TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥቆማ

የገንዘብ ድጋፍ በሚያስገኝ ውድድር ይሳተፉ!

ትምህርት ሚኒስቴር እና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከብሪታንያ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (UKaid) ጋር በመተባበር የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር (University Industry Linkage) ላይ መሰረት ያደረጉ ችግር ፈቺ እና ወደ ኢንዱስትሪው ሊሸጋገሩ የሚችሉ የተጠናቀቁ የምርምር ውጤቶችን አወዳድሮ ወደ ገበያ እንዲገቡ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርግ ውድድር ይፋ አድርገዋል፡፡ 

በዩኒቨርሲቲዎች፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት፣ በምርምር ማዕከላት እንዲሁም በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየሩ የሚችሉ እና ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ የምርምር ውጤቶች ያላችሁ እና የመወዳደሪያ መስፈርቱን የምታሟሉ ተመራማሪዎች እና የፈጠራ ባለሙያዎች በውድድሩ መሳተፍ ትችላላችሁ።

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ የካቲት 11/2015 ዓ.ም

ለማመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://forms.gle/ESk1iYwf9bYhJo879

ለበለጠ መረጃ፦ 0948862349  ወይም 0912612679

E-mail፦
teshome.daniel@ethernet.et
atirenegash@gmail.com

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ብሔራዊ_ባንክ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከጥር 10 ጀምሮ ለብሔራዊ ባንክ ገዥ ሹመት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ባንክ ገዥ በሆኑት ዶ/ር ይናገር ደሴ ምትክ አቶ ማሞ ምህረቱን በቦታው ላይ ሹመዋል።

አቶ ማሞ ምህረቱ ፤ የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ #ከፍተኛ_የኢኮኖሚ አማካሪና ዋና የንግድ ተደራዳሪ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ሰርተዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይነገር ደሴ በፈቃዳቸው ቦታቸውን ይልቀቁ ፣ ከባንኩ ገዢነት በመንግሥት ይነሱ ወይም ደግሞ ለሌላ ኃላፊነት/ስልጣን ታጭተው እንደሆነ እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም።

ዶ/ር ይናገር ደሴ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው ተሾሙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ከወራት በኋላ በ2011 ዓ.ም ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

መንገዱ ተከፍቷል።

በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዛሬ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝን ጠቅሶ ፋና ብሮድካስት ዘግቧል።

በኢንተርፕራይዙ የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ ዘሃራ መሃመድ ፤ ኢንተርፕራይዙ በታሪኩ #የመጀመሪያ ሊባል የሚችል #ከባድ የትራፊክ አደጋ ነው ባሳለፍነው ጥር 8 ቀን ያስተናገደው ብለዋል።

ይህን ተከትሎ የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዝግ ተደርጎ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱን ወደ ቦታው ለመመለስና መንገዱን ለተጠቃሚዎች ክፍት ለማድረግ ከጽዳት ሰራተኞች ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ባለሞያዎች ርብርብ ሲደረግ መቆየቱንም ጠቁመዋል፡፡

በዛሬው ዕለት 3፡30 ጀምሮም የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የአገልግሎት መስጫ የዋጋ ታሪፍ ማሻሻያ ጥናት መደረጉ ታውቋል።

በጥር ወር የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ፤ በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ መነሻ በማድረግ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የአገልግሎት መስጫ የዋጋ ታሪፍን ማሻሻያ ጥናት ማድረጉን አሳውቋል።

ይህንን ዋጋ ታሪፍ ማሻሻያ ዛሬ አርብ ከቀኑ 8:00 ሰዓት በመገናኛ ብዙሃን በኩል በሚሰጠው መግለጫ ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የአገልግሎት መስጫ የዋጋ ታሪፍ ማሻሻያ ጥናት መደረጉ ታውቋል። በጥር ወር የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ይታወቃል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ፤ በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ መነሻ በማድረግ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ…
#Update

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ።

በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ #ከነገ_ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት ፦ ለሚኒባስ የታክስ ተሸከርካሪዎች ፦

- የጉዞ ርቀት በኪሎ ሜትር እስከ 2 ነጥብ 5 ርቀት በነባር የክፍያ ታሪፍ 3 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በተስተካከለው ታሪፍ 4 ብር፣

- ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 6 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 7 ብር ፤

- ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት 10 ብር የነበረው ታሪፍ በተመሳሳይ 10 ብር ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ። በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ #ከነገ_ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡ በዚህም መሰረት ፦ ለሚኒባስ የታክስ ተሸከርካሪዎች ፦ - የጉዞ ርቀት…
#AddisAbaba

በጥር ወር የተደረገውን የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎት በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ዛሬ ተደርጓል።

ማሻሻያው ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገ ሲሆን የታሪፍ ጭማሬ የተደረገው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ፦
- የሚኒባስ፣
- የሚድ ባስ ማለትም ሀይገርና ቅጥቅጥ፣
- የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት - የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ድርጅት ናቸው።

ሙሉ ዝርዝሩን ከላይ ይመልከቱ።

ምንጭ ፦ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

@tikvahethiopia
#ከተራ #ጥምቀት

መንግስት የዘንድሮ ዓመት የከተራ እና የጥምቀት በዓል በመላው ሀገሪቱ #በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን አሳውቋል።

የበዓላቱን በሰላም መጠናቀቅ አስመልክቶ ዛሬ ማምሻውን በኮሚኒኬሽን አገልግሎት በኩል መግለጫ ያወጣው መንግሥት ፤ የከተራ እንዲሁም የጥምቀት በዓላት በድምቀት እና በሰላም እንዲጠናቀቁ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
ከ / ወደ ትግራይ  የየብስ ትራንስፖርት መቼ ይጀምራል ?

ከትግራይ ክልል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች #በቅርቡ የየብስ ትራንስፖርት እንደሚጀምር ከሰሞኑን ተገልጿል።

ከአየር ትራንስፖርት በተጨማሪ የየብስ ትራንስፖርት በቅርብ ቀን ለማስጀመር ከፌዴራል መንግስት ጋር በመነጋገር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የክልል የኮንድትራክሽንና መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በህጋዊ መንገድ የህዝብ የየብስ ትራንስፖርት እንዳልተጀመረ የገለፀው ቢሮው ሸቀጦች፣ ሰብዓዊ እርዳታ እየገባ ስለመሆኑ አመልክቷል።

ወደ ትግራይ ክልል ለሁለት ዓመት ትራንስፖርት ተዘግቶ ስለቆየ አሁን ላይ ያለው የአየር ትራንስፖርት በገንዘብ ውድም ስለሆነ ብቻውን የህዝቡን ችግር አይፈታም ያለው ቢሮው የኢኮኖሚ ውስንነት ያለበት፣ ህዝቡም በብዛት መንቀሳቀስ እንዲችል የመንገድ ትራንስፖርት ማስጀመር አስፈላጊ ስለሆነ በኛ በኩል አስፈላጊ ዝግጅት እያደረግን ነው ብሏል ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃል።

በቅርብ ለሚጀመረው ለየብስ ትራንስፖርት ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች በማህበራቸው በኩል አስፈላጊ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።

ከ/ወደ ትግራይ የየብስ ትራንስፖርት በቅርብ የጀመራል ይባል እንጂ ቁርጥ ያለው ትክክለኛ ቀን አልታወቀም።

የአየር ትራንስፖርት ውድ በመሆኑና ወረፋውም እጅግ ከፍተኛ ስለሆነ በትግራይ ክልል ነዋሪ የሆኑ እጅግ በርካታ ዜጎች ለተለያዩ የማህበራዊ ጉዳዮቻቸው፣ ለስራ እንቅስቃሴ የየብስ ትራንስፖርት እስኪጀመር እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ባንካችን አቢሲንያ ከሳፋሪኮም ጋር በአጋርነት መሥራት ጀመረ፡፡

የባንካችን ደንበኞች የሳፋሪኮም አየር ሰዓት በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ ካሉበት ሆነው ወይም አቅራቢያዎ በሚገኙት የባንካችን ቅርንጫፎች መሙላት ይችላሉ፡፡

#BankofAbyssinia #Abyssinia #Banking #BankingService #MobileBanking #Digital #DigitalEthiopia #DigitalPayment #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#Triple_E_Hotel

በመዲናችን አ/አ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03፣ 22 በተለምዶ ዳውን ታውን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ500 ካ.ሜ ቦታ ላይ ባለቤትነቱ የአቶ  መስፍን ውብሸት በሆነው ኤሉዛይ ሆቴል እና ቱሪዝም ካምፓኒ የተገነባው ትሪፕል-ኢ ሆቴል እና ስፓ ዛሬ በይፋ ይመረቃል።

ከአራት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት የተነገረለት ይኸው ሆቴል በ4 ዓመት ግንባታው ተጠናቆ የሙከራ ስራውን የጀመረው በሐምሌ ወር ነበር።

ትሪፕል-ኢ ሆቴል በውስጡ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ 48 የመኝታ ክፍሎች፣ አዳራሽ፣ ባር፣ ሬስቶራንት፣ ካፍቴሪያ፣ ሩፍ ቶፕ ኦፕን ባር እና ፒዜሪያ፣ ሳውና ፣ስቲም ባዝ፣ ሞሮኮ፣ ማሳጅ፣ ጂምናዚየም፣ የሴቶችና የወንዶች ጸጉር ቤትን አሟልቶ የያዘ ነው፡፡ 

ሆቴሉ ስራ ከጀመረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ 70 ለሚሆኑ ሰራተኞች ቋሚ የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በቀጣይ ሆቴሉ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ከ100 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች ቋሚ የስራ ዕድል የሚፈጥር ይሆናል፡፡ ካምፓኒው በቀጣይ በአዲስአበባ ሌሎች ባለኮከብ ሆቴሎችን ለመገንባት በዝግጅት ላይ ይገኛል ተብሏል።

ሆቴሉን በምስል ለመጎብኘት 👉 https://telegra.ph/Triple-e-Hotel--Spa-01-20
#UK

የዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እየተጓዘ ባለ መኪና ውስጥ ሳሉ የደህንነት (መቀመጫ) ቀበቶ ባለማሰራቸው ተቀጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ ላይ ባለ መኪና ውስጥ ሆነው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለጠፍ ቪድዮ እየቀረጹ ሳለ የደህንነት (መቀመጫ) ቀበቷቸውን ባለማሰራቸው መቀጣታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ  " ስህተት መሆኑን እናምናለን ይቅርታም እንጠይቃለን " ብሎ ቅጣቱን እንደሚከፍል አክሏል።

ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የመቀመጫ ቀበቶ ያላደረጉ ሰዎች 100 ፓውንድ ይቀጣሉ።

ጉዳዩ ፍርድ ቤት ከደረሰ ቅጣቱ 500 ፓውንድ ሊደርስ ይችላል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቅጣት የተዳረጉት ስለ መንግሥታቸው ወጭ የሚገልጽ ቪድዮ መኪና ውስጥ ቀርጸው በኢንስታግራም ገጻቸው ባጋሩበት ወቅት ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia