥሞናል ያለውን ብሉ " አይነት ማስታዎቂያዎች መለጠፋቸውን ተከትሎ በበርካቶችን አነጋግሯል።

ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተለጠፉ ማስታወቂያዎች ምንድነው የሚሉት ?

- " እንደ ሀገር የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል። የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋም በየቀኑ #ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት ተቆጥሯል። "

- " ተቋማችን የሚያደርገው ድጎማ ተማሪዎቻችን ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ ባሉን የምግብ ጥሬ እቃዎች አገልግሎት እየሰጠን ቢሆንም በአሁን ሰዓት እጅግ በጣም #እየከበደ ስለሆነ የሜኑ ማሻሻያ ለማድረግ ተገደናል። "

- " ከአሁን በኃላ የተሻሻለው ሜኑ ተግባራዊ ይሆናል። "

- " በተወሰኑ በስቶራችን ውስጥ ባሉ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች እና በአትክልት የምግብ አገልግሎት እየሰጠን ነው። በአስቸኳይ የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ አቅርቦት እንዲሟላ ጠይቀናል እስከዛ ታገሱ። "

... ይላሉ ማስታወቂያዎቹ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥ በዲላ እንዲሁም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ካሉ የቤተሰቡ አባላት ማህተም ያረፈባቸውን ማስታወቂያዎች ተልኮለት ተመልክቷል።

ይህ ነገር የቤተሰብ የጭንቀት ምንጭ ከመሆኑ በላይ ፦

° ዩኒቨርሲቲን የሚያክል እጅግ ትልቅ ተቋም እንዴት መጭውን የዋጋ ንረት እንዲሁም የዓመቱ የምግብ ወጪ ያላገናዘበ በጀት ይይዛል ?

° ለረጅም ዓመታት ለተማሪ በቀን የሚመደበው ገንዘብ አነስተኛ ሆኖ ሳለ እንዴት ይህ ሊፈጠር ቻለ ? የሚሉና ሌሎች ነቀፌታዎች ተሰምተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ " የምግብ በጀት እጥረት ገጥሞናል " የሚል ማስታወቂያ ከተለጠፈባቸው ተቋማት አንዱ ወደሆነው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ደውሏል።

▪️የተከሰተው ችግር ምንድነው

▪️በዚህ አይነት ሁኔታ ተማሪዎች ከመጎዳታቸው በላይ ወላጆችንስ አያስጨንቅም ወይ ... ሲል ለዩኒቨርስቲው የምርምር እና ቴክኖሎጂ ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ሀብታሙ ተመስገን ጥያቄ አቅርቧል።

ዶ/ር ሀብታሙ ፤ ማስታወቂያውንም ሆነ ሀሳቡን እንደማያዉቁት በመግለጽ " ማን ይህን ሀሳብ እንዳመጣ እንዲሁም ማስታወቂያ እስከ መለጠፍ ድረስ እንደደረሰ እናጣራለን " ብለዋል።

" ተማሪዎች ሆኑ ወላጆች ምንም የሚያሳስባቸዉ ነገር ሊኖር አይገባም " ያሉ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዉም ሆነ እርሳቸዉ የሚመሩት የተማሪዎችን ጉዳይ የሚመለከት ቢሮ ችግሩ እንደሌለበት ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ማስታወቂያ ወደ ተለጠፈበት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ደውሏል።

የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር አክብር ጩፋ ፥ " ሶሻል ሚዲያ ላይ መረጃው ሲንሸራሸር እያየን ነው " ብለዋል።

" ሁኔታዉን ለማጣራት #ማኔጅመንቱ ስብሰባ ይቀመጣል። የስብሰባዉን ወጤት የተመለከተ መረጃ በፍጥነት አደርሳችኋለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

NB. ከላይ ተየያያዙት ማስታወቂያዎች ማህተም ያረፈባቸው ናቸው።

መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ ነው የተላከው።

@tikvahethiopia
አስደሳች ዜና ከሳፋሪኮም !

🎁 ልዩ ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎችን ከ M-PESA ሳፋሪኮም APP ላይ በመግዛት 50% ተጨማሪ ዳታ አግኝተን በነጻ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም እንደዋወል! 🤳 ዳታ እንግዛ! በነጻ እንደዋወል!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://publielectoral.lat/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ  እንጋብዛለን።

👉Facebook: https://www.facebook.com/SafaricomET
👉Twitter:
https://x.com/SafaricomET?t=y2XAHAhPNvFeZqXa2YE6aQ&s=08
👉Instagram: https://www.instagram.com/safaricomet?igsh=MWJtcjJrMzNhMzVsNg==
👉 YouTube: https://youtube.com/@safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm
#Mekelle

በመቐለ የሚገኘው " ፍሬምናጦስ የአረጋውያን የአእምሮ ህሙማን የህፃናት እንክብካቤ ማእከል " በእሳት ቃጠሎ አደጋ ምክንያት ከፍተኛ ወድመት አጋጥሞታል። 

አደጋው ያጋጠመው ሚያዝያ 7/ 2016 ዓ.ም ሲሆን ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ የእርዳታ ጥሪ ተማጽኖ አቅርቧል።

የምግባረ ሰናይ ድርጅቱን የተለያዩ በጎ አድራጊዎች ሲረዱት ቆይተዋል።

የሚያዘያ 7ቱ የእሳት አደጋ ከአጋዦቹ አንዱ የሆነው መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ ሚሊዮን ብሮች በመስጠት ባሰራው አዳራሽ ነው የደረሰው።

በተነሳው ቃጠሎም አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ሲወድም በተረጂዎች ማደሪያ ፣ መመገብያና ፣ መስሪያ ክፍሎች ወድመት ደርሷል።

በከፍተኛ ውጪ የተሰራው አዳራሽ ሚያዝያ 6/2016 ዓ.ም. የተመረቀ ሲሆን በነጋታው  ሚያዝያ 7/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ነው በእሳት ሙሉ በሙሉ የወደመው።

የአደጋው መንስኤ በኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ በተነሳ ቃጠሎ ነው ተብሏል።

ያጋጠመው ቃጠሎ ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም በህዝብና በመቐለ የእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ የተቀናጀ ርብርብ በማእከሉ በሚገኙ አቅመ ደካሞች የህይወት ማጣት አደጋ  አልደረሰም።

ምግባረ ሰናይ ድርጅቱ በእሳት አደጋ ቃጠሎ ምክንያት የመኝታ፣ መመግብያ ክፍሎቻቸው የተቃጠለባቸው የሚንከባከባችው አቅሞ ደካሞች ሜዳ ላይ ተጥለው እንደሚገኙ በመጠቆም በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ሰብአውያን ሁሉ እንዲረዱት ጥሪ አቅርበዋል።    

መርዳት የሚፈልጉ ወገኖች ፍሬምናጦስ  የአረጋውያን የእአምሮ ህሙማንና የህፃናት እንክብካቤ ማእከል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000622132404 ሂሳብ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ።

#TikvahFamilyMekelle

@tikvahethiopia