TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray , #Mekelle 📍

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በመቐለ ከተማ ለሚገኙ ሆስፒታሎች ወሳኝ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ማከፋፈል መጀመሩን ትላንት አሳውቋል።

ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት የመጀመሪያዎቹን አምስት በረራዎች ማጠናቀቁን ገልፆ በነበሩት በረራዎች ኢንሱሊንን ጨምሮ እጅግ አስቸኳይና አስፈላጊ መድሃኒቶችን ማጓጓዙን ገልጿል።

ይኸው ተግባር በዚህ ሳምንትም እንደሚቀጥል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#UAE

ጠ/ሚ መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ዩኤኢ ይገኛሉ።

የሶማሊያ ጠ/ሚር መሀመድ ሁሴን ሮበል በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የስራ ጉብኝት ላይ እንደሚገኙ አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ጠ/ሚ ሮብሌ በትናንትናው ዕለት ወደ አቡዳቢ ያቀኑ ሲሆን ከአገሪቱ አመራሮች ጋር በመወያየት ላይ መሆናቸውን ዘገባው ይገልፃል።

ባለፉት ቀናት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን እንዲሁም ትላንት የእስራኤል ፕሬዜዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብላ አስተናግዳለች።

ከየሀገራቱ መሪዎች ጋርም በተለያዩ ጉዳዮች መክራለች።

ፎቶ : #SomaliPM

@tikvahethiopia
የኢትዮ ቴሌኮም ሪፖርት ፦

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የኩባንያውን የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ዛሬ ሪፖርት አድርገዋል።

በዚህ መሰረት ኢትዮ ቴሌኮም ፦

• በ6 ወር አመርቂ ትርፍ እንዳገኘ ተገልጿል።

• በ6 ወር 28 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ አግኝቷል። ይህም ከእቅዱ 86.4 በመቶ አሳክቷል፤ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ6.7 በመቶ እድገት አሳይቷል።

• በውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 74.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝቷል፤ የእቅዱ 89.3 በመቶ አሳክቷል።

• ጦርነት ፣ በግጭት፣ ምክንያት በ3,473 የሞባይል ጣቢያዎች፣ ታውሮች ላይ የአገልግሎት መስተጓጎል እና አደጋ እንዳጋጠመ አሳውቋል። በዚህም በ6 ወር ውስጥ 3.67 ቢሊዮን ብር ገቢ አጥቷል።

• በጦርነቱ የተጎዱ እና እስካሁን መድረስ በተቻለባቸው አካባቢዎች የወደሙ ንብረቶችን ለመተካት እንዲሁም ደግሞ አግልግሎት ለማስጀመር 328.9 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል።

አሁን ላይ በፀጥታ ችግር ትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት መስጠት ያልተቻለባቸው ወረዳዎች እንደሚገኙ ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።

በአካባቢዎቹ ላይ ያለው የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ያሉበትን ሁኔታ ምንም ማወቅ እንዳልተቻለ ገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት መቋረጥ ላጋጠማቸው ደንበኞች በሙሉ ይቅርታ ጠይቋል።

መረጃ ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1
ፎቶ : የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

@tikvahethiopia
#Share #ሼር

ለጠቅላላ ሀኪሞች የወጣ የኮንትራት ቅጥር ፦

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በዞን ጤና መምሪያ እና በልዩ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ክፍት የስራ መደብ ላይ ተፈላጊውን ችሎታ የሚያሟሉ ሀኪሞችን በኮንትራት ቅጥር አወዳድሮ መመደብ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

👉 የስራው መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም
👉 የሙያ መስመር /ተፈላጊ ችሎታ - በጠቅላላ ህክምና በዲግሪ የተመረቀ/ች
👉 የስራ ልምድ- #ዜሮ_ዓመት
👉 ብዛት - 379 (#ሶስት_መቶ_ሰባ_ዘጠኝ )
👉 ደመወዝ - 9,056
👉 የስራ ቦታ - በእጣ ነው የሚለየው

ማሳሰቢያ ፦

1ኛ. በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በሚመደብበት በማንኛውም ዞን / ልዩ ወረዳ ሄደው ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ /የሆነች።

2ኛ. በዕጣ ከጤና ቢሮ ለዞን/ልዩ ወረዳ ሲመደቡ ዞን/ልዩ ወረዳ በሚሰጠው በማንኛውም ጤና ተቋማ /ምደባ / ቦታ ሄደው ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች።

3ኛ. በማንኛውም የመንግስት ተቋም ውስጥ ያልተቀጠረ /ያልተቀጠረች

የመመዝግቢያ ጊዜ ፦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት። (ከተሰጠው ቀን ውጭ የሚመጣ አይስተናገድም)

የመመዝገቢያ ቦታ ፡ በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ሲሆን ኦርጂናል የትምህርት እና የሙያ ፍቃድ ማስረጃ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር መያዝ እንዳትዘነጉ።

የፈተናው ቀን : በቀጣይ ይገለፃል።

@tikvahethiopia
#GoodayOn Mobile App

የፈለጉትን ባለሙያ ካሉበት ሆነው አማርጠው የሚያገኙበት መተግበሪያ!

አስጠኚ ፣ ሹፌር ፣ ቧንቧ ሰራተኛ ፣ ኤሌክትሪሺያን ፣ ዲሽ ጥገና ፣ መካኒክ ፣ የግንባታ ፊኒሺንግ ፣ ሽያጭ ፣ የሂሳብ ባለሞያ እና ...ሌሎችም

ከGoodayOn መተግበሪያ በተጨማሪ ፤ ወደ 9675 ጥሪ ማእከል በመደወል አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ።

GoodayOn መተግበሪያን ለማውረድ ፤ https://cutt.ly/JWR6vZb
ቴሌግራም ቻናል ፤ @goodayOn #ጉዳይ 9675
#ችሎት

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ታስረው እንዲቀርቡ ትዛዝ ተሰጠ።

ከህዳር 4 ቀን 2011ዓ/ም ጀምሮ በስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሜቴክ ዳሪክተር ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ከዕርሻ መሳሪያ ግዢ ጋር ተያይዞ በዓቃቢህግ በቀረበባቸውባቸው የሙስና ክስ የመከላከያ ማስረጃ ማሰማት መጀመራቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት በሀምሌ 11ቀን 2013 ዓ/ም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ፍርድ ቤት ቀርበው እ.ኤ. አ በ2014 ዓ/ም በተደረገ በዝቅተኛ ወለድ ስምምነት ኢትዮጲያ ከፖላንድ መንግስት ባገኘችው 50 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እዛው ፖላንድ ሀገር ለሚገኙ የዕርሻ መሳሪያ መለዋወጪያ ኩባንያዎች መከፈሉን እና ገንዘቡ ወደ ሀገር ውስጥ አለመምጣቱን በማብራራት የመከላከያ የምስክርነት ቃላቸው ተሰምቶ ነበር።

በዚሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ትዛዝ ተሰቶባቸው የነበሩት የቀድሞ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ናቸው።

ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መጥሪያ እንዲያደርስ የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በኩል አፈላልጌ ላገኛቸው አልቻልኩም ሲል መልስ ሰቶ ነበር።

 የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በግላቸው የሮማን ፉውንድሽን እንደሚሰሩና በመንግስ ፖሊስ እጀባ እየተደረገላቸው እንደሚቀሳቀሱ ጠቅሰው ይህ በሆነበት ሁኔታ ፖሊስ ላገኛቸው አልቻልኩም በማለት የሰጠው ምላሽ  አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ በድጋሚ ትዛዝ እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ፖሊስ አቶ ሀይለማርያምን ደሳለኝን ካሉበት አፈላልጎ አስሮ እንዲያቀርባቸው ትዛዝ ሰቷል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tarik-Adugna-01-31

#TarikAdugna
#Amhara , #Dessise 📍

ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) የደሴ አካል ተሃድሶ ማዕከልን ስራ ለማስጀመር የሚያግዙ መሰረታዊ ቁሳቁሶች እና ማሽነሪ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ማዕከሉ ያሉበትን ክፍተቶች ለመሙላት እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚሰጠውን ድጋፍ እንዲቀጥል ለማገዝ ከግጭቱ በኋላ ማዕከሉ የሚገኝበትን ሁኔታ ላይ ዳሰሳ አድርጓል፡፡

#ICRC

@tikvahethiopia
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመቐለ ፣ አክሱም ፣ ዓዲግራት እና ወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዚያዊነት ወደ ተቋሙ የተመደቡ የመደበኛ መጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 21 እስከ 24/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም በተገለጹት ቀናት የትምህርት ማስረጃችሁን (የምዝገባ ስሊፕ ፣ ግሬድ ሪፖርት እና የተማሪነት መታወቂያ) በመያዝ በተቋሙ በመገኘት ሪፖርት አድርጉ ብሏል።

የመጀመሪያ ዓመት ትምህርት ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ደግሞ ለ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች (አዲስ ገቢዎች) ጥሪ እስከሚደረግ መጠበቅ ይኖርባቸዋል ተብሏል።

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar #Abala #Tigray • " ወደታች ከባድ መሳሪያ እየጣሉ ነው። እንኳን የእርዳታ መኪኖች እና እዛ ያሉ የሚሸሹ ማህበረሰብ አባላት በትራንስፖርት እንዳይሸሹ አድርጓቸዋል ፤ ... የፌዴራል መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል " - አቶ አብዶ አሊ • " የኢትዮጵያ ጦር ከዚህ ቀደም በተወሰነው ውሳኔ ባለበት ፀንቶ ነው የሚገኘው። በአካባቢው ላይ ምንም አይነት የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ በሌለበት…
#Update

የአፋር ክልል ተፈናቃዮች ከ250 ሺህ በልጠዋል።

የአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አህመድ ካሎይታ ህወሓት በሁለት ዙር ባካሄደው ወረራ የኢትዮጵያ የወጪ እና ገቢ ንግድ የሚሳለጥበትን ሚሌን ለመያዛ እና ለመዝጋት አስቦ ነበር ያ ግን ሳይሳካ ቀርቷል አሁን ደግሞ በሶስተኛ ዙር ወራር በሰርዶ በኩል ያሰበውን ለማሳካት ተነስቷል ብለዋል።

አቶ አህመድ ፤ ክልሉ ከዚህ ቀደም ቡድኑ ባካሄደው ወረራ የተፈናቀለውን ህዝብ ለማቋቋም እየተሰራ ባለበት ሁኔታ ዳግም ለሶስተኛ ዙር ወረራ ተፈፅሞብናል ብለዋል።

አክለውም ፥ " አሻባሪው የህወሓት ቡድን 150 ኪሎ ሜትር ድረስ ወደ አፋር ክልል ዘልቆ በመግባት ከዚህ ቀደም በአፋር እና አማራ ክልል የፈፀመውን አይነት ጭካኔ እየፈፀመ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ህወሓት ወደአፋር ክልል 150 ኪሎ ሜትር ዘልቆ በመግባት ኤሬብቲ ወረዳ፣ መጋሌ እና አብአላን መቆጣጠሩ ተሰምቷል።

አዲስ በተከፈተው ጥቃት ከቀደሞው በተጨማሪ ለሶስተኛ ጊዜ ከ250 ሺህ በላይ ህዝብ ከገዛ ቄየው ተፈናቅሎ መጠለያ ካምፕ ውስጥ እንደሚገኝ የአፋር ክልል ሪፖርት አድርጓል።

ከዚህ ቀደም ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን እነሱን መልሶ በማደራጀት እና በማቋቋም ሂደት ውስጥ በተገባበት ሰዓት ነው ድጋሚ 250 ሺህ ሰዎች የተፈናቀሉት።

የአፋር ክልል ለደረሰው ጉዳት የሁሉንም እገዛ እና ትብብር እንደሚያስፈልገው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ : ዛሬ በእንጅባራ ከተማ የተከበረው 82ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓል ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ ነው የዋለው።

በዛሬው በዓል ላይ ከታዩት የፈረስ ትርዒቶች መካከል ጥቂቶቹ ከላይ ተያይዘዋል።

Photo Credit : APP & AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ThomasSankara በቶማስ ሳንካራ ግድያ ተባባሪ በመሆን አስራ አራት ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ከ34 ዓመታት በፊት ነበር የወቅቱ የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራ " የአፍሪካው ቼ ጉቬራ" አስደንጋጭ የሆነ ግድያ የተፈጸመባቸው። የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኙ ሳንካራ እአአ ጥቅምት 15/1987 በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት ነው በወታደሮቹ በጥይት ተገደሉት። እንሆ ከ34…
#ThomasSankar

የቶማስ ሳንካራ የፍርድ ሂደት ዛሬ ይቀጥላል።

የወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በተካሄደባት ቡርኪና ፋሶ ለሳምንት ተቋርጦ የነበረው የቶማስ ሳንካራ ግድያ የፍርድ ሂድት ዛሬ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊው ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ጄነራል ጊልበት ዲንዴሬ ነፃ መውጣቱን የሚገልጹ ወሬዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ ሀሰተኛ ናቸው ሲል ወድቅ በማድረግ አሁንም በማካ እስር ላይ እንደሆኑ አረጋግጧል።

#Update

የሳንካራ ግድያ ክስ በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ በሚገኘው ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኞ ይቀጥላል ተብሎ ነበር።

ፍርድ ቤቱ የፍርድ ሂደቱ መታገዱን አሳውቋል። " ህገ መንግስቱ ወደ ቦታው ከተመለሰ በኋላ የፍርድ ሂደቱ ይቀጥላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የሳንካራ ስም ዛሬም ድረስ ለምን ተደጋግሞ ይነሳል ?

ቶማስ ሳንካራ ምድር ላይ ለ37 ዓመታት ብቻ የተራመደ ነገር ግን በማእበል የማይጠፋ ዱካ አሳርፎ ያለፈ የዘመናችን አፍሪካዊ አብዮተኛ ነው።

በቅኝ ግዛት ወቅት "አፐር ቮልታ" ትባል የነበረችውን በርሀማ ደሀ ሀገሩን "ቡርኪና ፋሶ" ወደሚል ይፋዊ መጠሪያ የቀየረ፣ ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን ህዝቦቿን "ቡርኪናቤ" የተሰኘ የጋራ ማንነት እንዲጋሩ ያደረገ፣ ለዜጎቹ ህይወት የሚገደው ባለራዕይ መሪ ነበር።

ለምዕራባውያን ኃያላን ሀገራት ጫና ፍፁም ሳይንበረከክ በታደመባቸው ዓለምአቀፋዊና አፍሪካዊ ስብሰባዎች ላይ ሁሉ ዓለምን በማናለብኝነት ሲመዘብሩ ከነበሩ ሀገራት መሪዎች ጋር ጎሮሮ ለጎሮሮ ሲተናነቅ ያሳለፈ፣ ለጥቁር ህዝቦች እና በደል ላጎበጣቸው ምንዱባን ልሳን ሆኖ ያለፈ፣ ዓለም ከማይረሳቸው አብዮተኞች መካከል ጎልቶ የሚታወስ አፍሪካዊ እንቁ ነው።

"የራስን የተፈጥሮ ሀብት በራስ ጉልበት ማልማት" በሚለው የሀገሩን ህዝብ ባነቃነቀ ዘመቻ ያስመዘገባቸው አስደናቂ ድሎች አፍሪካ የራሷን ተፈጥሯዊ እድገት እንድታድግ ለማይፈልጉት ምእራባውያን ሀገራት እንደ ስጋት እንዲቆጠር አድርጎት ነበር።

ድሎት የማያሸንፈው ቆፍጣናው ወጣት ወደ ፕሬዝዳንትነት ከመጣ ጊዜ አንስቶ የቅንጦት ኑሮን ኖሮ አያውቅም። ከህዝብ ጋር የዩኒፎርሙን እጅጌ ከፍ አድርጎ ስሚንቶ የሚያቦካ፣ አካፋና ዶማ አንስቶ ጥቁር ላብ በግንባሩ እስኪንዠቀዠቅ ድረስ ሰርቶ የሚያሰራ፣ ድሆች ያለ ልኬት የሚሳሱለት መሪ ነበር።

አካሄዱ ባስፈራቸው ምዕራባውያን መሪዎች እና ስልጣን ባናወዛቸው የቅርብ ጓዶቹ በአጭር ቢቀጭም ተራማጅ ሀሳቦቹና ያስመዘገባቸው ተጨባጭ ለውጦች ዛሬም ድረስ ስሙ ተደጋግሞ እንዲነሳ አስችሎታል።

(ከሰለሞን ዳኜ - ቶማስ ሳንካራ ጥቁሩ አብዮተኛ)

@tikvahethiopia
#NewsAlert

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጡረታ እንደሚወጡ ማሳወቃቸውን ተከትሎ አሜሪካ በአዲስ አበባ ለሚገኘው ኤምባሲ አዲስ ሰው በተወካይነት በኃላፊነት ቦታ ላይ መድባለች።

አሜሪካ በአዲስ አበባ ላለው ኤምባሲዋ ትሬሲ አን ጃኮብሰንን ነው በጊዜያዊነት በኃላፊነት ቦታ ላይ ያስቀመጠችው።

አሜሪካዊቷ ዲፕሎማት ትሬሲ አን ጃኮብሰን በቱርክሜኒስታን፣ ታጂኪስታንና ኮሶቮ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፤ በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዓለም አቀፍ ድርጅት ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ፀሀፊ ሆነውም አገልግለዋል።

@tikvahethiopia
#Update

የ2ኛው ዘር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ነገ ይጀመራል።

በፀጥታ ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ፈተናቸውን መውሰድ ይጀምራሉ።

#AmharaRegionEB

• 37 ሺህ 55 ተማሪዎችን ለፈተና ይቀመጣሉ።

• ፈተናው በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደርና በደሴ ከተማ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ ይሰጣል።

• በዋግ ኽምራ ከአበርገሌ ወረዳ በስተቀር በሁሉም ወረዳዎች፣ በሰሜን ሸዋ ዞን 3 ወረዳዎች እና በሰሜን ጎንደር ዞን በአንድ ጣቢያ ፈተናው ይሰጣል።

• በኦሮሚያ ክልል ከምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተፈናቅለው ለመጡ 220 የክልሉ ተወላጅ ተማሪዎች በቡሬ ከተማ በተዘጋጀ የፈተና ጣቢያ ፈተናው ይሰጣል።

• ለብሔራዊ ፈተና ከሚቀመጡት ተማሪዎች መካከል 34 ሺህ 970 የሚሆኑት መደበኛ ተማሪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የግል ተፈታኞች ናቸው።

• ፈተናው በአጠቃላይ በ129 ጣቢያዎች ይሰጣል።

• ለፈተናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና የመፈተኛ ወረቀቶች ወደተዘጋጁ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተጓጉዘው አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ ነው።

#OromiaRegionEB

• በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አራት ዞኖች በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይካሄድ የቀረው የ2013 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል።

• በቄሌም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ17 ወረዳዎች 55 ትምህርት ቤቶች ከ21 ሺ በላይ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የተሰጠውን ፈተና በጸጥታ ምክንያት አልወሰዱም።

• ፈተና ተፈትነው ውጤት በመጠባበቅ ላይ ላሉና እስካሁን በትዕግሥት ፈተናውን ለመውሰድ የተጠባበቁ ተማሪዎች ምስጋና ቀርቧል።

• በሁለተኛው ዙር የተፈታኞች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ ውጤት ለመግለጽ ብዙ እንደማይቆይ ተገልጿል።

@tikvahethiopia