TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#attention

በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ስለሚገኙት ተማሪዎች እና በስጋት ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው ስለሄዱት የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ትኩረት እንዲሰጥ እንጠይቃለን!

በአንድ በኩል ዩኒቨርሲቲዎች በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታችሁ ተመለሱ ካልሆነ ካምፓስ እስከመዝጋት እንደርሳለን እያሉ ማስታወቂያ ሲለጥፉ በሌላ በኩል ያልታወቁ አካላት ጥያቄያችን ምላሽ አላገኘም ክፍል አካባቢ ድርሽ እንዳትሉ፤ ብትሉ ግን ለሚደርስባቹ ጉዳት እራሳቹ ነው የምትጠየቁት የሚሉ ማስፈራሪያዎችን ይለጥፋሉ።

ነገ ተምረን የቤተሰባችን ህይወት እንቀይራለን፣ ለህዝብ እንሰራለን ብለው የሚያስቡ ምስኪን ተማሪዎች ምን ያድርጉ? ትላንት ከትላንት በስቲያ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የሰማችሁት ነው። በያዝነው ሳምንት የተማሪ ህይወት እንደጠፋም ይታወቃል። እከሌ ከዚህ አካባቢ ስለመጣህ ውጣ የሚል መልእክትም ያለ ከልካይ ሲሰራጩ እየተመለከትን ነው።

የተለያዩ ተጠርጣሪዎች እየተያዙ መሆኑ መንግስት እየገለፀ ይገኛል፤ አስተማማኝ ዘላቂ መፍትሄው ምን እንደሆነ ግን እየተነገረ አይደለም። ተማሪዎች በአግባቡ ሳይማሩ ሴሚስተሩ እየተገባደደ ነው። የመንግስት ስራ ምንድነው? ዘላቂ፣ አስተማማኝ፣ መፍትሄ የለውም? ለተማሪዎች ጥያቄ መልስ የለም? ነገም እንዲሁ ነው የሚቀጥለው? የሚከለተከታቸው አካላት ከችግሩ ክብደት አንፃር ማድረግ የሚችሉት ይህን ብቻ ነው? ግለቸቦች፣ ሚዲያዎች ችግሩ እንዲፈታ እያደረጉ ያለው ጥረት ምን ያህል ነው?

ዉሎ አድሮ የሀገር ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል አደገኛ ክስተት ነውና ለተፈጠረው ችግር ልዩ ትኩረት ይሰጥ እያልን ደጋግመን እንጮሃለን!

የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮች በ @tikvahethmagazine ላይ መከታተል ትችላላችሁ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FederalPolice

ዩኒቨርስቲዎች "በፌደራል ፖሊስ" እንዲጠበቁ በተወሰነው መሰረት በፌደራል ጥበቃ ስር የማድረጉ ስራ እየተካሄደ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች የጠ/ሚንስተር ዶ/ር አብይ የሰላም ኖቤል ሽልማት በመቀበላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለፁ፡፡

"የኖብል ሰላም ሽልማቱ ዓለም ለኢትዮጵያ የሰጠው እውቅና ነው" በሚል መሪ ቃል የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች የፓናል ውይይት በማድረግ ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡ መርሃ ግብሩን የጋሞ ባይራ በሽማግሌዎች ምርቃት አስጀምረዋል፡፡

የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የአመራር ጥበብ እና ለሰላም ያበረከቱት አሰተዋፅኦ በአለም ውድ የሆነውን የኖቤል ሽልማት በማስገኘቱ የኢትዮጵያ ስም በአለም አደባባይ ከፍ እንዲል እና በወርቅ ቀለም እንዲፃፍ አስችሏታል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

‹‹የራስ ሀገር ዜጋ ትልቅ ለሆነ የክብር ሽልማት ሲበቃ ደስ የማይለው ሰው ቢኖር እጅግ በጣም ጥቂት ነው። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ደስ ብሎኛል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የነበረው ክብርና ዝና የሚያመጣውን ኃላፊነት መሸከም ከባድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጫዊ ሰላም ያደረጉትን ሀገር ውስጥ ያለውን ሰላም ከፍ በማድረግ፣ የህዝቦች ወድማማችነት እንዲጠናከር፣ ሰው በነፃነት ወጥቶ እንዲገባ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር ለማድረግ መስራት ይጠበቅባቸዋል። ከጎረቤት ሀገራትና ከሌላው አለምም ጋር መልካም ግንኙነት ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም አሁን በሀገር ውስጥ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አስተማማኝ የሆነ ዘላቂ ሰላም ያስፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማቱ ያሸከማቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ፈጣሪ ይርዳቸው።" - አቶ በቀለ ገርባ (የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ /ኦፌኮ/ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ዩኒቨርስቲዎች ከማንኛውም አይነት ሁከትና ግርግር የፀዱ ሊሆኑ ይገባል!

“ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት የተማረ የሰው ኃይል ያስፈልጋታል፡፡ ይሔንን የተማረ ኃይል ለማፍራት ደግሞ ዩኒቨርስቲዎች ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት ብቻ የሚከናወንባቸው፤ ከማንኛውም አይነት ሁከትና ግርግር የፀዱ ሊሆኑ ይገባል፡፡ የዩኒቨርሲቲዎችን ሰላም አስጠብቆ፣ የተማሪዎችን ደህንነት አስከብሮ ለመቀጠል የሁሉም አካላት የተግባር ቁርጠኝነት ያስፈልጋል።” ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር )

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ከትናንት በስቲያ በኖርዌይ ኦስሎ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን ለተቀበሉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በአሁኑ ሰዓት በብሔራዊ ቤተመንግስት አቀባበል እና የእራት ግብዣ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በተዘጋጀው በዚህ አቀባበል እና የእራት ግብዣ ላይ የፌደራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይ የቤት ስራ...

"ጠቅላይ ሚኒስትር በሽልማት ሥነሥርዓቱ ላይ በራስ መተማመንና በብቃት ያደረጉት ንግግር መልዕክት ስቦኝ ነው እንደተከታተሉት፤ ሀገርንም የሚያኮራ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሽልማቱ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሀገራት መካከል የነበረውን ችግር በመፍታታቸው ብቻ ሳይሆን፣ በሌሎችም አስተዋጽኦዎች ጭምር ነው። ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ባለሙያዎችና መሪዎች አንዱ መሆናቸውና ሽልማቱም በዘፈቀደ የተሰጠ እንዳልሆነ ግንዛቤ ሊያዝ ይገባል። ስሙ እንዲህ ገኖ ሲወጣ የማያስደስተው ኢትዮጵያዊ ሊኖር አይገባም። ይሁን እንጂ በሁለቱ ሀገራት ሰላም ቢሰፍንም በሰነድ የተደገፈ ስምምነት አለመኖሩ ወደፊት የቤት ሥራ እንደሚጠብቃቸው፣ ህዝብን ይዘው ሀገርን ማረጋጋት፣ ዜጎች በሀገራቸው እንዳይፈናቀሉ እነዚህንና ሌሎችንም ተግባራት ለማከናወን ሽልማቱ የሞራል ግንባታ ይሆናቸዋል።" - ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ (የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADAMA

ወጣቶች "የሰላም ኃይል" በመሆን በሀገሪቷ ውስጥ የሚስተዋሉ ግጭቶች ለማስቆም የድርሻቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ። “ወጣቶች ለሰላም ”በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ዛሬ አዳማ ከተማ ተጀምሯል።

የጉባኤው ምክትል ፀሐፊ አቶ ሂሉፍ ወልደስላሱ በኮንፍረንሱ መድረክ  እንዳሉት በቅርቡ በሀገሪቱ እየተበራከቱ በመጡት ግጭቶች ውስጥ ወጣቶች ተሳታፊና ተጎጂዎችም ናቸው። በተሳሳተ መረጃና በስሜት በመገፋት ግጭቱ የሚያስከትለውን ጉዳትና ቀውስ ካለማመዘን ወጣቶች የሚሳተፉበት እንደሆነ አመላክተዋል።

“ግጭቶች በባህሪያቸው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚጎዱ በመሆኑ ችግሮቹን ለማከምና ለማስወገድ ሁላችንም አንድ ሆነን መስራት አለብን“ ብለዋል። በተለይም ወጣቶች የሰላም ኃይል መሆናቸውን ተገንዝበው በሀገሪቱ ውስጥ የሚስተዋሉ ግጭቶች ለማስቆምና አለመግባባቶች ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

https://telegra.ph/ETH-12-12-2

(ENA)

@tikvahethiopia
#CNNHero2019 #FerweyniMebrhatu

«አሸናፊ መሆኔ የሚገርም ነገር ነዉ። ብቻ እንደ ግለሰብ በጣም ያኮራል። ትልቁ ግን ግን ሃገርን ማስጠራት ማለት ኩራት ነዉ። ለአፍሪቃም ኩራት ነዉ። ስለዚህ ይህን ጉዳይ ጉዳያችን ብለን ለዓለም ሕዝብ ፤ ለመጀመርያ ጊዜ ለመላዉ ዓለም ያሳወቅንበት ነዉ። ጥሩ ስራ ተሰርቶአል እስካሁን ድረስ ፤ ግን ብዙ ስራ እንደሚጠብቀን ነዉ የሚያሳየን። ሆኖም ግን ብቻችንን የምንሰራዉ ስራ ስላልሆነ፤ የዓለም ሕዝብ በሙሉ ድምፅ ሰጥቶ እዚህ ደረጃ ላይ አድርሶናል። ዘንድሮ ለዉድድር ከኔጋ የቀረቡት አስሩም ጀግኖች በጣም ጥሩ ስራን ሰርተዉ ነዉ የቀረቡት። ሆኖም ግን የኛ በለጥ ብሎ የታየበት ምክንያት፤ ሁሉንም ማኅበረሰብና ዜጋ የሚነካ ጉዳይ በመሆኑ ነዉ። የሴቶች ጉዳይ ደግሞ ለዘመናት የቆየ ጮክ ብለን የማንናገርለት ችግራችን ነበር። አሁን ግን እዚህ ላይ የደረስነዉ የችግሩን መፍቺያና የግንዛቢ ማስጨበጫ በመስራታችን ነዉ። እናም ለሃገር በተለይ ጥሩ ጥሩ መፍትሄ ነዉ የሚሆነዉ። እንደ አፍሪቃዉያንም በጣም ትልቅ ኩራት ነዉ። አንድ የ «CNN» ጀግና ከአፍሪቃ ሲገኝ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነዉ። ለ «CNN» ኖች ስለሸለሙኝ ምስጋናዬን ገልጬላቸዉ ነበር። ነገር ግን « ድምፅ የሰጠሽን ህዝብሽን አመስግኝ» ነዉ ያሉኝ መላዉ ኢትዮጵያዉያንን አመሰግናለሁ!» - ፍሬወይኒ መብርሃቱ

#DW

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UNESCO #ETHIOPIA

#መስቀል
#ፍቼ_ጫምባላላ
#የገዳ_ስርዓት
#ጥምቀት

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNESCO ) ያስመዘገበቻቸው የቅርሶች ብዛት 13 ደርሷል። እነዚህ ቅርሶች በሚዳሰሱና በማይዳሰሱ ቅርሶች ዘርፍ የተመዘገቡ ናቸው። ከእነዚህም መካከል የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ አክሱም፣ የኮንሶ ባህላዊ እርከን ይገኙበታል። በሚቀጥለው ዓመት በማይዳሰስ ቅርስነት ይመዘገባል ተብሎ የሚጠበቀው አሸንዳ አሸንድዬ ይገኝበታል።

(BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#IMF

የዓለም ገንዘብ ድርጅት « IMF» ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እና የምጣኔ ኃብት ችግር ላጋጠማት ኢትዮጵያ ወደ ሦስት ቢሊዮን የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር ሊሰጥ ነዉ። ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ የሚታተመዉ ጋዜጣ «ፋይናንሻል ታይምስ» እንደዘገበዉ የገንዘብ ድርጅቱ የሚሰጠዉ ብድር የኢትዮጵያ የክፍያ ተባለጥን « መዛባትን» ለመደገፍ እና ሃገሪቱ ምጣኔ ኃብትዋን ነፃ ለማድረግ ለምታደርገዉ ጥረት ቴክኒካል ድጋፍ የሚዉል ነዉ ተብሎአል። ብድሩን የዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት ቦርድ ሲያፀድቀዉ ለኢትዮጵያ መሠጠት እንደሚጀምርም «ፋይናንሻል ታይምስ»ጋዜጣ የጠቀሳቸዉ የኢትዮጵያ የገንዘብ ምኒስቲር ዲየታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ቶሊና አስታዉቀዋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰው እርቅንና ይቅርታን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አምኖ ሊቀበለውና ሊተገብረው ይገባል!

ሰው እርቅንና ይቅርታን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አምኖ ሊቀበለውና ሊተገብረው ይገባል፡፡ ምክንያቱም በምንም መመዘኛ እርቅና ይቅርታ ጥቅሙ ለራስ ነውና፡፡ እርቅና ይቅርታን የማይቀበልና የማይተገብር ሰው ሰላማዊ ኑሮን ገንዘቡ አያደርጋትም፡፡

ሰው መታረቅ ያለበት እርቅ የነፍስ መድኅን የአእምሮም ነፃነት ስለሆነ ነው። ጥላቻ ነፍስን ያቆስላል። አእምሮን ያቆሽሻል። ሰው መታረቅ ያለበት እርቅ የሰላምና የመረጋጋት ምንጭ ስለሆነ ነው።

ሰው ይቅር መባባል ያለበት የትኛውንም የጥፋትና የበደል ዓይነት ነው። ለጥፋትና በደል ደረጃ አውጥተን ይህንን ይቅር እንበል… ይህኛው ግን ይቅር ሊሉት ይከብዳል አንበል። በደል በደል ነው።

ይብዛም ይነስም በእርቅና ይቅርታ ካልተወገደ በሽታ ነውና ሰብዓዊ ጤንነትን ያዛባል። “ይቅርታ አይገባውም” የምንለው የበደል ዓይነትና መጠን ሊኖር አይገባም። እንደዚያ ካልን እኛም በየግላችን ይቅር ሊባል የማይገባ ጥፋት ሊኖርብንና ያለ ምህረት ልንኖር ነው ማለት ነው።

ሰው እርቅን መፈጸም ያለበት መተማመንን ለመመለስ እንጅ ለይስሙላ አይደለም። ሰው በደሉን አምኖ ይቅርታ ከጠየቀ በኋላ የቀድሞ ጥፋቱ ለነገ ሕይወቱ ተጠያቂ ሊያደርገው አይገባም። ያንንማ ጥፋት መሆኑን አምኖና ይቅርታ ጠይቆበት ጥሎት መጥቷል። ሰው መታረቅ ያለበት አንድነትን ለማምጣት ነው። እርቅና ይቅርታ የአንድነትና የመረጋጋት ምሥጢሮች ናቸው። የነፍስና የሥጋ አንድነት፣ የሐሳብና የተግባር መመሳሰል፣ የእርስ በርስ መግባባትና መተማመን… በጥል ይጠፋሉ – በእርቅና ይቅርታም ይመለሳሉ።

More👇
https://telegra.ph/Melegnaw-12-12

(Melegnaw)

#ሼር #share

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#update የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ የኖርዌይ ምክትል የፍትህ ሚኒስትር የሆኑትን ክርስቶፈር ሲቨርሴንን ዛሬ ታህሳስ 03 ቀን 2012 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ማጠናከር በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
#UPDATE

የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ወግ አጥባቂ ፓርቲ ከፍተኛ የበላይነት በማግኘት ሲያሸንፍ ተቀናቃኛቸው ሌበር ፓርቲ ደግሞ ቀደም ሲል አሸንፎባቸው በነበሩ ቦታዎች ላይ ሽንፈት ገጥሞታል። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ወግ አጥባቂዎች የብዙኀን መቀመጫን በማግኘት አሸነፉ። ገና ውጤታቸው ያልታወቁ የምርጫ አካባቢዎች እያሉ ነው 326 መቀመጫዎችን በማግኘት የሚያስፈልጋቸውን የበላይነት አግኝተዋል። ቢቢሲ አንደተነበየው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን 74 የሚሆኑ መቀመጫዎችን ጨምረው በጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበሩ ላይ ይቆያሉ።

(BBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
የሱዳን ፖሊስ በሀገሩ ለበርካታ ዓመት የኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ማሰሩ በሱዳን የኢትዮጵያ ቆንሲላ አስታውቋል!

በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ዜጎች በሱዳን ፖሊስ መታሰራቸዉን በካርቱም የኢትዮጵያ ቆንሲላ አስታወቀ።

በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሽፈራ ጃርሶ፥ ሰሞኑን በተደረገዉ አሰሳ የሀገሩ ጸጥታ ኃይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ማሰሩን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

(ቪኦኤ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize

100ኛው የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት አንደኛው ሜዳሊያና ዲፕሎማ በብሔራዊ ሙዚየም እንዲቀመጥ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ወስኗል። ሜዳሊያውና ዲፕሎማው በብሔራዊ ሙዚየም የሚቀመጠው እሁድ ታህሳስ 5 ከቀኑ 8፡30 ነው ተብሏል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
እንዳትጭበረበሩ ተጠንቀቁ!

"የሎተሪ እጣ ደርሶሻል!" በሚል የማጭበርበሪያ ስልት በተለያዩ የሞባይል ቁጥሮች ካርድ እንድትሞላ የተደረገችው ግለሰብ ከ9ሺብር በላይ በተጭበረበረ መንገድ ማጣቷ ተገለጸ፡፡

በቃሉ ወረዳ በ01 ደጋን ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ዚነት አደም ይመር በትላንትናው እለት ከኢትዮጲያ ሬድዩ የዝግጅት ክፍልነው የተደወለልሽ በሚል የሎተሪ እጣ እንደደረሳትና ለዚህም ዋናው ምክንያት ደግሞ በህገወጥ መንገድ ወደአረብ ሀገራት የሚሄዱ ወንድምና እህቶቻችንን ከእንግልት ለመታደግ ከምንተገብራቸው ተግባራት መካከል በሀገራቸው ሰርተው እንዲለወጡ ለማድረግ የሀብት ማሰባሰብ እንደሚሰሩ ገልጸውላት የእድሉ ተጠቃሚ እንደሆነች ነገሯት፡፡

ስለዚህ የአንች ስልክ ቁጥር ከኢትዮ ቴሌኮም አግኝተነው የዚህ እድል ተጠቃሚ ነሽ በማለት በሰቷት ቁጥር ካርድ እንዲትሞላ ያደርጓታል፡፡

በመሆኑም 55 ባለመቶና 20 ባለ አምሳ ብር ካርድ በይሙሉ 6015 ብር በጥቅሉ 9575ብር በሶስት የተለያዩ ስልክ ቁጥሮች አስገብታለች ፡ በአሁኑ ሰአትም ስልክ ቁጥሮቹ አገልግሎት እንደማይሰጡ ተረጋግጧል፡፡ በእንደዚህ አይነትና መሰል የማጭበርበሪያ ዘዴዎች እየተጠቀሙ ህዝብን ከሚያታልሉ አካላት ህረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅና እንዳይጭበረበር መልእክት ተላልፏል፡፡

(ቃሉ ወረዳ)

@tikvahethioia @tikvahethiopia
ሹፌር ለሃገር የጀርባ አጥንት ነው!

በየበረሃው ለቀናቶች እንዲህ እየተሰቃዩ በሚያጓጉዟቸው ነገሮች የኛ ምትጠቀመው ምንም ነገር ቢሆን የሹፌር አስተዋጽኦ የሌለበት ነገር የለም ሃገራችን ላይ። ክብር ዳገት፣ ቁልቁለት፣ በርሃ፣ ርሃብ፣ ጥማትን፣የቤተሰብ ናፍቆት፣ ሙቀት፣ብርዱን ብዙ ችግርና ፈተና ተቋቁመው ሁሉን ነገር ለሚያጓጉዙ አሽከርካሪዎች።

ለእናተ ክብር አለን!
ወጥታችሁ በሰላም ግቡ!

(ከሹፌሮች አንደበት የተገኘ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለቀይ መስቀል ህንፃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተጣለ!

ክቡር ኢንጅነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ለቀይ መስቀል ህንፃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ በብሄራዊ ሎተሪ እና በቀይ መስቀል አባላት መዋጮ የተገዙ ሶስት አምቡላንሶች ርክክብ ላይ ተገኝተው ለቀይ መስቀል አባላት፣ በጎ ፈቃደኞችና ቤተሰቦች መልዕክት አስተላልፈዋል። ይህ ቦታ በፒያሳ አካባቢ የሚገኝ እና G+11 የሆነ ሁለገብ ህንፃ ነው። ይህ ግንባታ በህዝቡ ትብብር እና ድጋፍ የሚሰራ ነው።

(ማንደፍሮ ነጋሽ)

PHOTO: BIRUK
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጀኔራል ኻሊፋ ሃፍታር የሚመራው ጦር የትሪፖሊ ከተማን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጦሩን እንደሚያዘምት አስታወቀ!

በተመድ ድጋፍ የሚደረግለት የሊቢያ መንግስት መቀመጫ የሆነችውን ትሪፖሊ በቁጥጥር ስር ለማዋል ጀኔራል ኻሊፋ ሃፍታር ትዕዛዝ ማስተላለፈቸው ተገልጸዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የሚደገፈውን መንግስት ጠራርጎ በማስወጣት ዋና ከተማዋ  ትሪፖሊን  ለመቆጣጠር ምንም ዓይነት የምናባክነው ግዜ የለንም ብሏል ጀነራል ካሊፋ ሃፍታር፡፡

ጀኔራል ኻሊፋ ሃፍታር  የሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊን ነጻ ለማውጣት የሚስችላቸውን ወሳኝ ውግያ ለማድረግ  ቅድመ ዝግጅት ማጠናቃቀቸውን ገልፀዋል፡፡

ጀኔራል ኻሊፋ ሃፍታር  ይህን ቢሉም በጀነራል ካሊፋ ሃፍታር ወታደሮች በኩል ተቃውሞ ሳይገጥሟቸው እንዳልቀረ ተገልጸዋል፡፡ እስከ አሁን  በአካባቢው  ምንም ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ መኖሩን የሚያሳይ መረጃ  አልተገኘም ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው።

(አልጀዚራ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia