TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ነው። የም/ ቤቱ አባላት ጥያቄዎችን እየቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጠያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁን ፦ - ከኦነግ ሸኔ፣ - ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ፣ - ከሰሜኑ የሰላም ስምምነት፣ - ከዜጎች መፈናቀልና ግድያ፣ - ወደ አዲስ…
#ፓርላማ

" እነኚህ ሰዎች ሰላም ቢኖር ምን ያጣሉ ? #ከህወሓት ጋር ሰላም ወረደ ሰላም አገኘን ምን አጡ ? #ከኦነግ_ሸኔ ጋር ሰላም ቢወርድ ምን ያጣሉ ? "

ዶክተር ከፈና ኢፋ (የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል) ጠቅላይ ሚኒስትሩን ምን ጠየቁ ?

" .... በኦሮሚያ ክልል ጦርነት በኢኮኖሚ ላይ በፖለቲካ ላይ ፣ በማህበራዊ ህይወት ላይ ያስከተለውን መጠነ ሰፊ ጥፋት እና ጉዳት ዘርዝሬ መጨረስ አልችልም፤ ህዝብ ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው።

ህዝባችም በጣም እየተንገላታ ነው፤ በቅርቡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ታጥቆ ለሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪ አቅርቦላቸዋል፤ ይሄ የሰላም ጥሪ ምን ላይ ደርሷል ? ጅምሩ ምን ይመስላል ? ህዝባችን በአሁን ጊዜ በጉጉት አይደለም እየጠበቀ ያለው ይሄን የሰላም ድርድር በፀሎት ጭምር ነው በፆም በፀሎት ጭምር የዚህን ድርድር መጀመር እየጠበቅን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው።

ስለዚህ #ሰላም ለተጠማው ህዝባችን ሰላም ለማውረድ በዚህ ረገድ መሬት ላይ ምን እየተሰራ ነው ?

ከኦነግ ሸኔም ጋር ይሁን ከህወሓት ጋር ለተደረገው የተሳካ ስምምነት ኢትዮጵያውያን ሆነው የሚቃወሙ ሰዎች አሉ፤ ይሄን የሚያደርጉት ከውሥጥም ከውጭም ነው።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ ሰላም ከምንም በላይ ብሄራዊ ጥቅማችን ነው ፤ ኢትዮጵያውያን ሆነው ከራሳቸው ብሄራዊ ጥቅም በተፃራሪነት መቆም ትርጉሙ ምንድነው ? ምን ለማግኘት ነው ? ምን ለማጣት ነው ?

እነኚህ ሰዎች ምን ያጣሉ ሰላም ቢኖር ? ከህወሓት ጋር ሰላም ወረደ ሰላም አገኘን ምን አጡ ? ከኦነግ ሸኔ ጋር ሰላም ቢወርድ ምን ያጣሉ ? መፈናቀል ነው የሚቀረው ፣ ተጨማሪ የሰው ስቃይ ነው የሚቀረው ፣ የንብረት መውደም ነው የሚቀረው፣ የመሰረተ ልማት መውደም ነው የሚቀረው ይሄን የሚቃወም ኢትዮጵያዊ ምን አይነት ኢትዮጵያዊ ነው ? ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ አመሰግናለሁ !! "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓርላማ " እርስዎስ ስልጣንዎን በመልቀቅ የመፍትሄው አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ ? በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ እንዲሁም በማንነት ተኮር የዘር ማጥፋት ፣ የዘር ማፅዳት እና የማንነት ማሳሳት ወንጀሎች ተጠያቂ ለመሆን ምን ያህል ዝግጁ ኖት ? #አቶ_ክርስቲያን_ታደለ (የህ/ተ/ም/ቤት አባል) ጠቅላይ ሚኒስትሩን ምን ጠየቁ ? " የጥያቄዬ መንደርደሪያ የሚሆን ማስታወሻ ብዬ ወደ ጥያቄዬ አመራለሁ። ክቡር…
#ፓርላማ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ስልጣን በመልቀቅ የመፍትሄው አካል አይሆኑም ወይ ?  ለሚለው ጥያቄ ምን መለሱ ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ስልጣን ብትለቅ የተባለው በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ፤ ግን ጥሩ የሚሆነው ስልጣን ብንለቅ ነበረ ምክንያቱም መንግስት ማለት አስፈፃሚ ብቻ ማለት አይደለም።

ህግ አውጪ መንግስት ነው፣ ህግ ተርጓሚ መንግስት ነው ፣ አስፈፃሚ መንግስት ነው እኛ እዚህ ያለን ሰዎች የመንግስት ባለስልጣኖች ነን።

ይልቁኑንም የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ደግሞ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው የአንድ ሚኒስትር አለቃ ናቸው እና በጋራ ብንለቅ ቢሆን ምክንያቱም እርሶም እንደሚገነዘቡት የሁሉ ችግር ምንጭ እና ባለቤት እኔ ብቻ ልሆን አልችልም።

ኃላፊነት ከወሰድንም በጋራ ቢሆን ጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

ነገር ግን ይሄን ጥያቄ እሳቸው ቢያነሱትም እሳቸው ላይም ይነሳ ነበር በውጭ ያሉ እንደሳቸው ፓርላማ አሸንፈው መግባት ያልቻሉ ሰዎች ለምንድነው እኚህ ሰውዬ የቋሚ ኮሚቴ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡት አይለቁም እንዴ ? እያሉ ከዚህ ቀደም በሚዲያ እንደምትሰሙት ብዙ ይተቻሉ፤ እርሶ ምርጫ አሸንፈው ነው የገቡት እዚህ ተቀምጠው የህዝቡን ጥያቄ ማንሳትዎ ተገቢ ነው ብዬ ማስበው መቆጣጠሩም የሚያደርጉት ጥረትም።

ግን ከስልጣን ጋር ተያይዞ ያለውን ጉዳይ በአንድ ቀላል ምላሴ ለማስረዳት በደቡብ ህንድ ጦጣን የማጥመድ ቴክኒክ አለ ጦጣን እንደምታውቁት ቁንጥንጥ ናት፣ ቅብዝብዝ ናት  ለአደን አትመችም እና በደቡብ ህንድ ያሉ አዳኞች ጦጣን ለማጥመድ የኮኮናት ፍሬ በጦጣ እጅ ልክ በቀጭኑ ይቀዱና ከውሥጥ ሩዝ ያስቀምጣሉ ሲቀዱት የጦጣ እጅ ቀጭን ስለሆነ በዚያ ልክ ይቀዱትና ውስጥ ግን ሰፋ አድርገው ሩዝ ያስቀምጣሉ፤ሊይዟት ስለማይችሉ ጦጣ ሩዝ አየሁ ብላ እጇን ሰዳ ካፈሰች በኃላ ልውጣ ስትል የተሰራው ለቀጭኑ ስለሆነ ከጨበጠች በኃላ አይለቃትም።

ይቺ ጦጣ የሰው ሩዝ ነው የያዝኩት የማይገባኝን ሩዝ ነው የያዝኩት ይዤው ከቆየሁ ልያዝ እችላለሁ በትኜው ልሂድ አትልም እንደጨበጠች ትታገላለች በዚህ ጊዜ ያን የኮከናት ፍሬ መውሰድ ስለማትችል አዳኙ መጥቶ ይይዛታል። ጦጣዋን ያደናት የያዛት ምንድነው ያላችሁ እንደሆነ ሃሳቧ ነው እንጂ ወጥመዱ አይደለም፤ እዛው በትና በትለቅ ትወጣለች በሀሳብ ግን ሩዝ አፍሼ ካልወጣሁ ስላለች ሀሳቧ አጥምዶ ያስቀራታል እዛው።

ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እንደሚባለው ቁጭ ብለው የሚያልሙ ሰዎች አሉ ሁል ጊዜ በዚያ መንገድ ጥሩ አይሆንም።

ሁለተኛ ቢጨበጥ ጥሩ የሚሆነው ስልጣንን በሚመለከት በእኔ እና በተከበሩ አቶ ብናልፍ መካከል የሚደረግ ድርድር የለም።

የስልጣን ባለቤት ህዝብ ነው፤ስልጣን ሰጪም ነፋጊም ህዝብ ነው፤እኔ ና አቶ ብናልፍ ማድረግ ያለብን የተሻለ ሃሳብ ይዘን ህዝባችን ጋር መቅረብ እና የኔን ሃሳብ ምረጥልኝ ብለን በሰጪው ነው የምንመረጠው እንጂ በምክር ቤት ውስጥ ስጠኝ ልቀቅልኝ በሚል አይሆንም።

ሰጪው ጋር ሃሳብ የተሻለ ይዞ መቅረብ ታስፈልጋል፤ ስለዚህ ስልጣን በኮሮጆ እንጂ በመናጀ አይያዝም እና ሶስት ዓመት ይቅራል ለምርጫ በውጭም አሉ ይሄ የኦሮሞ መንግሥት ይሄ የኦሮሞ መንግስት እያሉ የሚዘፍኑ ዘፋኞች አሉ እነሱን ጨምሮ ሰብሰብ ብሎ ሃሳብ አጠናክሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረብ ነው እኛ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደተባለድ የተገባውን ቃል ካልመለስን የኢትዮጵያ ህዝብ በእኛ አስተዳደር ካልረካ በምርጫ ከጣለን በተደጋጋሚ እንዳልነው በደስታ እናስረክባለን።

ፓርቲዎች መዘጋጀት ያለባቸው ሃሳብ ይዘው መምጣት ነው፤ አሁን ሃሳብ የለም፤ ሰብሰብ ብሎ ሃሳብ ይዞ ያን ወደ ህዝብ አቅርቦ ለመመረጥ እና ለማሸነፍ የሚደረግ ጥረት ለሁላችን የሚጠቅመን ይሆናል "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓርላማ " እነኚህ ሰዎች ሰላም ቢኖር ምን ያጣሉ ? #ከህወሓት ጋር ሰላም ወረደ ሰላም አገኘን ምን አጡ ? #ከኦነግ_ሸኔ ጋር ሰላም ቢወርድ ምን ያጣሉ ? " ዶክተር ከፈና ኢፋ (የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል) ጠቅላይ ሚኒስትሩን ምን ጠየቁ ? " .... በኦሮሚያ ክልል ጦርነት በኢኮኖሚ ላይ በፖለቲካ ላይ ፣ በማህበራዊ ህይወት ላይ ያስከተለውን መጠነ ሰፊ ጥፋት እና ጉዳት ዘርዝሬ መጨረስ አልችልም፤…
#ፓርላማ

መንግሥት ከ " ኦነግ ሸኔ " ጋር የሚደረግን የሰላም ድርድር የሚመራ ኮሚቴ አቋቁሞ እየሰራ እንደሚገኝ ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለፓርላማ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ "  ኦነግ ሸኔ " ምን አሉ ?

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ሸኔን በሚመለከት ለተነሳው ጥያቄ ... ላለፉት አራት ፣ አምስት ዓመታት ወለጋ አካባቢ ልማት እንዳይሰራ ሰዎች እንዲፈናቀሉ እንዲገደሉ ብዙ መጎሳቀል ግጭት ነው።

ይሄ ግጭት በሰላም እንዲፈታ መንግሥት ከፍተኛ ፍላጎት አለው። ከፍተኛ ፍላጎት አለው ብቻ ሳይሆን በባለፈው በማዕከላዊ ኮሚቴ ተወያይቶ በፓርቲያችን ምክትል ፕሬዜዳንት የሚመራ ኮሚቴ አቋቁሟል። የሰላም ድርድሩን የሚመራ።

ከቤኒሻንጉል ጋር የተሻለ ውጤት ተገኝቷል፣ ከጋምቤላ ጋር የተሻለ ውጤት ተገኝቷል፣ ከቅማንት ጋርም እንዲሁ የተሻለ ውጤት ተገኝቷል የሚቀሩ ጉዳዮች ቢኖሩም ሸኔን በሚመለከት ባለፉት አንድ / ሁለት ወር ገደማ ከ10 በላይ ሙከራዎች ተደርገዋል ያስቸገረው ነገር አንድ የተሰባሰበ ኃይል ባለመሆኑ ምንነጋገርባቸው ኃይሎች የተለያየ ሃሳብ እና አቋም ይዘው ስለሚመጡ ነው።

የሆነው ሆኖ በእኛ በኩል የኦሮሚያ መንግስት ያቀረበው የሰላም ጥሪ የሚባለው የኦሮሚያ መንግስት ያቀረበው ሳይሆን እንደ ፓርቲ ተወያይተን ወስነን በምክትል ፕሬዜዳንት የሚመራ ኮሚቴ አቋቁመን የዛን ተቀጥያ ነው የኦሮሚያ መንግሥት የገለፀው/ ያብራራው።

ሰላሙን የሚጠላው ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም ኢትዮጵያዊና ጤነኛ ሰው ከሆነ ምክንያቱም ብዙ ሰው እየተጎዳ እየተፈናቀለ ስለሆነ ሰላሙን ሁሉም ይፈልገዋል የሚል ተስፋ አድርጋለሁ በእኛ በኩል ጉዳዩ በሰላም እንዲፈታ አበክረን እንሰራለን። ጉዳዩ በሰላም እንዲፈታ አበክረን እየሰራን ተጨማሪ ደግሞ ማፈናቀል እና መግደል እንዳይፈጠር / እንዳይቻልም ኃይሎቻችን በስፋት እዛ አካባቢ ጠንከር ያለ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።

ለሰላሙ ግን ጥርጣሬ መኖር የሌለበት ለአገው ሸንጎም፣ ለቅማንትም፣ ለTPLFም ፣ ለኦነግም ለሁሉም የታጠቁ ኃይሎች የኢትዮጵያ መንግስት የሚፈልገው ጉዳዩን በንግግር ፣ በምክክር ፣ በውይይት መፍታ ነው። መገዳደል አይጠቅምም የሚል የፀና አቋም አለን የሚያዋጣንም መንገድ እሱ ይመስለኛል።

በዚህ አግባብ ቢታይ የሸኔ ጉዳይ እየተመራ እንደሆነ ኮሚቴዎች ተቋቁመው እየተነጋገሩ እንደሆነ ውጤቱን ደግሞ በጋራ የምናይ ይሆናል ። "

@tikvahethiopia
#ቴሌብር #ኢትዮቴሌኮም

ገና በአጭር እድሜው 30 ሚሊየን ተጠቃሚ ያፈራ ፤ 370 ቢሊየን ብር በገበያ ያዘዋወረ ፤ ከ18 ባንኮች ጋር የተጣመረ ፡ እነሆ ቴሌብር ሱፐርአፕን አበሰረ!!!

ከእንግዲህ ለተለያዩ አገልግሎቶች በርካታ መተግበሪያዎችን አይጭኑም፦

በቴሌብር ሱፐርአፕ ሁሉም ስለተጣመሩ
ጊዜና ጉልበት ሳይባክኑ እልፍ ጉዳይዎን እዛው ይከውናሉ።

የትራንስፖርት፣ የመዝናኛ፣ ኢ-ኮሜርስ፣ የመሠረታዊ አገልግሎቶች፣ የምግብ እና ዴሊቨሪ አገልግሎት ሰጪዎች ኧረ ማን የቀረ አለ በቴሌብር ሱፐርአፕ ሁሉም በአንድ ተሰብስበዋል።

የስራ ውጥረት ሲበዛ የክፍያዎች ቀን ይረሳል ፤ ሱፐርአፕ አያንቀላፋም ቀደም ብሎ ያስታውሳል።

የደህንነት አጥሩ አስተማማኝ እና ጠንካራ ፤ ከይለፍ ቃል በተጨማሪ በፊት ገፅና በአሻራ

እልፍ ጉዳይ በአንድ መተግበሪያ
onelink.to/75zfa5 አውርደው ይሞክሩት

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#አቢሲንያ_ባንክ

ጊዜ ገና ብዙ ያሳየናል!

አፖሎን ይበልጥ ተመራጭ የሚያደርገው የጣት አሻራዎን በመጠቀም የባንክ ሒሳብዎን ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ ማስቻሉ ነው።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ Telegram: https://publielectoral.lat/apollodigitalproduct
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 "የቀድሞ" አባቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አስገብተዋል ሲል የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል።

ደብዳቤውን ያስገቡት 17 ሲሆኑ አንዱ ወደ ጸበል መሄዳቸውን ገልጸው ደብዳቤአቸውን በተወካይ አስገብተዋል።

በጥቅሉ ደብዳቤ ያስገቡት18 ሲሆኑ ቀሪዎቹ  6 የቀድሞ አባቶች በህመም ምክንያት እንዳልተገኙ በዛሬው ዕለት የተገኙት የቀድሞ አባቶች ገልጸው በቅርብ ጊዜ ቀሪዎቹ ግለሰቦች ማመልከቻቸውን ይዘው እንደሚመጡ አስረድተዋል ነው ያለው።

መምሪያው ፥ " በቪዲዮ የይቅርታ መልዕክት እንዲያስተላልፉ እድል እንዲሰጣቸው የተደረገ ቢሆንም ግለሰቦቹ አልተቀበሉትም " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" #አስቸኳይ የፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው ተቋርጧል " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት እንዲሁም በ11ዱ የክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ሲሰጥ የነበረው “ አስቸኳይ ” የፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው መቋረጡን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ለምን ተቋረጠ ?

አገልግሎቱ የተቋረጠው #ከአቅም_በላይ የባለ ጉዳይ ፍሰት ከመፈጠሩ ጋር ተያይዞ መጠነ ሰፊ #የሠነድ_ማጭበርበሮች በመስተዋላቸው ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ተገልጋዮች ሊገለገሉ ሌሊት ላይ በሚመጡበት ወቅት በተለያዩ ህገ-ወጥ ግለሰቦች የሚደርስባቸው እንግልትና ጉዳት በአገልግሎት አሰጣጥና በተገልጋዩ ላይ ተግዳሮት በመፍጠሩ ነው።

ስለሆነም የማስተናገድ አቅም እና ሌሎች ክፍተቶች እስከሚስተካከሉ ድረስ ይሰጥ የነበረው የ “ አስቸኳይ ” ፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው ተቋርጧል።

አስቸኳይ ጉዞ ያላቸው በምን ይስተናገዳሉ ?

ቀድሞ ይሰራበት በነበረው አሰራር መሰረት #አስቸኳይ_ጉዞ ያላቸው አገልግሎት ጠያቂዎች ማስረጃዎቻቸውን አቅርበው #በዋና_መስሪያ ቤት ብቻ ከመጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ይስተናገዳሉ።

ማሳሰቢያ ፦ ተገልጋዮች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከህገወጥ ደላሎች እንዲጠነቀቁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ ፓስፖርትን በተመለከተስ ?

የመደበኛ ፓስፖርት ተገልጋዮች ቀድሞ በነበረው ሂደት መስተናገድ #ይቀጥላሉ

ምንጭ፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

@tikvahethiopia
የIMF ሰዎች እዚህ ኢትዮጵያ ናቸው።

ብሉምበርግ የዜና ወኪል ፤ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ለኢትዮጵያ ሊሰጥ በሚችለው ድጋፍ አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ የድርጅቱ ባለሥልጣናት አዲስ አበባ ይገኛሉ ብሏል።

በእርስ በርስ ጦርነቱ ሳቢያ ኢትዮጵያ ከIMF ጨምሮ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር የነበራት ግንኙነት ተቀዛቅዞ መቆየቱ ይታወሳል።

እንደ ብሉምበርግ ዘገባ የተቋሙ የባለሙያዎች ቡድን ኢትዮጵያ ከIMF ሊደረግላት ስለሚችለው ድጋፍ አስፈላጊውን “ቴክኒካዊ ሥራ ለማከናወን” ነው አዲስ አበባ የሚገኘው።

ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ በተመለከተ ውይይት እና አስፈላጊውን ሁኔታ እንዲያመቻቹ የተላኩት የIMF ባለሥልጣናት ለ10 ቀናት ያህል ይቆያሉ።

ቃላቸውን ለሮይተር የዜና ወኪል የሰጡ የIMF ቃል አቀባይ በበኩላቸው ፤ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው ምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግላት ተቋሙን እንደጠየቀች ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ፤ " ሊሰጥ የሚችለው ድጋፍ አገሪቱ ለምታካሂደው አገር በቀል የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እና ምጣኔ ሀብቷን በማረጋጋት ለሰብአዊ ድጋፍ፣ ለሥራ ፈጠራ እና ለድህነት ቅነሳ የሚውል ይሆናል " ብለዋል።

የIMF ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ የሚያደርጉት ቴክኒካዊ ውይይት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና በተቋሙ መካከል ሰብአዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮችን ለማሻሻል የተደረገ ንግግር ተከታይ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም መካከል ሲካሄድ የነበረው የድጋፍ፣ የብድር ስረዛ እና ሽግሽግ ንግግር በከፊል በትግራይ ሲካሄድ ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶ ነበር።

ብሉምበርግ እንደዘገበው ኢትዮጵያ ጦርነቱ ያስከተለውን ውድመት መልሶ ለመገንባትና የገጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመሸፈን አስፈላጊ ለሆኑ የገቢ ምርቶች ክፍያ ለመፈጸም ድጋፍ ያስፈልጋታል።

ጦርነቱ ካስከተለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ባሻገር በአፍሪካ ካሉ የመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች መዳረሻ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን እና ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የተነሳ ከዓለም ባንክ (World Bank) አንዲሁም ከIMF የምታገኘውን ድጋፍ ገትቶት መቆየቱን አስታውሷል።

በጦርነቱ እና በዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ምክንያት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር የገጠማት ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ከመመዝገቡ በላይ እጥረትም ተከስቷል።

#ቢቢሲ #ብሉምበርግ #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
" ከአፍጥርና ከፆም ሰዓታት በኋላ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች እንታደግ " - ደም ባንክ

በተያዘው የጾም ወቅት በቂ ደም ከማግኘት አንፃር ውስነነት መኖሩን የኢትዮጵያ ደም እና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡ ባንኩ በዚህ ወቅት በቂ ደም እያገኘ አለመሆኑን ነው ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ለፋብኮ ተናግረዋል።

#ሕይወትን_ማትረፍ ከፆሙ ዓላማ አንፃር ያለው ፋይዳ ትልቅ ስለሆነ ከአፍጥር እንዲሁም ከፆም ሰዓታት በኋላ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ለመታደግ ሕብረተሰቡ በንቃት ደም እንዲለግስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ደም የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ሕይወት ለመታደግ በተንቀሳቃሽ እና በቋሚ ቦታዎች እንዲሁም በሥራ ቀናት በትምህርት ቤቶች፣ መንግሥታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በመዘዋወር የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ቅዳሜ ቅዳሜ አደባባይ ላይ ድንኳን በመትከል የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾችን በመቀስቀስ እና እሁድ በቤተ እምነቶች የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተከናነ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

#ኤፍቢሲ

More : @tikvahethmagazine
#ድሬ

ትላንት ምሽቱን በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በጎርፍ የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ እንዳሳወቀው ፤ በቀበሌ 07 አፈተ-ኢሳ / አሸዋ ሰልባጅ ተራ / ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጎርፍ መውረጃ አሸዋ ውስጥ ተኝቶ የነበረው የ55 አመት ጎልማሳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በተኛበት ህይወቱ አልፎ የተገኘ ሲሆን የሰልባጅ ልብስ መሸጫ ቦታው ላይ ጉዳት ደርሷል።

የ55 አመቱ ጎልማሳ በአካባቢው ላይ የቀን ስራ እየሰራ ራሱን እና ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ግለሰብ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ አስክሬኑ ወደ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ተልኳል ብሏል።

ከመጋቢት 7 - መጋቢት መጨረሻ ድረስ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል የሜትዮሮሎጂ ትንበያ መረጃ የሚያመለክት ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የድሬዳዋ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳሬክቶሬት መረጃ ሲሰጥ ቆይቷል ተብሏል።

በሌላ ዜና ፦ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ገደማ ቀበሌ 09 " ገንደ ገመቹ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት የገባ #ከርከሮ በቤቱ ባለቤት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሷል።

በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በድልጮራ ሪፈራ ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ ዳርቻ የሚኖሩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተገቢውን #ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ አሳስቧል፡፡

#ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://publielectoral.lat/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
#AddisAbaba

ዛሬ ከሠዓት ላይ በአዲስ አበባ፣ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 1 መርካቶ በተለምዶ " ማር ተራ " ተብሎ በሚጠራው ቦታ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበር።

የእሳት አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

የእሳት አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር የተቻለው በእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የፖሊስ አባላት እና በአካባቢው #ወጣቶች ከፍተኛ ርብርብ መሆኑ ተመላክቷል።

የእሳት አደጋው መንስኤ እንዲሁም ያስከተለው የጉዳት መጠን በቀጣይ ተጣርቶ ይገለፃል ተብሏል

መረጃው የክ/ከተማው ኮምንኬሽን ነው።

@tikvahethiopia