TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዛሬም እስር እና ማንገላታት ቀጥሎ መዋሉን ገለፁ። ተሚማ የተሰኘው ሚዲያ ፤ በዛሬው ዕለት የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ታምራት ወልዴ መታሰራቸውን ገልጿል። ሚዲያው ፤ " ሕገ ወጡን ቡድን የሚደግፉት የመንግሥት አካላት ሥራ አስኪያጁን ቁልፍ አስረክበው እንዲወጡ ቢነግሯቸውም አልቀበልም በማለታቸው ዛሬ ጠዋት ታሥረዋል…
#Update

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፤ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተከሰተው ክስተት አየተባባሰና እየተካረረ መሄዱ በእጅጉ እንዳሳሰበው አሳውቋል።

የስድስቱ አባል የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ስለጉዳዩ በመጨነቅ አብዝተው ከመጸለይ ባለፈ ከቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ችግሩ በሰላማዊ ሁኔታ ስለሚፈታበት ሁኔታ መወያየታቸው ተገልጿል።

ቤተክርስቲያኒቱ ለዘመናት የኖረ ሕገ ቤተክርስቲያን፣ ቀኖናና ሥርዓት ያላት አንጋፋ ተቋም ከመሆኗ አንጻር ያጋጠማትን ውስጣዊ ችግር በቤተክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት ሊፈታ እንደሚችል እንጠብቃለን በማለት ጉባኤው ገልጿል።

የጉባኤው ባለ 5 ነጥብ መግለጫ ፦

- ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አማኞች በተጨማሪ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪ በመመለስ ጸሎት ወይም ዱዓ እንዲያደርግ ብሏል።

- የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ከማክበር ጎን ለጎን የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ተገንዝበው ውይይትን፣ ይቅርታንና እርምትን እንዲያስቀድሙ በፈጣሪ ስም በማሳሰብ ይህም ሊደርስ የሚችለውን አደጋ አስቀድሞ እንድትከላከሉ ብሏል።

- የፌዴራልና የክልሎች መንግሥታት በቤተክርስቲያኒቱ  ውስጥ የተፈጠረው ችግር በራሷ በቤተክርስቲያኒቱ ሕግ፣ ቀኖና እና ሥርዓት ብቻ ተመሥርቶ እንዲፈታ ኃላፊነታቻውን በአግባቡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 27 መሠረት እንዲወጡ አሳስቧል።

- ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ አመራሮችና አባላት፤ የማኅበረሰብ አንቂዎች ወቅታዊ የቤተክርስቲያኒቱን ውስጣዊ ችግር ከማባባስ እንዲታቀቡ አሳስቧል።

- የመገናኛ ብዙኋን ባለሙያዎች፣ ዘጋቢዎችና ተንታኞች የሚያስተላልፏቸው መልእክቶችና ንግግሮች ችግርን የሚያባብሱና ሌላ ግጭትና ሁከት የሚቀሰቅሱ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
ቪድዮ ፦ ቱርክ እና ሶሪያ በሚወሰኑበት የድንበር አካባቢ ባጋጠመው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን ባለስልጣናት አሳወቁ።

ዛሬ ሰኞ ጠዋት በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርክ አስካሁን ከአንድ ሺህ በላይ እንዲሁም በሶሪያ በኩል ደግሞ ወደ 800 የሚደርሱ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል።

ቱርክ ከሶሪያ ጋር በምትዋሰንባት በደቡብ ምሥራቋ ጋዚያንቴፕ ግዛት ውስጥ ባጋጠመው በዚህ አደጋ በአጠቃላይ በሁለቱ አገራት ወደ ሁለት ሺህ እየተጠጉ ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

የነፍስ አድን ሠራተኞች በፍርስራሾች ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን ፈልጎ የማውጣት ሥራ እያከናወኑ ሲሆን፣ በዚህም የአደጋው ሰለባዎች ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል ስጋት መኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቪድዮ ፦ Ahmit Sahu

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ መንግሥት በተርኪዬ በመሬት መንቀጥቀጥ ለደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገለፀ።

መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ ፤ በደቡባዊ ተርኪዬ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት መውደም  ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

መንግስት ጉዳት የደረሰባቸው በቶሎ እንዲያገግሙ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ገልጾ ፤ " በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ከቱርኪዬ መንግሥት እና ህዝብ ጎን የምትቆም መሆኗን እንገልፃለን " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፖሊስ ዛሬ ስለነበረው ሁኔታ ምን አለ ?

የአዲስ አበባ ፖሊስ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፤ ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጠዋት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ድንበር በተለምዶ ፊሊዶሮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰላማዊ እንቅስቃሴን የማወክ ህገ ወጥ ድርጊቶች ተስተውለዋል ብሏል።

በኦሮሚያ ልዩ ዞን ክልል ውስጥ በምትገኘው ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን  የተሰበሰቡ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ገብተው " የታሰሩብን ሰዎች ይፈቱልን " በሚል ምክንያት በድንጋይ መንገድ በመዝጋት የፀጥታ ችግር እንዲከሰት ለማድረግ ሞክረዋል ሲል ገልጿል።

ፖሊስ ፤ " ምንም አይነት የታሰረም ሆነ የተያዘ ሰው እንደሌለ በመግለፅ የተዘጋው መንገድ እንዲከፈት ቢያሳስባቸውም ፈቃደኛ አልሆኑም " ሲል አስረድቷል።

ከፖሊስ በተጨማሪ የቤተክርስቲያኒቱ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ወጣቶች የታሰረ ሰው አለመኖሩን በማስረዳት መንገዱን ለማስከፈት የፀጥታ አካሉን እያገዙ በምክር እና በተግሳፅ የበኩላቸውን ጥረት ቢያደርጉም የተሰበሰቡት ሰዎች ከቦታው ለመንቀሳቀስ እና መንገዱ እንዲከፈት ፍላጎት አልነበራቸውም ብሏል።

ፖሊስ በመግለጫው፤ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በወቅቱ ተዘግቶ የነበረው መንገድ እንዲከፈትና ሰላማዊ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል የማድረግ ስራ ሰርቷል ብሏል።

በዚህ ወቅት ግጭቱ እንዲፈጠር በግልፅም ሆነ በስውር ሲቀሰቅሱና በተባባሪነት ሲሳተፉ በነበሩ ሃይሎች በተወረወረ ድንጋይ በ19 የፖሊስ አመራርና አባላት ላይ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል ሲል አሳውቋል።

(የፖሊስ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#MoE

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታስተካክሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና #የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች፣ ነፍሰጡር የሆናችሁ፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ያለባችሁ ተማሪዎች፣ ...) ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አለባችሁ፦ https://student.ethernet.edu.et

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NEBE

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው የሕዝበ-ውሳኔ ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ መደረጉን ገልጿል።

ቦርዱ የድምፅ ቆጠራው ትናንት ማታ ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቱም የድምጽ አሰጣጥ በተካሄደባቸው በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺህ 771 ምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ጠዋት ለህዝብ ይፋ ተደርጓል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#ቱርክ #ሶሪያ

በቱርክ እና ሶሪያ ድንበር አቅራቢያ ባሉ ከተሞች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ4,800 በላይ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው።

የነፍስ አድን ሠራተኞችም በፍርስ ራሾች ውስጥ ተቀብረው የሚገኙ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በቱርክ የሰባት ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጀዋል።

ፕሬዝዳንቱ የሀዘን አዋጁን ያወጁት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎችን ለማሰብ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል፣ መቐለ እና ዙሪያው #የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፤ በትግራይ ክልል በመቐለ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች  የሚገኙ 31 የባንኩ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል፣ መቐለ እና ዙሪያው #የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፤ በትግራይ ክልል በመቐለ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች  የሚገኙ 31 የባንኩ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል። ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ @tikvahethiopia
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል ተከስቶ በነበረው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የባንክ አገልግሎት ዛሬ አስጀምሯል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከብሄራዊ ባንክ ለክልሉ የተላከውን ብር ለቅርጫፎች በማከፋፈል በመቐለ ከተማ በሚገኙት ሁሉም ቅርንጫፎች እንዲሁም በዓብይ ዓዲ፤ ማይ ለሚን፤ ሳምረ፤ ግጀት፤ ሃይቂ መስሓል፤ወርቅ አምባ፤ አፅቢ እና አጉላዕ በሚገኙ በአጠቃላይ በ31 ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

በተጨማሪም በዓዲግራት፣ ውቕሮ፣ ፍረወይኒ፣ ሓውዜን፣ ዓዲጉዶም፣ ሒዋነ፣ ዓዲሽሁ፣ መኾኒ፣ ማይጨውና አካባቢው በሚገኙ ቅርንጫፎች በቅርብ ሰዓታት ውስጥ ባንኩ የተሟላ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የባንኩ መቐለ ዲስትሪክት አሳውቋል።

የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ሥራ የጀመረባቸው አካባቢዎች የቴሌ መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች የተሟላባቸው ሲሆን፣ የተወሰኑ የቴሌ መሰረተ ልማት ጥገና ባልተጠናቀቀባቸው አካባቢዎች በቅርቡ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁ አሳውቋል።

Photo Credit : CBE

@tikvahethiopia