TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድፍድፍ ነዳጅ⬆️ ኢትዮጵያ የድፍድፍ ነዳጅ የሙከራ ምርትን በይፋ ጀመረች። የቻይናው ፖሊ ሲ ጂ ኤል ኩባንያ በምስራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሲያደርግ የቆየው የድፍድፍ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ውጤት አስገኝቶ ዛሬ በይፋ የሙከራ ምርት ጀምሯል።

©FBC

ፎቶ ©RICHO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር⬆️ለታላቁ የድጋፍ ሰልፍ ዝግጅቱ ተሟሙቆ ቀጥሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር! የኤርትራ ሰንደቅ ዓላማ ከ200-250 ብር ድረስ ሲሸጭ ውሏል። ሎተሪ እና መፅሀፍ አዟሪዎች ከሰልፉ ጋር በተያያዘ ወደ ባነር እና ሰንደቅ አለማ ሽያጭ ፊታቸውን አዙረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
🏆🏆 የአለም ዋንጫን ከጥሎ ማለፍ እስከ ፍፃሜ ያሉትን ጨዋታዎች በድሎት
ይመልከቱ

⚽️በትልቅ እስክሪን
⚽️በVIP መቀመጫዎች
⚽️ነፃ ፈዘጣን WiFi
⚽️መጠጥ እና ምግቦችን ከ ማይጠበቅ በቅናሽ ጋር

#የመግቢያ ዋጋ #50 ብር ብቻ
#ከነፃ ቢራ /ኮካኮላ ጋር።

በተጨማሪም ቲኬቱ ላይ ባሉት ቁጥሮች በየቀኑ

🏤በሞዛይክ ሆቴል 2ቀን ሙሉ ወጪ
🎬በ ሴንቸሪ ሲኒማ የነፃ ፊልም የመግቢያ ቲኬቶችን
📱እና ሞባይሎችን ይሸለማሉ

💰እንዲሁም
በ HULL SPORT BEATING እስከ
300,000 ብር ድረስ ተወራርደው ያሸንፉ

😉ማንም ማይቀርበት ፕሮግራም

👨‍👨‍👧‍👦በቡድን ለሚመጡ ልዩ መስተንግዶ አለን

አድራሻ፦
ቦሌ,CUPCAKE ጀርባ
ሞዛይክ ሆቴል

@aratkilo_entertainment
+251944101400

አዘጋጅ;-
The mosaic hotel
&
4kilo entertainment
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
ሩዋንዳ⬆️ሰሞኑን "የኤርትራው ልኡክ ቡድን በቀድሞው ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ መቃብር ላይ ጉንጉን አበባ አኖረ" እየተባለ ሲሰራጭ የነበረው የሀሰት ዜና ነው። የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ርዋንዳ ውስጥ በ1994ቱ የዘር ጭፍጨፋ ለረገፉ ያስቀመጡት የአበባ ጉንጉን ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስጦታ⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ስጦታ ላኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ዛሬ የቡና ስጦታ ወቅታዊ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከሚያሳይ ምስል ጋር አያይዘው ልከዋል፡፡

የኤርትራው ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂም ቡናውን በመቅመስ ‘ጥዑም ቡና!’ በማለት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የሚያጠናክር ፍሪያማ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

.የኤርትራው ልዑካን ወደ ሀገራቸው ተሸኝተዋል።

ምንጭ፦የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ ዩኒቨርሲቲ! የመላው አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጨዋታ በመጪው ዕሁድ በመቐለ ይጀመራል። በመቀለ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅት የሚዘጋጅው ይህ ውድድር ለ5 ተከታታይ ቀናት ነው እንደሚካሄድ የተሰማው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደህዴን ሀላፊነቱን ወስዷል! በደቡብ ክልል ከተስተዋለው የፀጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ ለተፈጠረው ችግር ደኢህዴን ኃላፊነቱን እደሚወስድ አስታወቀ፡፡

የዴኢህዴን ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እንደተናገሩት በሀዋሳ ፣ ወላይታ ሶዶና ወልቂጤ የተከሰተውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ ንቅናቄው በሚወሰዱ የመፍትሄ አምጃዎች ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዋናነት ንቅናቄው ለችግሩ ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስድ ገልፀው ፣እየተወሰዱ ካሉ እርምጃዎች አንዱ የአመራር ተጠያቂነት ማምጣት ነበር፡፡

በፀጥታ መደፍረስ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ ከ1ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝም ሊቀመንበሯ
ተናግረዋል፡፡

ውይይቱን ተከትሎም የንቅናቄው ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤና ሲራጅ ፈጌሳ በገዛ ፈቃቸው ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

በተዋረድ ያሉ የዞን አመራሮችም ከኃላፊነት ለመነሳት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የአመራር ተጠያቂነትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመልክቷል፡፡

ከፀጥታ ተያየዞ የተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋም ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ዴኢህዴን ከስምምነት ደርሷል፡፡

©ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አሶሳ! በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ ገንዘብ በመክፈል ሁከት የፈጠሩትን አካላት መንግስት እያጣራሁ ነው ብሏል። የመከላከያ ሰራዊት ወንጀለኞችን የመያዝ እና ህዝቡን የማረጋጋት ስራ እየሰራ ነው።

*በአሶሳ በተፈጠረው ሁከት የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 49 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

@Tsegabwolde @tikvahethiopia
ጉንችሬ⬆️በጉንችሬ ሊደረገ የታቀደው የድጋፍ ሰልፍ እውቅና አግኝቷል። ሁሉም እንዲሳተፍም አስተባባሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትግራይ ህዝብ ክብሩ ክብራችን፥ ስኬቱ ስኬታችን፥ ችግሩ ችግራችን መከራው መከራችን ነው ብለን የምናምን ወገኖቻችሁ መኖራችንን አትርሱ። የሰፊው ሕዝብ ክብር በጥቂት ሆዳሞ በስሙ በሚነግዱ ሆዳሞች አይፈርስም አብረናችሁ ነን።

ክብር ለሀውዜን ሰማዕታት!

ሕዝብና ሆዳም ፖለቲከኛን የለየ

ኑ እንደመር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia