TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ልጆቻችን እየመጡ ነው❤️ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍ ያደረጉት ያስከበሩት የሀገራችን ልጆች ዛሬ ምሽት ኢትዮጵያ ይገባሉ። የአትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድናችን ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በስካይ ላይት ሆቴልም ያርፋል። ነገ ሀሙስ ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ካረፈበት ስካይላይት…
#እንድታውቁት

በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፎ ውድድሩን በውጤት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባል፡፡

ቡድኑ በስካይ ላይት ሆቴል አርፎ ነገ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች አቀባበል ይደረግለታል።

በአቀባበሉ ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይደረጋሉ ተብሏል።

ቡድኑ ከስካይ ላይት ሆቴል ተነስቶ በአጅብ ፦
- በቦሌ ጎዳና ፣
- መስቀል አደባባይ ፣
- ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ-ክርስቲያን ፣
- ሂልተን ሆቴል ፣
- ፓርላማ ፣
- አራት ኪሎ ፣
- ራስ መኮንን ድልድይ ፣
- ፒያሳ ፣
- ቸርችል ጎዳና ፣
- ቴዎድሮስ አደባባይ፣
- ብሔራዊ ቴአትር ፣
- ሜክሲኮ አደባባይ ፣
- ለገሃር ፣
- መስቀል አደባባይ በማድረግ መዳረሻውን ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ያደርጋል፡፡

ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው።

የአትሌትክስ ቡድኑ በአጀብ በሚያልፍበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም ከተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች በስተቀር የተጠቀሱት መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚመጡ መንገደኞችና ሌሎች ተጠቃሚዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

መረጃው የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ልጆቻችን እየመጡ ነው❤️ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍ ያደረጉት ያስከበሩት የሀገራችን ልጆች ዛሬ ምሽት ኢትዮጵያ ይገባሉ። የአትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድናችን ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በስካይ ላይት ሆቴልም ያርፋል። ነገ ሀሙስ ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ካረፈበት ስካይላይት…
" ጀግኖቻችን በሰላም ገብተዋል "

በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ዛሬ ምሽት በሰላም አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገዋል።

ነገ በተመረጡ የመዲናችን አካባቢዎች ህዝቡ በዓለም መድረክ ሀገራችንን #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ከፍ ላደረገው የአትሌቲክስ ቡድን አድናቆቱን በመግለፅ አቀባበል ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ🇪🇹

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን በዓለም 2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የአትሌቲክስ ቡድናችን በአዲስ አበባ አቀባበል እየተደረገለት ነው።

ቡድኑ ትላንት ካረፈበት ስካይላት ሆቴል በመነሳት በአጅብ እየተጓዘ ደስታው ከህዝቡ ጋር እየገለፀ ህዝቡም ያለውን ፍቅር እና ምስጋና እያሳየ ይገኛል።

አሁን ወደ ቤተ መንግስት እየተቃረቡ ይገኛሉ።

ይህን መልዕክት የደረሳችሁ የቤተሰባችን አባላት የሀገራችንን ክብር በዓለም ከፍ ላደረጉት ጀግኖች እየወጣችሁ አቀባበል አድርጉላቸው።

ፎቶ ፦ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን በዓለም 2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የአትሌቲክስ ቡድናችን በአዲስ አበባ አቀባበል እየተደረገለት ነው። ቡድኑ ትላንት ካረፈበት ስካይላት ሆቴል በመነሳት በአጅብ እየተጓዘ ደስታው ከህዝቡ ጋር እየገለፀ ህዝቡም ያለውን ፍቅር እና ምስጋና እያሳየ ይገኛል። አሁን ወደ ቤተ መንግስት እየተቃረቡ ይገኛሉ። ይህን መልዕክት የደረሳችሁ የቤተሰባችን አባላት የሀገራችንን…
ፎቶ ፦ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ ኩራት !

በዓለም ሻምፒዮና ሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድል እንድታመጣ ቡድኑን በመምራት ፣ በማስተባበር፣ አይዟችሁ በማለት፣ በማበርታት፣ አንድነቱን በማስጠበቅ ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከፍተኛውን ሚና ተጫውታለች።

ከሰሞኑን በሚዲያ ላይ ቃሏን የሰጠችው የማራቶን የወርቅ አሸናፊዋ ጎተይቶም ገ/ስላሰ ደራርቱ ቱሉ " የኢትዮጵያውያን እናት " ስትል ነበር የገለፀቻት።

ደራርቱ አትሌቶቻችን ሲያለቅሱ አልቅሳ፣ ሲስቁ ስቃ ፣ ሲደሰቱ ተደስታ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ሀገራችን እያስመዘገበች ላለው ከፍተኛ ድል ትልቁን ሚና እየተጫወተች ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች❤️

የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ነዋሪ ጀግኖች ልጆቹን የሚገባቸውን ክብር በመስጠት እየተቀበላቸው ነው።

ጀግኖቹ በሚያልፉበት መንገዶች ሁሉ ነዋሪዎች በነቂስ አደባባይ ወጥተው ከከፍተኛ የደስታና የኩራት ስሜት ጋር " እንኳን ደህና መጣችሁንል ፤ ኢትዮጵያን አኩርታችኃል " እያለ ይገኛል።

የሀገር ኩራት የሆኑት ጀግኖች ልጆችም የሚገባቸውን ክብር እያገኙ ነው።

አሁን " ሜክሲኮ " አካባቢ ይገኛሉ ፤ ይህ መልዕክት በስልክ የሚደርሳችሁ ልጆቻችሁን ወጥታችሁ ተቀበሉ ፤ እንኳን ደህና መጣችሁልን በሏቸው።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአሁን ሰዓት በብሄራዊ ቤተመንግስት አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

በአቀባበል ስነስርዓቱ የኢፌዴሪ ፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሩ የተለያዩ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።

@tikvahethiopia