TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዙር30-ቅጽ2-ቁጥር 2.pdf
2.3 MB
ዙር30-ቅጽ2-ቁጥር 2
ዙር ሰላሳ!!
የካቲት ወር አስራ ሁለተኛ እትም!!
ዲጅታል መፅሔት!!
በሐገርኛ ቋንቋ
@AccessAddis
@AccessAddis
Forwarded from TIKVAH-SPORT
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ !

ቲኪቫህ ስፖርት በየወሩ ወደ እናንተ በሚያደርሰው የወሩ እጩዎች በዚህ ወር የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሰርዳን ዝቪጂኖቭ አሸናፊ መሆን ችለዋል ::

ሰርዳን ዚቪጂኖቭ ማግኘት ከሚገባቸው 21 ነጥቦች 14 ነጥቦች ሲያገኙ ካደረጉት ሰባት ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ሽንፈትን አስተናግደዋል ::

@tikvahethsport @kidusyoftahe @GoitomH
Forwarded from TIKVAH-SPORT
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ወጣት ተጫዋች !

ቲኪቫህ ስፖርት በየወሩ ወደ እናንተ በሚያደርሰው የወሩ እጩዎች በዚህ ወር የወልቂጤ ከተማው ጫላ ተሺታ አሸናፊ መሆን ችለዋል ::

ጫላ ተሺታ ባለፉት ጨዋታዎች ላይ በሶስት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን ማድረግ ሲችል የቲኪቫህ ቤተሰቦች አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል ::

@tikvahethsport @kidusyoftahe @GoitomH
#Election2012

የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ /ትዴፓ/ በመጪው አገራዊ ምርጫ በትግራይ ክልል በዴሞከራሲያዊ መንገድ መወዳደር የሚያስችል እንቅስቃሴ ለማድረግ ተቸግሬያለሁ አለ፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ እንደገለፁት ፓርቲያቸው በመጪው አገራዊ ምርጫ በክልል ደረጃ ተወዳድሮ ለማሸነፍ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። ነገር ግን በአካባቢው ከሚንቀሳቀሰው ህወሃት የተለያዩ ችግሮች እየገጠማቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ፓርቲው በክልሉ በመቀሌ ብቻ ቅርንጫፍ መክፈቱን የገለጹት ዶክተር አረጋዊ ፤ በአብይአዲ፣ በሽሬና በአድዋ ቅርንጫፎች ለመክፈት ሙከራ ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

ይሁንና በትግራይ ክልል ነጻና ፍትሃዊ የምርጫ እንቅስቃሴ ለማድረግ መቸገሩንና አባላቱም ለእስራት፣ ለድብደባና ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ጠቁመዋል። “ይህ ባለበትና ምርጫ ቦርድ ባለሙያዎች ባልመደበበት ሁኔታ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ምርጫ ለማከናወን ማቀዱ ተገቢ አይደለም” ነው ያሉት።

ችግሩን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ለምርጫ ቦርድና ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በደብዳቤ በማሳወቅ ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑንም ዶክተር አረጋዊ አስረድተዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል!

ጅማ ዩኒቨርስቲ በቅድመና በድህረ ምረቃ ዘርፎች ያስተማራቸውን 3 ሺህ 139 ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ነው። ከእነዚህ ምሩቃን ውስጥም 237 የህክምና ዶክተሮች፣ 27 የጥርስ ህክምና ዶክተሮች 8ቱ ደግሞ የሶስተኛ ድግሪ ተመራቂዎች ናቸው፡፡ ከተመራቂዎች መካከልም 13ቱ ከሶማሊላንድና ከሩዋንዳ የመጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

#EPA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ለኮሮና ቫይረስ- COVID-19 የቅድመ መከላከልና ጥንቃቄ ስራዎች የሚያግዙ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶች ከአለም ጤና ድርጅት በድጋፍ ማግኘቱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስ- COVID-19 የቅድመ መከላከልና ጥንቃቄ እንዲሁም የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ስራዎች የሚያግዙ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶች ከአለም ጤና ድርጅት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ግብዓቶቹም በተለይ ለጤና ባለሙያዎች የስራ ላይ የደህንነት መጠበቂያ ሁነው ያገልግላሉ ተብሏል፡፡ ግብዓቶቹም አጠቃላይ ወጪ ከ 43 ሺህ ዶላር በላይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በኮሮና ቫይረስ - COVID-19 ዙርያ የቅድመ መከላከልና ጥንቃቄ እንዲሁም የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ስራዎች እየተሰራ እንደሆነና አስካሁንም በኮሮና ቫይረስ #COVID19 ምልክቱ ታይቶበት በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኝ አንድም ተጠርጣሪ የለም፡፡

ምንጭ፦ ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን ለኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኢንፌክሽን የሚያጋልጠንን አጋጣሚ እንቀንስ ዘንድ ጤና ሚኒስቴር እጃችንን በሳሙና እና በንፁህ ውሃ በሚገባ እንድንታጠብ መልዕክቱን አስተላልፎልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEW

በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ አዲስ ለተቀጠራችሁ በሙሉ፦

የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የቅድመ ስራ ስልጠና ስለሚሰጥ በተጠቀሰው የማሰልጠኛ አድራሻዎች ላይ ሰኞ ከጥዋቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ተገኝታችሁ ስልጠናውን በጥብቅ ድሲፕሊን እንድትከታተሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ አሳውቋል።

የማሰልጠኛ አድራሻዎች : https://telegra.ph/ETH-02-22

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEW

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ 0 አመት አዲስ ቅጥር የ2010 እና 2011 ዓ.ም በተለያዩ የመንግስትና የግል ዩንቨርሲቲ በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቃችሁ የተወዳደራችሁ እና ፈተና ከወሰዳችሁ ውስጥ በኮድ አፃፃፍ ስህተት እና በሌሎችም ቅሬታ ያቀረቡና ያላቀረቡትንም ጨምሮ ለየካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ምላሽ እንደምንሰጥ በማስታወቂያ መለጠፋችን ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. በኮድ (ID) ስህተት ምክንያት ውጤታቸው የተሰረዘ ቅሬታ ያቀረቡም ሆነ ያላቀረቡ በሙሉ የማጣራት ስራ የተሰራ በመሆኑ ፤

2. ከማለፊያ ነጥብ በላይ የሆኑ waiting በተጠባባቂ የሚመደቡ የሚል የሚያሳይ መሆኑ፤

3. ከማለፊያ ነጥብ በታች የሆኑ Failed የሚል የሚያሳይ መሆኑ፤

More https://telegra.ph/ETH-02-22-2

[የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

ፕ/ሩን በሚመለከት የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው!

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት 'ህወሓት ወንጀል ፈጥሮላቸው የፍርድ ቤት ክስ እና ማዘዣ ወጣባቸው' በሚል በፌስቡክ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጀ ሀሰተኛ ነው። መረጀው የፈጠራ ወሬ እንደሆንም ሰምተናል። ፕሮፌሰር ክንደያም መረጃውን 'ውሸት' ሲሉ ገልፀውታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የድጋፍ ሰልፎች ዛሬም ቀጥለዋል...

ዛሬም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን የለውጥ አመራር የሚደግፉ ሰልፎች እየተካሄዱ እንደሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። ዛሬ የድጋፍ ሰልፍ እየተደረገ ከሚገኝባቸው ከተሞች መካከል የቡሌ ሆራ ከተማ አንደኛዋ ስትሆን በሰልፉ ላይ የተሳተፉ አካላት በጥላቻ እና በስድብ ሀገር መገንባት እንደማይቻል መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል፦

ዱከም በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ስራ የሚደግፍ ሰላማዊ ስልፍ እያስተናገደች ነው። ሰልፈኞቹ “በሀገሪቱ እየተከናወነ ያለውን የለውጥ ስራ እንደግፋለን”፣ “ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አመራር ጎን ነን”  የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ነው የድጋፍ ሰልፉን በማካሄድ ላይ የሚገኙት። በከተማዋ እና በዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎችም በሰልፉ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው ተብሏል።

#TikvahFamily #FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የምዕራብ ኦሮሚያ የፀጥታ ሁኔታ...

የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ከተሰማራ በኋላ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው መባሉን ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ አጥብቀው ተቃውመዋል።

ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል፦

"ይህ ስህተት ነው በተጨባጭ ህዝቡ እያለው የለው ሽፍታን አሰወግዱልን ነው እንጂ መከላከያ ይህን በደለን፣ እንዲህ አደረገን የሚል አንዳችም ነገር የለም። የመንግስት ወታደር ህዝብ ላይ ጉዳት አድርሶ ከሆነ ግን መንግስት ይጠየቃል። እኔም እንደኃላፊነቴ እጠየቃለሁ። እውነት ለመናገር እኔ ያደራጀሁትና እኔ የምመራው ወታደር ህዝብ አይነካም። በደል ተፈፅሞ ከሆነ እኔም በግሌ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቃለሁ፤ እክሳለሁም!"

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ከተንቀሳቀሰ ከአንድ አመት በላይ ሆኖታል። አሁን እያካሄደ ያለው ኦፕሬሽን ከከዚህ ቀደሙ የተለየ ነው?

"ይህ ይለያል፤ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ከዚህ በፊት የነበረው ልመናም ጭምር ነበር። ያ ሲሆን ደግሞ ይባስ መጠናከር ጀመሩ፤ ህዝቡ ላይ የሚደርሰው በደል ይልቁንም ተጠናክሮ ቀጠለ። ህዝቡን ያስፈራራሉ፣ ህዝብ ይዘርፋሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አፍነው 70 እና 60 ኪሎ ሜትር ይዘው ሄደው ለሁለት ሳምንት ደብድበው ይለቃሉ። በዚህ መሰል ዘግናኝ ፀረ ዴሞክራሲ ተግባር የሚታወቀው 'አልሸባብ' ነበር አልሸባብ እራሱ አሁን ላይ እንዲህ ያለ ተግባር አይፈፅምም። ስለዚህ ይህ ሊድን የማይችል የተበላሸ አእምሮ ያለው ኃይል ነው ተብሎ ስለታመነበት መንግስት ከሰሞኑን ጨከን ብሎ ጠንከር ያለ እርምጃ እየወሰደ ነው። እስኪወገዱ ድረስ እርምጃው ይቀጥላል። የደገጣ ውጊያ ስነ ምግባር እንኳን የላቸውም!"

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምዕራብ ኦሮሚያ በኮማንድ ፖስት ስር መተዳደር ከጀመረ በኃላ ሰዎች ይታሰራሉ፣ ይለቀቃሉ እንደገና እንደሚታሰሩ ይነገራል በጉዳዩ ላይ ምክትል ኤታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦

ይህ ሀሰት ነው! የስነ ልቦና ጦርነት የሚባል ነገር አለ። አንድ ወታደር ሳይገድሉ 80 ወታደር ገደልን ይላሉ፤ መልሰው ደግሞ እንዲህ በሚባል ቀበሌ ውስጥ ወታደር ገብቶ ሰው ገደለ ብለው ሀሰት ይነዛሉ፤ ገንዘብ እያዋጡ የሚልኩላቸው ደጋፊዎቻቸውን ለማስደሰት በማሰብ የላገኙትን ድል እንዳገኙ አድርገው ያወራሉ።

ይህ ደግሞ የደፈጣ ተዋጊ ባህሪ ነው። አንድም ቀን ከእኛ ጋር ፊት ለፊት ተዋግተው አያውቁም። ሁሌም ሲሸሹ ነው የሚመቱት። እየሸሹ ነው የሚያዙት። ከእኛ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው የመዋጋት አቅምም የላቸውም። ስለዚህ በእነሱ በኩል የሚመጣው ሁሉ እውነት ነው ብሎ መቀበል ስህተት ነው።

#BBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በምዕራብ በኩል ቀድሞ ኦነግ ስር ከነበሩት ታጣቂዎች ውጪ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ሌላ ኃይል አለ ተብለው ከBBC የተጠየቁት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦

የለም! ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሄዷል። የቀሩት ደግሞ አመራሮቹ ናቸው። እነዚህ የቀሩት አመራሮች ደግሞ ታዳጊዎችን እየመለመሉ ይልኩ ነበር። እጅ የሰጡ ተዋጊዎች ትምህርት ተሠጥቷቸው ተመልሰዋል።

አሁን የቀሩት ስፖንሰር ያላቸው ህይወታቸውን በዚህ መልኩ ለመምራት ፍላጎት ያላቸው ብቻ ናቸው የቀሩት። እነሱ ደግሞ ተደብቀው ነው የሚገኙት። የሀገር መከላከያ እየፈለጋቸው ይገኛል።

አሁን ላይ እየተመቱ ጥለው እየወጡ ነው። ባለፉት ሶስት ሳምንታት ሰላም ሆኗል። ለምለም በረሃ በሚባለው ቦታ እንጂ ሌላ አካባቢ ሰላም ነው።

ሁሉም አካባቢ እስኪፀዳ የሰላም ማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። መሮ እራሱ ጦሩ የማይደርስበት ቦታ ተደብቆ ነው የሚኖረው። ሰራዊት እሱ ያለበት ቦታ መድረሱን ሲሰማ ቦታ ይቀይራል። አንድም ቀን መሳሪያ ሳይተኩስ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ታዳጊዎችን ግን ከቀያቸው ሰብስቦ እያስጨረሰ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወሎ ዩኒቨርሲቲ 419 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል!

የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ከወሎ ዩኒቨርስቲ እና ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ጋር በሶስትዮሽ ስምነነት በድግሪ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 419 ተማሪዎች የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሴኔት አባላት ተጋባዥ የክልል እንግዶች በተገኙበት ተማሪዎቹን በአሁኑ ሰአት በኮሌጁ የማስመረቂያ አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኦሮሞ ፌደራሊት ኮንግረስ ከህዝብ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል። በትለንትናው እለት የፓርቲው አመራሮች በሰበታ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ውይይት አድርገዋል።

PHOTO : JAWAR MOHAMMED
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የመድረክ አባል የሆነው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ ከደጋፊዎቹና አባላቱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያየ ይገኛል። በህዝባዊ የውይይት መድረኩ ላይ የመድረክ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተገኝተዋል።

PHOTO : SMN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADDISABABA

‹‹የአማራ አብሮነት እሴቶች ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ሐሳብ የተለያዩ አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የአማራ ክልል የበይነ መንግሥታት ቢሮ ኃላፊ ደስታ ተስፋው (ዶክተር) ‹‹አማራ የመቻቻልና የመከባበር እሴት ያለው አቃፊ ሕዝብ ነው፤ እውነታው ይህ ቢሆንም በተዛቡ ትርክቶች ምክንያት እንደጨቋኝ መታየቱ ተገቢ አይደለም›› ብለዋል፡፡

ዶክተር ደስታ አብሮነት እና ጠንካራ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ለመፍጠር መሠራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በመድረኩም የአማራ የአብሮነት እሴቶችና ተሞክሮዎች፣ የተሳሳቱ ትርክቶች ያስከተሏቸው ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳቦች ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia