TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
TPLF እና OLA ወታደራዊ ጥምረት ፈጠሩ። በኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር በማለት የሚጠራው (በመንግስት ደግሞ ሸኔ ተብሎ የሚጠራው) በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ኃይል ከTPLF ጋር ወታደራዊ ጥምረት መፍጠሩን አስታውቋል። በሀገሪቱ አሁን ያለው ብቸኛ መፍትሔ "ይህንን መንግስት ማስወገድ ነው" ለዚህም ከTPLF ጋር ጥምረት ፈጥረናል ሲሉ የኦሮሞ ነጻነት…
"...ህወሓት እና ሸኔ አብሮ ለመስራት መስማማታቸው አዲስ ነገር አይደለም " - ቢልለኔ ስዩም

መንግስት " ሸኔ " እያለ የሚጠራው እና እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) የሚለው በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው ቡድን ከሌላኛው ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ ከተፈረጀው ቡድን ህወሓት / TPLF ጋር አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን ትላንት መግለፁ አይዘነጋም።

በዛሬው ዕለትም ህወሓት በይፋዊ መግለጫ ከOLA ጋር ለመስራት መስማማቱን አሳውቋል።

ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢልለኔ ስዩም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዛሬው መግለጫቸው ላይ ትላንት ከተሰማው የስምምነት ዜና ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ቢልለኔ ፥ "ህወሓትና ሸኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በጋራ ሲሰሩ የቆዩ የሽብር ቡድኖች ናቸው፤ ጋብቻቸው አዲስ ጉዳይ አይደለም" ብለውታል።

ህወሃት በተለይ በኦሮሚያ አካባቢ ሸኔን በመጠቀም የሽብር ስራውን ሲያከናወን መቆየቱን አስታውሰዋል። መንግስት ሁለቱ ቡድኖች ሀገር ለማፍረስ በጋራ እየሰሩ መሆኑን በተጨባጭ መረጃ በመገንዘብ በአሸባሪነት ፈርጇቸዋል ብለዋል።

ከዚህ ህወሓት እና ሸኔ ቡድኖች "ጋብቻ" መፈጸማቸውን ማወጃቸው አዲስ ጉዳይ አለመሆኑን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኖቹ ሀገር ለማፍረስ በጋራ እንደሚሰሩ በግልጽ ያረጋገጡበት ሆኗል ብለዋል።

መንግስት 2ቱን የሽብር ቡድኖች በሚለከት ያለውን ምልከታ ትክክለኝነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያረጋገጠ ክስተት መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

ቢልለኔ ስዩም ሁለቱ ቡድኖቹ ቆምኩለት የሚሉትን ህዝብ በመግደልና በማሰቃየት ይታወቃሉ ሲሉ አስታውሰው የፈጠሩት ጋብቻ የትግራይ እና የኦሮሞ ህዝቦችን አይወክልም ሲሉ አስገንዝበዋል።

ፎቶ ፦ ኢብኮ

@tikvahethiopia
የተፈናቃዮች ቁጥር 300 ሺህ ደርሷል።

በአማራ እና አፋር ክልሎች የተፈናቀሉ ሰዎች 300 ሺህ መድረሱ ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው ዛሬ የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት የውጭ ቋንቋዎች እና የዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ የሆኑት ቢልለኔ ስዩም በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

ቢልለኔ ስዩም ህውሃት የተናጠል ተኩስ አቁም ስምምነቱን ባለመቀበል በአፋር እና በአማራ ክልሎች ላይ ጥቃት በመፈፀም 300 ሺህ ዜጎችን እንዲፈናቀሉ እና የተለያዩ ሰብዓዊ ጥሰቶች ፈጽሟል ብለዋል።

እነዚህ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ቢያስፈልጋቸውም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት አልሰጣቸውም ሲሉም ገልፀዋል።

ችግሩም ለመፍታት መንግስት ከአለም ምግብ ድርጅት (WFP) ጋር በመሆን ምግብና ምግብ ነክ የሰብዓዊ እርዳታዎችን እያቀረበ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ቢልለኔ ወደትግራይ ከሚገባው እርዳታ ጋር በተያያዘ እስከ ትላንት ድረስ 277 የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ወደ ወደ መግባታቸውን አሳውቀዋል።

በሌላ መረጃ ደግሞ ከቀናት በፊት በጠ/ሚ ጽ/ቤት ይፋ የተደረገው ብሔራዊ ጥሪ ከትግራይ ህዝብ ጋር የተገናኘ ሳይሆን በመንግስት በሽብር የተፈረጀውን ቡድን አውዳሚ እንቅስቃሴ ለማስቆም ነው ብለውታል።

በትግራይ ክልል ውስጥ "የትግራይ ኃይል" በሚል በአለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚዘገበው ከፋፋይ መረጃ ትክክል አይደለም ያሉት ቢልለኔ ስዩም፥ "አሁን ላይ መንግስት እየተፋለመ ያለው በትግራይ ክልል እና አጎራባች አካባቢዎች ከሚንቀሳቀሰው ህወኃት ከተባለ የሽብር ቡድን ጋር ነው" ሲሉ አስገንዝበዋል።

"አሁን እየተካሄደ ያለው ጦርነት እና መንግስትም እየተዋጋ ያለው ከትግራይ ህዝብ ጋር ሳይሆን በትግራይ ህዝብ ውስጥ ተደብቆ ከሚንቀሳቀሰው የሽብር ቡድን (ህወሓት) ጋር ነው" ሲሉ ቢልለኔ ጠቁመዋል፡፡

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ፤ ጄፍሪ ፌልትማንን በድጋሚ ወደኢትዮጵያ ሊልኳቸው ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ትላንት ለሊት አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጄፍሪ ፌልትማን በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

ፌልትማን ከነሃሴ 9 ቀን 2013 ዓ/ም እስከ ነሃሴ 18 ቀን 2013 ዓ/ም ባሉት ቀናት ወደጅቡቲ ፣ ኢትዮጵየ እና UAE እንደሚጓዙ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ልዩ መልዕክተኛው በጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ እና UAE በሚኖራቸው ቆይታ ከ3ቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይነጋገራሉ ተብሏል።

የፌልትማን ውይይት ዋነኛ አላማው አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ "ሰላምን የምታበረታታባቸው" እና የቀጠናውን "መረጋጋት እና ብልጽግና የምትደግፈባቸውን" ዕድሎች የተመለከተ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ADAMA : የጠበቃ እና ህግ ባለሞያው አብዱልጀባር ሁሴን ስርዓተ ቀብር ትላንት በአዳማ ከተማ ተፈፅሟል።

የህግ ባለሙያ እና ጠበቃው አብዱልጃባር ሁሴን ነሃሴ 5 ቀን 2013 ዓ/ም በአዳማ ከተማ (ገንደ ገዳ ቀበሌ) ነው ህይወታቸው አልፎ የተገኘው።

ከቤተሰቦቻቸው በተገኘው መረጃ በዕለቱ ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ከቤት ወጥተው ምሽት አንድ ሰዓት አካባቢ ነው ማረፋቸው የተሰማው።

በወቅቱ አስክሬናቸው ወደአዳማ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አ/አ "ሚኒሊክ ሆስፒታል" ተወስዷል፤ በኃላም ምርመራው ሲጠናቀቅ አስክሬናቸው ወደአዳማ ተመልሶ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።

በስርዓተ ቀብራቸው ላይ ቤተሰቦቻቸው ፣ ወዳጆቻቸው እንዲሁም የስራ ባልደረቦቻቸው ተገኝተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ከአሟሟታቸው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የአስክሬን ምርመራ ውጤት ሪፖርቱን እስካሁን በይፋ ለማወቅ ባይቻልም እሳቸው አባል የሆኑበት የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን ስለአሟሟታቸው ምክንያት እና ሁኔታ ለማወቅ እየሰራ እንደሆነ መግለፁ ይታወሳል።

የህግ ባለሞያ እና ጠበቃ አብዱልጀባር ሁሴን ከእነ አቶ ጃዋር መሀመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ ሌሎችም እስረኞች ጠበቃዎች መካከል አንደኛው ሲሆኑ ለፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው እና ለሌሎች በርካታ ታሳሪዎች ጥብቅና በመቆም በሞያቸው አገልግለዋል።

@tikvahethiopia
ነዋሪዎችን ያማረረው ህገወጥ ተኩስ...

በጎንደር ከተማ በተለይም ማራኪ ክፍለ ከተማ ሰሞኑን የተለያዩ ምክኒያቶች ስበብ በማድረግ ህገ ወጥ ተኩስ እየተፈጸመ ይገኛል።

ይህን ምክኒያት በማድረግ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ትላንትናው ውይይት አድርገዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በአካባቢያቸው የሚፈፀመውን ህገወጥ ተኩሱን አውግዘዋል።

የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦች የወታደራዊ የጦር መሳሪያው አያያዝ ህግና ስርዓቱን ማክበር ይገባቸዋል ያሉት ነዋሪዎች ሁሉም ህገወጥ ተኩስን ማውገዝና መከላከል ይገባል ብለዋል።

ህገወጥ ተኩስ የሚፈፅሙ ግለሰቦች ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የህወሓት ቡድን አጀንዳ አሰፈፃሚ በመሆናቸው መንግስት እርምጃ ሊወስድ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ፥"ለጠላት ሊተኮስ የሚገባው ጥይት የህገ ወጥ ተኩስ የህፃናትንና የእናቶችን ሰላም በመንሳት በእጅጉ ከመጉዳቱ በተጨማሪ ተኳሾቹ ለታሪካዊቷ ጎንደርና አካባቢው ህዝብ ያላቸውን ንቀት ያሳያል" ብለዋል።

"ለህዝብ ሰላምና ክብር ያልሰጠ ህገወጥ በአፀፋው ክቡሩን ገፈን በህግ የሚጠየቅ ይሆናል" ሲሉ ጠቁመዋል።

በህገ ወጥ ተኩስ በሚሳተፋ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ገልፀዋል።

"መሳሪያቸውን በማስወረድ በህግ ተጠያቂ እናደርጋለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ህገወጥ ተኩስ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦች በማወቅ ይሁን ባለማወቅ የጠላት አጀንዳ እየተቀበሉ በመሆኑ ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ከንቲባው መንግስት በሚወስደው አርምጃ ነዋሪዎች ተባባሪ ሊሆኑ ይገባል ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከጎንደር ኮ/ሽን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ከዚህ ቀደም ጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በከተማቸው የሚፈፀም ህገወጥ ተኩስ መፍትሄ እንዲበጅለት በተደጋጋሚ ሲጠይቁ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

#አዲስአበባ ወደ #ጎጃም በሚወስደው መንገድ ዓባይ በረሃ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ልዩ ስሙ #ፍልቅልቅ በሚባለው ስፍራ ላይ ዛሬ ሌሊቱን ባጋጠመ የድንጋይ መንሸራተት ናዳ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጓል አጋጥሟል።

ችግሩን በቶሎ ለመቅረፍ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን (ኢመባ) በስፍራው አሰቸኳይ ጥገና የሚያደርግ ግብረ ሃይል በመላክ በስፍራው ከሚገኘው አሰቸኳይ ጥገና ቡድን ጋር በጋራ እየሰሩ ሲሆን ስራው ተጠናቆ መንገዱ ክፍት ሲደረግ ይገለፃል ተብሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን

@tikvahethiopia
ሲኖትራክ መኪና የዘረፉ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው ሶስት ሲኖትራክ እየተባሉ የሚጠሩ ተሽከርካሪዎችን የሰረቁ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ወንጀሉ የተፈፀመው በየካ ክፍለ ከተማ አያት አደባባይ አካባቢ በሚገኘዉ ቻርጄር ጀኔራል ቢዝነስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ውስጥ ነው፡፡

ድርጅቱ በቁጥር 4 የሚሆኑ ሲኖትራክ ተሽከርካሪዎችን የመሸጥ ፍላጎት ስለነበረው ተጠርጣሪዎቹ መኪናዎቹን እንገዛለን በማለት ወንጀሉን ከመፈፀማቸው ከአንድ ሳምንት በፊት መጥተዉ እንደተመለከቱ ፖሊስ በምርመራ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ሀምሌ 22/2013 በግምት ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ድርጅቱ በመምጣት እና ለተቋሙ የጥበቃ ሰራተኞች እኛ የመረጃ እና ደህንነት አባሎች ነን ብለው በመንገር አፍነዉ ወደ ህንፃው የምድር ወለል ውስጥ ካስገቧቸው በኋላ ቆመው ከነበሩት አራት ሲኖትራክ ተሽከርካሪዎች መካከል 7.8 ሚሊዮን ብር የዋጋ ግምት ያላቸው 3 ሲኖትራክ መኪናዎች ይዘው ተሰውረዋል።

አ.አ ፖሊስ የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ክትትል ሁለቱን ሲኖትራክ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን እና አንደኛውን ተሽከርካሪ በ860 ሺ ብር የሸጡት በመሆኑ እሱንም ለማስመለስ እየሰራ ስለመሆኑ አመልክቷል፡፡

ከጎዳዩ ጋር በተያያዘ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

የመረጃ ባለቤት : አ/አ ፖሊስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በራያ ዩኒቨርሲቲ ይገኙ የነበሩ ሁሉም ተማሪዎች ወጥተዋል። በራያ ዩኒቨርሲቲ የነበሩ 1 ሺህ 400 የሚጠጉ የሌሎች ክልሎች ተማሪዎች ከግቢው መውጣታቸውን የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ምንጮች ተናግረዋል። ተማሪዎቹን የያዙ 22 አውቶብሶች ከአፋር ክልል አብዓላ ከተማ ተነስተው ወደ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ እየተጓዙ መሆኑን ሠምተናል። አውቶቡሶቹ ዛሬ ማታ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ እንደሚደርሱ ይጠበቃል። የሠመራ…
#Update

ከራያ ዩኒቨርሲቲ የወጡ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ላይ ናቸው።

በራያ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ የነበሩ 1 ሺ 240 ተማሪዎች ትላንት ነሐሴ 06/2013 ዓ.ም በአብዓላ በኩል ሠመራ ከተማ ገብተዋል።

በ24 አውቶቡሶች ተጭነው ሠመራ ከተማ ትላንት ከመሸ የደረሱት ተማሪዎቹ ፤ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ አቀባበል ተደርጎላቸው በእዛው እንዲያድሩ ተደርጓል።

ዛሬ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ መጓዝ መጀመራቸውን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ (@tikvahuniversity) አረጋግጧል።

በትምህርት ላይ የነበሩት የራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፤ ከሰኞ እስከ ረቡዕ ድረስ የሴሚስተር ፈተናቸውን በማጠናቀቅ መውጣታቸው ታውቋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በኩል መከታተል ትችላላችሁ : t.me/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity
"በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁበት ሁኔታ አመቻቻለሁ።" - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

ተመራቂ እና ያልተጠናቀቀ የትምህርት ተግባር ያላቸው ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁበትንና የሚመረቁበትን ሁኔታ እንደሚያመቻች የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፦
- ከዓዲግራት 2,355
- ከአክሱም 2,992
- ከመቐለ 3,668
- ከራያ 1,149 በድምሩ 10 ሺህ 164 ተማሪዎችን ማስወጣቱን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ተማሪዎቹ እስከ ነሐሴ 06/2013 ዓ.ም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ በኩል ወደ አዲስ አበባ ተጓጉዘዋል፡፡

የክረምት ተከታታይ ትምህርት ያላቸው እና በፀጥታ ችግር ወደቦታው መሄድ ያልቻሉ በቀጣይ በሚቀመጥ አቅጣጫ መሰረት ትምህርት የመከታተል እድል ይመቻቻላቸዋል ብሏል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በኩል መከታተል ትችላላችሁ : t.me/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity
#HachaluHundessaBonsa

በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ስም የተሰየመው የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ስም የተሰየመው የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሃሰን የሱፍ ÷ የትምህርት ቤቱ ዓላማ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በህይወት ዘመኑ የሰራውን የጥበብ ስራ ለትውልድ ማስተላለፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

መጪው ትውልድም በአርቱ ዙሪያ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ሁኔታዎችን ማመቻቸት መሆኑም ተነግሯል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ አባ ገዳዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በሌላ በኩል ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነገ ለ16ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል፡፡

የመረጃ ባለቤት : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia