TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ መንግስት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ የተጀመረውን የሶስትዮሽ ቴክኒካዊ ምክክር ለማስቀጠል ቁርጠኛ ነው!

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-05-4
#EGYPT

የግብፅ ፕረዜደንት ቢሮ በካርቱም ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ የውሀ ሚኒስትሮች ውይይት ካለ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ መግለጫ አውጥቶ ነበር፤ ባወጣው መግለጫም አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ዙርያ የማደራደር ሚና እንድትጫወት እንደሚፈልግ ገልጿል።

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethioia
"የግብጽ መንግስት ሶስተኛ ወገን በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ እያቀረበ ያለው ሃሳብ በሶስቱ አገራት የትብብር መድረክ የታየውን አበረታች ሂደት የሚያጣጥል እና ሶስቱም አገራት በመጋቢት 2007 ዓ.ም. የፈረሙትን የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት የሚጥስ ተግባር ነው፡፡ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት ኢትዮጵያ እና ሱዳን የማይቀበሉት እና ተገቢ ያልሆነ፤ በአገራቱ መካከል ያለውን ዘላቂ ትብብር የሚጎዳ፤ ለውይይት ያለውን በቂ እድል ወደጎን የሚያደርግ እና ገንቢ የሆነውን የውይይት መንፈስ የሚያደፈርስ ነው፡፡" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

The Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia commends the Water Affairs Ministers of Ethiopia, Sudan, and Egypt for convening in Khartoum to continue with the trilateral dialogue on the filling and operation of Great Ethiopian Renaissance Dam.

Ethiopia reiterates rights of all the 11 basin countries of the Nile to utilize Nile waters based on principles of equitable utilization & causing of no significant harm, which underlines the right of Ethiopia to develop its water resources to meet dev’t needs of its people.

The Government of Ethiopia will reinforce its effort to make the ongoing trilateral dialogue a success. It also expects a similar commitment from the two downstream countries, Egypt and Sudan. Ethiopia stands ready to resolve any differences and outstanding concerns by consultation among the three countries.

#PMOEthiopia

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EliasMelka

የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ የቀብር ስነ ስርዓት ሰኞ፣ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቹ በተገኙበት ይፈፀማል።

ዛሬ ከሰዓት በፋና ኤፍ ኤም 98.1 የከሀ እስከ ፐ ፕሮግራም ላይ በቀጥታ ቆይታ ያደረጉት ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ እና ሰርፀ ፍሬስብሃት እንዳስታወቁት፣ ከቀብር ስነ-ስርዓቱ አስቀድሞ ሙዚቃን በተማረበት ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት አሊያም በሚሊንየም አዳራሽ አሸኛኘት ይደረግለታል። ይህን የሚያስፈጽም ኮሚቴ ተዋቅሮም በስራ ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ ከሀ እስከ ፐ የሬድዮ ፕሮግራም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጎንደር ከተማ የተያዘው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ከሱዳን በመተማ በኩል አደርጎ የገባ እንደሆነ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽ ገልጿል። የተያዘው ህገ ወጥ መሳሪያ፦ •ከ2000 በላይ ሽጉጥና •ከ70 በላይ ክላሽ ጠበንጃ ነው። ህገወጥ ከጦር መሳሪያው በነዳጅ ውስጥ ተይዞ ሲጓዝ በነበረ ቦቲ መኪና ውስጥ ነው ጎንደር ከተማ ላይ በተደረገ ፍተሻ የተያዘው። @tsegabwolde @tikvahethiopia
ህገ ወጥ መሳሪያውን ጭኖ ከሱዳን በመተማ አድርጎ ጎንደር የገባው ተሽከርካሪ ይህ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ነው። የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-99935 ኢት የተሳቢው ሰሌዳ ቁጥር ደግሞ ኮድ 3-30056 ኢት የሆነው የነዳጅ ቦቴ ተሽከርካሪ ነው።

የፀጥታ አካላት ባደረጉት ፍተሻ -- 71 ክላሽንኮቭ እና ከ2ሺህ በላይ ሽጉጥ ተይዟል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቅድሚያ እንኳን ደስ አለን!

ሌሊት በተካሄደው የወንዶች ማራቶን ዉድድር ኢትዮጵያ በሌሊሳ ዲሳሳ ወርቅ እንዲሁም በሞስነት ገረመዉ ብር አግኝተናል።

🇪🇹🥇 ሌሊሳ ዴሲሳ - 2:10:40
🇪🇹🥈 ሞስነት ገረመዉ - 2:10:44

@tikvahethsport
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እኛም ኮራን በናተ...
እውነት ኮራን በናተ...


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Irreechaa2019

የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል!

PHOTO: FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከትምህርት ሚኒስቴር!

ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች በትምህርት ሚንስቴር "እኛ ለኛ "የበጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር ላይ በበጎ ፈቃደኝነት የሰራችሁት ሥራ ለብዙ ህጻናት የመማሪያ ቁሳቁሶችን እንድናደርስ አስችሎናል፡፡

ባለፈው የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ በ 30 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ አልባሳትን በአገራችን የተለያዩ ክፍሎች በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ትምህርታቸውን ላቋረጡ እና ባግባቡ ላልተከታተሉ ተማሪዎች ይውል ዘንድ በእርዳታ መልክ መለገሳቸው የሚታወስ ነው።

ስለሆነም እነዚህን አልባሳት ለክልሎች በአግባቡ ለይቶ ለማሰራጨት ይረዳን ዘንድ ከሰኞ መስከረም 26 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 11:00 ድረስ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ አልባሳትን የመለየት ስራ ለመስራት እቅድ ስለያዝን በዚህ ሁለተኛ ዙር ላይ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት የምትፈልጉ ሁሉ፡ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመመዝገብ በዚህ በጎ ስራ ላይ አሻራችሁን እንድታኖሩ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የመመዝገቢያ ስልክ ቁጥሮች

+251911485705
+251944260072

ከትምህርት ሚንስቴር "እኛ ለእኛ" የበጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሟቾች ቁጥር 100 ደርሷል፤ ኢንተርኔት በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞችም ተዘግቷል!

በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድና አከባቢዋ 6 ቀናትን ባስቆጠረው ታቀውሞ የሞቱት ሰዎች 100 ደርሰዋል። በኢራቅ የተለያዩ ክፍሎች የሀገሪቱን መንግስት በመቃውም ተቃውሞ ከተቀሳቀሰ ስድስት ቀናትን አስቆጥሯል። በዚህ ታቃውሞ በርከት ብለው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ወጣቶች ሲሆኑ  ሙስናን ፣ ስራ አጥነትን እና ዝቅተኛ መንግስት አገልግሎትን በመቃወም ነው ተቃውሟቸውን እያሰሙ የሚገኙት፡፡

#የኢንተርኔት_አገልግሎት በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ተቋርጧል። ዛሬ ጥዋት ለጥቂት ሰዓት ተከፍቶ የነበረ ቢሆንም የኢራቅ መንግስት ዳግም እንዲዘጋ አድርጎታል። ኢንተርኔት በተከፈተበት ወቅት የኢራቅ ዜጎች #VPN በመጠቀም በርካታ አሳዛኝና ለማየት የሚከብዱ ቪድዮዎችን ሲያጋሩ ነበር።

#IRAQ

•100 ሰዎች ሞተዋል
•4000 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል
•በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል
•ሙሉ በሙሉ በሚል ደረጃ ኢንተርኔት ተዘግቷል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
BAGHDAD

#DijlahTV -- ባልታወቁ ቡድኖች ጥቃት ደርሶበት ስርጭቱ ቆሟል!

#ArabicNrtTV -- ማንነታቸው እስካሁን ባልታወቁ ቡድኖች ጥቃት ደርሶበት ስርጭቱን ለማቆም ተገዷል። የጣቢያው ሰራተኞችም ታስረዋል።

#AlArabiyaTV -- ይህ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጭምብል ባጠለቁ ቡድኖች ጥቃት ተፈፅሞበታል። ፈፃሚዎቹ እነማን እንደሆኑ አልታወቀም።

#Baghdad
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል በሰላም ተጠናቋል!

በቢሾፍቱ የተከበረው የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ግርማ ሃይሉ እና የቢሾቱ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አለምፀሃይ ሽፈራው የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓላት በሰላም መከበርን አስመልክተው በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሃላፊው በመግለጫቸው ትናንት በአዲስ አበባ እና በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ የተከበረው የኢሬቻ በዓል እሴቱን በጠበቀ መልኩ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች በማሳተፍ በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅም አባ ገዳዎች፣ ፎሌዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት በቅንጅት መስራታቸውን የገለጹት ሃላፊው፥ለዚህ ውጤታማ ስራቸውም ምስጋና አቅርበዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethioia
#Irreechaa2019 ኢሬቻ ሆራ አርሰዲ! #ቢሾፍቱ

PHOTO: OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia