TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኢራን የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር 4,683 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት 98 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በዩናይትድ ኪንግድደም ባለፉት 24 ሰዓት 778 ሰዎች ሞተዋል። 5,252 ሰዎችም በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በሩሲያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 20,000 ደርሷል።

- በህንድ የእንቅስቃሴ ገደብ እስከ MAY 3 ድረስ መራዘሙን ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ አሳውቀዋል።

- በስፔን በመጠኑም ቢሆን መቀነስ አሳይቶ የነበረው የሟቾች ቁጥር ዛሬ ከፍ ብላል፤ ባለፉት 24 ሰዓት 567 ሰዎች የሞቱ ሲሆን አጠቅላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎችም ከ18,000 በልጧል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.9 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ462,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ123,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- ሜክሲኮ የሚገኘው የኬኬር ሕንፃ ባለቤቶች ወ/ሮ አስካል ሀብቴ እና አቶ ሣህሌ ልጋ ከሶስት መቶ ሃምሳ በላይ ለሚሆኑ የግል ድርጅቶች እና ለግል ተከራይ ደንበኞቻቸው የሁለት ወር ኪራይ ነፃ ማድረጋቸውን አረጋግጠናል።

- ሳውዝ ጌት ፕላዛ ለተከራዮቹ የሁለት ወር ኪራይ ነፃ ማድረገን ከኢ/ር ታከለ ኡማ ሰምተናል።

- ኮሜት ህንፃ በህንፃው ላይ ለሚገኙ ተከራዮች (1ሚሊየን ብር) የሚገመት የአንድ ወር ኪራይ ነፃ ማድረጉን ከኢ/ር ታከለ ኡማ ሰምተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ የሚገኘው ኤም ኤም ዲ /MMD/ ህንፃ ባለቤት ዶክተር ከበደ ከቻራ እና ሲ/ር ንግስት በየነ ህንፃቸውን ለተከራዩት ቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሶስት ወር የህንፃ ኪራይ በግማሽ መቀነሳቸው ተነግሮናል። በገንዘብ ሲተመን ወደ 1,000,000 ብር ይደርሳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

የአሶሼትድ ፕሬስ /Associated Press/ ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ሀገራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በዛሬው ዕለት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ40,000 ብር እገዛ ማድረጉን ከኢ/ር ታከለ ኡማ ሰምተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነጃሺ መስጂድ!

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ቀበሌ 24 የሚገኘው ነጃሺ መስጂድ ምዕመናትን በማስተባበር በአካባቢው ለሚገኙ 270 ቤተሰቦች የአስቤዛ ድጋፍ አድርጓል።

የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ከጥንቃቄ አዃያ የመስጂዱን ወጣቶች በማስተባበር ድጋፉን በየቤቱ ያደረሰ ሲሆን ከድጋፉ ጎን ለጎን የተለያዩ ማስተማሪያ መንገዶችን በመጠቀም ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ጥንቃቄ አጠናክሮ እንዲቀጥል አስታውሰዋል።

የአስቤዛ ድጋፉ የመጀመሪያ ዙር ሲሆን በቀጣይም ድጋፉ የሚቀጥል ሲሆን ድጋፉ በውስጡ ዘይት ፣ ዱቄት ፣ መኮሮኒ እና የንፅህና መጠበቂያዎችን አካቷል።

ምንጭ፦ ነጃሺ መስጂድ እና መድረሳ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ አሳሳ ከተማ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች በዛሬው ዕለት በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሲሰሩ መዋላቸውን ገልፀውልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

በጋምቤላ ክልል በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ዲያቆን አልሸሽም ተካ የተባሉ ባለሀብት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለሚደረው ጥረት የሚያግዝ 15 የሙቀት መለክያ መሳርያዎችን ድጋፍ አድርገዋል።

(ከጋምቤላ ፕረስ ሴክረታሪያት ጽህፈት ቤት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ከቴፒ ከተማ ቲክቫህ አባላት!

የኮሮና ቫይረስ እንዳይሰራጭ እና የኢትዮጵያን ህዝብ ለከፋ ሁኔታ እንዳያጋልጥ ትግል እየተደረገ በሚገኝበት በዚህ ወቅት የፀጥታው ችግር አሳሳቢ ሆኖብናል ሲሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቴፒ ከተማ አባላት መልእክታቸውን አድርሰዋል።

ለዓመታት ያልተፈታው ችግር ዛሬም የህዝቡን ደህንነት አደጋ ላይ መጣሉን ቀጥሏል፤ የህዝብ ደህንነት ያሳስበኛል የሚል አካል ካለ መፍትሄ ይፈልግ ሲሉ ጠይቀዋል። ከሰሞኑን በከተማው የሰው ህይወት መጥፋቱን የቤተሰባችን አባላት ሪፖርት አድርገዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

ከፌም ኢምፔክስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ሴፍ ወይ ሱፐር መርኬት) የተላከ መልዕክት ፦

- በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ለገዳዲ ለገጣፎ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በዝቅትኛ ኑሮ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ለህፃናት ለአዋቂ የሚሆን የታሽጉ ምግቦች እና የፅዳት እቃ ፣ እገዛ አድርጓል። ዋጋው 105,000.00 ብር በላይ እንደሚሆንም ተነግሮናል።

- በተጨማሪም የድርቅ ጭነት ለማጓጓዝ የሚያገለግል ቫን ተሽከርካሪ ጥሪ በተደረገለት ወቅት የነዳጅ ወጪን በመሸፈን አገልግሎቶች እንዲሰጥ ተውስኗል። የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተርም ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሴንትራል ሆቴልና ከሴንትራል ግራንድ ሞል ሀዋሳ ባለቤት ወ/ሮ አማረች ዘለቅ የተላከ መልዕክት ፦

- መጪው የትንሳኤ በአልን ምክንያት በማድረግ በሴንትራል ሆቴልና በሃዋሳ ግራንድ ሞል በኩል አቅም ለሌላቸው ወገኖች የበአል ስጦታ ተበርክቷል።

- ድጋፉ ለበአል ፍጆታ የሚውሉ ዘይት ፣ ዱቄት፣ እንቁላል ፣ ፓስታ፣ እሩዝ እና ሳሙናዎችን ነው ለአካባቢው ነዋሪዎችና በድርጅቱ ለሚገኙ ሰራተኞች ነው የተሰጠው።

ይህ የተደረገው ድጋፍ በገንዘብ ከ150 ሺህ ብር በላይ እንደሚተመን ደግሞ የሴንትራል ሆቴል ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍትህ ወልደሰንበት ነግረውናል።

ከዚህ በፊት ወ/ሮ አማረች የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ገበያ ስለማይኖራቸው ኪራይ መክፈል ይቸግራቸዋል በማለት 1 ሚሊየን ብር የሚያገኙበትን የሁለት ወር ኪራይን ለሃዋሳ ሴንትራል ግራንድ ሞል ተከራዮቻቸው ነፃ ማድረጋቸው አይዘነጋም።

በተጨማሪ ሰራተኞቻቸው ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እስኪገታ ድረስ 'ያለምንም እቀነሳለሁ ስጋት' ስራቸውን ከነሙሉ ደሞዛቸው ይዘው እንደሚቀጥሉ መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia