TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ፤ ከሰሞኑን ከክልል ልዩ ሀይል መልሶ ማደራጀት ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት፣ በመግባባት መፈታቱን አሳውቋል።

ከዚህ ስምምነት በኃላ የፋኖ አባላቱ ምንድነው ያሉት ?

ፋኖ ምሬ ወዳጁ ፦

" ያላሰንብነው መከላከያ ጋራ የሆነ accident ተፈጠረብን፤ መከላከያ ማለት በዚህ ትግል ላይ ብዙ አስተዋጽኦ ያደረገ እጅግ የምንወደው የምናከብረው ወደፊትም ቢሆን አገር ነው ተቋም ነው።

ይሄ በተደረገው በዚህ ሰበብ በጠፋብን ህይወት በተለያየ ቦታ እጅግ አዝነናል እኛም ያጣናቸው ጓዶች አሉ የመከላከያም ተመሳሳይ ይሄን ባለው በሀገር ሽማግሌ፣ በሃይማኖት አባት በሁሉም ተደራድረን ፥ ይሄን ያደረግንበት ምክንያት ምንድነው ጠላት ሲደሰት ስላየሁት ነው ፤ አባት የሌለበት ሀገር ሽማግሌ የሌለበት ሀገር ሀገር አይደለም ብለን እናስባለን።

ስለዚህ የሃይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች ለሀገር ትልቅ ባለውለታ ናቸውና ደም ከመፋሰስ ከግጭት ሳይደረስ የሀገር ችግሮች በእነደዚህ አይነት አባቶች ይፈታሉ።

አሁን በሰላም ቦታ ውለናል ወደፊትም የእየተማከርን ነገሮችን እንድንፈታ መልዕክታችን ነው። "

ሌላ ቃሉን የሰጠ የፋኖ አባል አበበ ፈንታው ተከታዩን ተናግሯል ፦

" ድንገት በጊዜያዊ አለመግባባቶች የተፈጠሩ ሁኔታዎች ናቸው። ከግጭቱ ምንም የተተረፈ ነገር የለም።

ከዛ አንፃር የነበረውን የተፈጠረውን ችግር በሀገር ሽማግሌ ፣ በሃይማኖት አባቶች በታዋቂ ግለሰቦች አጠቃላይ እንደ ህዝብ በሽምግልና ጠንካራ የሆነ የሽምግልና ስርዓት ስላለ እኛንም ያለንበት ቦታ በየተራራው ድረስ መጥተው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ባሉበት ሄደው ሽማግሌዎች አቀራርበውን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ደርሰናል።

በዚህ አጋጣሚ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሁላችንም ዋስትና ጠበቃ ነው ከፈጣሪ በታች ፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ በተፈጠረው ድንገተኛ ችግር ብዙ ጓዶች በግራም በቀኝም በሁላችንም ጠፍተዋልና ለዚህ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እንደተቋም ትልቅ ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን።

የአማራ ህዝብ ብዙ ጥያቄዎች ያሉት ህዝብ ነው ፤  ከዛ አንፃር ወደፊትም ግጭቶች ሊኖሩ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ ግን እነዚህን ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ በውይይት ልክ አሁን እንደፈታነው በቀጣይ በዛ መንገድ መፈታት አለባቸው አሁንም በዘላቂነት ጥያቄዎችን መንግሥት መፍታት አለበት። "

ሊንክ ፦ https://www.youtube.com/live/r17AHZmGQa4?feature=share

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ፤ ከሰሞኑን ከክልል ልዩ ሀይል መልሶ ማደራጀት ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት፣ በመግባባት መፈታቱን አሳውቋል። ከዚህ ስምምነት በኃላ የፋኖ አባላቱ ምንድነው ያሉት ? ፋኖ ምሬ ወዳጁ ፦ " ያላሰንብነው መከላከያ ጋራ የሆነ accident ተፈጠረብን፤ መከላከያ ማለት በዚህ ትግል ላይ ብዙ አስተዋጽኦ ያደረገ እጅግ የምንወደው የምናከብረው…
#ENDF

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ም/አዛዥ ሜጄር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን በሰሜን ወሎ ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት ምን አሉ ?

"  ይሄ ችግር መረገብ አለበት። ለማንም ለምንም አይጠቅምም ፤ አሁን ደግሞ ችግር በውይይት ነው መፍታት የምትችለው ወይስ በጠብመንጃ ነው በጠብመንጃ የፈቱ  ሀገሮች የትም የሉም። ህይወት ጠፋ ስለዚህ ሌሎችም ቢሆን ረጋ ብለው ይዩ ሁኔታውን ትክክል አይደለም ፤ በስተጀርባ ያለውን በትክክል ማየት አለባቸው።

ይሄ ግጭት ፤ ይሄ ንትርክ፣ ይሄ በየመንገዱ የነበረውን ሁከት ያቆመው ማንም አይደለም የሀገር ሽማግሌ መሃል እየገባ ነው ያቆመው ነፍሥ እንዳይጠፋ፣ ህፃናት እንዳይጎዱ ፣ የመንግስት እና የግል ንብረት እንዳይወድም ፣ ቤት እንዳይቃጠል ፣ ወንጀለኛ ያለአግባብ ተፈቶ እንዳይወጣ ከፍተኛ ስራ የሰራው የሀገር ሽማግሌ ነው።

ሌላው እዛ ያለው የፀጥታ ኃይልም ከሀገር ሽማግሌ ጋር ሆኖ መስራት አለበት ፣ ችግሩን ማስረዳት አለበት።

ሀገርን የሚጠቅም፣ ህዝብን የሚጠቅም መመሪያ ነው የወረደው ስለዚህ ያልተረዱና በጀርባ ሌላ መልክ የሚሰጡ ሰዎች ግፊት የተፈጠረ ችግር አሁን ህብረተሰቡ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው   ስለዚህ ይሄንን ለመፍታት የመንግስትን መመሪያ ለማክብረ ተስማምተናል ከነሱ ጋር።

ሌላው በእነሱ ላይ ሲደርስ የነበረው ችግር፣ በእኛ ላይ አንዳንድ ነገሮች ይስተካከልልን የተባለው በሙሉ መንግሥት / የክልሉ መንግሥት ያደርጋል።

ስለዚህ ይሄን በተለየና በተጣመመ መንገድ የሚረዱ ሰዎች ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ነው እየቃኙ ያሉት ይሄ እንዲስተካከል ነው ጥረት ያደረግነው  ፤ ችግሩን ለመፍታት በትዕግስት መከላከያ እየሞተም ቢሆን ለማስተካከል ጥረት አድርጓል ፣ ዛሬ ተሳክቶልናል። "

ሊንክ ፦ https://www.youtube.com/live/r17AHZmGQa4?feature=share

@tikvahethiopia
#ERC

" በባልደረቦቼ እና በአምቡላንስ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በፅኑ አወግዛለሁ፤ ታጣቂ ሃይሎች ከመሰል ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እማፀናለሁ " - የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አምቡላንስ ሾፌርና አዋላጅ ነርስ ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂ ኃይሎች ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል።

ማህበሩ ጥቃቱን በአፅኖት አውግዟል።

የማኅበሩ አምቡላንስ ሾፌር እንዲሁም አዋላጅ ነርስ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ አይባሽካ ቀበሌ ሚያዝያ 01 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 2፡30 ሰዓት በምጥ የተያዘች እናትን ከመኖሪያ ቤቷ ወደ ጤና ተቋም ለማድረስ ወደ ቤቷ እያመሩ እያለ ነበር ጥቃቱ የተፈፀመባቸው፡፡

በተፈፀመው ጥቃት ከሠራተኞቹ በተጨማሪ በአምቡላንስ ተሸከርካሪው ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡   
የአምቡላንስ ሾፌሩና አዋላጅ ነርሱ በጥቃቱ በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት በአሁኑ ወቅት በጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል እና በምስራቅ በለሳ ወረዳ ጓላ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ህክምናቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ማህበሩ አሳውቋል።  

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በመላው ሀገራችን በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ሠራተኞችና በጎፈቃደኞች ሰብዓዊ ተግባራቸውን በገለልተኝነት እና በአለማዳላት መንፈስ በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ እንዲሁም ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ታጣቂ ሃይሎች ከእንደዚህ አይነት ጥቃት እንዲቆጠቡ ተማፅኗል።

@tikvahethiopia
#አሁን

በትግራይ ስለተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና የሽግግር ፍትህ በማረጋገጥ ሂደት ዙርያ ያለመ የውይይት መድረክ በመቐለ እየተካሄደ ይገኛል።

ውይይቱ ፤ የፍትህ ሚኒስትሩን ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ያካተተ የፌደራል ልኡካን ቡድን እንዲሁም የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ እንደሚገኝ ድምፂ ወያነ ዘግቧል።

ፎቶ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
#ቁሳቁስ

በአሉን በበለጠ ድምቀት እንዲያሳልፉ ለልጆችዎ ለፋሲካ እና ለኢድ የሚሆኑ  ምርጥ ምርጥ አልባሳት እና ጫማዎች እንደተለመደው አስገብተናል።

በሁሉም እድሜ ክልል ላሉ ልጆች ካሉን ሰፊ አማራጮች የወደዱትን ለመሸመት ለቡ ቫርኔሮ፣ ለቡ ኮሜርሻል ህንፃ (ጋራ ማርት) 3ኛ ፎቅ የሚገኘውን Qusaqus Kids Store ይጎብኙ ዋጋቸውን ለማየት https://publielectoral.lat/Qusaqus ይቀላቀሉ ስልክ +251944032449
+251987308753
+251941993049
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ሐሰተኛ መረጃ ዓይነቶች ምን ያህል ያውቃሉ?

1. ምፀት/ስላቅ (Satire or parody)

2. የውሸት ግንኙነት (False Connection)

3. አሳሳች ይዘት  (Misleading Content)

4. የውሸት ዐውድ (False Context)

6. የተዛባ ይዘት (Manipulated Content)

7. የተፈበረከ ይዘት (Fabricated Content)

Source: www.firstdraftnews.org

💬 ሙሉ ይዘቱን ከቪዲዮው ላይ ይመልከቱ

#ግራቀኝ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ ልኮልናል።

ምክር ቤቱ ከሰሞኑን የክልሎችን ልዩ ሀይልን መልሶ ለማደራጀት ከተደረሰው ውሳኔ ጋር ተያይዞ እየተፈጠሩ ያሉ ሁኔታዎችን በአንክሮ ሲከታተል መቆየቱን አመልክቷል።

በተለይ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እና የህይወት መጥፋት መድረሱን ገልጿል።

ህይወታችው ካለፉ ሰዎች መካከል የካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሁለት ሰራተኞች እንደሚገኙበት እንዲሁም በስራ ላይ በነበሩ የቀይ መስቀል ሰራተኞች ላይም ጉዳት የደረሰ መሆኑን ለማወቅ እንደቻለ ገልጿል።

ይህ በሰብአዊ ድጋፍ ስራ ላይ በተሰማሩ ሰራተኞች እየደረሰ ያለው ተደጋጋሚ ጥቃት እና ህልፈተ ህይወት በእጀጉ ያሳዘነው መሆኑን የገለፀው ምክር ቤቱ መሰል ጥቃቶች በሰብአዊ እርዳታ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች የሚያከናውኑትን የሰብአዊ ድጋፍ ስራን በማስተጓጐል፣ የዕለት እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች ተገቢው ድጋፍ በወቅቱ እንዳይደርሳቸው የሚያደርግ በመሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳስበው አመልክቷል።

የኢትዮጲያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በዜጎች እንዲሁም በሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት እና ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲቆም፤ ተገቢው ጥበቃም እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

ምክር ቤቱ በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፤ የሚፈጠሩ ግጭቶች እና አለመግባባቶች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኙ የጀመረውን ሁለንተናዊ ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

@tikvahethiopia
" የሰላም ስምምነት ቢፈረምም ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም " - የህፃናት አድን ድርጅት

በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም የሰላም ስምምነት ቢፈረምም ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ የሕፃናት አድን ድርጅት አሳውቋል።

ድርጅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም በያዝነው ዓመት ሕዳር ወር የሰላም ስምምነት ቢፈረምም ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ አመልክቶ ፤ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ ያስፈልጋል ብሏል።

በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ ከ3.5 ሚሊዮን ሕፃናት በላይ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ይህም እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሰ ፣16 ኢትዮጵያውያን ሕፃናት መሃከል አንዱ ከትምህርት ገበታ መገለሉን ሲያሳይ ይሄ አሃዝ ኢትዮጵያን ከትምህርት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቀውስ ካስተናገዱ ሃገራት አንዷ ያደርጋታል ብሏል።

በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልል ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን በትምህርት ሚኒስቴር፣ በሴቭ ዘችልድረን እና ዩኒሴፍ የሚመራው የትምሀርት ክላስተር ያወጣው የቅርብ ጊዜ መረጃ ያሳያል።

በተለይ በትግራይ 85 በመቶ ትምሀርት ቤቶች ከባድ ወይም ከፊል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሁሉም የህዝብ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ናቸው። ይህም በክልሉ 2.3 ሚሊዮን የሚJቱ ህጻናት በኮቪድ ወረርሽን ጀምሮ የሁለት አመቱ ጦርነት ሲታከልበት ለሶሰት አመታት ከትምህርት እንዲገለሉ ያደረገ ሲሆን 22,500 መምህራን ያለ ደሞዝ ከሁለት አመት በላይ ቆይተዋል።

ለረጅም ጊዜ ከትምህርት ቤት የራቁ ሕፃናት ለበርካታ የመብት ጥሰት እና ብዝበዛ እንዲሁም ጥቃት የመጋለጥ እድላቸው ይጨምራል ሲል ድርጅቱ ገልጻል።

የህፃናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን) በጦርነት ሳቢያ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ህጻናት ባሉበት ስፍራ ደህንነቱ የተጠበቀ የመጫወቻ እና መማሪያ ስፍራዎችን በማሰናዳት፣ ስሜታቸውን ጤናማ በሆነ መልኩ እንዲገልጹ እና የስነልቦና ድጋፍ እንዲያገኙ ሰራዎችን እያከናወነ እንደሆነ አሳውቆናል።

ድርጅቱ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማገዝ መጽሃፍትን እና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን እያቀረበ ቢሆንም ትምህርትን ጨምሮ ሌሎች ፍላጎታቸውን ለማሟላት ከዚህ የበለጠ ስራ እና መዋእለ- ነዋይ ይጠይቃል ብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያን የዚህ አመት ሰብአዊ እርዳታ ጥያቄ ለማሟላት ያስፈልጋል ብሎ ከጠየቀው የገንዘብ መጠን 18.4% ብቻ የሚያሟላ የገንዘብ ድጋፍ የተሰበሰበ ሲሆን እቅዱን ሙሉ በሙሉ ለመደገፍ ተጨማሪ 3.26 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ሲል አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
" ድርቱን የፈፀመው ግለሰብ በፖሊስ እየተፈገለ ነው "

ሆን ብሎ፥ የታመመ ከብት በድብቅ አርዶና ደግሶ ባበላ ግለሰብ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት አለፈ።

በምስራቅ ሀረርጌዞን ባቢሌ ወረዳ አንድ ግለሰብ የታመመ ከብት በድብቅ አርዶ የአካባቢውን ሕብረተሰብ በማብላቱ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን 46 ሰዎች ለጤና ችግር መጋለጣቸው ተገልፃል፡፡
 
የባቢሌ ወረዳ ኤረር አባድር ቀበሌ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ መጋቢት 25/2015 የታመመ በሬ በድብቅ በእርሻ ውስጥ በማረድ ድግስ በመደገስ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲመገቡት አድርጓል ነው የተባለው፡፡

ግለሰቡ ድግሱን በደገሰበት ወቅት እርሱ እና ቤተሰቡ ስጋውን ያልተመገቡ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ድርጊቱ ሆን ብሎ በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረስ መሆኑን ፖሊስ አስረድቷል፡፡

በኤረር አባድር ቀበሌ የእንስሳት ጤና ባለሞያ የሆኑት አቶ አብዱልፈታሕ መሀመድ እንስሳቶች ታመው መድሃኒት ከተሰጣቸው እስከ 28 ቀን ስጋቸው እና ወተታቸው ለምግብነት ሊውል አይገባም ብለዋል፡፡

ይህ ግለሰብ ግን የታመመ በሬውን ያለ ባለሙያ እገዛ በራሱ ከከተማ መድሃኒት እየገዛ በመርፌ ሲሰጠው ቆይቶ ከበሽታው መዳን ሳይችል ሲቀር በድብቅ አርዶ ሰዎችን መመገቡ ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል ነው ብለዋል፡፡

ድርቱን የፈፀመው ግለሰብ ባሁን ግዜ ከአካባቢው የሸሸ መሆኑን እና በፖሊስ እየተፈገለ መሆኑ ተገልፃል፡፡

የቢሲዲሞ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አይመን ሙሳ መጋቢት 27 እና 28 የተመረዘ ስጋ የተመገቡ 47 ሰዎች ለህክምና ወደ ሆስፒታሉ የገቡ መሆኑን ገልፀው የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ ለ4 ሰዎች ህክምና መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ዘገባው የምስራቅ ሀረርጌ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው።

More : @tikvahethmagazine
" መንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን እስር እና እንግልት ያቁም " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር

የኢትዮጵየ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ባወጣው መግለጫ ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ባለሙያዎች የሚሰሩበት አውድ እየጠበበ ጋዜጠኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ በመንግስት የፀጥታ አካላት #እየተሸማቀቁ እና #እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ መታዘቡን ገልጿል።

ከሰሞኑን ፤ የማህበሩ መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል እንዲሁም የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን ጨምሮ ፦
👉 ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ ፣
👉 ጋዜጠኛ ገነት አስማማው ፣
👉 ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ ፣
👉 ጋዜጠኛ በየነ ወልዴ፣
👉 ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በመንግስት ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።

አንዳንዶቹ ያሉበት ቦታ እና ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንኳን ቤተሰቦቻቸውም በቂ መረጃ ሳይኖራቸው በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ማህበሩ ፤ ጋዜጠኞች ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ እየታሰሩ፣ እየታፈኑና ቤታቸውና ቢሯቸው እየተበረበረ መሆኑ ባለሞያዎች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ፤ የፕረስ ምህዳሩ የበለጠ እንዲጠብ እያደረገ ነው ሲል ገልጿል።

ማህበሩ የተቋቋመው እንደዚህ አይነት ሙያውን የሚያቀጭጩ ጫናዎችን ለመታገል መሆኑን በመግለፅ የመንግሥት እርምጃዎችን በፅኑ አውግዟል።

ጋዜጠኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ጉዳያቸውን እስር ቤት ሳይቆዩ መከታተል እንደሚችሉ ከሁለት ዓመት በፊት በወጣው በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቢደነገግም ይህ ግን #ተግባራዊ_አለመደረጉ ማህበሩ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር መንግስት፦
- የፕረስ ነፃነት እንዲረጋገጥ
- ያጸደቃቸውን ህገ-መንግስታዊና ዓለም አቀፋዊ ህጎች እንዲያከብርና ውስጡን እንዲፈትሽ
- ያለምንም የህግ አግባብ ያሰራቸውን የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ
- ባለሙያዎች ላይ የሚያደርሰውን ማሸማቀቅ እንዲያቆም ጠይቋል።

@tikvahethiopia