TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፦

በኃይል ማስተላለፊያ ስርዓታችን ላይ በገጠመን ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ ኃይል ተቋርጧል።

በአሁኑ ወቅት ችግሩ የተከሰተው በዚህ ምክንያት ነው ለማለት አስቸጋሪ ቢሆንም ከጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

የጣና በለስና የፊንጫ ኅይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ከሲስተም ጋር ማገናኘት በመቻሉ የአዲስ አበባን የተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።

በቀጣይም በየደረጃው ሁሉንም የሀገሪቱ ክፍሎች ኃይል እንዲያገኙ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው።

በዚህ አጋጣሚ ለተፈጠረው ችግር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይቅርታ ይጠይቃል።

የካቲት 20/2012 ዓ/ም

#EthiopianElectricPower
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

"ከጥቂት ሳምንታት በኃላ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ክትባት ይኖረናል!" - የእስራኤል ሳይንቲስቶች

የእስራኤል ሳይንቲስቶች የኮሮና ቫይረስ [#COVID19] ክትባትን ለማዘጋጀት መቃረባቸው እየተነገረ ይገኛል። ጥረቱ በታሰበው ልክ የሚሄድ ከሆነ ክትባቱን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ማዘጋጀት እና ከ3 ወራት በኃላ ለገበያ ማቅረብ እንደሚቻል የእስራኤል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ኦፊር አኩኒስ ለእየሩሳሌም ፖስት ተናግረዋል።

#እየሩሳሌምፖስት #አልዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የብዙዎችን ልብ የሰበረው የካሌብ ህልፈት...

እውቁ ዩትዩበር፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወጣቶችን ለውጥ በማነሳሳት የሚታወቀው፣ ስራ ፈጣሪው፤ እንግሊዛዊ - ኢትዮጵያዊው ካሌብ ሜኪንስ በደረሰበት የመኪና አደጋ ጉዳት ደርሶበት ባለፉት ቀናት ህይወቱን ለማትረፍ ብዙ ጥረት ቢደረግም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CalebMeakins

ካሌብ ሜኪንስ አባቱ እንግሊዛዊ እናቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነበሩ፤ እስከ ስምንት አመቱ ድርስም እዚሁ ነው ያደገው። ወደ ቤተሰቦቹ ሃገር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የተለያዩ የስራ ፈጠራ ሀሳቦችን በማቅረብ ወጣቱን ለለውጥ ሲያነሳሳ ቆይቷል።

በጣም የታወቀበት የታክሲ ስራን ከረዳቶች ጋር በመሆን እየሰራ በዩቲዩብ ቪድዮ በመልቀቅ ማህበረሰቡን ግንዛቤ ማስጨበጥ አንዱ ነበር፣ እንዲሁም ካሌብ በስራ ፈጠራ እና በአመራር ብቃቱ ይታወቅ ነበር። ሆኖም በደረሰበት የመኪና አደጋ ጉዳት ደርሶበት ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ዛሬ ህይወቱ አልፏል።

ካሌብ አባቱንም በህይወት ያጣው ገና በልጅነቱ ነበር። በኮሞሮስ በወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፍረው ወደ ለንደን ሲያቀኑ የነበሩት አባቱ ህይወታቸው ያለፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደረሰበት ጠለፋ ምክንያት በኮሞሮስ በተከሰከሰበት ወቅት ነበር።

#BENEYAM

📹9 MB [WiFi]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ከግልገል ጊቤ 3 ከሚቀርበው የኃይል አቅርቦት መስመር ጋር የተያያዘ እንደሆነ የተገመተው የኃይል መቋረጥ መዲናዋን ጨምሮ መላው የሀገሪቱ ከተሞች ለሰዓታት ጨለማ ውስጥ ከቶ ነበር።

የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ የነበረባቸው የአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በአንዳንድ የክልል ከተሞች የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል እየተመለሰ እንደሆነ ሪፖርት እያደረጉ ነው።

አሁንም የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ያልተመለሰባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች እና በርካታ የክልል ከተሞች መኖራቸውን ማረጋገጥ ችለናል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም ችግሩን ለመፍታት እየሰራ እንደሆነ ሰምተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19 #ETHIOPIA

የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የቻይና መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን ገለጹ።

አምባሳደሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ከቻይና ጋር በዚህ ወሳኝ ሰዓት አብሮ መሆኑን አንስተው ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል። አምባሳደር ታን ጂያን በሰጡት መግለጫ፣ ቫይረሱ በቻይና ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን የኢትዮጵያ መንግሥት ከጎናችን ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድና ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ለቻይና መንግሥት ያስተላለፉትን መልዕክትም ጠቅሰዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና በረራ አለማቋረጡን ጠቁመው ኢትዮጵያ የቻይና ቁርጠኛ ወዳጅ መሆኗን ያሳያል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲም ከሚመለከተው ተቋም ጋር በመተባበር ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ በጥንቃቄ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ቻይናውያን ወደ ኢትዮጵያ አላስፈላጊ ጉዞ እንዲያቆሙና፣ ከመጡም 14 ቀናት ለብቻቸው እንዲቀመጡ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በቻይና ኤምባሲ የሚገኙት ሰራተኞችም ቫይረሱን መከላከል በሚቻልበት ምቹ ሁኔታ ዙሪያ በአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠር ማዕከል ሥልጠና እየተሰጣቸው መሆኑንም ተናግረዋል። በቻይና ሁቤይ ግዛት የሚገኙ 311 ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎችም እንደ ማንኛውም ቻይናውያን ጥበቃና ከለላ እየተደረገላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#COVID19 #ETHIOPIA የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፦ "ይህ መረጃ እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በ አገራችን የተረገገጠ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የለም ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረዉ በመለያ ማእከል ክትትል ተደርጎላቸዉ ከቫረሱ ነጻመሆናቸዉ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አንድ ተጠርጣሪ በማለያ ማእከል ተለይቶ ክትትል እየተደረገለት ሲሆን ናሙና…
#COVID19 #ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፦

"ከዚህ ቀደም ብሎ አንድ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ያሳየ በማለያ ማእከል ተለይቶ ክትትል እየተደረገለት መሆኑን እና ናሙናው ተወስዶ ላብራቶሪ እተሰራ መሆኑን የገለጽን መሆኑ ይታወቃል፣ በመሆኑም አሁን በደረሰን ውጤት መሰረት ግለሰቡ ከበሽታው ነጻ (ኔጋቲቭ) መሆኑ በላቦራቶሪ እንደተረጋገጠ መግለጽ እንወዳለን፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ጤናሚኒስቴር

አንድ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ያሳየ ግለሰብ በመለያ ማዕከል ተለይቶ ክትትል እየተደረገለት መሆኑን እና ናሙናው ተወስዶ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዪት ላብራቶሪ እተሰራ መሆኑን ገልጸን ነበር። ሆኖም በተደረገለት ምርመራ ግለሰቡ ከበሽታው ነጻ መሆኑ በላቦራቶሪ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ኮሮና ቫይረስ ገብቷል?

እስካሁን ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] አለባቸው ተብለው የተረጋገጡ የአፍሪካ ሀገራት ግብጽ፣ አልጀሪያ እና ናይጀሪያ ናቸው። በአሁን ሰዓት በደቡብ አፍሪካ የተረጋገጠ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ የለም። ነገር ግን በጃፓን ክሩዝ መርከብ ላይ ከሚሰሩ 12 የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ሁለቱ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እስካሁን ደቡብ አፍሪካ ከቫይረሱ ነፃ ናት!

በደቡብ አፍሪካ ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ጋር በተገናኘ የ133 ሰዎች ናሙና በላብራቶሪ ተመርምሮ ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ተገኝተዋል።

#ደቡብአፍሪካቲክቫህቤተሰቦች
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#US #ETHIOPIA #SUDAN #EGYPT

በ3ቱ ሀገራት መካከል በሚደረገው ድርድር በታዛቢነት የተጋበዘችው ሀገረ አሜሪካ ስምምነት ላይ ሳትደርሱ የግድቡን የሙከራ ስራዎች መስራት ሆነ ውሀ መሙላት አትችሉም ብላን አርፋዋለች።

https://home.treasury.gov/index.php/news/secretary-statements-remarks/statement-by-the-secretary-of-the-treasury-on-the-grand-ethiopian-renaissance-dam

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመብራት ምሰሶ ወድቆ 6 ግመሎች ገደለ...

በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ የመብራት ምሰሶ ወድቆ ስድስት ግመሎች መግደሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው በቦራ ወረዳ ቱጂ ደካ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ለግጦሽ በተሰማሩ ግመሎች ላይ መሆኑን ገልጠዋል።

ለግጦሽ የተሰማሩ ግመሎች ምሶሶ ወድቆ በተንጠንጠለው የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ ገመድ ሾልከው ለማለፍ ሲሞክሩ ነው ብለዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

የአዋሽ ወንዝን ተከትሎ በውሃና የአርሶ አደሩ ማሳ ውስጥ የቆሙ የመብራት ምሰሶዎች ከጊዜ ቆይታ አንፃር አርጅተው እየወደቁ ነው። ምሰሶዎቹ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የከፋ አደጋ ሳያደርሱ የሚመለከተው አካል ክትትል በማድረግ በኮንክሪት የሚተኩበት ሁኔታዎች መፈጠር አለባቸው።

#ምስራቅ_ሸዋ_ዞን_ቦራ_ወረዳ #ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19 #ETHIOPIA #AMHARA_REGION

የኮሮና ቫይረስ ወደ አማራ ክልል መግባት የሚችልባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸውን በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያ አቶ አሞኘ በላይ ለአብመድ ተናገሩ፡፡ አማራ ክልል ሰፊ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ያሉበት በመሆኑ በርካታ የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ወደ ክልሉ ይገባሉ፡፡

ምንም እንኳን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የቫይረሱ ምርመራ ቢደረግም በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ላልይበላ እና ኮምቦልቻ የአውሮፕላን ማረፊያዎች በኩል የመግባት ዕድል ሊኖረው እንደሚችል በኢንስቲቲዩቱ ታሳቢ ተደርጓል፡፡

የተለያዩ የውጪ ሀገር ዜጎች የሚሠሩባቸው ካምፖች ፣ ኢንዱስትሪዎች እና ክልሉን በሚያዋስነው የሱዳን ድንበር ያለው የምድር ትራንስፖርት ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] ወደ ክልሉ እንዲገባ ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ በስጋትነት ተለይተዋል፡፡

ይህንን ታሳቢ በማድረግ ኢንስቲቲዩቱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ባለሙያው አስታውቀዋል። በተለዩት ቦታዎች የቫይረሱን ምንነት እና ቢከሰት መከናወን ያለባቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለባለሙያዎች ሥልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝም አቶ አሞኘ አስታውቀዋል፡፡

#AMMA

[በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኤፍ ቢ ሲ የተናገሩት፦

የሀይል መቋረጡ ከጊቤ 2 የሀይል ማመንጫ ከሚነሳው የሀይል ማስተላለፊያ መስመር ጋር የተያያዘ ነው። ከጊቤ 2 የሀይል ማመንጫ የሚነሳው እና ወደ ሰበታ እና ወደ ሶኮሮ የሚሄደው 400 ኪሎ ቮልት ሀይል ተሸካሚ ከፍተኛ መስመር በአካባቢው በነበረ ንፋስ በቀላቀለ ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ችግር ገጥሞት ነበር።

በዚህ ምክንያት በዚህ መስመር የሚያልፈው ሀይል ከጊቤ 3 ተነስቶ ከወላይታ ሶዶ ወደ ገላን ወደሚገባው መስመር ሀይሉን ልኳል። በዚህ ወቅት ከጊቤ 3 የሚነሳው እና ብዙሃኑን የሀገሪቱን የሀይል ፍላጎት የሚያሟላው መስመር ይህ ሀይል ሲመጣበት ራሱን በራሱ አቋርጣል።

ሰዓቱ ከፍተኛ ሀይል ጥቅም ላይ የሚውልበት በመሆኑም ከቀሩት የሀይል ማመንጫዎች የሚገኘው ሀይል ፍላጎቱን ማሟላት እንዳልቻለ እና አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል አቅርቦቱ ተቋርጧል።

የችግሩ ምንጭ በመታወቁ እና ማስተካከያ በመደረጉም እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት ድረስ ሀይል ተቋርጦባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል አብዛኛዎቹ አገልግሎቱ ተመልሶላቸዋል። ችግሩ ሙሉ በሙሉ ቢቀረፍም የአዳንድ መስመሮችን ደህንነት የማረጋገጥ ስራ እየተከናወነ በመሆኑ በተወሰኑ አካባቢዎች አሁንም ሀይል እንዳልመጣ እና ደህንነት የማረጋገጡ ስራ እንደተጠናቀቀ አገልግሎቱን ያገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US #ETHIOPIA #SUDAN #EGYPT በ3ቱ ሀገራት መካከል በሚደረገው ድርድር በታዛቢነት የተጋበዘችው ሀገረ አሜሪካ ስምምነት ላይ ሳትደርሱ የግድቡን የሙከራ ስራዎች መስራት ሆነ ውሀ መሙላት አትችሉም ብላን አርፋዋለች። https://home.treasury.gov/index.php/news/secretary-statements-remarks/statement-by-the-secretary-of-the-treasury…
#GERD

ትናንት ለሊት የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር  ባወጣው መግለጫ ሶስቱ አገራት [ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ] ስምምነት እስኪፈራረሙ ድረስ ከህዳሴው ግድብ ድርድር ጋር በተያያዘ የአሜሪካ ተሳትፎ እንደሚቀጥል ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD

"የግድቡ ውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት ስምምነት መፈረም አለበት" - አሜሪካ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በውሃ የመሙላት እና የሙከራ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በአገራቱ መካከል ስምምነት መፈረም እንዳለበት አሜሪካ አርብ ለሊት ባወጣችው መግለጫ አመልክታለች።

የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው ቀደም ሲል የነበረውና ግንባታው በታችኛው የተፋሰሱ አገራት ላይ ጉልህ ጉዳት እንዳይደርስ በሚለው የመርህ ስምምነት መሰረት "ግድቡን በውሃ የመሙላትና ሥራውን የመሞከር ሂደት ስምምነት ሳይደረግ መከናወን የለበትም" ብሏል።

More https://telegra.ph/BBC-02-29

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን የማስፋፊያ ሕንጻ አስመርቋል።

23 ክፍሎች ያሉት የማስፋፊያ ሕንጻው ለስነ-አዕምሮ ድንገተኛ ሕክምና እንዲሁም ለእናቶችና ሕጻናት ጤና አገልግሎት እንደሚውል ተገልጿል።

የሕንጻው ግንባታ የተከናወነው ከሔኒከን ኢትዮጵያ የቢራ አክሲዮን ማኅበር በተገኘ የ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰቦች፦

በአይነቱ ልዩ የሆነ እና በቀጣይ ወደ ባንክ የማደግ ራእይ ያለው 'ምድረ ግእዝ ማክሮ ፋይናንስ' ዛሬ 21/06/12 በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል የክልሉ ም/ርእሰ መስተዳደርና የከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አብርሃም ተከስተና ባለአክስዮኖች በተገኙበት የምስረታ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

#HailuMehari
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam

ትላንት የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው ማስጠነቂያ አዘል በሚመስለው መግለጫ 'የግድቡ ስምምነት ሳይፈረም ኢትዮጵያ የውሀ ሙሌትና ሙከራ ማድረግ የለባትም' ማለቷ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱን በማህበራዊ ሚዲያ ቅኝታችን እየተመለከትን ነው።

በርካታ ኢትዮጵያውያ የአሜሪካ መግለጫ እንዳስቆጣቸው በመግለፅ ድሃው ህዝብ ከሌለው ላይ ቀንሶ እያሳራ ከሚገኘው ግድብ ላይ አሜሪካም ሆነች ሌሎች ሀገራት እጃቸውን እንዲሰበስቡ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ነው።

መልዕክት መቀበያ @tikvahethiopiaBot

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

አሜሪካ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ትዕዛዝ የሚመስል መግለጫ ማውጣቷን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተደራዳሪ ቡድን አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ።

አሜሪካ ኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ከስምምነት ሳይደርሱ የህዳሴው ግድብ ውሃ መሙላት አይችልም የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወቃል።

ኢትዮጵያም አሜሪካ ባስተላለፈቸው ውሳኔ ዙሪያ እንደ አገር አቋም ለመያዝ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ብሔራዊ ተደራዳሪ ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጡን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia