TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIVAH-ETH
AudioTrim
"ማንም ረግጦ የወጣ አባት የለም!"

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅ/ቤትን ለማቋቋም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ከነበሩ አካላት ጋር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውይይት ይካሄድ በነበረበት ወቅት ማንም ረግጦ የወጣ አባት እንዳልነበረ የስብከተ ወንጌልና የሃዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ አስታውቀዋል። ረግጠው ወጥተዋል ከተባሉት የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አንዱ የሆኑት ብፁህ አቡነ ዲዎስቆሮስም ለVOA በሰጡት ቃል የተባለው እውነት አይደለም በሲኖዶስ ስብሰባ ተረግጦ አይወጣም ብለዋል።

ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መካንን👇

"...ስምምነት ላይ ደርሰን ነበር፤ ነገር ግን የወጣው መግለጫ እኛ ያልጠበቅነውና ከተነጋገርነው ውጪ ነው። አሁንም በዚህ ጉዳይ ላይ ከአባቶች ጋር #እየተነጋገርን ስለሆነ ምንም ልል አልችልም።"

NB. ከላይ ያለው ፅሁፍ ከቀናት በፊት በፌስቡክ እና በቴሌግራም ሲሰራጭ የነበረ ነው!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ‹‹የዓቃቤ ህግ መተዳደሪያ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀ በመሆኑ ዓቃቤያን ህግ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን አይችሉም›› ሲሉ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ገለፁ። በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት የጨለማ እስር ቤቶች አለመኖራቸውንም አስታውቀዋል። ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ‹‹እኔ ለህግ ተገዢ ነኝ›› በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ የሚከበረውን የፍትህ ቀንን አስመልክተው ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናሩት፤ ከዚህ በፊት ዓቃቤ ህግ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን ይችል ነበር። ነገር ግን አሁን በሚኒስትሮች ምክር ቤት በፀደቀው አዲስ የዓቃቤ ህግ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ዓቃቤያን ህግ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን አይችሉም። ‹‹ፖሊስና ፍርድ ቤቶች ድሮውንም ቢሆን በፓርቲ አባልነት ውስጥ መግባት ስለማይችሉ ጉዳዩ አይመለከታቸውም›› ያሉት አቶ ብርሃኑ፣ ዓቃቤያን ህጉ ግን ምንም እንኳ ቀደም ሲል በየትኛውም ፓርቲ አባል የመሆን እድሉ ነበራቸው ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🤔ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ 1 ነጥብ 75 ግራም የጆሮ ጌጥ ወርቅ የዋጠው ዶሮ!

ለሽያጭ ገበያ የወጣው ዶሮ 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ወርቅ ይውጣል። ነገሩ የተከሰተው ጳጉሜ 03 ቀን 2011 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ነው፡፡ ባለቤትነቱ የአቶ ደነቀ ሸለመ የሆነው ዶሮ ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ ገዢዎችን በመጠባበቅ ላይ እንዳለ የወይዘሮ ሃጫልቱ በድሩን 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ላይ አነጣጥሮ ከጆሮዋ ላይ በጥሶ ይውጣል።

ነገሩ ከተከሰተ በኋላ የዶሮው ባለቤትና የወርቋ ባለቤት ሰጣ ገባ ውስጥ ይገባሉ፡፡ የወርቋ ባለቤት ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው ወዲያው ታርዶ ወርቃቸው እንዲሰጣቸው ቢሹም የዶሮው ባለቤት ደግሞ በጉዳዩ አልተስማሙም።

ነገሩ መክረሩን ያዩት ገቢያተኞች ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄድ በማድረግ በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኝ የወሊሶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ያመራሉ፡፡ ጉዳዩ እንግዳ የሆነበት የወሊሶ ከተማ አስተዳዳር ፖሊስ ጣቢያም ጉዳያቸውን በመስማማት እንዲፈቱ ትዕዛዝ ይሰጣቸዋል።

የዶሮው ባላቤትም ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው የሚያወጣውን ዋጋ ከፍለው ዶሮውን ይረከቡኝ ሲሉ ይስማማሉ። አቶ ደነቅም የወርቁ ባለቤት 250 ብር እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም ባለ ወርቋ የተጠየቀውን ብር የለኝም በማለታቸው 150 ብር ሰጥተዋቸው ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን ነው የወሊሶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ሃላፊ ኮማንደር ከበደ በዳዳ የተናገሩት።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎዛመን ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአንዲት ወጣት ህይወት ሲያልፍ በ15 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ ጎንደር ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ  ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ድልድይ ጥሶ 14 ሜትር ጥልቀት ያለው ወንዝ ውስጥ  ትናንት ሌሊት አስር ሰዓት አካባቢ በመግባቱ  ነው፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው እንደገለጹት በጎዛመን ወረዳ ወይንማ ግራሞ ቀበሌ  ተሽከርካሪው ድልድይ ጥሶ 14 ሜትር ጥልቀት ወርዶ “ቁልች” በተባለው ወንዝ ውስጥ በመግባቱ አደጋው ሊደርስ ችሏል። አደጋውን ያደረሰውም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-62442 ኦሮ ሚኒባስ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በጨለማ በህገ ወጥ መንገድ ጎንደር ሲጓዝ በነበረበት ወቅት ነው።

በዚህም  የአንዲት ወጣት ሴት ህይወቷ ወዲያው ማለፉን የተናገሩት ኢንስፔክተሩ 11 ሰዎች በከባድና አራት ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። የሟቿ አስክሬን ለቤተሰብ ለማስረክብ ፖሊስ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ ኢንስፔክተር ጎበዜ ጠቅሰው፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነው።

አሽከርካሪው አደጋውን ከደረሰ በኋላ ቢሰወረም ፖሊስ ለመያዝ በክትትል እንደሚገኝ አመልክተው የአካባቢው ማህበረሰብ ተጎጂዎቹን ለመታደግ ላደረገው ርብርብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
5 ኢትዮጵያዊያን ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ!

ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 285 ኪሎ ሜትር ርቀት በስተሰሜን የምትገኘው የአይሲኦሎ ግዛት ፍርድ ቤት ያለ ፈቃድ በኬንያ ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀሱ አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን አምስት ኢትዮጵያዊያን ላይ የእስር ቅጣት አስተላልፏል። ጥፋተኛ ናቸው የተባሉት ኢትዮጵያዊያን የተከሰሱበትን ጉዳይ ያመኑ ሲሆን ከቤተሰብ ጋር ለመኖር ወደ ኬንያ እንደገቡ እና ያለ ፈቃድ መግባት ይህን ያህል ከባድ አገራዊ ጉዳይ መሆኑን እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሚዋሰኑበት የማርሳቤት ግዛት ተነስተው ወደ ዋና ከተማዋ ናይሮቢ በመኪና ሲጓዙ አይሲኦሎ ግዛት ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያዊያን በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ኹለት ወራትን በእስር ቤት የሚቆዩ ሲሆን የእስር ጊዜያቸውን ሲያጠናቅቁም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተወስኗል።

ነፃ የሰዎችን ዝውውር በሚመለከት የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከወራት በፊት ‹‹ማንኛውም ምስራቅ አፍሪካዊ ኬንያዊ ነው ፤ በሚኖርበት አገር መታወቂያ ፓስፖርት ሳያስፈልገው ወደ ኬንያ መግባትና መውጣት ይችላል›› ሲሉ በይፋ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

Via AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ARBAMINCH የ2011 ዓ/ም የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የማጠቃለያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሃያ ሁለት ኩባንዎች የተያዙ ሃምሳ ሁለት የማምረቻ ሼዶች በቀጣዩ ዓመት አጋማሽ ላይ ሙሉ በሙሉ ወደስራ እንደሚገቡ ተጠቆመ። ፓርኩ የፈጠረውን 27 ሺ የስራ እድልም ወደ 60 ሺ እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️አንኮበር ወረዳ በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ዘንቦ ነበር። አካባቢውን ከላይ ባሉት በፎቶዎች ተመልከቱ።

ፎቶ📸Haile/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የብልፅግናና የፍቅር እንዲሆን እመኛለሁ!" አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (#ሕወሓት) እና የአማራ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አዴፓ) ቅራኔን በተመለከተ “በአዲሱ ዓመት ችግሮቻችን በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀመጠን ተወያይተንና ተግባብተን ለመፍታት ዝግጁ ነን” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስሀን ጥሩነህ ተናገሩ። አቶ ተመስገን ይህን ያሉት አዲሱን 2012 ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመላው ብሔር ብሄሰቦችና በተለይም ለአማራ ክልል ህዝብ የመልካም ምኞት መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት ነዉ።

እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ ችግሮችንን ለመፍታት ዝግጁ ነን ያሉት አቶ ተመስገን ፤ ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከ(ሕወሓት) ወገንም ተመሳሳይ ፍላጎት ይኖራል ብለው እንደሚያምም ገልፀዋል፡፡ በአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር መኖሩን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳደሩ በአዲሱ ዓመት ለአንድ ሚሊዮን ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን ይፋ አድርገዋል። አዲሱ ዓመት ለመላው ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ በተለይ ለአማራ ክልል ህዝብ የሰላም፣ የብልፅግናና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎርብስ የ2019 የአለም ሀብታም ዝርዝር ይፋ በሚያደርግበት ገጹ እንዲህ በቅደም ተከተል አስቀምጧቸዋል፦

1🇺🇸 ጄፍ ቤዞስ : 131 ቢሊየን ዶላር
2🇺🇸 ቢል ጌት: 96.5 ቢሊየን ዶላር
3🇺🇸 ዋረን ቡፌት : 82.5 ቢሊየን ዶላር
4🇫🇷 በርናልድ አርኑሌት: 76 ቢሊየን ዶላር
5🇲🇽 ካርሎስ ስሊም ሄሉ: 64 ቢሊየን ዶላር
6🇪🇸 አርማኒኮ ኦርቴጋ : 62.7 ቢሊየን ዶላር
7🇺🇸 ላሪ ኤሊሰን: 62.5 ቢሊየን ዶላር
8🇺🇸 ማርክ ዙከንበርግ: 62.3 ቢሊየን ዶላር
9🇺🇸 ሚካኤል ብሉምበርግ: 55.5 ቢሊየን ዶላር
10🇺🇸 ላሪ ፔጅ: 50.8 ቢሊየን ዶላር

(Forbes)

#ቲክቫህ_ልዩ_ልዩ

Join👇
@tikvahethmagazine
#ጅማ #JIMMA

•በጅማ ከተማ ምንም ቤተክርስቲያን አልተቃጠለም
•የሃይማኖት አባቶች አልታረዱም፤ አልተገደሉም
•ከፍተኛ እልቂት እየተፈፀመ ነው የሚባለውም ሀሰት ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን👇

√በጅማ ከተማ በሃይማኖት ሽፋን ብጥብጥ ለመፍጠር ሲደረግ የነበረው እንቅስቃሴ በሕዝቡ እና በፀጥታ አካላት ተሳትፎ ከሽፏል።

√በከተማው በሃይማኖት ሽፋን ክልሉን እና ሀገሪቱን ለማመስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት በሕዝቡ እና በፀጥታ ኃይሎች ድጋፍ ሴራቸው ሊከሽፍ ችሏል።

√"በጅማ ከተማ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተቃጠለ" በሚል የሐሰት ወሬ ሕዝቡን በመቀስቀስ ብጥብጥ ለመፍጠር እና ክስተቱም ወደሌሎች ከተሞች እንዲስፋፋ በተቀናጀ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር።

የተለያዩ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ለTIKVAH-ETH የተገሩት፦

ስለውጥረቱ መነሻ ተመሳሳይነት ያለው መረጃ አላገኘንም! የሚመለከታቸውን አነጋግረን እናቀርባለን!

•ከትላንት 7:00 ጀምሮ ውጥረት ነበር።

•ቁጥራቸው ብዙ ባልባልም በመኪና ሆነው የሚንቀሳቀሱ አካላት ነበሩ።

•ወጣቶች ቤተክርስቲያን ሲጠብቁ ነው ያደሩት። አሁንም እዛው ናቸው።

•ፖሊስ በከተማው ውስጥ ለየት ያለ እንቅስቃሴ ሲታይ አስቸኳይ መፍትሄ አልሰጠም።

•የተቃጠለ ቤተክርስቲያን የለም፤ ግን ሙከራ ነበር ብለን እናምናለን።

•በፌስቡክ ላይ የሚነገረው ግን በተሳሳተ ምልኩ ነው።

•ፖሊስ ይህን ያህል ውጥረት ሳይፈጠር በከተማው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላትን መቆጣጠር ይችል ነበር።

•አመሻሹን ከቤተክርስቲያን የሚመለሱ አካላት በሚመለሱ ወቅት ግርግር ተፈጥሮ ነበር።

•አንዳንድ ወጣቶች በግርግሩ ውስጥ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

•የከተማይቱን ሁኔታ መንግስት ትኩረት ይስጠው።

•ዛሬም አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እየሰማን ነው። ውጥረት አለ!

•የከተማው ፀጥታ ኃይል ነገሮች እንዲ ስሳይባባስ ማስቀረት ይችል ነበር፤ ትኩረት አልተሰጠውም።

•ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ቤተክርስቲያን እየጠበቀ ነው።

•ያለውን ስጋት ለመቅረፍ መንግስት አስፈላጊውን ትኩረት ይስጥና ይስራ።

•ሚዲያዎችም ከአንድ ወገን ብቻ የሚያቀርቡትን መረጃ ማስተካከል አለባቸው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መዋዥቅን ለመቀነስ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ!

በመጪው የ2012 ዘመን መለወጫ በዓል የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መዋዥቅን ለመቀነስ፤ ከተከሰተም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በአገር አቀፍ ደረጃ ዝግጅት የተደረገ መሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡

የኃይል መቆራረጥ ዜሮ ማድረግ ባይቻልም የመቆራረጥ ሁኔታን ለመቀነስ የሚያስችሉ ቅደመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ተናግረዋል።

ከበዓሉ ጋር በተገናኘ ከፍተኛ የሆነ የኃይል ፍላጎት ሊያጋጥም ስለሚችል፤ የድንጋይ ወፍጮ፣ የብረታ ብረት፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የሲሚንቶ፣ የፕላስቲክ፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት ፋብሪካዎች ከጳጉሜ 6 ቀን 2011 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 እስከ መስከረም 1 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽቱ 12፡00 ድረስ ከዋናው የኃይል ቋት /ከግሪድ/ የምታገኙትን ኃይል እንድታቋረጡ የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን ብለዋል ኃላፊው፡፡

እንዲሁም ኤሌክትሪክ በሚቋረጥበት ጊዜ የጥገና ስራ ለማከናወን የተቋሙን መታወቂያ ወይም የስራ ትዕዛዝ የያዙ ባለሞያዎቻች በተለያዩ አካባቢዎች ለስራ ጉዳይ ሊንቀሳቀሱ ስለሚችሉ፤ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል። ህብረተሰቡ የሃይል መቆራረጥና ሌሎች ችግሮች ሲከሰቱ በነፃ የጥሪ ማአከል 905 ላይ በመደወል አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ብለዋል ዳይሬክተሩ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

መስከረም 4/2012 ዓ.ም የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመለክተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት መግለጫ ሰጡ፡፡ መግለጫውን የሰጡት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በቤተክርስቲያን እየደረሰ ያለውን የመቃጠል፣ የካህናት መገደልና ሌሎች በቤተክርስቲያንቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሰልፉን በማስመልከት ዝርዝር መግለጫዎችን በመስከረም 2/2012 ዓ.ም እንደሚሰጥ የገለጹት ኮሚቴዎች፣ የነበራቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ከመንግስት አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሆነና በውይይቱ አጥጋቢ መልስ ካገኙ ሰልፉ ሊቀር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ማህበራቱ የሰላማዊ ሰልፍ መካሄድ አለመካሄዱንም በቀጣይ መስከረም 2 በሚኖረው ድጋሚ መግለጫ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል ሰልፉ ከኦሮሚያ ክልል ቤተክህነት ምስረታ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ በመጠቆም ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምስረታ ጋር በተያያዘ በጉዳዩ ዙሪያ በቅርቡ ሲኖዶሱ የሰጠው መግለጫ በቂ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ሰልፉን ለማዘጋጀት ከባለፈው አንድ ወር ጀምሮ እየተንቀሳቀሱ እንደቆዩም የጠቆሙ ሲሆን፤ የሰልፉ አላማም በሰላማዊ መንገድ በቤተክርስቲያኒቷ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የታቀደው ሰልፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሆንና ህዝበ ክርስቲያኑ ከቤተክርስቲያንቷ ጎን እንዲቆሙም ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia