TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሶማሊያ መንግሥትን አስጠነቀቀች። ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍም ይሁን ለመቃረን የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ይሁን አካል ላይ እርምጃ ወስዳለሁ ብላለች። የራስ ገዟ ሶማሌላንድ" የሚኒስትሮች ምክር ቤት " ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ነበር። ከስብሰባው በኃላ ባወጣው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፦ - ምክር ቤቱ እ.ኤ.አ. ጥር 1/2024…
#ሀርጌሳ

" ሀገራችንን አልሸጥንም " - ሙሴ ባሂ አብዲ

ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል።

ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

አደባባይ ወጥቶ ለተቀበላቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑ ገልጸዋል።

ፕሬዜዳንቱ " ሀገራችንን አልሸጥንም " ያሉ ሲሆን " ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ጦር ሰፈር #በሊዝ ነው የምትከራየው " ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ እውቅና ለመስጠትም ተስማምታለች " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ መቼ እንደሆነ ቀኑን በግልፅ ባይናገሩም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት #በቅርቡ ለሶማሌላንድ እውቅና እንደሚሰጥ በድጋሚ ለህዝባቸው ገልጸዋል።

" ይህ የሶማሌላንድ ህዝብ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት የደረሰበት ትልቅ ስኬት ነው " ሲሉም ገልጸዋል።

ስምምነቱ በሁለቱም ወገን በኩል ፍላጎትና ጥቅማቸውን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል ፤ ሶማሌላንድን እንደ ራሷ አንድ ግዛት የምትቆጥራትና የተፈረመው ስምምነት ሉዓላዊነቴን ጥሷል በሚል የተቃወመችው ሶማሊያ ውስጥ ዛሬ የተቃውሞ የአደባባይ ሰልፎች ሲደረጉ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል።

ፎቶ / ቪድዮ ፦ ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ (ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 206 ዓ/ም)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ‘ልጆቼን ልያቸው’ ብሎ ማታ ሲመጣ ከሁለት አቅጣጫ ተተኮሰበት ሞተ። " - የመተሃራ ነዋሪ ከታህሳስ 19/2016 ዓ/ም ወዲህ ባሉት ቀናት ብቻ በተለያዩ ቦታዎች ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ አሽከርካሪዎችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን፣ ከአሥር በላይ ተጓዦች መታገታቸውን፣ እንዲሁም ስምንት ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን የዓይን እማኞችና የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። አንድ…
" ጉዞ አድርጎ መመለስ / ወጥቶ በሰላም መግባት ሰቀቀን ሆነብን " - የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት

ዜጎች መንገድ እንደወጡ በታጣቂዎች የጥይት ድብደባ ይገደላሉ።

ታግተው ፣ ታፍነው ይወሰዳሉ፤ በሚሊዮን ብር ገንዘብ ይጠየቅባቸዋል።

ስንት ደክመው፤ ላባቸውን ጠብ አድርገው ያፈሩት ሃብት ፣ የቤተሰብ ማስተዳደሪያ ተሽከርካሪያቸው እንደዋዛ ይቃጠላል።

የድርጊቱ ፈፃሚዎች " ታጣቂዎች ናቸው " ይባላል። ጉዳዩ የአንድ ሰሞን ወሬ ሆኖ ያልፋል ፤ ተበዳዮች ግን ፍትህ ሳያገኙ በተስፋ መቁረጥ እያነቡ ይቀመጣሉ።

ለችግሩ መፍትሄ ባለመሰጠቱ ከሆነ ጊዜ በኃላ ተመሳሳይ ድርጊት ይፈፀማል።

ዜጎች ለጉዳያቸው፣ ቤተሰብ ለመጠየቅም ሆነ ለስራ ረጅም ጉዞ አድርጎ ለመምጣት ስጋት ያድርባቸው ከጀመረ አመታት አልፈዋል። ጉዞ የሚደረገው በሰቀቅን ሆኗል።

አንዳንዶች ፤ " በምሽት አትጓዙ ለዛ ነው እንዲህ የሚያጋጥመው " ሲሉ ይመክራሉ ግን የሀገሪቱ ህግ አስከባሪ ምሽት ላይ አይሰራም ወይ ? የዜጎች ደህንነት ምሽት ላይ አይጠበቅም ወይ ? የሚል ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል።

የዜጎች ደህንነት መቼ ነው የሚጠበቀው ? ፣ እስከዛሬው ለፈሰሰው ደም መቼ እና ማነው የሚጠየቀው ? ይህና ሌሎች ብዙ ጥያቄዎች በበርካታ ፍትህ የተነፈጉ ወገኖች አእምሮ አለ።

አንድ ከሰሞኑን ጉዳት ያስተናገዱ ሹፌር ፤ " በቅድሚያ ከምንም ስራ በፊት የዜጎች ደህንነት፣ በሰላም ወጥቶ መግባት የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለበት የመንግሥት አካል በየደረጃው መጠየቅ አለበት " ብለዋል።

ተጎጂዎችም ፍትህ ይሻሉ ሲሉ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ቀጠና ተደጋጋሚ ግዜ እገታ፣ ግድያ፣ ዘረፋ፣ ቃጠሎ ሲፈፀም እየታየ ድርጊቱን በዘላቂነት ማስቀረት እና አጥፊዎች ወደ ፍርድ አደባባይ ማቅረብ አለመቻል ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል።

ድርጊት ፈፃሚዎቹ የማይታዩ፣ የማይገኙ፣ መንፈስ ናቸው ?

(በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል)

@tikvahethiopia
#ስጋ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰይድ እንድሪስ የ2016 ዓ/ም የገና በዓል ዝግጅትን በተመለከተ ምን አሉ ?

* ሰሞኑን የተለያዩ ኦፕሬሽኖች ሰርተናል። 200 ቤቶች አካበቢ ለማየት ሞክረን ከዛ ውስጥ በ30 ቤቶች ሕገ ወጥ ስጋ የተገኘበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው።

* 15 ቤቶች ሙሉ ለሙሉ #አንዲታሸጉ ያደረግንበት ፣ ሌላ ተጨማሪ 10 ቤቶች ደግሞ ሕገ ወጥ (ሀሰተኛ) የስጋ ምርመራ ሰነድ ይዘው ህብረተሰቡን እያታለሉ ሥጋ ሲሸጡ የነበሩበት ሁኔታ መኖሩን ያዬንበት ሂደት አለ።

* አጠቃላይ ባደረግነው ሂደት 1,500 ኪሎግራም ሕገ ወጥ በሦስት ቀናት ውስጥ ተሰብስቦ እዚህ መጥቶ እንዲወገድ የተደረገበት ሂደት አለ። 

* ባደረግነው ዳሰሳ #የሕገወጥ እንስሳት እርድ አለ። ከዚያ ውጪ ግን በእምነትም ይሁን በባህላችን ባዕድ የሆኑ እንስሳት ታርደው ወደ ገበያ የቀረቡበት ሂደት የለም። የተያዘው ሥጋ፦
- የበሬ ፣
- የፍዬል
- የበግ ፣ ግን በሕገ ወጥ መንገድ የታረደ ነው።

* የበሬ ስጋ የአንድ (1) ኪሎ ዋጋ ከ550 እስከ 570 ብር በዕለቱ ሽያጭ ይከናወናል። በአራት መስኮቶች የበግ እና የፍየል ስጋም ሽያጭ ይከናወናል። የበግ ስጋ በ500 ብር ፣ የፍየል በ510 ብር በኪሎ ግራም ለበዓሉም ለመደበኛ ቀናትም የሚያቀርቡበት በዚህ ደረጃ ተዘጋጅቷል።

" የባዕድ እንስሳት / #አህያ ስጋ እየተሸጠ ነው " ሲባል በነበረው ጉዳይ ምን ተባለ ? ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-05

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበት እየተገነባ ነው የሚገኘው የተባለው የዓድዋ ዜሮዜሮ ፕሮጀክት #ወደመጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል። ፕሮጀክቱ በውስጡ ፦ - በዓድዋ ጦርነት የተሰዉ ጀግኖችን የሚዘክር ሙዚየም፣ - የመዝናኛ ሥራዎች፣ - ካፍቴሪያዎች፣ - ሲኒማ ቤቶችና ሁለገብ አዳራሾችን - የህፃናት መጫወቻ - አንድ ሺህ (1000) መኪና ማቆም የሚያስችል ፖርኪንግ - የንግድ ቤቶችን የያዘ ነው ተብሏል።…
#አፄምኒሊክ #እቴጌጣይቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር " በዓድዋ ዜሮ ዜሮ " ፕሮጀክት መግቢያ ፊለፊት ላይ የአፄ ምኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት እንደሚኖር ገልጿል።

ምኒሊክ አደባባይ የሚገኘው " የአፄ ምኒሊክ ሃይውልት ሊፈርስ ነው፤ ከቦታው ተነስቶ ወደ ሙዚየም ሊገባ ነው " የሚባለው ፍፁም #ሀሰት ሲል ገልጿል።

የከተማው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰጡት ቃል ፤ " በዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎሜትር ፕሮጀክት የአፄ ምኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊትለፊት ላይ ገና መግቢያው ላይ አለ፤ አዲስ ተጨምሮ። ያንን አዲስ የሚሰራ እንዴት ነው አሮጌውን የሚያፈርሰው ? ይሄ ያስኬዳል ? እንዴት ነው የበዓል ማክበሪያ ቦታ በዛ በኩል የሚደረገው ? " ሲሉ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ፤ " አፄ ምኒሊክ የራሱ ትክክል አይደለም የምንለው የሰራቸው ጥፋቶች አሉ ብለን እናምናለን። በዓድዋ ላይ ደግሞ የሰራቸው ትልልቅ ታሪኮች አሉ። አንድ የሆነ ጥፋት ካለ  ሌላውን ሁሉ እውነት በዛ እንሸፍናለን ማለት አይደለም። የሆነ እውነት ካለ በጥፋቱ ሸፍነን እናያለን ማለት አይደለም። ታሪክን ጥፋትም ይኑር በጎ ገፅታውን ፣ መልካም ገፅታውንም እንዳለ እውነቱን ማስቀመጥ ነው ከእኛ የሚጠበቅ " ሲሉ ተናግረዋል።

" እኛ አልሰራነው፤ ለምን የአሁኑ ትውልድ መከራውን እንደሚያይ ብዙ አይገባንም። እኛ አልሰራነው ፤ ይሄ ትውልድ አልሰራው የጥፋቱንም የጀግንነት ፓርቱንም ይሄ ትውልድ አልሰራውም። ግን የራሱ ሃገር ታሪክ ነው፤ የራሱ ህዝብ ታሪክ ነው በመልካምነት የሚይዘውን ይኮራበታል፤ ይይዘዋል፤ ያሳይበታል። ትክክል አልነበረም የምንለውን አንደግመውም፤ በእኛ ዘመን መደገም የለበትም። " ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች " አሮጌ አካባቢን ባደስን ቁጥር ቅርስ ፈረሰ ነው የሚባለው ይሄ አዲስ አበባ ላይ ትልቅ የልማት እንቅፋት ሆኖብናል " ሲሉ አክለዋል።

የ " ዓድዋ ዜሮ ዜሮ " ፕሮጀክት ከጥቂት ቀናት በኃላ ለህዝብ ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
Discover unrivaled connectivity at Ethio telecom – your ultimate destination for up to 30% discounted special welcoming packages.

Stay effortlessly connected with our exclusive offers, available at our shop in Bole International Airport or your nearest location.
Stay connected, stay ahead.

#Ethiotelecom #telebirr #Backtoyourorigins
25 ዓመታት በሕብረት

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ቴሌግራም- https://publielectoral.lat/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

- ከአገሪቱ ህዝብ 1 በመቶ ደም መለገስ ቢጠበቅበትም አሁንም የሚለገሱት 0.4 በመቶ ብቻ ናቸው።

- በአማራ ክልል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ከለጋመሾች ደም ለመሰብሰብ ፈተኝ በመሆኑ ከዕቅድ በታች አፈጻጸም እንዲመዘገብ አድርጓል።

- በአማራ ክልል ካሉት አሥር የደም ባንኮች ውስጥ ባህር ዳር ደም ባንክ በጣም ጥሩ የደም ማሰባሰብ ሥራ የሚሰራ ተቋም ነበር። የጸጥታ ችግር አውት ብሬክ ሲያደርግ ተንቀሳቅሰው መስራት አልቻሉም።

- በአምስት ወራት ወራት ውስጥ 168,700 ዩኒት ደም እናሰባስባለን ብለን አስበን ነበር፣ የተሰበሰበው ወደ 136,560 ዩኒት ደም ነው። ይሄ ማለት ከታቀደው አንጻር ወደ 83 በመቶ የሚሆን ነው።

- በ2016 ዓ/ም 5 ወራት ውስጥ የተሰበሰበው ደም 139,560 ዩኒት፣ በ2015 ዓ/ም በአንድ ዓመት ሙሉ የተሰበሰበውም 352,900 ዩኒት ደም ነው። ይህ ማለት ከሚጠበቀው 0.4 በመቶ አካባቢ ብቻ ነው የሚሆነው አንድ በመቶ የሚጠጋ አይደለም።

- ኢትዮጵያ በዓመት ከለጋሾች የሚያስፈልጋት የደም ብዛት 1 ሚሊዮን ዩኒት ቢሆንም በ2015 በጀት ዓመት ያገኘችው 352,900 ዩኒት ወይም ከፍላጎቷ ከግማሽ በታች ነው።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-05-2

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#አማራክልል

በደብረ ብርሃን በፋኖ እና በመከላከያ መካከል ተደረገ በተባለ የተኩስ ልውውጥ ንጹሐን ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችና የከተማው ከንቲባ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ከተማ ሰሞኑን በፋኖ ከታጣቂዎችና በመከላከያ ሠራዊት ተደረገ በተባለ የተኩስ ልውውጥ፣ “በርካታ ንጹሐን ተገድለዋል። ባለሥልጣናትም ታግተው ተወስደዋል” ሲሉ አንድ የከተማው ነዋሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ሌላኛው ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነዋሪ፣ “እኔ ባለኝ መረጃ 5 ንጹሐን ተገድለዋል” ብለው፣ ከንጹሐን ሰዎች በተጨማሪ የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የአቶ ሰለሞን ጌታቸው ሹፌርም እንደተገደሉ፣ የፋኖ ታጣቂዎች ኃላፊውን ጨምሮ በርካታ ሠራተኞችን አግተው እንደወሰዱ አስረድተዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረባለቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፣ የተወሰኑ ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ፣ የሟቾችን ብዛት እያጣሩ መሆኑን፣ እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ) ድረስ ከአራት ሰዎች በላይ መገደላቸውን ተናግረዋል።

አክለውም፣ የብልጽግና ጽሕፈት ኃላፊው ሹፌር ተገድሏል መባሉ እውነት መሆኑን፣ ይሁን እንጂ ኃላፊውና ሌሎች ሠራተኞች ታግተው #እንዳልተወሰዱ አስረድተው፣ የጸጥታውን ሁኔታ በተመለከተም፣ “ወደ መደበኛ ሥራው ተመልሷል። መደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ነው” ብለዋል።

ከደብርሃን ከተማ በተጨማሪ በሰሜን ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች፣ በጎንደርና በጎጃም መስመሮች በተለያዩ አካባቢዎች በየወቅቱ የተኩስ ልውውጥ እንደሚደረግ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ሰሞንኛውን የደብረ ብርሃን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ ወደ ሸዋ ሮቢት፣ ደሴ፣ ወልዲያና ሌሎች አካባቢዎች መጓዝ አለመቻላቸውን፣ አሁንም ለገና በዓል ወደ ቤተሰብ ለመሄድ የመንገዱ ደህንነት ሥጋት እንደደቀነባቸው ተጓዦች ሲያማርሩ ተስተውለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከላም በረት መናኸሪያ ስምሪት ባደረገው ቅኝት ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር ስምሪት እንደሌለ፣ ለዚሁ መስመር የጉዞ ትኬት የሚጠይቁ ሰዎችም የለም እየተባሉ መሆኑን ተመልክቷል።

በሌላ በኩል በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ከተማ ወጣ ብሎ በስተምዕራብ በኩል ጠበለት ተራራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሰሞኑን ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር፣ ከቆቦ ወደ ተኩለሽ ታዳጊ ከተማ በጸጥታው ችግር ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት ከቆመ ዓመታት ማስቆጠሩን ነዋሪዎቹን አማሯል።

ከዚህም ባሻገር በክልሉ በተለይ ድርቅ በተከሰተባቸው ዋግኽምራ አስተዳደር ዞን፣ በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች እርዳታ ለማድረስ የጸጥታው ችግር ፈተና እንደሆነ የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው፣ ነዋሪዎች በበኩላቸው የጸጥታው ችግር የኑሮ ውድነቱን እንዳባባሰው ተናግረዋል።

በፋኖ ታጣቂዎችና መከላከያ ሠራዊት መካከልበአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በየወቅቱ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ ይስተዋላል።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ…
#Update

ትምህርት ሚኒስቴር በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ማለቱ ይታወሳል።

ይህ ተከትሎ አንዳንድ ተቋማት ለተማሪዎቻቸው ጥሪ አድርገዋል።

ጥሪ ካደረጉት ውስጥ አንዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነው።

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎቹ ባደረገው ጥሪ ፤ የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ተማሪዎች እንዲሁም የ3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ እና የማታ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ከጥር 15-17/2016 ዓ.ም ወደ ተቋማቸው እንዲገቡ ብሏል።

በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ (Freshman፣ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላቸው ተማሪዎ ከጥር 21-23/2016 ዓ.ም ወደ ተቋማቸው እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎቹ የ2016 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ ጥር 6 እና 7/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

በዚህ ጥሪ መሰረት ፤ ነባር የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች፣ በ2015 ዓ.ም በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ትምህርታቸው ሲከታተሉ የቆዩና የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፣ በ2014 ዓ.ም እና በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ምክንያቶች Withdrawal በመሙላት ያቋረጡ ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት አምጥተው ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ተማሪዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ብሏል።

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች ጥሪ እስከሚደረግ በትዕግስት እንድጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ ሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ነባር ተማሪዎቹ ጥር 2 እና 3/2016 ዓ.ም ምዝገባ እንዲያከናውኑ ጥሪ አቅርቧል።

ለአንደኛ ዓመት እና ለሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ እሰከሚደረግ በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ሌሎች በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

በአማራ ክልል ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች አስር ሲሆን በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎችን ሳይጠሩ ወራትን አስቆጥረዋል።

ተማሪዎች መፍትሄ እንዲፈለግላቸው በተለያዩ መንገዶች ጭና ሲፈጥሩ የቆዩ ሲሆን በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዩኒቨርሲቲዎች ከጥር 1 አንስቶ ባሉት 2 ሳምንታት ትምህርት እንደሚጀምሩ ማሳወቁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia