TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ትግራይ አስመልክቶ በብድር ወለድ አከፋፈል  ያወጣው መመሪያ መልሶ እንዲያጤነው ተጠየቀ።

የመቐለና የዓዲግራት የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ለቲክቫህ የትግራይ ቅርንጫፍ ቤተሰብ በሰጡት ቃለመጠይቕ ብሄራዊ ባንክ የተለያዩ ባንኮች ከጦርነቱ በፊት  ለትግራይ የንግድ ማህበረሰብ የሰጡት በድርና አመላለሱ አስመልክቶ ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ.ም ያወጣው መምሪያ ዳግም ሊጤን ይገባዋል ብለዋል።

የመቐለ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ አቶ በርሀ አርከበ በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ የንግድ ማህበረሰብ የደረሰው ኢኮኖሚያ ፣ ሰብአዊና ማህበራዊ ኪሳራ እጅግ ግዙፍ ነው። ጉዳቱ እጅግ እጅግ ከባድ ነው፤ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ ብቻ ለይተን ብናይ የንግድ ማህበረሰቡ አካላዊ ጥቃት ደርሶታል። ተዘርፈዋል ፤ ኪሳራ አጋጥሞታል ብለዋል።

የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ያጋጠመውን ኪሳራ የሚሽር አሰራር ያወጣል ብለን እንጠብቅ ነበር ያሉት ዋና ፀሃፊው ፤ ይሁን እንጂ ብሄራዊ ባንክ ከተለያዩ ባንኮች የተወሰደው በድር ከነወለዱ ይከፈል የሚል መመሪያ ማውጣቱ በንግድ ማህበረሰቡ ዘንድ ድንጋጤ እና መረበሽ ፈጥረዋል ብለዋል።

ብሄራዊ ባንክ ያወጣው እጅግ አስደንጋጭና ተስፋ አስቆራጭ መመሪያ በሰላም ስምምነቱ ምክንያት በንግድ ማህበረሰቡ የተፈጠረውን መነቃቃትና መነሳሳት ያደበዘዘ ነው ያሉት የዓዲግራት የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕረዚደንት አቶ ዲበኩሉ አለም በርሃነ በበኩላቸው ፤ ብሄራዊ ባንክ ያወጣው መመሪያ እንዲሻር የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች ለክልሉ ግዚያዊ አስተዳደርና ለብሄራዊ ባንክና ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበናል ብለዋል።

በትግራይ የንግድ ማህበረሰብ የደረሰው ውድመትና ያጋጠመው ኪሳራ የክልሉና የፌደራል መንግስት ተወያዮቹ እንደ አንድ ኢኮኖሚያዊ የመወያያ አጀንዳ ማየት ይገባቸዋል ያሉት አቶ ዲበኩሉ ፤ ብሄራዊ ባንክ ያወጣው መምሪያ የሚያስትለው ኢኮኖሚያዊ ቅጣት የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ የሚያቀጭጭ ፤ ከገበያ ውድድር የሚያስወጣ በውጤቱም ክልሉንና አገርን የሚገዳ በመሆኑ የፌደራል መንግስት ለችግሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መፍታት አለበት ሲሉ አክለዋል።

'አገራዊ ፋይዳ ያላቸው እቃዎች እና ምርቶች ከውጭ ለሚያስገቡ ተጨማሪ ብድርና የውጭ ምንዛሬ ቅድሚያ እንዲያገኙ የሚል ብሄራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ የተካተተው ለንግድ ማህበረሰቡና ለአገር ጠቃሚ እንደሆነ የተናገሩት የመቐለ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ አቶ በርሀ አርከበ ፤ ከጦርነት በፊት በክልሉ ለተወሰደው የብድር ወለድ አንዲነሳ አለማድረግ ነጋዴው ተጨማሪ ብድር  እንዳይወስድ ስለሚከለክል እጅግ ጎጂ ነው ብለዋል።

ከተለያዩ ባንኮች የተወሰደው የብድር ወለድ ይነሳ ሲባል ባንኮች ለኪሳራ እንደሚዳረጉ እንገነዘባለን ያሉት አመራሮቹ ፤ ለኪሳራ ማካካሻ የሚሆን መፍትሄ ከፌደራል መንግስት፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ፣ ከብሄራዊ ባንክን ከገንዘብ ሚኒስቴር ይጠበቃል ብለዋል።

በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት 4.3 ሚሊዮን ቆጣቢዎች 70 ቢሊዮን ብር ቆጠብው ፣ ከጦርነቱ በኋላ ወለድ ጨምሮ 90 ቢሊዮን መድረሱ ፣ በብድር የተወሰደው 35 ሚሊዮን ብር ከጦርነቱ በኋላ ወለድ ጨምሮ 50 ቢሊዮን ብር መድረሱ የክልሉ የፋይንናስ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ያካሄዱት ጥናት ያመለክታል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-23-2

@tikvahethiopia
#Update

የመውለጃ ቀናቸው የደረሰ ነፍሰ ጡር እና ጡት የሚያጠቡ ሴት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሚቀጥለው ዓመት እንደ መደበኛ ተፈታኝ መፈተን እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

" መውለጃ ወራቸው የደረሰ ነፍሰ ጡር እና ጡት የሚያጠቡ ሴት ተፈታኞች በሚቀጥለው ዓመት ተዘጋጅተው እንደ መደበኛ ተፈታኝ እንዲፈተኑ እንመክራለን " ብሏል አገልግሎቱ።

" ሆኖም ለመፈተን የወሰኑ ጡት የሚያጠቡ ተፈታኞች አንድ ሴት ሞግዚት ይዘው በመግባት እንዲፈተኑ ተገቢው ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑን " አገልግሎቱ ገልጿል።

የተፈታኞች መብትና ግዴታ እንዲሁም የተከለከሉ ነገሮች በተፈታኟና በሞግዚቷ ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን አገልግሎቱ ጠቁሟል።

Via @tikvahuniversity
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም
=========
 ፋይል ጠፋ አልጠፋ ብለው ከመጨነቅ ይገላግልዎታል፣
 አንድ ቦታ ሆነው ሁሉ ቦታ ያደርስዎታል፣
 የመምህራንና የወላጆች መረጃ፣ እጅግ ዘመናዊ የክፍያ አሰባሰብና የቅጣት መቆጣጠሪያ ሥርዓት እንዲሁም ሌሎችም ጥቅም የሚያገኙበት
 በአዋሽ ኢ-ስኩል ቤተ መጽሀፍት የተለያዩ ለትምህርት አጋዥ የሆኑ መጽሀፍትን የሚያገኙበት
 ያሉበት ቦታ ሆነው የገፅ ለገፅ ትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችልዎታል፡፡
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም የግዜው ውድ ስጦታ!
አዋሽ ባንክ!
https://eschool.awashbank.com/

Telegram: https://publielectoral.lat/awash_bank_official
#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ የሚሰተዋለዉ የሞተር ስርቆት ትኩረት ያሻዋል ሲሉ  ነዋሪዎች ገለጹ።

ፖሊስ በበኩሉ  በተዘረጉ ጠንካራ የጸጥታ ሰንሰለቶችና በከተማዉ ዋና ዋና መንገዶች በተተከሉ ካሜራዎች በመታገዝ ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ላይ መሆኑን አስታዉቋል።

ቅሬታቸዉን ካጋሩን የከተማዉ ነዋሪዎች  መካከል  መምህር  ወንድሙ በየነ ከወራት በፊት መንገድ ዳር ያቆሙት ሞተር ጠፍቶባቸዉ ለፖሊስ ቢያመለክቱም መፍትሄ እንዳልተሰጣቸዉና ሞተራቸዉ ጠፍቶ መቅረቱን ይገልጻሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ግቢያቸዉ ዉስጥ ያቆሙት ሞተር የተሰረቀባቸዉ አሰተያየት ሰጭም በተመሳሳይ ሞተራቸዉ ጠፍቶ መቅረቱን ያወሳሉ ።

በዚህ ጉዳይ ምን እየተሰራ ነዉ ስንል ላነሳነዉ ጥያቄ ምላሽ የሰጡን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር  መልካሙ አየለ ችግሩ በሚነገርለት ደረጃ አለመሆኑን  ገልጸዉ ፖሊስ ችግሩን ለመፍታት ባደረገዉ የተቀናጀ ጥረት ጥሩ ዉጤት መመዝገቡን ያነሳሉ።

ኢንስፔክተሩ አክለዉም በቅርቡ በከተማዉ ዋና ዋና መንገዶች  የተተከሉ  ካሜራዎች ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ መሆኑንና በዚህ አመት ብቻ 41 የተሰረቁ  ሞተሮችን  ለባለቤቱ በመመለስ ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረባቸዉን ያነሳሉ።

በመሆኑም አሁን ላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ ካሉ ሰላማዊ ከተሞች አንዷ ሀዋሳ መሆኗን በማንሳት  ከተማዉን ከዚህ በተሻለ ሰላማዊ ለማድረግ ግን የሁሉም ነዋሪ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
' ሕዝበ ውሳኔ ' የአማራ ክልል መንግሥት የማንነት እና የወሰን ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ እንዲፈታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ሲል አሳወቀ። የክልሉ መንግሥት ይህን ያሳወቀው ዛሬ በኮሚኒኬሽን ቢሮው በኩል በሰጠው መግለጫ ነው። የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫቸው ፤ የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ጥያቄ የሚያነሱባቸውን የማንነት እና የወሰን ጉዳዮችን…
" እኛ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ እየጠበቅን ነው " - ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ

የአማራ እና የትግራይ ክልሎች የሚዋሰኑባቸውን የወልቃይት፣ የጠለምትና የራያ አካባቢዎችን " ይገባኛል " ጥያቄን በተመለከተ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ እየተጠበቁ መሆናቸውን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል አሳውቀዋል።

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በአሁን ሰዓት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ  ምክትል አስተዳዳሪ እና የሰላምና የፀጥታ መምርያ ኃላፊ በመሆን እያገለገሉ ሲሆን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ በቀረቡበት ወቅት " ሁለቱ ክልሎች የሚዋሰኑባቸውን አካባቢዎች በሕዝብ ውሳኔና በሕጋዊ መንገድ መፍታት አለባቸው " በሚል ስለሰጡት አስተያየት ተጠይቀው መልሰዋል።

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ምን አሉ ?

" በወልቃይት ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ እናደርጋለን ሲሉ በግልጽ አልሰማንም፡፡

ነገር ግን በሕጋዊ መንገድ ቢፈታ ይሻላል የሚለውን ምክር አዘል ነገር ለፓርላማው ሲናገሩ ሰምተናል፡፡

ግን በዚህኛው ቀጣና በዚህኛው ዞን ብለው ሲያነሱ እኔም በግል አልሰማሁም፣ እኛም የምናውቀው ነገርም የለም። ነገር ግን የወልቃይት ጉዳይ በየትኛው መንገድ ነው ሊፈታ የሚገባው የሚለውን ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ተናግረናል፡፡

ሊፈታ በሚገባው መንገድ እንዲፈታ ለመንግሥት አመልክተናል።

ራያም፣ ጠለምትም፣ ወልቃይትም ስላሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለየትኛው እንደተናገሩ ግልጽ አልሆነልኝም። በግምት መልስ ለመስጠት ያስቸግራል።

ብዙ ሰው መላምት ሊኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን የወልቃይት ጉዳይ ሊፈታ የሚገባበትን መንገድ ጠቅሰን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ስላቀረብን ውሳኔውን እየጠበቅን ነው።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅትም ሆነ አሁን ከማኅበረሰቡ ጋር ነኝ ፤ የአገር መከላከያ ሠራዊት የወልቃይት አካባቢን እየተከላከለና እየጠበቀ እንዳለ ነው የምናውቀው።

በአካባቢው ከመከላከያ ጋር ምንም ዓይነት ጦርነት የለም፣ ተባብረን ነው እየሠራን ያለነው፡፡ አካባቢው ሰላማዊ በመሆኑ ፋኖ በሚል ምክንያት ምንም ዓይነት ግጭትም ሆነ ጦርነት የለም። "

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር በበኩሉ የክልሉ አስተዳደራዊ ወሰን ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት እንዲመለስ፣ በጦርነቱ ምክንያት ከምዕራብ ትግራይና ከሌሎች የአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የክልሉ ነዋሪዎቸ በአፋጣኝ ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ በተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረበ ነው፡፡

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የፌዴራል ፖሊስ ለልጆቻችሁ #ሙሉ_ኃላፊነት ይወስዳል ፤ አስተማማኝ ጥበቃም ያደርግላቸዋል " - የጋምቤላ ትምህርት ቢሮ ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የፀጥታ ችግር መከሰቱና የሰዎች ህይወት ማለፉ ፣ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም በክልሉ የሰዓት እላፊ ገደብ ታውጆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ…
#NewsAlert

በጋምቤላ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ቦታዎች እንዲሰጥ ተወሰነ።

በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ እና በጋምቤላ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደሚሰጥ የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ፤ " በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ብቻ ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ያለውን ጫና ለመቀነስ ታስቦ ፈተናው በኮሌጅም ጭምር እንዲሰጥ ተወስኗል " ብሏል።

የክልሉ መንግስት ውሳኔውን ያሳወቀው ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ መግባት ጀምረዋል።

በተለይም በ #ኑዌር_ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ መግባት መጀመራቸው ተገልጿል።

#አኙዋ_ዞን፣ በከፊል ከ #ኢታንግ ልዩ ወረዳና ከ #ጋምቤላ_ከተማ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ በጋምቤላ ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በነገው ዕለት እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት ወደተመደቡበት የመፈተኛ ጣቢያ በመሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የክልሉ መንግስት አሳስቧል።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርና ሀገር አቀፍ የፈተናዎች አገልግሎት ከክልሉ መንግስት ጋር በመነጋገር ነው በሁለት ቦታ ፈተናው እንዲሰጥ የተወሰነው።

መረጃው ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም
=========
ከጊዜው ጋር እየተሽቀዳደመ ከዘመኑ ጋር አብሮ እየዘመነ የመጣው አዋሽ ባንክ ት/ቤቶች ትውልድን ለመቅረፅ ያለባቸው ትልቅ ሃላፊነት በመረዳትና የትምህርት ጥራትን ለማሳካት በማሰብ የዲጂታል ትምህርት አስተዳደር ሥርዓት ወይም የኢ-ስኩል ሲስተም ቴክኖሎጂን አቀረበልዎ!
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም የግዜው ውድ ስጦታ!

Learn More- https://eschool.awashbank.com/
#AwashBank #Awash #ESchool #Management #System #Ethiopia #ኢትዮጵያ

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉 https://publielectoral.lat/awash_bank_official
🔊🔊🔊 Cohort 5 Application Now Open at http://jasiri.org/application

Jasiri's mission is to attack poverty. Hence we are driven by a need to address the fast-growing challenge of unemployment for young Africans.

The path to prosperity and equal opportunity in Africa lies in high-potential individuals becoming high-impact and responsible entrepreneurs.

Through the Jasiri Talent Investor, we present an entrepreneurial development intervention in the Eastern African Region, aimed at motivating, supporting, enabling, and spurring value-based responsible entrepreneurs to succeed.

We have succeeded with our previous Cohorts, and look forward to welcoming entrepreneurial gems from across Kenya, Ethiopia, and Rwanda to our Cohort 5.

Apply now at http://jasiri.org/application
#ጋምቤላ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የጋምቤላ ክልል አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩ የትጥቅ ግጭቶችን፣ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃቶችንና አጠቃላይ የጸጥታ ችግሮችን እና በዚህ ሳቢያ የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ተጎጂዎችን፤ የአካባቢዎቹን ነዋሪዎች እንዲሁም የክልሉን የጸጥታ እና የአስተዳደር ኃላፊዎችን በማነጋገር ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

በተለይ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ላለው የጸጥታ ችግር መነሻ፣ በኢታንግ ልዩ ወረዳ በተወሰነ ነዋሪዎች መካከል የተነሳ አለመግባባት መሆነ ማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ይሄው አለመግባባት በፍጥነት ወደ ብሔርን መሠረት ያደረገ ውጥረት እንደተሸጋገረ ነዋሪዎች ያስረዳሉ።

ይህንኑም ተከትሎ የተለያየ ብሔር ታጠቂ ቡድኖች በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ጎግ ወረዳ፤ በጋምቤላ ከተማ ብሔር ብሔረሰቦች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እና በከተማው በሚገኙ ሌሎች ሰፈሮች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በርካታ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀል እና ንብረት ውድመት ደርሷል።

ኢሰኮ በጸጥታው ችግር ምክንያት ገና ወደ አካባቢዎቹ በአካል ደርሶ ምርመራ ለማድረግ ያልቻለ ቢሆንም፣ ነዋሪዎች በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ መንደሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የወደሙ መሆናቸውን አስረድተዌ።

ጋምቤላ ክልል በተደጋጋሚ ከጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን በሚመጡ ታጣቂ ቡድኖች በሚደርሱ ጥቃቶች፣ እንዲሁም አልፎ አልፎ በክልሉ በሚኖሩ ብሔሮች መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስ መሆኑ እንደሚታወቅ ኢሰመኮ በመግለጫው አመልክቷል።

ክልሉ ወደ 350 ሺህ የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን በስምንት የተለያዩ ካምፖች ያስተናግዳል።

ከሁለት ወራት በላይ ለዘለቀው የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ችግር እና በክልሉ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በመድረስ ላይ ያሉ ግጭቶች ተሳታፊዎችን በተመለከተ ተጎጂዎችም ሆነ የክልሉ የጸጥታ እና የአስተዳደር ኃላፊዎች የተለያዩ ብሔር ታጣቂ ቡድኖችን ኃላፊነት ይጠቅሳሉ።

በአንዳንድ አካባቢዎች የክልሉ ኑዌር ብሔረሰብ ታጣቂዎች፣ በሌላ አካባቢ የአኝዋ ብሔረሰብ ታጣቂዎች፣ እንዲሁም ከጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች እና በአንዳንድ የስደተኛ ካምፖች ውስጥ አንደሚኖሩ የተገለጸ ሰዎች ጭምር በግጭቶቹ ተሳታፊ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡

እነዚህ ጥቃቶች እና ግጭቶች በአብዛኛው ብሔር ተኮር ሲሆኑ በሌላ በኩል ግጭት የሚደርስባቸውን አካባቢዎች ያለ የብሔር ልዩነት ሁሉንም ነዋሪዎች አካባቢውን ሸሽቶ ለመፈናቀል፣ ለንብረት ውድመት እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ያጋለጠ ነው ሲል ኢሰመኮ አመልክቷል።

የክልሉ ጸጥታ ሁኔታ በነዋሪዎች ላይ ያደረሰው ከፍተኛ ጉዳት እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰትም የመንግሥትን ተጨማሪ ትኩረት የሚሻ መሆኑን አስገንዝቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ሀዋሳ

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀምሌ 19 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ክብረ ንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።

ለበዓሉ ሰላማዊነት ከመምሪያውና 8ቱም ክ/ከተማ ፖሊስ ማናጀመት ፣ከ8ቱም ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች፣ ለፀጥታው አጋዥ ከሆኑ ሀይሎች ፣ ከሀይማኖት አባቶች ፣ ከሁቴል ባለቤቶች ፣ከየክፍለ ከተማ የተደራጅ ማህበራት ጋር ውይይት ተደርጓል።

ፖሊስ ከፀጥታ ኃይሉ እና ከአጋዥ ኃይሎች በተጨማሪ በከተማው በተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎች  የፀጥታውን ስራ አስተማማኝ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጾ የደህንነት ካሜራዎች ተደራሽ ባልደረገባቸው ቦታዎችን ካሜራ የመግጠም ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል።

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም የበዓሉ ታዳሚያን በጠቅላላ አከባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁና የወንጀል ድርጊትም ሲመለከቱ ለፖሊስ እንዲጠቁሙ መልዕክት ተላልፏል።

በተመሳሳይ የሲዳማ ክልል የፀጥታ ግብረሃይል ፤ በዓሉ በሰላም እንዲከበር በቅ የፀጥታ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ መገባቱን እና ለፀጥታ ኃይሉ ስምሪት መሰጠቱን አሳውቋል።

ከበዓሉ ጋር በተያያዘ የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ እንዳይከሰት
ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችንም ይፋ አድርጓል።

በዚህ መነሻ ከሐምሌ 18/04/2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ፦
1. ከሎጊታ - ሱሙዳ ገብርኤል
2. ከማር ስል ቤተክርስቲያን - ሱሙዳ ገብርኤል
3. ከዋርካ አደባባይ - ሱሙዳ ገብርኤል
4. ከዳሽን- ሱሙዳ ድረስ ያሉ መንገዶች በዓሉ ተከብረው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

ህብረተሰቡ ማንኛውን ጥቆማ ካለው በ0462209164  እና 046 212 2468 ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን  እንዲሁም በ0462201046 ለሀዋሳ ፖሊስ መምሪያ ጥቆማ መስጠት ይችላል።

ሀዋሳ የሚከበረው የሀምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ላይ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር እጅግ በርካታ እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#ቁልቢ

ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር ወደ ስፍራው የሚመጡ ምዕመናንና እንግዶችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅት ማድረጉን ፖሊስ አሳውቋል።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ እና የበዓሉ የጸጥታ ኮማንድ በመጪው ረቡዕ በሚከበረው ዓመታዊ የቁልቢ ንግስ በዓል ላይ ከተለያየ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ብዛት ያላቸው ምዕመናን፣ ቱሪስቶችና ሌሎችም እንግዶች ወደ ስፍራው እንደሚመጡ ይጠበቃል ብለዋል።

የምዕመናኑን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅም ከምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፣ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ ከሐረሪ ክልል እና ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከመከላከያ ሠራዊት፣ ብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ጋር በመቀናጀት ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

የበዓሉ ታዳሚዎች የግል ንብረቶቻቸውን እንዳይሰረቅ በጥንቃቄ በመያዝና የወንጀል ድርጊት ሲመለከቱ በማጋለጥ የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ተብሏል።

በንግስ በዓሉ ላይ ሶስት ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያና ተጠርጣሪ ወንጀለኞችም ሲያዙ ውሳኔ ለመሰጠት ዐቃቤ ህግና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ተቋቁሟል።

ወደ ስፍራው በሚያመራው መንገድ አልፎ አልፎ ያለው አካባቢ የመሬቱ አቀማመጥ ዳገታማ፣ ቁልቁለታማና ጠመዝማዛ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግና ደንብ በማክበር አደጋን ለመከላከል የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል።

ከዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ባለው ዋናው የተሸከርካሪ መንገድ ላይ #ከባድ_መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑንም ተገልጿል።

ምዕመናን ወደ ንግስ ስፍራው በሚመጡበት ወቅት ተገቢነት የሌላቸው አርማና ምልክቶችን ይዘው መገኘት እንደሌለባቸውም ፖሊስ አሳስቧል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia