TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NBE

የኢንሹራንስ ዘርፉ ፤ ከ " ብሔራዊ ባንክ " ውጪ በሆነ ተቆጣጣሪ ተቋም እንዲመራ ለማስቻል ተፈላጊ የሆነው ጥናት በዓለም ባንክ አማካይነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በዓለም ባንክ በኩል የሚደረገው ጥናት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ሰፊ የሆኑ ተግባራትን እንደሚሸፍን ተጠቅሷል።

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ ይህ በተመለከተ ለሪፖርተር ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

አቶ ሰለሞን ደስታ ፦

" የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚቆጣጠር ከብሔራዊ ባንክ ውጪ የሆነ ተቆጣጣሪ እንዲቋቋም ጥናት ተጀምሯል።

Terms of Reference እና ሌሎችም ጉዳዮች እየተሠሩ ነው።

በጥናቱ የመጀመርያ ሥራ ተብሎ የተያዘው ጉዳይ ገለልተኛ ተቋም ‹እንዴት ይዋቀር ? የሚለው ሲሆን ከዚያም ተጠሪነቱ ለማን ይሁን ? ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ነው ? ለፓርላማው ነው ? የሚለውን ጨምሮ ሌሎችም ጉዳዮች ናቸው።

ይህ ብቻም ሳይሆን የኢንሹራንስ ዘርፉን ለውጭ ክፍት ለማድረግ ሪፎርም መደረግ እንዳለበትና ብዙ የሕግ ማዕቀፎች ጎን ለጎን መሠራት ስላለበት ሥራው በአሁኑ ወቅት ተጀምሯል። "

በሌላ በኩል ፦

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ " ለውጭ ተወዳዳሪዎች " ክፍት እንዲሆን ከተወሰነ በኋላ በ2009 ዓ/ም የወጣው የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ የማሻሻል ሥራ እየተጠናቀቀ እንደሆነ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ ፦

" ከአንዳንድ የድጋፍ ሰጪዎች ግብዓቶች ካሉ እየጠየቅን ነው፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥው ከዚህ በፊት ባሉት መሠረት በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ለፓርላማ እናቀርባለን ተብሏል፡፡ ስለዚህ እየተፋጠነ ነው።

አዋጁ እንደወጣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከሦስት እስከ አምስት ለሚጠጉ የውጭ ባንኮች ፈቃድ ይሰጣል ተብሎ ታቅዷል።

ቁጥሩ ከዚያ በላይ ከፍ የማድረግ ዕቅድ የለም፤ ይህም ከአቅም በላይ እንዳይሆን ከሚል ዕሳቤ ነው። " ሲሉ ተናግረዋል።

Credit - Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia
የኢድ አል አድሃ በዓል መቼ ይውላል ?

ዛሬ ጨረቃ በመታየቷ የዙልሒጃ ወር ነገ ሰኞ አንድ ብሎ ይጀምራል።

በዚህም የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሰኔ 21 ዕለተ ረቡዕ እንደሚከበር ታውቋል።

Credit : Haramain / Ustaz Abubeker Ahmed

@tikvahethiopia
#ExitExam

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ " የሀገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ይረዳኛል ፤ ትውልድ እና ሀገርንም ከውድቀት ይታደጋል " በሚል ዘንድሮ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መስጠት ይጀምራል።

ለዚህ ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች በኦንላይን ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና 180 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናው ላይ ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተቋማት ለፈተናው ተማሪዎቻቸውን ዝግጁ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከዚህ የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ፈተናውን የማለፍ የማይችሉ ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው እንዲወስዱ ዕድል ያላቸው ሲሆን በተማሪዎች ምረቃ ላይ ግን የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው።

ይህን የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ሁሉም ተቋማት ለማስፈፀም እየሰሩ ይገኛሉ።

ለአብነት ፤ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ " የመውጫውን ፈተና ያለፉ ብቻ " የመመረቂያ ጋዎን እንዲሰጣቸው ክትትል እንዲደረግ አሳስቧል።

የተቋሙ የሬጅስትራር እና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን በሚመለከት ለሁሉም የተቋሙ አካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራሮች በፃፈው ደብዳቤ የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው " የመውጫ ፈተና አፈፃፀም መመሪያ " መሰረት ፤ ኮርስ አጠናቀው ያልተመዘገቡ እንዲሁም ያልተመዘገቡትና ያልፋቁት " F " ያላቸው ተማሪዎች በስህተት ለመውጫ ፈተና ዝርዝራቸው የተላኩ ካሉ የመውጫ ፈተናውን እንደማይፈተኑ ከወዲሁ እንዲነገራቸውና የመውጫ ፈተና ኮርስም እንዳይመዘገቡ አዟል።

የመውጫ ፈተና " መመዝገብ የሚችሉት " ብቻ ኮርሱን እንዲመዘገቡና የምዝገባ ስሊፕ ለመውጫ ፈተና መግቢያ እንዲያገለግላቸው ከወዲሁ ለተማሪዎች እንዲሰጣቸውም ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ዳይሬክቶሬቱ ፤ ለምረቃ መሟላት ከሚገባቸው መመዘኛዎች በተጨማሪ የመውጫ ፈተና ያለፉ (50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ) ብቻ ለምረቃ እንዲቀርቡ ፤ የምረቃ መስፈርቱን ያሟሉና የመውጫ ፈተና ያለፉ ብቻ የመመረቂያ ጋዎን እንዲሰጣቸው ክትትል እንዲደረግ ዳይሬክቶሬቱ አሳስቧል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዘንድሮ የተማሪዎችን ምረቃ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ ይችላሉ።

More : @tikvahUniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Wolaita

ነገ ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ/ም በዎላይታ ዞን የድጋሜ ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ (ሪፈረንደም) ድምፅ አሰጣጥ ይካሄዳል።

ስለ ሪፈረንደሙ ምን እናውቃለን ?

- የመራጮች ምዝገባ እና የድምፅ መስጠት ሂደት በአንድ ቀን የሚደረግ ይሆናል።

- የቀረቡት ሁለት አማራጮች ናቸው። እነሱም ፦

ነጭ እርግብ ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #እንደግፋለሁ

ጎጆ ቤት ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #አልደግፍም

- ድምፅ መስጠት የሚጀመረው ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ነው።

- በ1,812 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ ይሰጣል ፤ ለዚህም ዝግጅት ተደርጓል።

- ከአዲስ አበባ 5,215 ፤ ከዎላይታ ዞን 3,845 ተመልምለው በቦርዱ የሰለጠኑ አስፈፃሚዎች በምድብ ጣቢያዎቻቸው ላይ ይገኛሉ።

- ከነገ ድምፅ የመስጫ ቀን ጋር በተያያዘ በዞኑ በሚገኙ የፌዴራል እና የክልል መንግስታዊ ተቋማት ስራ አይኖርም።

- ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት #ዝግ ሆነው ይውላሉ።

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሆስፒታሎችን ጨምሮ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት …ወ. ዘ. ተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን ይችላሉ። እንዲዘጉ አይገደዱም።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ ይቀጥላል።

@tikvahethiopia
#ኮፔይ

የነዳጅ ክፍያን ለመፈፀም፣ ኮፔይ ኢብር ፈጣን እና ቀላል አማራጭ መሆኑን ስንገልጽልዎ በታላቅ ደስታ ነው።

የኮፔይ ኢብር መተግበሪያን አውርደው በመጠቀም፣ ጊዜ ሳያባክኑ ወደ ጉዞዎ ይመለሱ !

መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ማስፈጠሪያ ይጠቀሙ ፦ https://bit.ly/45f71CP

#Coopbank #DigitalPayment #Banking
#ኤክሶደስ

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ!

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት፤ አድራሻችን 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን። ስልክ ቁጥር 0979099909/ 0911039377
  √በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://publielectoral.lat/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ ዛሬ ከንጋት 12 ሰዓት ጀምሮ በዎላይታ ዞን የድጋሜ የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ እየተካሄደ ይገኛል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በዎላይታ ሶዶ ምርጫ ጣቢያዎች የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

Photo Credit : NEBE & FBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa በሀዋሳ ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሜላት መሀመድ ትላንት ሰኔ 5/2015 ዓ.ም ቀትር ላይ በሁለት ተሽከርካሪ በመጡ ግለሰቦች 'መጠለፏን' ቤተሰቧቿ ተናግረዋል። የ14 ዓመት ከ 8 ወር ታዳጊዋ ሜላት ከትምህርት ቤት ወደ ወደ መኖሪያ ቤቷ በመመለስ ላይ እያለች በሀዋሳ ከተማ ሞኖፖል ተብሎ በሚጠራው አከባቢ " ቤት ልትደርስ ጥቂት ሜትሮች ሲቀራት " በሃይል ታግታ…
" የጠለፋ ወንጀሉ ሰለባ የሆነችው ታዳጊ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች " - የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ

ሐዋሳ ከተማ ውስጥ ታዳጊ ሜላት መሐመድን በመጥለፍ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪውን ግለሰብ ትናንት እሁድ ምሽት 5: 30 አካባቢ  ይርጋለም ከተማ ዉሃ ልማት ቀበሌ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ ተሸሽጎ መገኘቱን ረዳት ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ ተናግረዋል።

በጠለፋ ወንጀል የተጠረጠረው ሳምሶን ሸኑ የተለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የወንጀል ማጣራት ስራ እየተከናወ እንደሚገኝ ረዳት ኢንስፔክተር መልካሙ ገልጸዋል።

የጠለፋ ወንጀሉ ሰለባ የሆነችው ታዳጊ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዷን በማከል።

ታዳጊዋ ከጠለፋ መለቋቋን ታላቅ ወንድሟ እንዳልካቸው አስራትም አረጋግጧል።  ታዳጊዋ በሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት እያገኘች እንደምትገኝም ገልጿል።

ታዳጊ ሜላት መሐመድ ፤ ከቀናት በፊት በሐዋሳ ከተማ #በኃይል ወደ ተሽከርካሪ እንድትገባ ተደርጋ መወሰዷን ቤተሰቦቿ መግለፃቸው ይወሳል።

በወቅቱ የአካቢው ሰው ሊታደጋት መሞከሩን፤ ሜላት ስትጮህም ይዟት የጠፋውን መኪና የፊትለፊቱን መስታወት የአከባቢው ሰው መሰባበሩን ፤ ከዛ በኋላ እየበረረ ማመለጡን የታዳጊዋ ቤተሰቦች ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር በሚያቀኑ የጭነት የተሽከርካሪ ሾፌሮች እና ረዳቶች ላይ " እገታ ተፈፅሟል " ሲሉ የታጋች ቤተሰቦች ገለፁ። ድርጊቱ ዛሬ ንጋት 12 ሰዓት  " አሊዶሮ " በሚባለው አካባቢ ስለመፈፀሙ አንድ ወንድሜ ታግቷል ያለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ጠቁሟል። የታጠቁ አካላት " እስከ ሰላሳ / 30 የሚሆኑ ሰዎችን ከመኪናቸው አስወርደው አግተዋቸዋል ከነሱ ውስጥ ደግሞ አንዱ…
" ለማን ነው አቤት የምንለው ? "

በታጣቂዎች የታጋቱ ሹፌሮች እና ረዳቶች ገንዘብ እየተጠየቀባቸው መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ።

ከቀናት በፊት ሹፌሮች እና ረዳቶች ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር እና በተቃራኒው ጉዞ ላይ የነበሩ አዳራቸውን " አሊዶሮ " ላይ ካደረጉ በኃለ በታጣቂዎች መታገታቸውን ቤተሰቦች መግለፃቸው ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ድርጊቱ በተፈፀመበት ዕለት መልዕክት ካደረሱት ተጨማሪ የታጋች ወዳጆችን ፣የሚያውቋቸውን እንዲሁም በዕለቱ ጉዞ ላይ ከነበሩ አባላት መልዕክት ተቀብሏል።

አንድ በዕለቱ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ እየመጣ የነበረ የቤተሰባችን አባል ፤ ገብርጎራቻ 2 ሰዓት በደረሱበት ወቅት " አሊዶሮ " ላይ ወደ 14 መኪና ሹፌርና እርዳት መወሰዳቸውን እንደሰሙ ገልጿል። " ለ4 ሰዓታት ያህል ቁመን መከላከያ መጥቶ ነው መንገዱ ተከፍቶ ወደ አ/አ የሄድነው " ሲል አስረድቷል።

አንድ የቤተሰባችን አባል " የኔም ጓደኝዬ ከታገቱት አንዱ ነው " ሲል ቃሉ ሰጥቶ ትላንት ለቤተሰቡ ተደውሎ " አንድ ሚሊዮን ብር ላኩ " መባሉንና ቤተሰብም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

" ለማን ነው አቤት ምንለው ? " ሲልም አክሏል።

እንዲሁ ሌላ የቤተሰባችን አባል ፤ " አሊደሮ " ላይ ከታገቱት መካከል ሁለቱ የቻግኒ ልጆች እንደሆኑና  ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊየን ብር መጠየቁን እንደሚያቅ ፤ ለቤተሰቦችም ይህንን ብር ካላመጡ " እንገላቸዋለን " የሚል ማስፈራሪያ መላኩን አስረድቷል። በዚህም ምክንያት ቤተሰቦቻቸው በጭንቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

እገታው በተፈፀመበት ዕለት መልዕክቱን የላከልን አንድ ወንድሙ መታገቱን ያመለከተ የቤተሰባችን አባልም፤ አጋቾቹ ደውለው " 1 ሚሊዮን ብር አምጡ እኛ እነሱን አንፈልግም  " ማለታቸውን ገልጿል።

ሹፌሮች እና ረዳቶች መታገታቸው ከተነገረ ቀናት ቢያልፍም ከሚመላከታቸው የመንግሥት አካላት በኩል አንድም የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

Via @tikvah_eth_BOT

@tikvahethiopia