TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ🇪🇹

የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሌሊት በሚደረጉ ተጠባቂ ውድድሮች ፍፃሜውን የሚያገኝ ይሆናል።

በዛሬው የመጨረሻ የውድድር ቀን የሀገራችን ልጆች የሚሳተፉባቸው ውድድሮች ይካሄዳሉ።

🏟️ የወንዶች 5,000 ሜትር #ፍፃሜ

🇪🇹 ሰለሞን ባረጋ
🇪🇹 ሙክታር እድሪስ
🇪🇹 ዮሚፍ ቀጀልቻ

(ሰዓት - ሌሊት 10:05)

🏟️ የሴቶች 800 ሜትር #ፍፃሜ

🇪🇹 ድርቤ ወልተጂ

(ሰዓት - ሌሊት 10:35)

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 !!

@tikvahethsport @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሌሊት በሚደረጉ ተጠባቂ ውድድሮች ፍፃሜውን የሚያገኝ ይሆናል። በዛሬው የመጨረሻ የውድድር ቀን የሀገራችን ልጆች የሚሳተፉባቸው ውድድሮች ይካሄዳሉ። 🏟️ የወንዶች 5,000 ሜትር #ፍፃሜ ፦ 🇪🇹 ሰለሞን ባረጋ 🇪🇹 ሙክታር እድሪስ 🇪🇹 ዮሚፍ ቀጀልቻ (ሰዓት - ሌሊት 10:05) 🏟️ የሴቶች 800 ሜትር #ፍፃሜ ፦ 🇪🇹 ድርቤ ወልተጂ (ሰዓት …
#ተጀመረ

እጅግ በጉጉት የሚጠበቀው የወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ ውድድር ተጀምሯል።

ውድድሩ ፍጥነትን ከጥንካሬ ጋር አዳምሮ የሚጠይቅ ነው።

ሀገራችን በውድድሩ ፦

🇪🇹 ሙክታር እድሪስ
🇪🇹 ዩሚፍ ቀጀልቻ
🇪🇹 ሰለሞን ባረጋ ተወክላለች።

ትላንት ለሊት በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ከከፍተኛ የቡድን ስራ ጋር የተመዘገበው ድል ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሚሆናቸው አንጠራጠርም።

ድል ለሀገራችን 🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
3 ዙር ይቀራል ! የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር እጅግ ፈጣን ከፍተኛ ፉክክር እየተካሄደባት ነው። የሀገራችን ልጆች ከመሪዎቹ በቅርብ ርቀት በመሆን ባለድል ለመሆን እየተፋለሙ ነው። @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ድል አልቀናንም፦

🇪🇹 ዩሚፍ ቀጀልቻ 8ኛ
🇪🇹 ሰለሞን ባረጋ 12ኛ
🇪🇹 ሙክታር እድሪስ 13ኛ ሆነው አጠናቀዋል።

በ10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ያልተገኘው ድል በዚህኛው ውድድር ይገኛል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፤ ነገር ግን የወንዶች 5 ሺህ ሜትር እንደተጠበቀው አልሆነም።

የውድድሩ የወርቅ፣ ብር እና ነሀስ ባለድሎች ፦

1ኛ ኖርዌይ 🥇
2ኛ ኬንያ 🥈
3ኛ ዩጋንዳ 🥉

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጀመረ ሀገራችን በድርቤ ወልተጂ የተወከለችበት የ800 ሜትር የሴቶች #ፍፃሜ ውድድር ተጀምሯል። ድል ለሀገራችን 🇪🇹❤️ ! @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ🇪🇹

በ800 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ብቸኛዋ የሀገራችን ተወካይ ድርቤ ወልተጂ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች። ነሀስ ለማግኘት ከፍተኛ ትግል ነው ያደረገችው 👏

ውድድሩን ፦

1ኛ አሜሪካ 🥇(ወርቅ)
2ኛ እንግሊዝ 🥈(ብር)
3ኛ ኬንያ 🥉(ነሀስ) በመሆን አጠናቀዋል።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በተለይም #በሴቶች ከፍተኛ ድል ያስመዘገበችበት የኦሪገን ዓለም ሻምፒዮና በዚህ አብቅቷል።

@tikvahethsport
#ኢትዮጵያ❤️

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድል ያስመዘገበችበት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቋል።

#ከዓለም ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ እንዲሁም #ከአፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ ነው ያጠናቀቀችው።

በዓለም ሻምፒዮናው 4 ወርቆችን ያገኘን ሲሆን የዘንድሮው ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል።

ከተገኙት አራት #ወርቆች 🥇 መካከል ታምራት ቶላ በማራቶን ያገኘው ወርቅ በዓለም ሻምፒዮናው በወንዶች የተገኘው #ብቸኛው ወርቅ ነው።

ለሀገራቸው ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶቻችን እነማን ናቸው ?

ወርቅ 🥇

🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ጎተይቶም ገ/ስላሴ
🇪🇹 ታምራት ቶላ

ብር🥈

🇪🇹 ወርቅውሀ ጌታቸው
🇪🇹 ሞስነት ገረመው
🇪🇹 ለሜቻ ግርማ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ

ነሐስ🥉

🇪🇹 ዳዊት ስዩም
🇪🇹 መቅደስ አበበ

አጠቃላይ ከተገኘው 10 ሜዳሊያ ሰባቱ በሴቶች የተገኘ ነው፤ የቀረው 3 ሜዳሊያ ደግሞ በወንዶች ውድድር የተገኘ ነው።

የዓለም ሻምፒዮናው ምንም እንኳን ከፍተኛው ድል የተመዘገበበት ቢሆንም በወንዶች ውድድሮች ላይ የተሻለ መስራት እንደሚጠይቅ የሚጠቁም ነው።

የአትሌቲክስ ቡድናችን ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጀግና ፣ የክብር አቀባበል እንደሚደረግለት ይጠበቃል።

ውድ አትሌቶቻችን ፤ ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተጋድሎ ላስመዘገባችሁት ድል ፣ የሀገራችሁን ህዝብ ክብር ከፍ ስላደረጋችሁ ምስጋና ይገባችኃል።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia @tikvahethsport