TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኤጀንሲው የሰነድ ማረጋገጫ ማህተም አሰራርን ቀየረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ እየተበራከተ የመጣውን ሰነድ አስመስሎ የመስራት ወንጀል ለመቀነስ ኤጀንሲው በሚሰጣቸው የልደት፣ የጋብቻ ፣ የፍቺ ፣ የያላገባ እንዲሁም ሌሎች ማስረጃዎች አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረውን የማረጋገጫ አሰራር በዘመናዊ አሰራር በመተካት ፎርጀሪ እያደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳት ለመቀነስ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ተቋሙ በዋና መስሪያ ቤት የሚሰጠውን ለፖስፖርት አገልግሎት፣ ለውጭ ሃገራት የቪሳ ጥያቄ ፣ ለተለያዩ የውጭ እና የሃገር ውስጥ ጉዳዮች የሚውሉ ማስረጃዎች የሚረጋገጥበትን የቀድሞ የማህተም አሰራር በማስቀረት በውጭ ሃገር አሰርቶ ባስገባው ዘመናዊ የሆሎግራም ማረጋገጫ አሰራር ከዛሬ ህዳር 13 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመተካት ተግባራዊ ያደርጋል።

ይህ አሰራር ከፖስፖርት እና ከውጭ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በየቦታው ተመሳስሎ በመስራት ለማለፍ የሚሞከሩ ሌብነቶች ኤጀንሲውን እንዳያልፉ እገዛ የሚያደርግ እንደሚሆን ታምኖበታል።

በተያዘው በጀት ተቋሙ የሚሰጣቸውን ሰርተፍኬቶች የደህንነት ደረጃ ከፍ ለማድረግ አዲስ የPersonalization ቴክኖሎጂ ባላቸው ፕሪንተሮች ለመተካት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ምንጭ፦ ወ/ኩ/ም/መ/ኤጀንሲ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ዴንማርክ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ርዳታ ተጨማሪ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች።

አዲሱ አስተዋፅኦ የኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ፈንድ በኢትዮጵያ በጣም ለተቸገሩ ሰዎች ህይወት አድን ሰብአዊ ርዳታ ለመስጠት የሚረዳ ነው።

በሌላ በኩል የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገውን የ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚቀጥል ዛሬ ገልጿል።

USAID በአፋር፣ በአማራ፣ በትግራይ ክልሎችና በሌሎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች የህይወት አድን ሰብአዊ ድጋፉን እንደሚቀጥል አሳውቋል።

አሜሪካ በጤናና በትምህርት በኢትዮጵያ የምታደርገው ኢንቨስትመንት እንደሚቀጥል አሳውቃለች።

ከኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ጋር እየተሰጠ ላለው ምላሽ የምናደርገው ድጋፍና የኮቪድ ክትባት ልገሳውም ይቀጥላል ብላለች። ከግጭቱ በኋላ ሀገሪቷ እንድታገግም የያዝነው ዕቅድ ሁሉ አይቆምም ፣ ይቀጥላል ስትልም ገልጻለች።

የአሜሪካ ኤምባሲ ክፍት ነው ፣ የአሜሪካ ህዝብም የኢትየጵያን ህዝብ በሚያስፈልገው ሁሉ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቃለች።

ምንጭ፦ Embassy of Denmark in Ethiopia & US EMBASSY AA

@tikvahethiopia
#NO_MORE

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን #NO_MORE የሚለውን አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ እንቅስቃሴን በዛሬው እለት ተቀላቅለዋል ::

የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ በሚገኘው) የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለውን ጫና ለመቃወም እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ገልፀዋል ::

የዛሬው ሰልፍ የተጠራው በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሲሆን የሰልፉ አላማም #NOMORE በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ በተመሳሳይ ቀን የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ አንዱ አካል ነው በማለት የሰልፉ አስተባባሪዎች አስታውቀዋል ::

እዚህ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ ከጠዋቱ ጀምሮ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ግዛቶች በተዘጋጁ ትራንስፖርቶች ወደ ጆሃንስበርግ ያቀኑ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን እና አንዳንድ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት በርካታ ዜጎች በሰልፉ ላይ ተሳትፈዋል ::

በሰልፉ ላይ የተኙት በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በአሜሪካ መንግስት እና በምዕራቡ አለም ሚዲያዎች ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ አሰምተዋል ::

በተጨማሪ :-

November 29 ደግሞ በተባበሩት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር አስተባባሪነት የተጠራ የተቃውሞ ሰልፍ በድጋሚ በደቡብ አፍሪካ እንደሚኖር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ::

ፎቶ ፦ የኛ ሰው ሚዲያ እና ከማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የተሰባሰበ

FAYA (Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
#BREAKING

" ከፓርቲው ፕሬዝዳንት (የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ) ጀምሮ ወደ ግንባር ሄደን እኛ መስእዋት ሆነን ኢትዮጵያን ለማዳን ወስነናል " - ዶ/ር አለሙ ስሜ

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሮ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት በውስጥም በውጭም የተከፈተባት ጥቃት የተቀናጀ መሆኑን ገልጾ፤ ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሓትና ግብረአበሮቹ በኢትዮጵያ እስካሁን ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ ናቸው፤ ተጠያቂነቱም ይረጋገጣል ብሏል።

ውጊያው አሁን ካለው የበለጠ ኪሳራ እንዳያደርስ ከነገ ጀምሮ ሁሉም የፀጥታ አካላት ወደተለየ እርምጃ እንደሚሸጋገሩ ተገልጿል።

ዶ/ር አብርሃም በላይ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ፥ " መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ አካላት በቅንጅት ተዘጋጅተው ወደተለየ እርምጃ ይገባሉ ፤ ይህ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ለውጥ ይኖራል " ብለዋል።

በተጨማሪ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በስብሰባው ላይ ከዚህ በኃላ ሁሉም አመራር በየጦር ግንባር እየተገኘ የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ ከፊት ሆኖ እንደሚሰለፍ አሳውቋል።

ዶክተር አለሙ ስሜ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፥ " የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ ከፓርቲያችን ፕሬዜዳንት (ከሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር) ጀምሮ ወደ ግንባር መግባት እንዳለብን በእርግጥ ሌሎች ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ የተወሰነ የልማቱን ስራ ፣ የዲፕሎማሲውን ስራ፣ ከቢሮ የሚሰራውን ስራ እንድንሰራ ሌሎች ከዚህ ውጭ ያለን ከፓርቲያችን ፕሬዜዳንት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ ወደ ግንባር ሄደን እኛ መስእዋት ሆነን ኢትዮጵያን ለማዳን ወስነናል፤ ይሄንንም በተግባር ከነገ ጀምሮ በመንቀሳቀስ የምናሳየው ይሆናል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከነገ ጀምሮ ወደ ግንባር እንደሚዘምቱ አሳወቁ።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ዛሬ ምሽት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰራጩት ፅሁፍ ኢትዮጵያ አሁን እያደረገችው ያለው ትግል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ነው ብለዋል።

"ትግሉ ልጆቻችን ሀገር እንዲኖራቸው የሚደረግ ትግል ነው። ልጆቻችን ክብርና ነጻነትን ለብሰው፣ በዓለም አደባባይ በኩራት ቀና ብለው እንዲሄዱ የሚደረግ ትግል ነው፤ በዓለም ላይ በክብር የምንጠራበት ስም እንዲኖረን የሚደረግ ትግል ነው። መኖር ወይም አለመኖራችንን የሚወስን ትግል ነው። ያለ ጥርጥር ግን እናሸንፋለን። ኢትዮጵያን ጠርቶ መሸነፍ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው" ነው ሲሉ ገልፀዋል።

"ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው" ያሉት ዶ/ር ዐቢይ፥ " ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ" ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ፥ "የእኛ መዝመት የሚፈጥረውን ክፍተት ከግንባር የቀሩት በሙሉ ዐቅማቸው ሸፍነው ይሠራሉ" ያሉ ሲሆን "በግንባር ያልተሰለፉ የክልልና የፌደራል አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ የልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሙሉ ዐቅማቸው ይከውናሉ" ብለዋል።

"ጎልማሶች በዘዴና በብልሃት አካባቢያቸውን እየጠበቁ፣ አረጋውያን እናትና አባቶች በጸሎት እየተጉ፣ ሁሉም ሰው ተባብሮ የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያረጋግጣል" ያሉት ዶ/ር ዐቢይ "ከዚህ በኋላ በሩቁ ተቀምጠን ተቺና አራሚ የምንሆንበት ጊዜ አይደለም። መደረግ ያለበትን እኛው ራሳችን እናድርገው። ለኢትዮጵያ ከእኛ በላይ ከየትም አይመጣም" ሲሉ ገልፀዋል።

* ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#Update

የአብኑ አመራር ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር አብረው እንደሚዘምቱ አሳወቁ።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መከላከያን በግንባር ሆነው ለመምራት ከነገ ጀምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እንደሚዘምቱ ካሳወቁ በኃላ የአብን አመራር እና የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚዘምቱ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ፥ " ለአገር አንድነትና ለሕዝብ ደኅንነት የምንሰስተው ሕይወት የለምና እኛም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዘምታለን። ሕዝቤ ሆይ ተከተል " ሲሉ ነው በገፃቸው ላይ ያሰፈሩት።

@tikvahethiopia
" አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በአስተማማኝ ሰላም ላይ ይገኛል " - ዶ/ር ቀነዓ ያደታ

ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ላደረጉ የአፍሪካ የኤዢያና ፓስፊክ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ተደረገ።

በመድረኩ ላይ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ፤ የከተማዋን ሰላምና መረጋጋት ለማስቀጠል የከተማው የፀጥታ ሀይል ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ከሪፐብሊካን ጥበቃ ሃይል ፣ከኦሮሚያ ፖሊስ እና ከሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ጋር በመሆን በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል።

ከ27 ሺህ በላይ ወጣቶች እንዲሁም ህዝባዊ ሰራዊት የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታን የሚያስከብሩ አደረጃጀቶች እስከ ታችኛው የብሎክ መዋቅር ድረስ በመደራጀት ወደ ስራ መግባታቸውን ገልፀው በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በአስተማማኝ ሰላም ላይ መሆኗን አስረድተዋል።

በምዕራባዊያን ሚዲያዎች የሚነዙትን የፕሮፖጋንዳ እና የሽብር ወሬ መሬት ላይ ካለዉ የከተማዋ የተረጋጋ ሰላም ጋር ፍፁም የሚጋጭ በመሆኑ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባው ዶ/ር ቀነዓ ያደታ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መረጃውን ያገኘ ነው ከAAPS ነው።

@tikvahethiopia