TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrAbiyAhmed #JoeBiden የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በተለይም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን…
#Update

የነጩ ቤተመንግስት (ዋይት ሀውስ) መግለጫ ፦

ዋይት ሀዋስ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ መወያየታቸውን አሳውቋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት እና ሰላምና ዕርቅን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ላይ መክረዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደን በቅርቡ ስለተፈቱት በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምስጋና አቅርበዋል።

ሁለቱ መሪዎች በድርድር የተኩስ አቁም ስምምነትን ማፋጠን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፣በመላው ኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትን በአስቸኳይ ስለማሻሻል ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስር ስለታሰሩ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ሁሉም የተጎዱ ኢትዮጵያውያን የሰብአዊ መብት ጥያቄዎችን መፍታት በሚያስፈልግበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ጆ ባይደን በቅርቡ የተፈጸሙትን የአየር ድብደባዎች ጨምሮ እየቀጠለ ያለው ግጭት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳትና ስቃይ እያስከተለ እንደሚገኝና ይህም እንደሚያሳስባቸው ገልጸው አሜሪካ ከአፍሪካ ህብረት እና ከአካባቢው አጋሮች ጋር በመሆን ኢትዮጵያውያን ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ሁለቱም መሪዎች የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት አስፈላጊነት፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያለውን ትብብር ለማጠናከርና ግጭቱን ለመፍታት ተጨባጭ መሻሻሎች እንደሚያስፈልግ አስምረውበታል።

@tikvahethiopia
#Update

ከወራት በፊት በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተልከው ወደ አዲስ አበባ መጥተው የነበሩት ዴሞክራቱ ክሪስ ኩንስ የእስረኞችን መፈታት በደስታ እንደሚቀበሉ ገልፀዋል።

ኩንስ ፥ " የኢትዮጵያ መንግስት በርካታ ታዋቂ የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት እና የፖለቲካ እርቅ ሂደት ለመጀመር የወሰደውን እርምጃ በደስታ እቀበላለሁ " ነው ያሉት።

ኢትዮጵያን ወደፊት ለማራመድ ከTPLF ጋር የሚደረግ የሰላም ውይይትን ጨምሮ እውነተኛ ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ ውይይት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ክሪስ ኩንስ ፤ ያልተቋረጠው የአየር ላይ ድብደባ (የሰሞኑን 56 ሰዎች የገደለውን በተፈናቃዮች ካምፕ ላይ የደረሰውን ጨምሮ) የተሳሳተ ምልክት ይሰጣሉ ፤ ልክ እንደሌሎች እርምጃዎች ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶችን ወደ ትግራይ እንዳይደርሱ ነው የሚከለክሉት ብለዋል።

ኩንስ ፥ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሰላም የተደረጉት እርምጃዎችን ሲገነቡ ለማየት ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

@tikvahethiopia
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማብራሪያ፦

በቅርቡ በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ክሳቸው የተቋረጠ ተጠርጣሪዎች ዐቃቢ ሕግ በተለያዩ ምክንያቶች ክሱን መቀጠል እንደማይፈልግ በማስታወቁ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ገለፀ።

ታህሳስ 28/2014 ዓ.ም በሙሉ ወይንም በከፊል በተከሳሾች ላይ በ3 መዝገቦች የቀረቡ ክሶችን እንዲቋረጡ የፍትህ ሚኒስትሩ ለሚመለከተው ችሎት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ሕጋዊ ስርዓቱን ተከትለው መስተናገዳቸውን ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በመሆኑም የክስ ሂደታቸው እንዲቋረጥ ከቀረቡት በከሳሽ ዐቃቤ ሕግና በተከሳሾች እነ ጀዋር ሲራጅ መሀመድ (በድምሩ 20 ተከሳሾች)፣ በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች እነእስክንድር ነጋ (በድምሩ 7 ተከሳሾች) እንዲሁም በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች እነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (በድምሩ ስድስት ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ) የሚመለከቱ እንደሚገኝበት ፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሕገ-መንግስት እና ሽብር ጉዳዮች አንደኛ ወንጀል ችሎት የፍትህ ሚኒስትሩን ማመልከቻ በመመርመር በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(3)ሠ መሰረት ክሱን ያነሱ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ተከሳሾቹ እንዲለቀቁ “ተከሳሾች በሌላ ወንጀል የማይፈለጉ ከሆነ” ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ለማረሚያ ቤት አስተላልፎ ተፈጻሚ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

አሁን በስራ ላይ ባለው ሕግ መሰረት ከሳሽ ዐቃቢ ሕግ በተለያዩ ምክንያቶች ክሱን መቀጠል እንደማይፈልግ ሲያመለክት ፍ/ቤቱ የክስ ይቋረጥ ጥያቄውን በመቀበል በእስር ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎች እንዲለቀቁ የታዘዘ መሆኑ ሕጋዊ አሰራር መሆኑ ግንዛቤ እንዲፈጠር በሚል መግለጫውን እዳወጣ አስታውቋል፡፡

* ሙሉ ማብራሪያው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
' ሁሉም በሀገር ያምራል '
' ሁሉም የሀገር ያምራል '

ዳያስፖራዎች እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት የተደረገላቸውን ጥሪ ተከትሎ የተዘጋጀው 'Made in Ethiopia Great Homecoming' ባዛር ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ " ወዳጅነት አደባባይ " ተከፍቷል።

ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

በባዛሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችና የቱሪስት አገልግሎት ሰጭዎች ምርትና አገልግሎታቸውን በማስተዋወቅ ግብይት የሚፈጽሙበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

#MADE_IN_ETHIOPIA

@tikvahethiopia
#OFC

ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ከፍተኛ አመራሮች አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጃዋር መሀመድ ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ ፣ አቶ ሀምዛ ቦረና እና ሎሎችም በአቶ ጃዋር መዝገብ ስር ያሉ ግለሰቦች ከእስር መፈታታቸው ይታወሳል።

ከእስር ስለተፈቱ ግለሰቦች ኦፌኮ አሰተያየቱን ለቪኦኤ ሰጥቷል።

ኦፌኮ የፓርቲው አመራሮች እና አባላት መፈታታቸው ደስ እንዳሰኘው የፓርቲው የፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ተናግረዋል።

አቶ ጥሩነህ ፥ " በጣም ደስ ብሎናል ደስታችን ወደር የለውም፤ እነዚህ አባሎቻችን በመፈታታቸው አመራሮች ናቸው ያው ኦፌኮ አመራር የተሟላ ይሆናል ብለን ስለምናስብ እነሱም ከቤተሰቦቻቸው ፣ ከወዳጆቻቸው ፣ ከዘመዶቻቸው ጋር መቀላቀላቸው በጣም ደስ አሰኝቶናል። በዚህም የተነሳ አባሎቻችን ፣ ደጋፊዎቻችን ፣ መላው ህብረተሰባችን ፣ በሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጭ የሚገኙ በዚህ መጥፎ ጊዜ ከጎናችን በመቆማቸው አመስግነናቸዋል " ብለዋል።

አክለውም ፥ " ያሰራቸው መንግስትም ስለፈታቸው ፣ የተፈቱበት ምክንያት የፈለገው ነገር ይሁን እነዚህ ወገኖቻችን በመፈታታቸው ግን መንግስትንም አመስግነናል ደስ ብሎናል " ሲሉ ተናግረዋል።

መንግስት አሁን እየተዘጋጀበት ያለውን የብሄራዊ ውይይት ኦፌኮ በ2009 ዓ/ም ነው መጠየቅ የጀመረው ያለቱ አቶ ጥሩነህ የፓርቲው አመራሮች እና አባላት መፈታት ለውይይቱ ትልቅ አስተዋጾ ይኖረዋል ብለዋል።

መንግስት አሁን ጀመረውን ታሳሪዎችን የመፍታት እርምጃ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ያለቱ አቶ ጥሩነህ ፥ የኦፌኮ አባላት፣ የዞንና የወረዳ ኃላፊዎች ዛሬም ቢሆን እስር ላይ ናቸው እነዚህ ሁሉ ቢፈቱና የሀገሪቱን፣ ሰላም ፣ እድገት፣ ልማት አብረን እጅ ለእጅ ብንገነባ የተሻለ ይሆናል ይሄ ጥሪያችን አሁንም ይቀጥላል " ብልዋል ለሬድዮ ጣቢያው።

@tikvahethiopia
#Update

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ክሳቸው ስለተቋረጠላቸው የህወሓት አመራሮች ምን አሉ ?

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት የሆኑት ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫ ወቅት ክሳቸው ስለተቋረጠ የህወሓት አመራሮችም አንስተው ተናግረዋል።

ዶ/ር ይልቃል ፥ አመራሮቹ የአማራን ህዝብ ጠላት አድርገው በመሳል ባለፉት በርካታ አመታት በህይወት፣ በንብረትና በስነ ልቦናው ላይ በደል እንዲደርስበት በማድረጋቸው ህዝቡ በአመራሮቹ መፈታት ላይ ቅሬታ ቢይዝ እውነት አለው ብለዋል።

የአማራ ህዝብ በተከታታይ ሲደርስበት የነበረው በደል በእነዚህ ሰዎች ጠንሳሽነት እንደነበር ለአፍታም አንዘነጋም ሲሉም ገልፀዋል።

ነገር ግን አሁን ማየት ያለብን እና ጠቃሚ የሚሆነው የሰዎቹ መፈታት አለመፈታትን ሳይሆን ሊከፋፍሉንና ሊያዳክሙን የሚችሉ ሀሳቦችን ወደ ጎን በማቆየት በዋና ዓላማችንና መርሃችን ላይ አተኩረን አንድነታችንን መጠበቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ይልቃል ፥ " የእነስብሃት ነጋ መፈታት አለመፈታት ላይ አተኩረን ከተለያየን እንዳከማለን፤ ለሌላ ጥቃት እንጋለጣለን " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" ለእኛ እንደ አማራ ክልል የሚጠቅመው መርሃችን ላይ ትኩረት በማድረግ አንድነትን በማጠናከር ሊመጣ ከሚችል ዳግም ወረራ ራሳችንን መጠበቅ " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#DStv

የMyDStv Telegram Bot በመጠቀም የዲኤስቲቪ አካውንትዎን በማንኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ ይቆጣጠሩ።

1. መክፈል ያለብዎትን ሂሳብ ይወቁ
2. ሂሳብዎን ይክፈሉ
3. የቴክኒክ ችግሮችን በቀላሉ ያስተካክሉ
4. ጥቅልዎን ያሻሽሉ (ፓኬጅዎትን አፕ ግሬድ ያድርጉ)
5. የግል መረጃዎትን ይቆጣጠሩ
6. BoxOffice ፊልሞችን ይከራዩ (ለ Explora ዲኮደር ብቻ)
የ MyDStv Telegram Bot ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጫኑ👇
https://bit.ly/3t88uZg

#DStvSelfServiceET #DStvየራሳችን
#Update

በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ ማንሳቱን ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ መነሳቱን ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ባንክ ካለፈው ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የባንኮች ደንበኞች በሳምንት ከአምስት በላይ የባንክ ዝውውሮችን እንዳያደርጉ የሚያዝ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህም መመሪያ መደበኛ ባልሆነው የልውውጥ ገበያ ውስጥ ያሉ ተጫዋቾችን ተስፋ ለማስቆረጥ ያወጣው ደንብ መሆኑን አስታውቆ ነበር።

ይሁን እንጂ ካሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 27 ቀን 2014 ጀምሮ ይህ መመሪያ መነሳቱን በብሔራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው፣ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

“ የዝውውር ገደቡ አሁን ሙሉ በሙሉ በመመርያ ተነስቷል ” ያሉት ፍሬዘር፣ ነገር ግን ባሳለፍነው ዓመት የወጣው የገንዘብ ወጪ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ገደቦችም አሁንም ድረስ ተፈፃሚ ሆነው ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ / አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

@tikvahethiopia
አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ምን አሉ ?

• የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ "በተሳሳተ መንገድ ለእስር ተዳርገው" ላለፉት 18 ወራት በእስር መቆየታቸውን ገልፀዋል።

• እስራቸው " ፖለቲካዊ " እንደነበር ገልፀዋል። ለእስር የተዳረግነው ገዢው ፓርቲ በምርጫ የተሻለ ድምጽ እንዲያገኝ ከፖለቲካዊው ምኅዳር ገለል እንድንል ታስቦ ነው ብለዋል።

• በኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች በሲቪሎች ላይ የደረሰው ጉዳት አሳዛኝ ነው ብለዋል።

• ባለፉት 13 ወራት በአገሪቱ እና በሕዝቦቿ ላይ የደረሱትን ጉዳቶችን መቀልበስ ባይቻልም፤ ተጨማሪ ጉዳቶችን ማስቀረት የምንችልበት ጠባብ ዕድል አለ ብለዋል።

• በቅርቡ መንግሥት ሰላም እና መግባባትን ለመፍጠር ያሳየው አዎንታዊ ምላሽ ተጨባጭ እና በማይቀለበሱ ተግባራት መረጋገጥ አለባቸው ብለዋል።

• በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘው የእርስ በእስር ጦርነት በሰላም እንዲጠነናቀቅ እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋገት እንዲሰፍን የውጭ አካላት አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ጠይቀዋል።

• የውጭ አካላት ለተዋጊ አካላት ፖለቲካዊ እና ቁሳዊ ድጋፎችን በማቅረብ ግጭቱን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

• የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን በተመለከተ ተዓማኒነት ያለው ምርመራ እንዲደረግ፤ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

• ከጠበቆቻችን መካከል ለአቶ አብዱልጀባር ሁሴን ልዩ ክብር ለመስጠት እንወዳለን ብለዋል።

• በግንኙነታችን ወቅት ልዩ አክብሮትን ላሳዩልን የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥበቃዎች እና አስተዳዳሪዎች አድናቆታችንን እንገልፃለን ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/OFC-01-11

@tikvahethiopia
#MeskelSquare

መስቀል አደባባይን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያየ።

ሰሞኑን በመስቀል አደባባይ የተደረገውን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መንፈሳዊና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ የተነሱ የመብትና የይዞታ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም አንቲባ አዳነች አቤቤ አስተላለፉት የተባለውን መልዕክት ተከትሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 3 ረፋድ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጉባኤ አካሒዷል።

በጉባኤውም ላይ ከፍ ሲል የተገለጸውን ርዕስ መሰረት በማድረግ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ክብርት ከንቲባዋ አርብ ጥር 6 ጠዋት አራት ሰዓት በቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚካሔደው ጉባዔ ላይ እንዲገኙና ማብራሪያ እንዲሰጡ ቀጠሮ አንዲያዝ አና ጉዳዩ በተረጋጋ መንገድ ውሳኔ እንዲያገኝ መመሪያ ሰጥቷል።

#EOCT

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ ለሚገነቡ 10 ሺህ ተገጣጣሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በምዕራፍ 1 ፕሮጀክት የሚገነቡ የ5 ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳናች አቤቤ አስጀምረዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በአንድ አመት ዉስጥ ተገንብተዉ ለነዋሪዎች የሚተላለፉ መሆኑ ተገልጿል።

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከአሁን በፊት በከተማዋ ሲገነቡ የነበሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የግንባታ ጥራት ችግርና የሃብት ብክነትን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩን ለ54 ቢሊዮን ብር ዕዳ መዳረጉን ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ እነዚህንና መሰል ችግሮችን ከመቅረፍ ጎን ለጎን የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እየሰራ ነዉ ብለዋል።

ተገጣጣሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በተቀመጠላቸዉ ጊዜ ዉስጥ ተጠናቀዉ ለአገልግሎት እንዲበቁ አስፈላጊዉን ድጋፍና ክትትል እናደርጋለን ብለዋል።

በከንቲባዋ የተመራ ቡድንም የተገጣጣሚ ቤቶቹን ግብአት ማምረቻ ፋብሪካና እየተመረቱ ያሉትን ልዩ ልዩ ግብአቶች ተዘዋውሮ ጎብኝተዋል።

የሚገነቡት ቤቶች ባለ 4 እና ባለ 10 ወለል ሕንጻዎች ሲሆኑ ቤቶቹን የሚገነባዉ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ነዉ።

#ኦቢኤን

@tikvahethiopia