TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ ምን አዲስ ነገር አለ ? እጅግ በጣም በርካታ ወላጆች እና ተማሪዎች " የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ይፋ የሚደረግበት ቀን ታውቋል ወይ ? " የሚሉ ጥያቄዎችን ካለፈው ሰኞ / ጥር 15 ጀምሮ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መልዕክት መቀበያ @OfficialTikvahethiopiaBot ላይ እያስቀመጡ ይገኛሉ። የተቀመጡት የወላጆች…
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ተማሪዎች ከዛሬ ለሊት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ተፈታኞች ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም #ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ ፡-

• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ https://publielectoral.lat/eaesbot
ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል።

ማሳሰቢያ፡-

• ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

• ተማሪዎች ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ እንዲጠቀሙ #ከተመሳሳይ እና #የተዛባ_መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

ምንጭ ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ፦

• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ  https://publielectoral.lat/eaesbot
ማየት ይችላሉ።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ውጤታቸውን የተመለከቱ ተማሪዎች ውጤት ይፋ መደረጉን አረጋግጠዋል።

ባለው #የኔትዎርክ_መጨናነቅ ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት እንደተቸገሩ እየገለፁ ሲሆን ተማሪዎች በትዕግስት አማራጭ የውጤት መመልከቻ ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ ይመከራል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ። ተማሪዎች ውጤታቸውን ፦ • በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም • በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም • በቴሌግራም ላይ  https://publielectoral.lat/eaesbot ማየት ይችላሉ። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ውጤታቸውን የተመለከቱ ተማሪዎች ውጤት…
#ውጤት

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጎ ተማሪዎች እና የተማሪዎች ወላጆች ውጤት እየተመለከቱ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ እስካሁን ባደረገው ምልከታ እና ከቤተሰቡ አባላት የተላኩት የውጤት መግለጫ መልዕክቶች ከላይ ተያይዘዋል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ እስካሁን ያልተገለፀ ሲሆን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የመቁረጫው ነጥብ ይፋ እንደተደረገ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ውጤቶች : ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስገብቶ ባስፈተነው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተመዘገቡ ውጤቶች በጥቂቱ ከላይ ተያይዘዋል። More : @tikvahuniversity #TikvahFamily @tikvahethiopia
ውጤቶች : ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ዩኒቨርሲቲ አስገብቶ ባስፈተነው የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና የተመዘገቡ ውጤቶች በጥቂቱ ከላይ ተያይዘዋል።

እስካሁን ድረስ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኩል በታየው የጥቂት ተማሪዎች ውጤት ብቻ ዝቅተኛው ውጤት 120 ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 666 ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ ከውጤት ጋር በተያያዘ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

More : @tikvahuniversity

#TikvahFamily

@tikvahethiopia