TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
* Addis Ababa Police

የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀልና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሌሎች የፀጥታ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል መኖሪያ ቤት እና የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ልዩ ልዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነት እንዲያረጋግጡ አሳስቧል።

በአ/አ በተለያዩ አካባቢዎች ማንነታቸውን ሰውረው መኖሪያ ቤቶችን እና መኝታ ቤቶችን በመከራየት የወንጀል ተግባራትን ለመፈፀም አቅደው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ስለመኖራቸው የፖሊስ የምርመራ መዛግብት እንደሚያስረዱ ገልጿል።

በዋናነት ፦
- የመኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ፤
- የመኝታ አገልግሎት በሚሰጡ ሆቴሎች፣
- ፔንሰሊዮኖችና ተመሣሣይ አገልግሎት የሚሰጡ የንግድ ቤቶች ማንነታቸው በግልፅ ላልታወቁ ሰዎች ቤት እንዳያከራዩ እንዲሁም በሚያከራዩበት ወቅት የተከራዩን ማንነት የሚገልፁ የነዋሪነት መታወቂያና ሌሎች ሰነዶችን በሚገባ አረጋግጠው በመመዝገብ ይህንንም በየአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ፖሊስ ዛሬ ባሠራጨው መልዕክት አሳስቧል፡፡

☎️ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ለፖሊስ ጥቆማ መስጫ ስልክ ቁጥሮች ከላይ ባለው ምስል ላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

''አመጽና ጦርነት ለማቆም መቼም ቢሆን አይረፍድም። ለህዝብ ጥቅም ልንይዘው የሚገባን ብቸኛው መንገድ የእርቅ እና ሰላም አማራጭ ነው'' - የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት መልእክት

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ከሐምሌ 6 እስከ ሐምሌ 9 2013 ዓ.ም. በሞጆ የኮንሰላታ አባቶች ካቶሊክ ገዳም መደበኛ ጉባኤ አካሂደዋል።

በተለያዩ የቤተክርስቲያንና የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ጥልቅ ውይይቶችን ማድረጋቸውንም ከጉባኤው በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

በመልዕክቱ የተነሱ አንኳር ነጥቦች መካከል ፦

- ጦርነት ላይ የሚሳትፉ ሁሉ ጦርነት ሕይወት የማጥፋት ፣ ንብረት ከማውደም ሀገርን ከማደህየት ያለፈ ውጤት እንደሌለው ተረድተው የህዝባችን የመኖር ምርጫ ሁሉ የሠላም ግንባታና የእርቅ ሥራ እንዲሆንና እንዲቀጥል አሁንም ደግመን ደጋግመን እንማፀናለን።

- የህዝብን ስቃይ ሊያቃልሉ በሚችሉ ሰብአዊ ድጋፎች የምትሳተፉ ሁላችሁም ማንም የድጋፉ ተጠቃሚ ሳይሆን ወደኋላ እንዳይቀር እንማጸናለን። ለዚህም መሠረታዊ ሰብአዊ ደጋፍ ለሁሉም ወገኖች እንዲዳረስ ሁሉም ወገኖች ያልተገደበ ጥረትና ቀናተኛነት እንዲያሳዩ እናሳስባለን።

- ወደጦርነት መግባት ለተፈጠሩ ስህተቶች ማረሚያ ወይም ለተፈጠረው አለመግባባት መልስ ሊሰጥ በፍጹም እንደማይችል በሁሉም ዘንድ የታወቀ ይሆናል። ምክንያቱም ጦርነት መቼም የሰላም መፈለጊያ መንገድ ሆኖ አያውቅም።

- እኛ እንደእረኞች ለህዝባችን ልንሰጣችሁ የምንችለው ብቸኛ ነገር በክርስቶስ አማካይነት በእግዚአብሔር ያለን እምነት የሚመነጭ ተስፋ ነው። አመጽና ጦርነት ለማቆም መቼም ቢሆን አይረፍድም። ለህዝብ ጥቅም ልንይዘው የሚገባን ብቸኛው መንገድ የእርቅ እና ሰላም አማራጭ ነው።

@tikvahethiopia
#ItsMyDam

የግድባችን ሁለተኛው ዙር ውሃ ሙሌት እየተከናወነ ነው።

ግብፅ እና ሱዳን የግድባችንን ጉዳይ ወደተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ይዘውት ቢሄዱም ይህን ነው የሚባል ለውጥ አላመጡም ይልቁንም አብዛኛው የምክር ቤቱ ሀገራት ከሁለቱ ሀገራት በተቃራኒ የግድቡ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት መፍትሄ እንዲፈለግለት የሚል አቋም አንፀባርቀዋል።

ከምክር ቤቱ ስብሰባ በኃላ ግብፆቹም ሆኑ ሱዳኖቹ አላረፉም፤ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በግድቡ ጉዳይ ሃሳባቸውን ለማስረፅ እና ለማሳመን እየተነጋገሩ ነው።

ለአብነት ዛሬ የግብፁ ፕሬዜዳንት ከቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ስለግድቡ መክረዋል።

የግብፅ እና ሱዳን ሚዲያዎችም ቢሆኑ በየቀኑ ስለግድባችን ሳያነሱ አያልፉም። አሁንም ስለግድባችን የተሳሳቱ መረጃዎች ከማሰራጨት አልተቆጠቡም።

Egyptian Independent በተባለው ሚዲያ ብቻ ባለፉት 4 ቀናት ውስጥ ሰባት (7) የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ዘገባቸው ተሰርተዋል። በሌሎች ሚዲያዎች እንደነ Egypt Today ፣ Al-Ahram ፣ Daily News Egypt ላይ በርካታ ዘገባዎች ሲሰሩ ነበር።

ከፍተኛ መነጋገሪያ የነበረው ግን በ #Egypt_Today ላይ የወጣውና በሀገራችን ሚዲያዎች ተተርጉሞ የተሰራጨው ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ ሃያ ከሪማ ብሄራዊ ኮንፈረንስ ላይ ያደረጉት ንግግር ነው።

ንግግራቸው በሀገራችን ግዙፍ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት ከአውድ ውጭ ተተርጉሞ/ሆን ተብሎ ብዙዎችን አሳስቷል። አንዳንዶች ግብፅ አቋም የቀየረች እንዲመስላቸው ሆኗል።

በእርግጥ የግብፁ ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ ምንድነው ያሉት ? ያንብቡ telegra.ph/Grand-Ethiopian-Renaissance-Dam-07-18

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን ሁለተኛው ዙር ሙሌት #ዛሬ_ለሊት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተሰምቷል።

የውሀው መጠን ግንባታው የደረሰበት ከፍታ ላይ ደርሶ ዛሬ ለሊት ሞልቶ ይፈሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው "የሪፖርተር ጋዜጣ ድረገፅ" ሲሆን መረጃውን ከፕሮጀክቱ ስፍራ ማግኘቱን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ItsMyDam🇪🇹 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን ሁለተኛው ዙር ሙሌት #ዛሬ_ለሊት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተሰምቷል። የውሀው መጠን ግንባታው የደረሰበት ከፍታ ላይ ደርሶ ዛሬ ለሊት ሞልቶ ይፈሳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው "የሪፖርተር ጋዜጣ ድረገፅ" ሲሆን መረጃውን ከፕሮጀክቱ ስፍራ ማግኘቱን ገልጿል። @tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ በስፍራው ያሉ የግድቡ ሰራተኞች እየገለፁ ነው።

የውሀው መጠን ግንባታው የደረሰበት ከፍታ ላይ ደርሶ ሞልቶ ይፈሳል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ሂደቱ ትላንት ለሊት የተጠበቀ ቢሆንም ሳይሆን ቀርቷል።

Photo Credit : Boni Kita (ከፕሮጀክቱ ስፍራ)

@tikvahethiopia