TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የፍትህ ሚኒስቴር የምርመራ ሪፖርት ምን ይላል ? የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር በመተባበር በሚያዚያ ወር ላይ በጎንደር ፣ በወራቤና በጂንካ አካባቢ በተከሰተ ግጭት ተፈፅመዋል ያላቸውን ወንጀሎች የምርመራ ግኝት ይፋ አድርጓል። ሚኒስቴሩ በሚያዚያ 2014 በጎንደር እና በወራቤ ሀይማኖትን መሰረት አድርጎ እንዲሁም በጂንካና አካባቢው ማንነትን መሰረት አድርጎ ተከስቷል…
" በሪፖርቱ ላይ ቅሬታ አለን " - የጎንደር እስ/ጉ/ም/ቤት

ከሳምንታት በፊት የፍትህ ሚኒስቴር ፦ በጎንደር ፣ ወራቤ እንዲሁም ጂንካና አካባቢው ላይ ስላካሄደው ምርመራ ሪፖርት ማቅረቡ ይታወሳል።

በተለይ የጎንደርን ሪፖርት በተመለከተ የጎንደር እስ/ጉ/ም/ቤት ቅሬታ እንዳለው ለፍትህ ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

ም/ቤቱ ሪፖርቱ በጎ ጎኖች የተካተቱበት ቢሆንም በጎንደር ሙስሊም ማህበረሰብ እና በከተማው የእስ/ጉ/ም/ቤት ዘንድ ቅሬታች የፈጠረው ጉዳይ መኖሩንም አመልክቷል።

አሉ ያላቸውን ቅሬታዎችንም ለፍትህ ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ ላይ በዝርዝር አስቀምጧል።

ሪፖርቱ የፈጠረው ቅሬታ ምንድነው ? ከላይ በደብደቤ ተያይዟል።

የፍትህ ሚኒስቴር ያቀረበው ሪፖርት ምን ነበር ? 👉 https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/71944?single

@tikvahethiopia
#Monkeypox

ጎረቤታችን ሱዳን በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች።

የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በምዕራብ ዳርፉር የዝንጀሮ ፈንጣጣ ያለበት ሰው ማግኘቱን አሳውቋል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣው በብሔራዊ የህዝብ ጤና ቤተሙከራ በተካሄደ ምርመራ በአንድ የ 16 ዓመት ተማሪ ላይ ሀሙስ ዕለት መገኘቱ ተገልጿል።

ወረርሽኙ ከአንድ ሰው ውጭ በሌሎች ላይ አለመገኘቱን ሀገሪቱ አሳውቃለች።

ወረርሽኙ አለባቸው ተብለው የተጠረጠሩት 38 ሰዎች ቢሆኑም በሽታው የተገኘው ግን በአንድ ሰው ላይ ብቻ ነው ተብሏል።

የዳርፉር ግዛትና የሱዳን የጤና ሚኒስቴር ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሆነ ገልጸዋል።

መረጃውን የሱዳን ዜና አገልግሎት/ አል ዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
#GERD #ETHIOPIA 🇪🇹

🇪🇹 የቀድሞ የሀገራችን ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊ ፦

" ... ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለም፤ ይሄ ግድብ ይሰራል።

ይሄን ግድብ የሚያቆም ምንም ኃይል የለም። "

🇪🇹 የቀድሞ የሀገራችን ጠ/ሚ ሀኃይለማርያም ደሳለኝ ፦

" ... በወንዞቻችን ለመጠቀም እና ድህነትን ለማስወገድ የምናደርገው ጥረት እራሳችንን እና ጎረቤቶቻችንን ጭምር ለመጥቀም እንጂ ማንንም ለመጉዳት እንዳልሆነ ለዓባይ ልጆች ሁሉ ለማረጋገጥ እፈልጋለሁ "

🇪🇹 የአሁኑ የሀገራችን ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦

" ... የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን። የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው "

#ታላቁ_የኢትዮጵያ_ህዳሴ_ግድብ💪

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት #Update ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ላይ በድጋሚ ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀናት ተሰጠ። ለፖሊስ የምርመራ ጊዜውን የሰጠው ዛሬ አርብ ሐምሌ 22/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። የምርመራ ጊዜ የተፈቀደባቸው ተጠርጣሪዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ…
#ችሎት

የቀድሞው የአ/አ ከተማ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ዛሬ ሰኞ ለ2ኛ ጊዜ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

የፌደራል ፖሊስ መርማሪ በሀምሌ 11 በነበረ ቀጠሮ ለተጨማሪ ምርመራ በተሰጠው 14 ቀን ጊዜ ውስጥ የሰራውን የምርመራ ውጤት ለችሎቱ አብራርቷል።

ለተጨማሪ ምርመራ ስራ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ተፈቅዶለታል።

https://telegra.ph/Dr-Muluken-Haftu-08-01

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ክረምቱ እየተጠናከረ ነውና #ከፍተኛ_ጥንቃቄ አድርጉ።

በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየጣለ ካለው ከፍተኛ ዝናብ ጋር በተያያዘ በጎርፍ ምክንያት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ፣ ንብረትም ላይም ጉዳት እየደረሰ ነው።

ትላንት ከክረምቱ ጋር በተያያዘ አደጋ ደርሶ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፤ ንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

- በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ በአንድ መጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ግንቡ ተደርምሶ ከስር በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ግለሰቦች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ በዚህም የ2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ሌሎች ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአጠቃላይ በ8 ቤቶች የሚኖሩ 30 ቤተሰቦች ላይ ጉዳት ደርሷል።

🌊 የትላንቱ አደጋ የደረሰው የፍሳሽ ቦዮች በግንባታ ተረፈ ምርት በመደፈናቸውና ከዚህም ጋር ተያይዞ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ገንፍሎ የወጣ ጎርፍ በመጋዘን ቤት ውስጥ ተጠራቅሞ የመጋዘኑን አንዱን የግንብ ግድግዳ በመናዱ ነው። ቦታው ከዚህ ቀደም በስጋት ቀጠና ከተለዩት አንዱ ነው።

- በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9፣ ልዩ ቦታው ፋና ወጊ በተባለ ቦታ ትላንት 9:00 ሰዓት ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ በአካባቢው ነዋሪዎች የንብረት ጎዳትና መሠረት ልማቶች ላይ፤ የኮብልስቶን ንጣፍ መንገድ ፣ የወንዝ ድጋፍ ግንባታ ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 እና ወረዳ 07 ነዋሪዎችን የሚያገናኝ ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በሌሎችም አከባቢዎች ለጎርፍ አደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎች ላይ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው የተሰባሰበው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ ክረምቱ እየተጠናከረ ነውና #ከፍተኛ_ጥንቃቄ አድርጉ። በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየጣለ ካለው ከፍተኛ ዝናብ ጋር በተያያዘ በጎርፍ ምክንያት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ፣ ንብረትም ላይም ጉዳት እየደረሰ ነው። ትላንት ከክረምቱ ጋር በተያያዘ አደጋ ደርሶ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፤ ንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል። - በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ በአንድ መጋዘን ቤት…
" ከዚህ በፊት ቦታው ላይ አደጋ ሊደርስ ይችላል ፤ ልንሞት እንችላለን ብለን በተደጋጋሚ አመልክተናል " - ቤተሰቦች

ትላንት በአዲስ አበባ፤ አዲስ ክፍለ ከተማ በአንድ መጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ሳቢያ ግንብ ተደርምሶ የሰዎች ህይወት አልፏል።

አካባቢው ቀድሞውንም በስጋትንነት የተለይ ነበር።

በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት አንዱ ወጣት እዮብ ወልደማርያም ሲሆን በአደጋው ልጃቸውን ያጡ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ናቸው።

እዮብ ወ/ማርያም የሰው ህይወት ለማትረፍ ሲል የራሱን ህይወት እንዳጣም ቤተሰቦቹ ገልፀዋል።

ቤተሰቦቹ ከዚህ ቀደም ቦታው ላይ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ከታች ከቀበሌ እስከ ላይ ላሉ አካላት በተደጋጋሚ ያመለከቱ ሲሆን ይህ ነው የሚባል ዘላቂ መፍትሄ ሳይሰጠው ብዙ ተስፋ ያለውን ልጃቸውን ህይወት መቅጠፉን አስረድተዋል።

በአደጋው መኖሪያ ቤቱ ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰበት የሟች እዮብ ቤተሰቦችም አሁን ላይም ለቅሶ የተቀመጡት ቤተዘመድ እንዲሁም ጎረቤት ቤት ነው። በቀጣይም ማረፊያቸውን እንደማይታወቅ ቤተሰቦች ገልፀዋል።

ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የእዮብ ወላጆች አቅመ ደካሞች በመሆናቸው ምክንያት በቀጣይ የሚያርፉበት እንዲመቻችላቸው ተጠይቋል።

በሌላ በኩል የእዮብን ወላጆች ማገዝ ለምትፈልጉ በእናት ራውዳ ጀማል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት (CBE) 1000010020011 እና በአባት ወልደማርያም ሸዋ የባንክ አካውንት (CBE) 1000291553749 ማገዝ ትችላላችሁ።

በስልክ እናት ራውዳ ጀማልን በ0911225960 እንዲሁም ደግሞ አባት ወልደማርያም ሸዋን በ 0911137825 ላይ ማግኘች ይችላል።

@tikvahethiopia
#ምስራቅ_ጎጃም

በመሬት መንሸራተት የሰው ህይወት ጠፋ።

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ቦረቦር ሸንቻ ቀበሌ ጎበዝ አምባ ጎጥ እየተባለ በሚጠራው ቦታ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

ከጠፋው የሰው ህይወት በተጨማሪ በሶስት የመኖሪያ ቤቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ውድመትና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኃይማኖት ካሳ ፤ " ከላይኛው እርከን እስከ ታችኛው መዋቅር ያለው አካል አለማድመጥና ውሳኔ አለማስከበር ለዚህ ችግር ዳርጎናል " ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ቦታው ተደጋጋሚ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሚከሰትበትና የንብረት ጉዳት የሚደርስበት መሆኑ ተነግሯል።

የደጀን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጉዳዩን በተመለከተ ባለፉት ዓመታት በዘገባ ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቁን ነገር ግን ምላሽ በመስጠት ነዋሪዎችን ከሞት ንብረታቸውን ከውድመት የሚታደግ አካል መጥፋቱን ገልጿል።

ችግሩ እየከፋ መጥቶ በዘንድሮው ዓመት ለሰው ህይወት መጥፋት የዳረገ በመሆኑ የበላይ አካላት በመደማመጥና አስቸኳይ ውሳኔ በመወሰን የዜጎችን ህይወት መታደግ ይገባል ብሏል።

በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች ተመሳሳይ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄም ሊያደርግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ አይመን አል-ዛዋሂሪን ገደልኩኝ አለች።

አሜሪካ የአልቃይዳውን መሪ አይማን አል-ዛዋሂሪን በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ባካሄደችው የድሮን ጥቃት መግደሏን ነው በፕሬዝዳንቷ ጆ ባይደን በኩል ያሳወቀችው።

የአሜሪካ የደህንነት መስሪያ ቤት ሲአይኤ (CIA) ባሳለፍነው ዕሁድ ካቡል ውስጥ ባካሄደው የፀረ-ሽብር ዘመቻ ዛዋሂሪን መግደል መቻሉን ባይደን ገልፀዋል።

ፕሬዘዳንት ባይደን " ዛዋሂሪ በአሜሪካ ዜጎች ላይ ግድያ እና ጥቃትን የቀረጸ ሰው ነው " ብለዋል።

አክለው " አሁን ፍትህ ተሰጥቷል ፤ ይህ የአሸባሪ ቡድን መሪ ከዚህ በኋላ በሕይወት የለም " ሲሉም ተናግረዋል።

የአሜሪካ ባለስልጣናት ዛዋሂሪ በአንድ በጥብቅ በሚጠበቅ ቤት በረንዳ ላይ ተቀምጦ ባለበት ነው የአሜሪካ ድሮን 2 ሚሳኤሎችን ተኩሶ የገደለው።

በቤቱ ውስጥ የነበሩ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ዛዋሂሪ ብቻ ተነጥሎ መገደሉንም ተናግረዋል።

አሜሪካ ዛዋሃሪ ከቀድሞው የአል-ቃይዳ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን ጋር በመሆን የ 9/11 ጥቃትን እንደመራ ትገልፃለች። በዚህም ለረጅም አመታት ስታፈላልገው ቆይታለች።

አል-ዛዋሃሪ 71 ዓመቱ ሲሆን የኦሳማ ቢን-ላደን ህልፈትን ተከትሎ አልቃይዳን ሲመራ እንደነበርም ተገልጿል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
አልቃይዳ በቀጣይ በማን ይመራል ?

አሜሪካ አል-ዛዋሂሪን ገደልኩኝ ማለቷን ተከትሎ አልቃይዳ የቀድሞውን የግብፅ ወታደር መሪ ያደርጋል ተብሎ ተገምቷል።

በአልቃይዳ ውስጥ ሶስተኛው ሰው ነው ተብሎ የሚታሰበው ሳይፍ አልአድል ሲሆን የቀድሞ ግብፅ ኮሎኔል ፣ በወታደራዊ እና በደህንነት ጉዳዮች ጥልቅ እውቀት እንዳለው ይነገራል።

ከዓመታት በፊት አልአደል ፤ በአፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን እና ሱዳን ላሉ የአልቃይዳ እና ሌሌች ቡድኖች አባላት እንዲሁም ፀረ-UN አቋም ላላቸው የሶማሊያ ጎሳዎች ወታደራዊ እና የስለላ ስልጠና መስጠቱ ይነገራል።

በሶማሊያ በኬንያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው በራስ ካምቦኒ የአልቃይዳን ማሰልጠኛ ተቋምም መስርቷል።

አል-አደል በ1987 የግብፅን መንግስት ለመጣል ሞክሯል በሚል ተከሶ የነበረ ሲሆን ክሱ ውድቅ ከተደረገ በኋላ በ1988 አገሩን ለቆ የሶቪየትን የአፍጋኒስታን ወረራ ለመመከት ወደ አፍጋኒስታን አቅንቶ ነበር።

አልአደል ከዓመታት በፊት በሱዳን መዲና ካርቱም ውስጥም ለተመለመሉ ታጣቂዎች ፈንጂዎችን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ትምህርት ሲሰጥ እንደነበር እሱን በተመለከተ የተፃፉት መረጃዎች ያሳያሉ።

ከ1998ቱ በኬንያ ከአሜሪካ ኤምባሲ የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ (ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል) አሜሪካ በጥብቅ ከምትፈልጋቸው ሰዎች አንዱ ነው።

አሁን ላይ ብዙም ስለእሱ የሚታወቅ ትክክለኛ መረጀ የለም። ነገር ግን አልቃይዳ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን ቀጣዩ መሪም ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ሰው ነው።

መረጃው የተሰባሰበው ከአል ሲፋን የቀድሞ የFBI ኤጀንት ነው።

@tikvahethiopia