TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርታቸውን የሚያከፋፍሉላቸው ወኪል የንግድ ድርጅቶችን ስምና አድራሻ #በአስቸኳይ ለመንግስት እንዲያሳውቁ ትዕዛዝ ተላለፈ።

ትዕዛዙን ያስተላለፈው የማዕድን ሚኒስቴር እንደሆነና ሚኒስቴሩ ይህን ትዕዛዝ ሊያስተላልፍ የቻለው ከንግድ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትና ኮሚሽን ጋር በመሆን ከሲሚንቶ ምርትና የግብይትና ሥርጭት ሥርዓት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ለጀመረው የጋራ ጥረት መረጃ ለማግኘት እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

በማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተፈርሞ በአገሪቱ ለሚገኙ ሁሉም ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የተላከው ደብዳቤ ፥ " የፋብሪካችሁን የሲሚንቶ ምርት በወኪልነት የሚያከፋፍሉ ኩባንያዎች ስም ዝርዝርና የሚገኙበትን አድራሻ በመግለጽ በአስቸኳይ እንድትልኩልን " ሲል ያመለክታል፡፡

በሲሚንቶ ምርት ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን የሚፈታ አዲስ መመርያ እስኪዘጋጅ ድረስም ለአዲስ የምርት አከፋፋይ ወኪሎች ፋብሪካዎች ፈቃድ እንዳይሰጡ ደብዳቤው እንደሚያሳስብ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
" ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም " - ጄነራል ብርሃኑ ጁላ

የሱዳን ጦር በድንበር አካባቢ በርካታ ወታደሮቼ የኢትዮጵያ ወታደሮች በፈጸሙት ጥቃት ተገደሉብኝ ሲል ክስ አሰምቷል።

የሱዳን ጦር ትላንት ባወጣው መግለጫ ፤ “በአል-ፋሻቃ የሚገኘውን የመኸር ምርትን ለመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሃይሎቻችን… በኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች እና ሚሊሻዎች በቡድን ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፣ ገበሬዎችን ለማስፈራራት እና የመኸር ወቅትን ለማበላሸት ፈልገው ነበር” ሲልም ነው ክስ ያሰማው።

የሱዳን ጦር በመግለጫው ላይ ምን ያህል ወታደሮቹ እንደተገደሉበት ባይገልፅም ሮይተርስ የዜና ወኪል የወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበ በጥቃቱ ቢያንስ 6 ወታደሮች ተገድለዋል።

ይህንን መረጃ ከትላንት ጀምሮ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ሲሆን ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ላይ የቀረቡት የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም ብለዋል።

ጄነራል ብርሃኑ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያላቸው ትስስር ጥብቅ መሆኑን በመግለፅ ጎረቤት ሀገሯን ሱዳንን የምታጠቃበት ምንም ምክንያት የለም ሲሉ ገልፀዋል።

ጄነራል ብርሃኑ ጁላ "የድንበር ጭቅጭቅ አለ ይሄ የድንበር ጭቅጭቅ በሰላማዊ መንገድ ነው መፈታት ያለበት የሚል ፅኑ አቋም አላት ኢትዮጵያ ፤ ኢትዮጵያ አሁን ከጁንታው ጋር ጦርነት ላይ እያለች በጣም ብዙ ትርፍ ኃይል ኖሯት ሱዳንን የምታጠቃበት አይነት ቁመና ላይ አይደለችም ያለችው " ሲሉ ተናግረዋል።

መሬትን በተመለከተ በሰላምና በድርድር በህግ ይመለሳል ብለዋል።

ጄነራል ብርሃኑ ፥ " ብዙ ጊዜ የመሬት ጭቅጭቅ መጨረሻ ፍርድ ቤት ነው የሚሄደው ይሄን ስለምናውቅ እኛ ሱዳንን የመተናኮል ፍላጎት የለንም ነገር ግን ሱዳን የመተናኮል ምልክቶች እያሳየች ነው፤ ጁንታውን በብዛት አስገብታለች እንደገና የታላቁ የህዳሴ ግድብን ለማደናቀፍ እየሰራች ነው እናውቃለን፤ እነሱ የላኳቸው ኃይሎች እየመጡ እየደመሰስናቸው ነው።

የራሳችንን ተላላኪ መደምሰስ እንጂ ለምን ትልካላችሁ ብለን ከሱዳን ጋር ወደአታካራ መግባት አንፈልግም ፤ ከሱዳን ጋር ግጭትም ጦርነትም አንፈልግም፤ ከሱዳን ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሻሻል ነው የምንፈልገው በጣም ይሻሻላል ብለንም እናስባለን።

እንዳንድ የሱዳንን ህዝብ እና መንግስት የማይወክሉ ግን በሌላ ሶስተኛ ወገን የተገዙ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ግንኙነት ለማበላሸት የሚሰሩ አሉ ፤ እነማን እንደሆኑም ለይተን እናውቃቸዋለን፤ ታሪክ ይፈርዳል፤ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህዝብ ችግሩን በህዳሴ ግድብም ይሁን በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ይፈታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን " ሲሉ ለቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Niger

ትላንትና ቅዳሜ በምዕራብ ኒጀር ከቡርኪነፋሶ በኩል በአጀብ የገቡ የፈረንሳይ ወታደሮች ከተቃዋሚዎች ጋር በፈጠሩት ግጭት ቢያንስ 2 ሰዎች ሲገደሉ 18 መቁሰላቸውን የኒጀር መንግስት አስታውቋል።

የፈረንሳይ ጦር ሰራዊት ደግሞ ፥ ወታደራዊ አጀቡ በገጠመው ተቃውሞ የተነሳ ከቡርኪናፋሶ ለአንድ ሳምንት ያህል መውጣት አቅቶት እንደነበርና በዛው መቆየቱን ገልጿል።

የፈረንሳይ ወታደሮች አሸባሪዎች የሚወስዱትን ጥቃት ማስቆም አልቻሉም በሚል ነው በቡርኪናፋሶ ተቃውሞ የገጠማቸው።

አሸባሪዎች ቡርኪናፋሶን እና በአካባቢው ያሉ አገራትን እንዲያጠቁ የፈረንሳይ ጦር ድጋፍ እያደረገ ነው በሚልም ነው ጦሩ ተቃውሞ የገጠመው።

ምንም እንኳን ከአንድ ሳምንት እገታ በኃላ ኒጀር የገባው የፈረንሳይ ጦር በኒጀርም ኃይለኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።

እየተፈጸሙ ያሉ የሽብር ጥቃቶች በመጨመራቸው ምክንያት የአካባቢው አገራት ዜጎች ፈረንሳይ ጦሯን እንድታስወጣ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

ፈረንሳይ ወደ ቀድሞ የቅኝ ግዛቶቿ ወታደር ማዝመቷ ቡርኪናፋሶ፣ ኒጀር እና ሌሎችም የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#StateofEmergencySomalia ሶማሊያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች። ሀገሪቱ በከፍተኛ ድርቅ መጠቃቷን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀችው። እየተባባሰ በመጣው ወቅታዊ የድርቅ ሁኔታ ላይ የሃገሪቱን ካቢኔ ለአስቸኳይ ስብሰባ የጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ሮብል አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አውጀዋል፡፡ “ሃገራችን በድንገተኛ ሰብዓዊ አደጋ ላይ ትገኛለች” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያጋጠመውን አስከፊ…
#Somalia

ጎረቤታችን ሶማሊያ በድርቅ ክፉኛ እየተጎዳች ነው።

በደቡብ ሶማሊያ ውስጥ በድርቅ ከተመቱ አካባቢዎች አንዱ በሆነው በጌዶ ክልል ፣ ሉቅ ወረዳ የ5 ልጆች እናት በረሃብ መሞቷ ተነግሯል (ፎቶ ከላይ ተያይዟል) ።

ከአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ እንደተሰማው በረሃብ ህይወቷ ያለፈው እናት የሳምንት እድሜ ያቃስቆጠረ ልጇን ጡት ስታጠባ ነበር።

እንደ ጋሮዌ መረጃ ከብቶቻቸውን በድርቅ በማጣታቸው ምክንያት ነው ህይወቷ ያለፈው እናት ከምትኖርበት አካባቢ ተሰዳ ወደ ሉቅ የገባችው።

ሶማሊያ በከፍተኛ ድርቅ መጠቃቷን ተከትሎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ትገኛለች። በሀገሪቱ 2. 3 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች ለከፋ ድርቅ ተጋልጠዋል፡፡

@tikvahethiopia
#Somalia

በከፍተኛ ድርቅ ምክንያት በሰዎች እና በከብቶች ላይ ጉዳት እየደረሰ በሚገኝባት በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ አንዳንድ የደቡብ እና መካከለኛ ክልሎች ዴየር ዝናብ እንደጣለ ተሰምቷል።

ሶማሊያ ውስጥ ባለፉት ሶስት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ያልዘነበ ሲሆን በተለይ ጁባና ሸበሌ ወንዞች የውሃ መጠናቸው በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ በሀገሪቱ ያለውን ድርቅ እንዳባባሰው የUN መረጃ ይጠቁማል።

ፎቶ ፦ SNTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም " - ጄነራል ብርሃኑ ጁላ የሱዳን ጦር በድንበር አካባቢ በርካታ ወታደሮቼ የኢትዮጵያ ወታደሮች በፈጸሙት ጥቃት ተገደሉብኝ ሲል ክስ አሰምቷል። የሱዳን ጦር ትላንት ባወጣው መግለጫ ፤ “በአል-ፋሻቃ የሚገኘውን የመኸር ምርትን ለመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሃይሎቻችን… በኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች እና ሚሊሻዎች በቡድን ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፣ ገበሬዎችን ለማስፈራራት እና የመኸር…
" የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትኛውም ሉአላዊ ሀገር ላይ ጥቃት የመፈፀም አጀንዳ የለውም " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት በሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘረ እየተባለ የሚነዛው ወሬ #ሀሰተኛ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ ይህን ያሳወቁት ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው።

ዶ/ር ለገሰ ፥ " አሸባሪው ኃይል በተለያየ መልኩ ሱዳን ውስጥ የሚያሰለጥናቸውን ሰርጎ ገቦች በተለያየ ቦታ በተለይም በመተማ አካባቢዎች በተለያየ ጊዜያት ያስገባል ፤ በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያን የሚተናኮሉ ሰርጎ ገቦች ይገባሉ፤ በዚህ መሰረት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰርጎ ገቦች ፣ ሽፍታዎች እና አሸባሪዎች በዛ መስመር ገብተው ነበር በዛ መስመር የገባውን ኃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የአካባቢው ሚሊሻ መቷቸዋል ፤ ደምስሷቸዋል " ብለዋል።

የተለያዩ ሚዲያዎች እንደሚነዙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ፈፅሟል የሚለው መሰረተቢስ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትኛውም ሉአላዊ ሀገር ላይ ጥቃት የመፈፀም አጀንዳ የለውም ያሉት ዶ/ር ለገሰ ፥ " ቢኖረው ኖሮ የሱዳን ኃይሎች ወረው በግድ የያዙት መሬት አለ ፤ ይሄንንም በሰላማዊ ሁኔታ በውይይት እና በድርድር እንፈተለን ብሎ የተቀመጠ ነው የኢትዮጵያ መንግስት ፤ አዲስ የመጣ የተከሰተ ነገር የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

ነገር ግን የህወሓትን ተልዕኮ ለማስፈፀም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ሽፍታዎችን ደምስሰናቸዋል ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
የተቀጣጠለው የ #NoMore ንቅናቄ ፦

አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች የምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና በሀገራቱ ሚዲያዎች የሚሰራውን የኢትዮጵያን ህዝብ የማሸበር የሀሰተኛ መረጃ ዝውውር በመቃወም በተለያዩ ሀገራት #NoMore በሚል በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኤርትራ ዜጎች የተቀውሞ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

ትላንት እሁድ እንዲሁም ቅዳሜ በአይርላንድ (ደብሊን ፣ ኮርክ፣ ጋልዌይ) ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ኖርዌይ፣ ጣልያን የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል።

በተጨማሪ በአሜሪካ ነጩ ቤተ መንግስት መቀመጫ ዋሽንግቶን ዲሲ ትላንት የተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ የውሥጥ ጉዳዮች እጇን እንድትሰበስብና በሀገሪቱ ያሉት ሚዲያዎች በሀሰተኛ መረጃ ህዝብን ከማሸበር እንዲታቀቡ ተጠይቋል።

#NoMore ዘመቻ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያው ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች እየተሳተፉበት ሲሆን ከነዚህ መካከል በጉልህ የሚጠቀሱት የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው።

የቻይና መንግሥት ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ዌንቢን ፣ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁዋን ቹኒንግ፣ በሊባኖስ የቻይና ኤምባሲ ኮንሱላር ካኦ ይ የ #NoMore በቃ ንቅናቄ ድጋፋቸውን በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ያንፀባሩቁ ናቸው።

ባለስልጣናቱ፥ " O ዴሞክራሲ፤ በስምሽ ስንት ወንጀሎች ተፈጸመ "ብለዋል።

ባለስልጣናቱ ከመልእክታቸው ጋር ያያዙት ምስል " ለUS ኢምፔሪያሊዝም ቀጣዩ ማን ነው?" የሚል ሲሆን አፍጋኒስታን፤ ኢራቅ፤ ሊቢያ እና የመን ወድመዋል፤ ማነው ተረኛው? "ሲልም ያጠይቃል።

ከፖለቲካ ሰዎች በተጨማሪም ሴኔጋላዊ-አሜሪካዊው ዓለም አቀፍ ድምፃዊ ኤኮን #NoMore ንቅናቄን ተቀላቅሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthOmoZone በድርቅ ምክንያት ከብቶች እየሞቱ ነው። በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ላይ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 98 ሺህ ሄ/ር ለግጦሽ ሲውል የነበረው መሬት ሙሉ በሙሉ በጎርፍ በመያዙ በተከሰተ ድርቅ የአርብቶ አደሩ የኢኮኖሚ ምንጭ የሆኑ ከብቶቻቸው በግጦሽ ሳር እጦት እየሞቱ ነው። በዛሬው እለት የዞኑ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ምህረት አስራቱ የተመራ ቋሚ ኮሚቴ የመስክ…
#Dasenech

የኮንሶ ዞን ለዳሰነች ወረዳ ህዝብ 23 አይሱዙ መኪና የእንሰሳት መኖ ድጋፍ አድርጓል።

የዳሰነች ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎች ከኮንሶ ዞን ለተደረገላቸው የእንሰሳት መኖ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ዋና አስተዳደር በዝናብ እጥረት አማካኝነት እንሰሳት መሞታቸው አሳውቆ ከኮንሶ ዞን ለተደርገው ድጋፍ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርቧል።

የኮንሶ ዞን አስተዳደር አሁን ላይ ያደረገው 23 አይሱዙ መኪና የመኖ ሳር ድጋፍ ሲሆን ቀጣይነት እንደሚኖረው አሳውቋል።

በግጦሽ እጦት ምክንያት በርካታ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ከ45ሺህ በላይ ቤተሰብና ከ300 ሺህ በላይ የቀንድ ከብቶች ተፈናቅለው ከ207 ሺህ 700 በላይ ከፍተኛ አደጋ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

መረጃው ከኮንሶ ዞን መንግስት ኮ/ጉ መምሪያ ያገኘነው ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መግለጫ ፦ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ዛሬ ማምሻውን ተሰብስቦ፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተመለከቱ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ገምግሟል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተያዘለት ዓላማ አኳያ አፈጻጸሙ በመልካም ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን አረጋግጧል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተጀመሩ ሥራዎችን ለማጠናከርና ዕንቅፋት የሚሆኑትን ችግሮች ለማስወገድ የሚከተሉትን 4 ትእዛዞች አስተላልፏል። #1…
" ሀገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የሀገርን ህግ ከማክበር ነው " - ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ያወጣውን ክልከላ የሚተላለፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ መንግስት አሳሰበ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከቀናት በፊት ፦

" ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እና ውጤቶችን በተመለከተ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ፣ በየትኛውም የመገናኛ አውታር መስጠትና ማሰራጨት ክልክል ነው።

በየግንባሩ የሚገኙ የሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ከተሰጣቸው ሥምሪትና ተልእኮ ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እንዲሁም ውጤቶችን የሚመለከቱ መግለጫዎች መስጠት የተከለከለ ነው።

የጸጥታ አካላትም ይሄን ተላልለፈው በሚገኙት ላይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል። " የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የተላለፈውን ክልከላ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በመተላለፍ ላይ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት ያሳስባል ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ፥ ሀገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የሀገርን ህግ ከማክበር በመሆኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ያወጣውን ክልከላ የሚተላለፉ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia