TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የዒድ አልፈጥር በዓል #ነገ መሆኑ ታውቋል። የሸዋል ወር ጨረቃ በሳኡዲ አረቢያ በቱሚናር እና ሱዳይር ዛሬ ሀሙስ በመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ጁምዓ / አርብ ይውላል። እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ምንጭ፦ Haramain Sharifain #TikvahFamily @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።

1444ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል የኢድ ሶላት (በአዲስ አበባ ስታዲዮም እና አካባቢው) ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል ይፋ አድርጓል።

አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መንገዶች የሚዘጉ መሆኑን በማወቅ አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ ብሏል።

የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤

- ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ፤

- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፤

- ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ፤

- ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤

- ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤

- ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀኛ፤

- ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤

- ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውሃ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት ፤

- ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ፤

- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ ፤

- ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ እንዲሁም ለከባድ መኪና አጎና ሲኒማ አካባቢ #ይለፍ_ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#ዒድ_አልፈጥር

ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ዒድ ሙባረክ !

በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስታከብሩ የተቸገሩት ፣ ያጡትን ፣ በችግር ላይ የወደቁትን ፤ በሰላም እጦት የሚሰቃዩትን ፣ በጦርነት እና በግጭት ወገን ዘመዶቻቸውን ከጎናቸው የተነጠቁትን ፣ ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የቀሩ ወገኖቻችን በማሰብ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።

ሀገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!!
መልካም በዓል !

ፎቶ፦ አቤል ጋሻው (ፋይል)

#TikvahFamily ❤️

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቤተክርስቲያኗ ፦ 1. በትግራይ ክልል ለሚገኙ አህጉረ ስብከት በጀት እንዳይላክ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነ አንድም ውሳኔ የሌለና በተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት የባንክ አገልግሎት በመቆሙ የተከሰተ የግንኙነት መቋረጥ መሆኑን ገልጻ በጀቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቆመበት ጊዜ ጀምሮ ከአህጉረ ስብከት ጋር በመነጋገር ለመላክ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች። 2. በክልሉ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የደረሰውን…
#UPDATE

ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመው የሰላም ልኡክ በቀጣይ ሳምንታት ወደ ትግራይ ክልል ሊጓዝ ነው።

ይኸው የሰላም ልዑክ ትላንት መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሥር በትግራይ በሚገኙ አኅጉረ ስብከት መካከል የነበረው ግንኙነት መቋረጡን አስትውሷል።

በትግራይ ክልል የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል በትግራይ ከልል ለሚገኙ ብፁዓን አባቶች የግንኙነት ማስቀጠያ ደብዳቤዎች ሲጻፉ መቆየታቸውንም ገልጿል።

ልኡኩ የደብዳቤው ግንኙነት እንደታሰበው የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ምክንያት ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከብፁዓን አባቶች፣ ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከምዕመናን የተወጣጣ ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አመልክቷል።

ልዑኩ " የኮሚቴው ዓላማም የሰላም መድረክ ማመቻቸት፣ የምንቀራረብበትና አንድ የምንሆንበትን መንገድ በጋራ ማፈላለግ ነው " ያለ ሲሆን ከጉዞ ጋር በተያያዘ ማሟላት ያሉባቸውን ጉዳዮች ለማሟላት ሲባል ከሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ሊደረግ የነበረውን ጉዞ ማራዘሙን አሳውቋል።

ልኡኩ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ክልል ትግራይ በመጓዝ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚወጣ መሆኑን ትላንት በሰጠው መግለጫ አረጋግጧል።

መረጃውን ከEOTC TV ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ። 1444ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል የኢድ ሶላት (በአዲስ አበባ ስታዲዮም እና አካባቢው) ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል ይፋ አድርጓል። አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መንገዶች የሚዘጉ መሆኑን በማወቅ አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ…
" የዒድ ሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም ተጠናቋል " - የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል

የ1 ሺህ 444ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል የኢድ ሶላት ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ተካሂዷል።

ስነ ስርዓቱ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

የባህር ዳር ከተማ የእስልምና ምዕመናን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው የመስገጃ ቦታ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ ተሰማ።

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለመስገጃ የሚሆን 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ መሰጠቱን ዛሬ አስታውቋል።

የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ዛሬ የኢድ አልፈጥር በዓል በባህር ዳር ስታዲየም በሚከበርበት ወቅት ነው ይህንን የምስራች ለምዕመኑ ያበሰሩት።

ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ምን አሉ ?

" ለብዙ ጊዜ ስትጠይቁት የነበረ የመስገጃ ቦታ አሁን በክልልም ፀድቆ የመጣ ስለሆነ ምናልባትም በሚቀጥለው ዓመት በደንብ ሰርታችሁት እዚህ ሳይሆን እዛው ከተፈቀደላችሁ ቦታ ላይ የምታከብሩት ይሆናል።

ክልሉ ያቀረባችሁትን ጥያቄ እኛ አፅድቀን ልከን ክልሉም ተቀብሎት 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የኢድ አልፈጥር በዓል የምናከብርበት ቦታ ተፈቅዷል። "

ከንቲባው ይህንን ንግግራቸውን ሲያደርጉ የባህር ዳር ከተማ ሙስሊም ምእመን እጅግ በደስታ ስሜት " አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! " እያለ ድምፁን አሰምቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update RSF የግብፅ ወታደሮችን ለቀይ መስቀል አስረከበ። የሱዳን ጦርነት በጀመረበት ወቅት በጄነራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ የሚመራው የሱዳን ፋጥኖ ደራሽ (RSF) ኃይል እንደማረካቸው የገለፃቸውን የግብፅ ወታደሮችን ዛሬ ጥዋት ለዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ማስረከቡን አሳውቋል። RSF ለቀይ መስቀል ያስረከባቸው የግብፅ ወታደሮች በማራዊ ጦር ሰፈር የነበሩና ላለፉት 5 ቀናት ይዞ ያቆያቸው ናቸው…
#ሱዳን

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል / RSF የ72 ሰዓታት ተኩስ አቁም ማድረጉን አውጇል።

ይህን ያደረገው የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ እና ዜጎች ከግጭት ቀጠና እንዲወጡ የሰብዓዊ ኮሪደር ለማመቻቸት በተጨማሪም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ መሆኑን ገልጿል።

ምንም እንኳን RSF ይህን ቢልም በሱዳን በተለይም በካርቱም በዛሬው የዒድ አልፈጥር በዓል ዕለት ግጭት መቀጠሉ ፣ ከተማዋ በከባባድ መሳሪያዎች ድምፅ እየተናወጠች ስለመሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

RSF የሱዳንን ጦር በአስከፊ ጥቃቶችን እየፈፀመ ነው በሚል ከሷል።

ከሱዳን ጦር በኩል በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ለማድረግ ሃሳብ ይኖር እንደሆነ የታወቀ ነገር እንደሌለ አልጀዚራ ዘግቧል።

ባለፉት ቀናት ለሁለት ጊዜ ተኩስ አቁም ለማድረግ ተሞክሮ ምንም አልተሳካም።

በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት በከተሞች ውስጥ እየተደረገ በመሆኑ በርካቶች ከቤታቸው ለመንቀሳቀስ ተቸግረዋል።

@tikvahethiopia
#Update

አሜሪካ አንድ ዜጋዋ ሱዳን ውስጥ መገደሉን አስታወቀች።

አንድ የአሜሪካ ዜጋ ሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ውጊያ መገደሉ ተሰምቷል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፎክስ ኒውስ በሰጠው ቃል ፤ በሱዳን አንድ አሜሪካዊ ዜጋ መሞቱን አረጋግጧል።

መስሪያ ቤቱ ፤ ከሟች ቤተሰብ ጋር እየተገናኘ መሆኑንና በደረሰባቸው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን መግለፁን አመልክቷል።

" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለቤተሰብ ካለን አክብሮት የተነሳ ምንም የምንጨምረው ነገር የለም " ሲልም ስለ ሟች ዝርዝር መረጃ ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።

በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካ መከላከያ ጦር በአፍሪካ ኮማንድ በኩል በሱዳን ያለውን ሁኔታ እየተከታተለ መሆኑን አሳውቋል።

የአሜሪካ ጦር ፤ በካርቱም የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞችን እና ዜጎችን ለማስወጣት የሚያስችለውን ተልዕኮ ለመፈፀም ተጨማሪ ኃይሎቹን ጅቡቲ ለማስቀመጥ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል በዝግጅት ላይ እንደሆነ ገልጿል።

በመሆኑም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ #የማይገኙ ሁሉም የዲግሪ (መደበኛ፣ ኤክስቴንሽን፣ ክረምት) እንዲሁም የማስተርስ (መደበኛ፣ ኤክስቴንሽን ፣ ክረምት) ተማሪዎች ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ሊንክ ፦ http://196.190.28.50

ምዝገባው የሚያበቃበት ቀን ሚያዚያ 18 ቀን 2015 ዓ/ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

ለበለጠ መረጃ ደግሞ ዘውትር በየስራ ሰአት በሚከተሉት ቁጥሮች መወደወል ይቻላል ፦ 0914485592 / 0921990158

ከኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ #የራያ_ዩኒቨርሲቲም በጦርነት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት ለማስቀጠል እየሰራ ይገኛል።

በዚህም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ዓመት በራያ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የመማር እድል ያላገኙ ተማሪዎች ከ09/08/2015 ዓ/ም እስከ 13/08/2015 ዓ/ም ባሉ የስራ ቀናት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎች የሚመዘገቡት ለዩኒቨርስቲው ረጅስትራር እየደሉ ሲሆን የስልክ ቁጥሮቹ 0970140000፣ 0970240000 ፣ 0970230000 ናቸው። ተማሪዎች ዘውትር በስራ ሰዓት ብቻ እንዲደውሉ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሱዳን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል / RSF የ72 ሰዓታት ተኩስ አቁም ማድረጉን አውጇል። ይህን ያደረገው የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ እና ዜጎች ከግጭት ቀጠና እንዲወጡ የሰብዓዊ ኮሪደር ለማመቻቸት በተጨማሪም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ መሆኑን ገልጿል። ምንም እንኳን RSF ይህን ቢልም በሱዳን በተለይም በካርቱም በዛሬው የዒድ አልፈጥር በዓል ዕለት ግጭት መቀጠሉ ፣ ከተማዋ…
#Update

የሱዳን ጦር በ72 ሰዓታቱ የተኩስ አቁም ተስማማ።

ጦሩ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀን ድረስ ዜጎች የኢድ አልፈጥር በዓልን እንዲያከብሩ፣ እና ለሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት መሳለጥ ሲባል የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማቱን ዛሬ ማምሻውን አሳውቋል።

በጄነራል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር " አማፂያን " ሲል የጠራቸው የRSF ኃይሎች የተኩስ አቁሙን እንዲያከብሩና ይህንን የሚያደናቅፉ ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያቆሙ ተስፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

RSF ዛሬ ጥዋት ለዒድ አልፈጥር በዓል የ72 ሰዓታት የተኩስ አቁም ማወጁ እና የሱዳን ጦር ሃሳብ ምን እንደሆነ እንዳልታወቀ መነገሩ ይታወቃል።

ምንም እንኳን የተኩስ አቁም እወጃዎች ቢኖሩም ሱዳን፣ በተለይ ካርቱም ዛሬ በውጊያ ስትናጥ ነበር የዋለችው።

@tikvahethiopia
#ትዊተር

ለጥንቃቄ ...

የትዊተርን አዲስ አሰራር ተከትሎ የበርካታ ታዋቂ ሰዎች እና ተቋማት #የማረጋገጫ_ምልክት ከትላንት ጀምሮ ተነስቷል።

ታዋቂው ቱጃር ኤሎን መስክ በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን ከገዛው በኋላ በመተግሪያው ላይ የመጡ ለውጦች በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ እየሆኑ ይገኛል።

ከዚህም ውስጥ አንዱ ትዊተር ታዋቂ ግለሰቦች የሚሰጠውን የማረጋገጫ መልክት (Twitter verification) በክፍያ መጀመሩ ዋነኛው ነው።

ለግለሰብ በወር 8 ዶላር ለድርጅት ደግሞ 1000 ዶላር ማስከፈል የጀመረው መተግበሪያው ከትላንት ጀምሮ ክፍያ ያልፈጸሙ ያላቸውን አካውንቶች የማረጋገጫ ምልክታቸውን አንስቷል።

የማረጋገጫ ምልክታቸው የተነሳው በሀገራችን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ታዋቂ ሰዎች ፣ የሚዲያ ተቋማት ፣ ትልልቅ የመንግስት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ መስሪያ ቤቶች ነው።

በርካቶች ይሄንን ውሳኔ  በተመሳሳይ ስም የሚከፈቱ " የማረጋገጫ ምልክት " የሚኖራቸው አካውንቶች እንዲኖሩ እድሉን ይከፍታል በሚል የተቃወሙት ቢሆንም ውሳኔው ግን ተግባራዊ ተደርጓል።

ይህም ሀሰተኛ መረጃን ያባብሳል ተብሎ ተሰግቷል።

በተለይ አሁን ላይ የማረጋገጫ ምልክቱን በቀላሉ ማግኘት መቻሉ ለአጭበርባሪዎች (Scammers) በር በመክፈት በርካቶችን ሊጎዳ ይችላል።

የገጾችን ትክክለኛነት ለማሳየት የምንጠቀምበት ይህ የማረጋገጫ ምልክት ከዚህ በኋላ ለማረጋገጫነት ብዙም ጥቅም የሚኖረው አይመስልም።

የገጹ ተከታይ ብዛት እንደ ማረጋገጫ መውሰድ ብንችልም እንደ ሀገራችን የሀሰተኛው ገጽ ተከታይ ቁጥር ከትክክለኛው በሚበልጥበት ሁኔታ የገጹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥም አዳጋች ያደርገዋል።

ከዚሁ ከትዊተር ማረጋገጫ ምልክት መነሳት ጋር በተያያዘ ጦርነት ውስጥ ባለችው ሱዳን የሆነ አንድ ጉዳይን እናጋራችሁ።

በጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ (RSF) የትዊተር አካውንት ያለው ሲሆን አካውንቱም 82.7K ተከታይ እና የሰማያዊ ማረጋገጫ ምልክት ነበረው።

ትዊተር ትላንት ይህንን የማረጋገጫ ምልክት ባነሳበት ሰዓታት ውስጥ የሰማያዊ ምልክት #የገዛ በተመሳሳይ በRSF ስም የተከፈተ 26 ሺ ተከታዮች ያሉት ገፅ ጄነራል መሀመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) በጦርነቱ ላይ #እንደተሞቱ አድርጎ አንድ ፅሁፍ አስራጭቷል።

የዚህን የማረጋገጫ ምልክት ከትዊተር የገዛ ገፅ ያወጣውን ሀሰተኛ ፅሁፍ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች አይተውታል ፤ ይህን ሀሰተኛ ፅሁፍ ያመኑም አልጠፉም።

ውድ ቤተሰቦቻችን በትዊተር አዲስ አሰራር ሁሉም ሰው ሰማያዊ የማረጋገጫ ምልክት እየገዛ በመሆኑ የሰማያዊ ምልክት ያላቸው አካላት ናቸው የሚያሰራጩት በማለት ሁሉንም የምታዩትን መረጃዎች አትመኑ፤ መረጃዎችን መርምሩ፣ አጣሩ። እናመሰግናለን !!

#TikvahFamily

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine