TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በትግራይ የኤሌክትሪክ ኃይል ለምን ተቋረጠ ?

የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ከነሃሴ 21 /2015 ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ በመላ ትግራይ መቋረጡ ተገልጿል።

ከኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት ትግራይ ቅርንጫፍ በተገኘው መረጃ መሰረት አገልግሎቱ የተቋረጠው በመኾኒ ባጋጠመ የመስመር መቋረጥ ነው።

ችግሩን ዛሬ እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ ለመፍታት አስቀደመው ወደ ተላኩ ባለሙያዎች ተጨማሪ የሰው ኃይል መላኩን በኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት የትግራይ ቅርንጫፍ የኦፕሬሽን ትራንስሚሽን ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ገ/እግዚአብሄር ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን  ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " የእንጀራ ዋጋ በመጨመሩ በልተን ለማደር ተቸግረናል " - ነዋሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ከጤፍ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ የእንጀራ ዋጋ በመጨመሩ በልተው ለማደር መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። ለሪፖርተር ጋዜጣ ቃላቸውን የሰጡ የከተማው ነዋሪዎች ፤ ሰሞኑን የአንድ እንጀራ ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረበት 17 ብር ወደ 22 እና 24 ብር ከፍ በማለቱ፣ ገዝተው ለመጠቀም ተቸግረዋል፡፡ እንጀራን…
የዳቦ እና እንጀራ ዋጋ ስንት ገባ ?

በአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች (የመኖሪያ መንደሮች) የአንድ ትንሹ ዳቦ ዋጋ ከወራት በፊት ከነበረበት 4 እና 5 ብር አሁን  ላይ 9 -10 ብር መድረሱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

የዳቦ ዋጋ ባለፈው ዓመት 5 ብር በገባበት ወቅት ብዙ ሲባል የነበረ ሲሆን በተወሰኑ ወራት ልዩነት እጥፍ በሚያስብል ደረጃ እንደጨመረ አመልክተዋል።

ሁሉም ነገር የአንድ ሰሞን የማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ይሆንና መፍትሄ ሳይሰጠው በዛው ይቀጥላል ፤ የኑሮው ጫና እጅግ እየከበደ ነው ብለዋል።

መፍትሄው ግራ የሚያጋባ ነው ያሉት አስተያየታቸውን የላኩ የቤተሰባችን አባላት ፤ የአንድ ዳቦ ዋጋ ቀስበቀስ እየጨመረ መጥቶ ወደ 10 ብር ተጠግቷል ፤ ከዚህ ቀደም ጨመረ ተብሎ ለተነሳው ሮሮ መፍትሄ ሳይሰጥ #እንድንለማመደው ተደረገ አሁንስ እንዲሁ ይቀጥላል ? ሲሉ ጠይቀዋል።

ከሰሞኑን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከጤፍ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ የእንጀራ ዋጋ በመጨመሩ በልተው ለማደር መቸገራቸውን መገለፃቸው ይታወሳል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፤ ሰሞኑን የአንድ እንጀራ ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረበት 17 ብር ወደ 22 እና 24 ብር ከፍ በማለቱ፣ ገዝተው ለመጠቀም መቸገራቸውን ገልጸው እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዳቦ እና እንጀራ ዋጋ ስንት ገባ ? በአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች (የመኖሪያ መንደሮች) የአንድ ትንሹ ዳቦ ዋጋ ከወራት በፊት ከነበረበት 4 እና 5 ብር አሁን  ላይ 9 -10 ብር መድረሱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። የዳቦ ዋጋ ባለፈው ዓመት 5 ብር በገባበት ወቅት ብዙ ሲባል የነበረ ሲሆን በተወሰኑ ወራት ልዩነት እጥፍ በሚያስብል ደረጃ እንደጨመረ አመልክተዋል። ሁሉም ነገር የአንድ…
" ኑሮውን አልቻለነውም "

እጅግ በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በየአካባቢያቸው የዳቦና የእንጀራ ዋጋ አሁን ላይ የደረሰበትን ጠቁመዋል።

ከአዲስ አበባ ውጭ በክልል ከተሞች አንድ ትንሽ ተብሎ የሚታሰበው ዳቦ ከ5 ብር - 9 ብር ድረስ እንደየአካባቢው የሚሸጥ ሲሆን እንጀራ ከ15-20 ብር ድረስ ይሸጣል ፤ የፀጥታ ችግር ባለባቸው ቀጠናዎች ዋጋው እጅግ ተለዋዋጭ መሆኑን የገለፁት ቤተሰቦቻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ኑሮው እጅግ መክበዱን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግ ተማፅነዋል።

ከአዲስ አበባ የተለዩ አካባቢዎች በመጡት መልዕክቶች ምንም እንኳን እንደየአካባቢው ቢለያይም አንድ እንጀራ ያውም ስስ እንጀራ ከ20-25 አንዳዴም ደህና እንጀራ ከሆነ እስከ 27 ብር እንደሚሸጥ ጠቁመዋል።

ዳቦም በተመሳሳይ ዋጋው ቀስበቀስ እየጨመረ አሁን ላይ እስከ 10 ብር (ትንሽ የሚባለው) የሚሸጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ሲሉ ገልጸዋል።

የዋጋ መጨመር ብቻ ሳይሆን ጣራቱና መጠኑም መቀነሱን ሳይናገሩ አላለፉም።

አንድ በአዲስ አበባ በግል ስራ የምትተዳደር የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ " ጮኸን ጮኸን ደክሞናል ፤ መፍትሄ የሚሰጠንም አጥተናል። እኔ የማገኘው ገንዘብ ደህና ኑሮ ሊያኖረኝ ቀርቶ በልቶ ለማደርም ስለማይበቃ ከቤተሰቦቼ ጭምር ይላክልኛል " ብላለች።

አንድ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ " በጣም ከባድ ነው ፤ እኔ ነጋዴ ነኝ እገዛለሁ አትርፌ እሸጣለሁ ነገር ግን ማህበረሰቡ ያሳዝነኛል፤ በተለይ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኛ እንዴት ከ3000 ባነሰ ደመወዝ እንደሚኖሩ ሳስብ እገረማለሁ፤ ዱቄት 1200 ብር በላይ ጨምሯል፤ ዳቦ 10 ብር ነው፤ እንጀራም 20 ብር ነው ብቻ ይከብዳል፤ በጣም የማዝነው ደግሞ ጊዜው ላለው በመሆኑ ነው፤ መናገር የምፈልገው ነገር በዚህ የኑሮ ውድነት ላይ ከድሃ ጎሮሮ ላይ ቀምተው ሀብታም ለመባል የሚፈልጉትን ነው ሁሉም ሟች ነው ይህን እወቁት " ሲል ሀሳቡን ገልጿል።

ሌላ ነዋሪ እሱ ባለበት አካባቢ የእንጀራ ዋጋ የቤት የሚባለው 27 ብር እንደሚሸጥ የሱቅ ተብሎ ደግሞ የሚሸጠው 24 ብር መሆኑን ጠቁሞ ገዝቶ መግባት እንደከበደው ጠቁሟል።

አንዲት የቤተሰባችን አባል፤ እኛ ስቃይ ላይ ነን ዋጋውን ብንናገር ከወሬ የዘለለ መፍትሄ የለም ስትል ገልጻለች።

ሌላ ነዋሪ፤ ዛሬ ዳቦ መግዣ የሚባለው ከአንድ አመት በፊት የእንጀራ ዋጋ ነበር፤ በጣም ከባድ ነው ሲጨምርም መጠነኛ ቢሆን ጥሩ ግን ሁሉም ነገር እጥፍ በሚባል ሁኔታ ነው እየጨመረ ያለው ብሏል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ደግሞ፤ " ነገሩ በሶሻል ሚዲያ እየተወራ ስለሆነ ነው በሁሉም አካባቢ ዋጋዉ የጨመረው " ብለዋል።

" ለምን ዋጋ ጨመራቹ ሲባሉ ሚዲያ ያለቸው
ናቸው ነገሩ እያባባሱት ያሉት በቀናት ልዩነት
ከ15 ብር ወደ 17 ብር ከዛ ወደ 20 ብር፤ ዛሬ ደግሞ 22 ገባ የሚለው የሶሻል ሚድያ ወሬ ይሰሙና እንጀራ 22 ብር ገባ ማለታቸው የማይቀር ነው " ሲሉ ገልጻዋል።

" መልስ ሊሰጠው ካልተቻለ በሶሻል ሚዲያ ላይ ባይነገር ይሻላል " ብለዋል።

በርከት ያሉ የቤተሰባችን አባላት የሀገሪቱ የሰላም ሁኔታ አስተማማኝ ተደርጎ ፣ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ግጭት እና ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ በሙሉ ኃይል ወደ ምርት ካልተገባ ፤ ዜጎችም ደህንነታቸው ተጠብቆ በሀገራቸው እንደልብ ቀንና ማታ እየተጓዙ ያለስጋት ካልሰሩ ያለው ሁኔታዎች ከዚህ እንዳይከፋ እንደሚያሳስባቸው ገልጻዋል።

ህዝባችን ያለበት ጫና ይመለከተናል የሚሉ አካላትም ቀስ በቀስ እየጨመረ እና ዜጎችም በማይችለው አቅማቸው እንዲለማመዱት እየተደረገ ያለው በተለይ በምግብ ዋጋ ላይ የሚታየውን ከፍተኛ ጭማሪ እንዲቆጣጠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Addis Lissan Hamle 29-2015 ZM (1).pdf
" ውል ማዋዋል የምንጀምረው ረቡዕ ነው "

የ5ኛዉ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤቶች ግልጽ ጨረታ አሸናፊዎችን ውል ማዋዋል የሚጀመረው ከረቡዕ 24/12/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገልጿል።

አሸናፊዎች ይህ ተረድተው ለመዋዋል የሚጠበቅባቸውን ሰነድ አሟልተው እንዲቀርቡ ማሳስቢያ ተላልፏል።

ለዉል ሲኬድ ምን ማሟላት ይገባል ?

1ኛ. የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ሁለት ኮፒ
2ኛ. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN /
3ኛ. የጋብቻ ሁኔታን የሚገልጽ ማስረጃ ዋናውን እና ሁለት ኮፒ
4ኛ. አራት/4/ ጉርድ ፎቶ
5ኛ. የዉጭ ሀገር ዜግነት ያለዉ ከሆነ ካለበት ሀገር የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚሰጥ መታወቂያ እና ሙሉ የቤቱን ዋጋ 100% መክፈል ይጠበቅበታል፡፡

@tikvahethiopia
#BekeleGerba #USA🇺🇸

አቶ በቀለ ገርባ በአሜሪካ ሀገር #ጥገኝነት መጠየቃቸውን አሳወቁ።

ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በግል እና በፓርቲ ደረጃ ተሳታፊ የነበሩት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ተቀዳመ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ በቀለ ገርባ በፓርቲያቸው የነበራቸውን ተሳትፎ አብቅተው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናገሩ።

አቶ በቀለ ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ " በሰላማዊ መንገድ ለመታገልም ሆነ በግል በነጻነት መኖር " አሳሳቢ በመሆኑ በሄዱበት አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል የሆኑት አቶ በቀለ፣ በውጭ አገር ሆነው ሥልጣኑን ይዘው መቀጠጣለቸው ጠቃሚ ስላልሆነ እራሳቸውን ከፓርቲው ለማግለል መወሰናቸውን ተናግረዋል።

አቶ በቀለ ገርባ ፤ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተፈጥሮ የነበረውን ሁከት ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ውለው ለ18 ወራት በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። አሜሪካ ከሄዱ 1 ዓመት ከሶስት ወር ሆኗቸዋል።

አቶ በቀለ ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ዓላማቸው የእርሳቸውን ከእስር መለቀቅ ሲጠይቅ ለነበረው የዳያስፖራ ማኅብረሰብ ምስጋና ለማቅረብ ነበር።

ነገር ግን አሜሪካ በቆዩባቸው ያለፉት 15 ወራት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በመቀየሩ " ወደዚያ አገር መመለሱ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም "  በማለት እዛው ጥገኝነት መጠየቃቸውን እና ከፓርቲው ኃላፊነትም እራሳቸውን ማግለላቸውን ለቢቢ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

More - https://telegra.ph/BBC-08-28-2

@tikvahethiopia
Jasiri is a regional hub, dedicated to driving development in the wider East African area.

We carefully select candidates from Ethiopia, Rwanda, and Kenya to take part in our programs, which are designed to make a meaningful contribution to the African Union's vision of a progressive, dynamic, and united Africa.

Application to join our Cohort 5 is ongoing, apply today at http://jasiri.org/application

#Jasiri4Africa
በኮፔይ ኢብር ይክፈሉ!
የነዳጅ ክፍያዎን
ቀላል እና ፈጣን ያድርጉ!
@coopbankoromia
" ከKG-12 ክፍል የያዘ ሞዴል ትምህርት ቤት ከፍቼ ጥራት ያለውን ትምህርት እንድሰጥ እውቅና አግኝቻለሁ " - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደሙ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ዓመት ከዚህ ቀደም ይሰጥ የነበረውን የማህበረሰብ አገልግሎት አድማስ እንደሚያሰፋ ዛሬ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ኮሌጁ አስተባባሪነት ከKG-12 ክፍል የያዘ ሞዴል ትምህርት ቤት ከፍቶ ጥራት ያለውን ትምህርት ለመስጠት ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ት/ቢሮ እውቅና ማግኘቱን አሳውቋል።

በ2016 ዓ.ም. የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁን የገለፀው ተቋሙ የመመዝገቢያ ጊዜና መስፈርቶቹን በቅርቡ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን አቀባበል ስለሚደረግ የተወሰኑ መንገዶች ይዘጋሉ ብሏል።

ቡድኑ ነገ ነሀሴ 23 ቀን 2015 ዓ/ም ከቦሌ ኤርፖርት ጀምሮ እስከሚያርፉበት ሂልተን ሆቴል ድረስ የአቀባበል ስነ ስርዓት እንደሚደረግለት ተገልጿል።

በዚህም ነገ ከጠዋቱ 1፡00 ሠዓት ጀምሮ፡-

👉 ከኤርፖርት በቅዱስ እስጢፋኖስ ወደ አራት ኪሎ

👉 ከራስ መኮንን ድልድይ በደጎል አደባባይ ወደ ቸርችል ጎዳና

👉 ከድላችን ሀውልት በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ከዚያም በሚያርፉበት ሂልተን ሆቴል አካባቢ ለተወሰነ ሰዓት መንገዱ ይዘጋል ተብሏል።

አሽከርካሪዎች ይህን በመገንዘብ በቦታው የሚገኙ የትራፊክ ፖሊስ አባላትን መረጃ በመጠየቅና ተባባሪ በመሆን  ትብብር እንዲያደርጉ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒና ውድድር ላይ የተካፈለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ ከኬንያ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ የዓረና ሊቀመንበር ሆኑ።

የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉዓላዊነት ፓርቲ (ዓረና) ባካሄደው  5ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ አቶ ዓምዶም ገብረስላሴን ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል።

አቶ ካሕሳይ ዘገየ ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር ሁነው እንዲያገለግሉ መመረጣቸው ተነግሯል።

Via Abrha Desta

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ የኤሌክትሪክ ኃይል ለምን ተቋረጠ ? የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ከነሃሴ 21 /2015 ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ በመላ ትግራይ መቋረጡ ተገልጿል። ከኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት ትግራይ ቅርንጫፍ በተገኘው መረጃ መሰረት አገልግሎቱ የተቋረጠው በመኾኒ ባጋጠመ የመስመር መቋረጥ ነው። ችግሩን ዛሬ እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ ለመፍታት አስቀደመው ወደ ተላኩ ባለሙያዎች ተጨማሪ የሰው ኃይል መላኩን…
#Update

መቐለ ጨምሮ በመላ ትግራይ ከነሃሴ 21 ሌሊት ጀምሮ  የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት መቋረጡ ይታወቃል።

በመቐለ ከተማ ዛሬ ነሃሴ 22/ 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት መሰጠት ጀምሮ አንድ ሰዓት ሳይሞላ ከፊሉ የከተማው አከባቢ ጠፍቶ ከፊሉ አገልግሎቱ በማግኘት ላይ መሆኑ የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ መረጃ አድርሶናል።

የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ከነሃሴ 21 ሌሊት ጀምሮ በመላ ትግራይ የተቋረጠው መኾኒ ላይ ባጋጠመ የመስመር ችግር መሆኑን የኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት ትግራይ ቅርንጫፍ ማሳወቁ ይታወቃል።

ችግሩን ለመፍታት ርብርብር እየተደረገ እንደሆነ ተነግሯል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia