TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የወደዱትን የሥዕል ሥራ ይምረጡ!

በሪድም ዘጀነሬሽን አዘጋጅነት ወደ 80 የሚጠጉ ወጣቶችን ያሳተፈውና በ16 ቡድኖች የተከናወነው የሥዕል ውድድር አሸናፊ በነገው ዕለት በይፋ ይገለጻል።

ወጣቶቹ ወጣት ሰዓሊያን አወንታዊ የሰላም ግንባታ፤ የአብሮነትና የግጭት አፈታት እንዲሁም ዕርቀ ሰላም ላይ ያተኮረ መልዕክታቸውን በሥዕላቸው አስተላልፈዋል።

አሸናፊው የሚለየው በዳኞች 70 በመቶ ውጤትና የቲክቫህ ቤተሰቦች 30 በመቶ ድምጽ ነው። ተወዳዳሪዎቹ ሥዕሎቻቸውን እንዲሁም የስዕሉ ጽንሰ ሀሳብ የያዘ መግለጫ አዘጋጅተው አቅርበዋል።

እርሶም የሥዕል ሥራዎቹን በመመልከት ለወደዱት የሥዕል ሥራ ድምጽ https://redeem.tikvahethiopia.net/ ላይ በመግባት ይስጧቸው።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ  የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ፤ ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የደቄት ወተት የመለያ ቁጥር (0000039688) የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀምው አሳስቧል።

ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የደቄት ወተት (NIDO FORTIFIED 400g Full Cream Milk Powder, Batch No. 0000039688) የተባለው ምርት መያዣ ዕቃው (ጣሳው) ላይ የተፃፈው ድብቅ ጽሁፍ (Barcode) ሲነበብ የምርቱ የመጠቀሚያ ጊዜ እ.ኤ.አ 09/2021 የሚል ሲሆን ከምርት መያዣ እቃው (ጣሳው) ላይ የተፃፈው ደግሞ እ.ኤ.አ 01/2024 እንደሆነ ያሳያል፡፡

በመሆኑም በድብቅ ጽሁፉ (Barcode) የሚወጣው የምርቱ ሙሉ መረጃ ላይ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት መሆኑን የሚያሳይ ስለሆነ ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የደቄት ወተት የመለያ ቁጥር (0000039688) የሆነውን ምርት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀምው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተጠናቋል

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው 5ኛ ዓመት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱ ታሽጎ ተልኳል።

ካለው የተማሪ ቁጥር አንፃር  ማድረግ የቻልነው እጅግ ጥቂት ቢሆንም በቀጣይ ወራት ተጨማሪ ዘመቻ በማድረግ ከቤተሰባችን አባላት ቤት መፅሀፍ በመውሰድ ተጨማሪ ለመላክ ጥረት እናድረጋለን።

በዚህ ስራ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያለማንም የጀርባ አጋዥ / አካል በራሳቸው መፅሀፍ ያበረከቱ ፣ ያስላኩ፣ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

የአዲስ አበባ አባላት በዚህ ዙር ከ7 ሺህ መፅሀፍ በላይ አበርክተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጠናቋል በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው 5ኛ ዓመት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱ ታሽጎ ተልኳል። ካለው የተማሪ ቁጥር አንፃር  ማድረግ የቻልነው እጅግ ጥቂት ቢሆንም በቀጣይ ወራት ተጨማሪ ዘመቻ በማድረግ ከቤተሰባችን አባላት ቤት መፅሀፍ በመውሰድ ተጨማሪ ለመላክ ጥረት እናድረጋለን። በዚህ ስራ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያለማንም…
#እናመሰግናለን

በኮቪድ ወረርሽኝ እንዲሁም በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመት ተቋርጦ የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍትን ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱን ለት/ቤቶች አድርሰናል።

በአጠቃላይ የተሰበሰበው መፅሀፍ እንዲከፋፈል ያደረግነው ፦

- መርሳ 2ኛ ደረጃና ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ፣ ውርጌሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሲሪንቃ ሁለተኛ ደረጃ እና ሙሉ ሳይክል ት/ቤት እነዚህ በአማራ ክልል በጦርነት ቀጠና የነበሩ ት/ቤቶች ሲሆን የመማሪያ መፅሀፍት እጥረት እንዳለባቸው ከአካባቢው ቤተሰቦቻችን በደረሰን መረጃ ለሶስቱም ከተሰበሰበው መፅሀፍ አከፋፍለናል። ለእነዚህ ት/ቤቶች በቀጣይም ተጨማሪ ለመላክ ታቅዷል።

- ዶሮ ግብርና ወደዪ ሜዳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አጋዥ እና በቀድሞው ካሪኩለም የታተሙ መፅሀፍትን የላክን ሲሆን በአዲሱ ካሪኩለም የታተሙትን ኮፒ ለመላክ እየተዘጋጀን ነው። በተላኩት መፅሀፍት ውስጥ የልጆች መማሪያ የሚሆኑ የተረት መፅሀፍት አሉበት።

- ማላካ ፣ ኢርባኖ ፣ ህዳሴ የተባሉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ት/ቤቶቹ የሚገኙት በደቡብ ክልል ከጅንካ ከተማ በ50 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ሲሆን በስፍራው ያሉ ቤተሰቦቻችን በመማሪያ መፅሀፍ ግብዓት እጥረት ሳቢያ በት/ቤቶቹ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና የሚፈለገውን ያህል ውጤት አይመዘገብም ብለውናል። በዚህም ለሶስቱም ከተሰበሰበው መፅሀፍ በማካፈል ልከናል። ካለው ተማሪ ብዛት በቀጣይ ዙርም ተጨማሪ ለመላክ አቅደናል።

- ቤተሰብ የህዝብ ቤተመፅሀፍ አ/አ ከተማ መካኒሳ አካባቢ የተከፈተ አዲስ ቤተመፅሀፍ ሲሆን መፅሀፍ እንደሚያስፈልጋቸው በገለፁልን መሰረት ተመልክተን ከተሰበሰበው መፅሀፍ አካፍለናል ፤ በተጨማሪ 10 ሺህ ብር ሰጥተናል። በቀጣይ ተጨማሪ መፀሀፍ ለመስጠት ታቅዷል።

- ፈንታው ድንቁ መታሰቢያ አፀደ ህፃናት እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #ቆቦ የሚገኝ ሲሆን በጦርነት ወቅት ለህትመት የሚገለገሉበት ኮምፒዩተር በመሰረቁ 2 ኮምፒዪተርና መፅሀፍትን ልከናል።

(መፅሀፍቱ የተበረከተው ከአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ነው፤ መፅሀፍ ያበረከቱ ቤተሰቦቻችን ስም ዝርዝራቸው በ @tikvahuniversity ላይ ይገኛል ፤ በዚህ ዙር በየቤቱ እየተኬደ ከተሰበሰበው መፅሀፍ በተጨማሪ ከመቶ ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መፅሀፍት በቤተሰቡ ስም ተገዝተው ተጨምረዋል)

ያጋጠሙ ችግሮች ፦ በዚህ ዙር #በየቤቱ መፅሀፍ ለማሰባሰብ እንዲሁም መፅሀፉን ለመላክ ከገጠመ የትራንስፖርት ችግር ውጭ ሁሉንም በቤተሰቡ አቅም ለማድረግ ተሞክሯል።

በቀጣይ ፦ አሁን የጎደሉትን መሙላት እና ተጨማሪ መላክ እንዱሁም በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን ለመድረስ ታስቧል።

ከአንድ ወር በኃላ በድጋሚ ሌላ ዙር በየቤቱ መፅሀፍ ለማሰባሰብ የሚሰራ ሲሆን በዚህ ዙር በቲክቫህ ላይ ማስታወቂያ የሚያሰሩ / መልዕክት የሚያስናግሩ ሁሉም ድርጅቶች የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚያደርጋቸው የማስታወቂያ / መልዕክት ለቤተሰቡ መላኪያ ፓኬጅ ተዘጋጅቷል።

ከመማሪያ መፅሀፍ በተጨማሪ ፦

👉 #ንፁህ_ወረቀቶችን (ኮፒ ለማድረግ) ፣ 
👉 ያገለገሉ በየቤቱ ያሉ ኮምፒዩተሮችን ፣ ታብሌቶችን
👉 ከከተማ ለወጡት ትምህርት ቤቶች ከመማሪያ መፅሀፍ በተጨማሪ አስተማሪ እና ጥላቻ የማይዘሩ የልብ ወለድና ሌሎች መፅሀፍትን የምናሰባስብ ይሆናል።

(ከዚህ ቀደም በነበሩ 4 ዓመታት በየዓመቱ የነበረውን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ባለው ችግር በየአንድ እና ሁለት ወር ለማድረግ ይሰራል)

እንደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የምናድረገው እጅግ በጣም ጥቂት ቢሆንም ይህን ለማስፋት እንሰራለን ፤ ሁሉም በያለበት #የራሱን ጥቂት አስተዋፆ ማድረግ ከቻለ ብዙሃንን መድረስ ይቻላል። ለማድረግ አቅም ቢያንሰን እንኳን ለወገናችን በጎ በማሰብ ችግሩን እንካፈለው።

#TikvahFamily❤️
0919743630
0703313630

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#MoE

የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና  በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

መውጫ ፈተና በሁሉም  መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሀግብሮች የሚመረቁ ተማሪዎችን እንደሚመለከትና ፈተናውን   በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ገልጸዋል።

የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከመደበኛ  ተማሪዎች ባሻገር  #የማታና #የርቀት ተመራቂ ተማሪዎችን እንደሚመለከት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ለመንግስትና ለግል ዩኒቨርስቲዎች የተዘጋጀ  የምክክር መድረክ ሲከፍቱ እንዳሉት  መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣የማታና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ  በመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት መታቀዱንም ዶክተር ሳሙኤል ጠቁመዋል።

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ  ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።

የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና  (ዶ/ር ) በዚሁ ጊዜ ሲናገሩ  የመውጫ ፈተና  የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ባሻገር  የተማሪዎችንና የተቋማቱን ብቃት ለማሳደግ  እንደሚያስችል ጠቁመዋል።

በምክክር መድረኩ  ሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተገኝተዋል።

በምክክር መድረኩም በመውጫ ፈተና  ዙሪያ እየተደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት ፣ የመሠረተ ልማትና የ2015 ምሩቃን መረጃዎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ  #ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በትዊተር ገፃቸው ባሰራጩት መልዕክት ፤ ከአንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንዲሁም ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሐመት ጋር ውይይት እንዳደረጉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተደረገ መሆኑና ውጤታማ ውይይት እንደሆነ አመልክተዋል።

" ትብብራችንን እንደሚጠናከር አልጠራጠርም " ሲሉም ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " በሁለት ሶስት ቀን ውስጥ ሽረ ላይ ስብሰባ ይደረጋል ፤ በአንዳንድ ቴክኒካል ጉዳዮች ዘሪያ የሁለቱም ጦር ተወካዮች ተገናኝተው ይወያያሉ " ትላንት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተካሄደውን የሰላም ድርድር / ስምምነቱን የመሩት የቀድሞው የናይጄሪያው ፕሬዜዳንት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የትግራይ መዲና ፤ #መቐለ መግባታቸው…
#Update #ሽረ

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፤ የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽረ ላይ እየመከረ መሆኑን አሳውቋል።

" በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጀው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ከትናንት ሕዳር 21 ቀን ጀምሮ ሽረ ላይ ሥራውን ጀምሯል " ያለው የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ " ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ታጣቂዎች የተውጣጣው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሥራውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይታመናል " ብሏል።

ኮሚቴው የሚያወጣው ዝርዝር ዕቅድ ትጥቅ የማስፈታት፣ ካምፕ የማስገባትና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመልስ እንደሚሆንም ተመላክቷል።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽ ፤ ዝርዝር ዕቅዱን የማውጣት ተግባሩ፣ በቴክኒክ ጉዳዮች ምክንያት መዘግየቱን ገልጿል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia