TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,348 የላብራቶሪ ምርመራ 604 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 208 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 71,687 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,148 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 29,461 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲዎችን እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠናን ከተቋረጠበት ለማስቀጠል በመሪዎች ደረጃ ዛሬ በተካሄደው ስብሰባ የተቀመጠ አቅጣጫ!

- የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እስከ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት መጨረሻ የተቋማትን ዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም በአካል እየተገኘ ገምግሞ በቂ የኮቪድ-19 መከላከል ዝግጅት ላደረጉት የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ተማሪና ሰልጣኝ እንዲቀበሉ ይፈቅዳል።

- ያለ በቂ ዝግጅት እና ያለሚኒስቴሩ የመስክ ምልከታና ፈቃድ ተማሪዎችን ወይም ሰልጣኞችን ተቀብሎ መገኘት አግባብነት አይኖረውም።

- የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች እና የሥልጠና አጠናቃቂዎች እንዲሁም በሌሎች የትምህርት እና ሥልጠና እርከን ያላችሁ ሁሉ በቀጣይ በሚዲያ በሚታወጀው የተማሪ እና ሰልጣኝ ቅበላ መርሃግብር መሠረት በየተቋሞቻችሁ ጥሪ የሚደረግላችሁ በመሆኑ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ ይሁን።

ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ
ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች!

በበርካታ የትያትርና ፊልም ስራዎች የምትታወቀው አንጋፋዋ አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።

ለሳምንታት በህመም ላይ የነበረችው አርቲስቷ ዛሬ ማለዳ ነው ማረፏ የተሰማው።

የአርቲስቷ ስርዓተ ቀብር ነገ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ከኢ.ብ.ኮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 አጫጭር መረጃዎች ፦

- ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በህንድ የ1,144 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ 85,919 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በብራዚል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 818 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ሲያልፍ 32,129 ሰዎች በቫይረሱ መያቸው ተረጋግጧል።

- ሜክሲኮ ውስጥ በ24 ሰዓት 601 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።

- በአሜሪካ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር 207,538 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓታ 942 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል።

- በአፍሪካ በኮሮና የተያዙ ሰዎች 1,444,619 ደርሰዋል። በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ብዛት ደ/አፍሪካ ፣ ሞሮኮ ፣ ግብፅ፣ #ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።

- በመላው ዓለም በኮሮና መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 32,420,147 ደርሷል ፤ 987,815 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 23,934,098 ሰዎች አገግመዋል።

#መታጠብ #መቆየት #መራራቅ #መሸፈን😷
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...መከላከያ ሰራዊትን አትፈታተኑት" - ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ

የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን ብለዋል ፦

"ከመስከረም 30 በኃላ መንግስት የለም ብዬ እንደፈለኩ አደርጋለሁ የሚል ፤ ባለፈው የሆኑ የፖለቲካ ሰዎች ሲናገሩት የነበረ የወረደ ንግግር በመከላከያ ተቀባይነት የለውም።

ስልጣን ማግኘት የሚቻለው በምርጫና ምርጫ ብቻ ነው ፤ ሌላ የስልጣን ማግኛ መንገድ የለም።

ባላደራ የለም ፣ ሽግግር የለም ፣ ምንም የለም። እንደዛም አያስድኬድም ፤ ለሀገራችንም ጥሩ አይደለም ፣ ለእያንዳንዳችንም ጥሩ አይደለም። የመከላከያ ሰራዊትንም አትፈታተኑት።

ህገ መንግስት ለማስከበር ሲባል ፣ ህገመንግስቱን በጣሰ መንገድ ፍላጎቴን በኃይል እጭናለሁ ብሎ የሚመጣ ኃይል ካለ እርምጃ እንወስዳለን።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ከተማ በሚወስደው መንገድ የሚጓዙ መንገደኞች መጉላላት እየደረሰባቸው ነው!

(Ethiopia Check)

በዚህ መንገድ የሚያልፉ የመንገደኛ አውቶቡሶች አንዳንዶቹ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የታገዱ ሲሆን ሌሎች ደግሞ እንዲያልፉ እየተደረጉ መሆኑን 'ኢትዮጵያ ቼክ' አረጋግጧል።

ወጣቶች የበዙባቸው አውቶቡሶች በተለይ እገዳው የተጣለባቸው ሲሆን የአዲስ አበባ ነዋሪ መሆናቸውን የሚያሳይ መታወቂያ የተጠየቁም እንዳሉም ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ባሳለፍነው ሳምንት 2 አውቶቡሶች ወደ ደጀን ከተማ ተመልሰው፣ በነጋታው እንዲያልፉ ተደርጓል። ባለፉት ሶስት ቀናትም የከፊል እገዳው እንደቀጠለ ታውቋል።

የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ከመስቀል በዓል ጋር በተያያዘ ጥበቅ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ፣ ወደ አዲስ አበባ ያመሩ ከነበሩ አውቶብሶች የተወሰኑት ትናንት ጠዋት እንዲመለሱ ተደርገው እንደነበር ተናግረዋል።

ከረፋድ 4 ሰዐት በሗላ አውቶብሶቹ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ መቀጠላቸውን እንዲሁም መንገዱ ክፍት መሆኑን አቶ ግዛቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ በበኩላቸው "መንገዱ ክፍት ነው" ሲሉ ለ'ኢትዮጵያ ቼክ' ተናግረዋል።

PHOTO : TIKVAH FAMILY
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌዴራል ፖሊስ የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል !

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው ጣሰው በመግለጫው የተናገሩት ፦

- የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓላት በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጓል።

- የበዓሉን እንቅስቃሴ ለማደፍረስ ዕቅድ ያላቸው ሀይሎች እንዳሉ ፖሊስ በምርመራ ተደርሶበታል፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው ሊቀቆጠቡ ይገባል።

-በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ መግቢያ በሮች በሱልልታ፣ ለገጣፎ፣ ቡራዩ ፣ ገላንና ሰበታ ፍተሻ እየተደረገ ይገኛል።

- አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት በበዓሉ ለመታደም የሚመጡ ምዕምናንና እንግዶችም ትክክልኛውን የይለፍ ባጅ ማድርጋቸውን ማረጋገጥ አለባቸው። ይህን ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካላት ላይ ፖሊስ እርምጃ ይወስዳል። (ኢዜአ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌዴራል ፖሊስ ማስጠንቀቂያ !

ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከመስከረም 25 በኋላ “መንግስት የለም” በሚል አገራዊ ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ ርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቅ።

ፌዴራል ፖሊስ ፥ ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስን ማንኛውም አካል አይታገስም ፤ ህግን የማስከበር ስራውንም አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

ከህብርተሰቡ ጋር በትብብር እየሰራሁ ነው ያለው የፌዴራል ፖሊስ ፤ ህብረተሰቡ ለየትያለ እንቅስቃሴ ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትናንት ሌሊት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈፀመ ጥቃት የንፁኃን ሕይወት አለፈ!

(አብመድ)

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊት 10፡00 ገደማ ማንነታቸው ያልታወቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ የንፁኃን ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የበንገዝ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ደምለው በንገዝ ለአብመድ ተከታዩን ብለዋል ፦

- በአካባቢው ጥቃት ተፈጽሟል ፤ ከ20 በላይ ንፁኃን ተገድለዋል፡፡

- ችግሩ እንደሚፈጠር ስጋት ነበር ፤ ጥቃቱ ሌሊት የተፈጠረ በመሆኑ ለመከላከል እና አጥፊዎቹን ለመከታተል አልተቻለም።

የዳንጉር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ደሳለኝ እንድሪስ ለአብመድ ተከታዩን ብለዋል ፦

- ከጥቃቱ በኋላ በአካባቢው የተለየ እንቅስቃሴ የለም።

- የፀጥታ አካላት ወደ አካባቢው ተንቀሳቅሰው ችግሩን እያጣሩ ነው።

- ችግሩ የተፈጠረበት አካባቢ የደኅንነት ስጋት እንዳለበት ቀደሞ መረጃ ስላለ ወደ አካባቢው ሰዎች እንዳይሄዱ ተነግሯል ፤ ነገር ግን ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች በምን መንገድ ተመልሰው እንደሄዱ ዕውቅና የለንም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ 2ተኛ መደበኛ ስብሰባ ያደረገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ከተወያየና ከመከረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፤ ከውሳኔዎቹ መካከል ተከታዩ ይገኝበታል ፦

"ኮቪድ-19 በአገራችን እንዲሁም በከተማው ከተከሰተበት ከመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ የህክምና አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም በማስተባበር የተሠማሩ በከተማው አስተዳደሩ ስር በሚገኙ የጤና ተቋማት ሁሉ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ይህ ወረርሽኝ በአገራችን ስጋት መሆኑ እስከሚያበቃበት ጊዜ ድረስ የከተማ አስተዳደሩ የገቢ ግብር ወጪያቸውን ለመሸፈን ውሳኔ አሳልፏል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሚዘጉ መንገዶች!

ነገ የደመራ በዓል ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ

- ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ

- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት

- ከቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አገር አስተዳደር መብራት ወይም ኢሚግሬሽን መ/ቤት አካባቢ

- ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ

- ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ

- ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ

- ከሳሪስ በጎተራ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ

- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ

- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ፣ ሜክሲኮ ፣ ለገሀር መብራት የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት አካባቢ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናል።

ደመራው የሚደመርበት መስቀል አደባባይ እና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ስታዲዬም እንዲሁም ከሃራምቤ ሆቴል ወደ ሴንጅ ዮሰፍ የሚያቋርጠው መስቀለኛ መንገድ ለበዓሉ በሚደረገው ዝግጅት ምክንያት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ ይደረጋል።

#SHARE #ሼር

(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,227
በበሽታው የተያዙ - 486
ህይወታቸው ያለፈ - 7
ከበሽታው ያገገሙ - 273

መስከረም 15/2013 ዓ/ም
(ዶክተር ሊያ ታደሰ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስራኤል በኮሮና መባባስ ምክንያት ወደ ሙሉ የእንቅስቃሴ ክልከላ ተመለሰች!

እስራኤል ውስጥ የኮቪድ-19 ሥርጭት መባባሱን ተከትሎ ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ወደ ቀደሙት ሙሉ የእንቅስቃሴ ክልከላ መመለሷን VOA አስነብቧል።

ለ2 ሳምንታት በሚቆየው ዕገዳ ፦

- ትምህር ቤቶች ይዘጋሉ፤

- የመዝናኛ ሥፍራዎች ይዘጋሉ፤

- አብዛኞች የንግድ ድርጅቶች ይዘጋሉ፤

- ምግብ ቤቶች ለበላተኛ ማድረስ እንጂ አስገብተው ማስተናገድ አይችሉም።

- ነዋሪዎች ለሥራ ወይም መድሃኒት ለመግዛት ካልሆነ በስተቀር ከመኖሪያቸው ርቀው መውጣት ተከልክለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ትናንት ሌሊት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈፀመ ጥቃት የንፁኃን ሕይወት አለፈ! (አብመድ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊት 10፡00 ገደማ ማንነታቸው ያልታወቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ የንፁኃን ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የበንገዝ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ደምለው በንገዝ ለአብመድ ተከታዩን ብለዋል…
#FDREDefenseForce

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት ሌሊት 10:ዐዐ ላይ ጥቃት መፈጸሙን መረጃ የደረሰው ማለዳ 12:00 እንደሆነ በመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ 22ኛ ክፍለ ጦር ለአብመድ አሳውቋል።

የምዕራብ ዕዝ 22ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል ነገሪ ቶሊና ስለጉዳዩ #ለአብመድ (AMMA) ተከታዩን ብለዋል ፦

- ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት ሌሊት 10:ዐዐ ጥቃት መፈጸሙን መረጃ ያገኘነው ማለዳ 12:00 ነው።

- ሠራዊቱ አካባቢውን በመቆጣጠር ጥቃት አድራሾችን የማሰስ እና እርምጃ የመውሰድ ተግባር ፈፅሟል።

- ሽፍቶች በደፈጣ ውጊያ በማድረግ ከሠራዊቱ ለመሰወር ጥረት አድርገዋል ፤ ሠራዊቱ ስምንት (8) ሽፍቶች ላይ እርምጃ ወስዷል።

- የመከላከያ ሠራዊቱ በአካባቢው ተደራጅተው ንጹሐን ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ሽፍቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የተሰጠውን ሕዝባዊ አደራ በቁርጠኝነት ይወጣል።

PHOTO : FDRE Defense Force (FILE)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት ምን ይመስላል ?

#BahirDarUniversity

- የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል የዝግጅት ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል።

- በተለይ የዶርምተሪ ጥገናዎች ተደርገዋል፤ ተማሪዎች በዶርም ውስጥ የሚኖራቸው ቁጥር በመመሪያው መሰረት ከዛም በተሻለ መልኩ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

- የተለያዩ የግብዓት አቅርቦቶችም እየተሟሉ ይገኛል።

- ዩኒቨርሲቲው ካሉት ካምፓሶች ሁለቱ (2) ብቻ በኳራንቲን ማዕከልነት አገልግለዋል ፤ በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የጽዳት ሥራም ይሰራል።

#DireDawaUniversity

- ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ በኳራንቲን ማዕከልነት እያገለገለ ሲሆን በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ወደ ቀድሞ ተግባሩ ለመመለስ እየተሰራ ነው።

- በዶርም ውስጥ የሚገኙ ፍራሾች በአዲስ የሚተኩ ሲሆን የእድሳት ሥራዎችንም በአጭር ግዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል፡፡

- ትምህርትን በሚመለከት ተመራቂ ተማሪዎች እና የአራተኛ አመት ኢንጂነሪንግ ተማሪዎች በተለይ (አፓረንት) የሚወጡ ተማሪዎች ቀድመው ይጠራሉ።

- ተማሪዎች የአንደኛ (1) ሴሚስተር ፋይናል ፈተና ሳይወስዱ ከግቢ በመውጣታቸው ምክንያት ሲመለሱ የማጠናቀቂያ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

- ሆለስቲክ ፈተናም ይሰጣል።

- በተጨማሪም የተግባር ልምምድ (አፓረንት) በተመለከተ ከፈተናው በኃላ የሚወጡ ይሆናል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ቅድመ ዝግጅት በየጊዜው እየጠየቀ እና እየተከታተለ ለተማሪዎች እንዲሁም ለተማሪ ወላጆች ያሳውቃል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስከረም 16/2013 ዓ/ም

አጫጭር የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

- በኮሮና ቫይረስ መባባስ ምክንያት የኢንግላንድ እና የዌልስ መጠጥ ቤቶች ከሃሙስ ጀምሮ ደንበኞቻቸው በጊዜ አስተናግደው እየዘጉ ናቸው።

- በስኮትላንድ ትላንት ጀምሮ ከማታ አራት ሰዓት በኃላ ምግብና መጠጥ ቤቶች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

- ፈረንሳይ ውስጥ ካለፈው ሰኔ ወር ወዲህ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ታመው ጽኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ ህሙማን ቁጥር ሃሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ሽህ አልፏል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በህንድ ተጨማሪ 1,093 ሰዎች ሲሞቱ ፤ 85,468 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ብራዚል ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 836 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 32,670 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሚሊዮን እየተጠጋ ነው፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 32,771,253 ደርሰዋል።

- WHO ክትባት በስፋት ከመሰራጨቱ በፊት በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ሁለት ሚሊዮን ሊደርሱ ይችላሉ ብሏል። የድርጅቱ የድንገተኛ ቡድን መሪ ዶ/ር ማይክ ራየን እንዳሉት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ካልተባበረ የሟቾች ቁጥር ሊጨምርም ይችላል።

- ፈለክ የፊት ማስክ ለኮቪድ-19 መከላከያ የሰራቸው የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ (ማስክ) የውጤታማነት የብቃት ማረጋገጫ አግኝቷል።

(VOA, BBC , WORLDOMETERS)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደመራ በዓል ውስን ሰዎች በተገኙበት ይከበራል!

የመስቀል ደመራ በዓል ዛሬ ሲከበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ደግሞ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ውስን ሰዎች በተገኙበት ይከበራል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ባስተላለፉት 'እንኳን አደረሳችሁ' መልእክት ሁሉም ማህበረሰብ በመስቀል በዓል አከባበር ስነ-ስርዓት ላይ ለኮሮና ቫይረስ አጋላጭ ከሆኑ ድርጊቶች ራሱን እንዲቆጥብ አሳስበዋል።

ዶ/ር ሊያ ታደሰ “በደመራ ቦታዎች ላይ ርቀትን በመጠበቅ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ በመጠቀም ፣ እጅን በሳሙና እና በውሃ በመታጠብና/ ሳኒታይዘር በመጠቀም የበሽታውን ስርጭት የመከላከል ሃላፊነታችንን እንድንወጣ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል - (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የነበረው ምርመራ መጠናቀቁን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ አስታውቋል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና ኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጉዳዩን አስመልክተው በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ም/አቃቤ ህጉ አቶ ፍቃዱ ጸጋ በመግለጫው ተከታዩን ብለዋል ፦

- በ488 የክስ መዝገብ 5 ሺህ 728 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቶባችዋል።

- 3 ሺህ 377 ተከሳሾች በፌደራል መንግስት ስልጣን ስር የሚወድቅ ወንጀል በመፈጸማቸው ተጠያቂነታቸው በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሲሆን፤ 2 ሺህ 351 ተከሳሾች ደግሞ በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ስር ይሆናል።

- በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተከሳሾች በ114 የክስ መዛግብት ክሳቸው ተደራጅቷል።

- በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ደግሞ በ374 የክስ መዛግብት ክሳቸው ተደራጅቷል።

- የክስ መዝገብ ከተከፈተባቸው መካከል 63 ግለሰቦች በሀረር በፈረሱ ሃውልቶች ምክንያት በሽብር ህጉ መሰረት ተጠያቂ የሚሆኑ ናቸው።

- በኦሮሚያ ክልል ከአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኃላ በተከሰተው ሁከት 167 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፣ 360 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፣ ከ4 ቢሊየን 673 መቶ ሚሊየን ብር በላይ የንብረት ጉዳት ማድረሱ በምርመራ ተጣርቷል። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia