TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦሮሚያ እና የአፋር ክልል መንግስታት ለአማራ ክልል መንግስት አጋርነታቸውን ገለጹ፡፡ የክልል መንግስታት ርዕሰ መስተዳድሮች ትላንት ባህር ዳር በነበረው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በዓለ ሲመት ላይ ታድመዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባስተላለፉት የአጋርነት መልዕክት ‹‹ኢትዮጵያውያን የሚያዋጣን ለጋራ አንድነታችንና ለልማታችን በጋራ መትጋት ነው፤ ፈተናወች የጋራ ቤትን የሚያፈርሱ ከሆነ ማንም አይጠቀምበትም፤ የጋራ ቤት የሆነችውን ኢትዮጵያ በአንድነት ልማቷን እና ሰላሟን አስጠብቆ ለማሻገር መትጋት ይገባል›› ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ አንድነትና ቀጣይነት የማረጋገጥ ትልቅ ኃላፊነት መወጣት ተገቢ መሆኑንም አቶ ሽመልስ አሳስበዋል፡፡

የጥፋት መንገድ እንዳይደገም፣ ኢትዮጵያን ለዘመናት በአዙሪት ውስጥ ያኖራት በውይይትና በዴሞክራሲያዊ መንግድ ችግሮችን የመፍታት ችግር እንዲያበቃ ሁሉም በጋራ መታገል እንደሚገባውም ነው ያሳሰቡት፡፡ የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ እና መንግስትም ከአማራ ክልል መንግስት ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/BDR-07-23-2
#update አሜሪካ ስደተኞችን ፍርድ ቤት ሳታቀርብ ወደመጡበት ሀገር ልትመልስ ነው፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ያለፍርድ ቤት ውሳኔ ስደተኞችን ወደ መጡበት አገር መመለስ የሚያስችል መመሪያ አወጣ፡፡

በአዲሱ ደንብ መሰረት ማንኛውም ማስረጃ የሌለው ስደተኛና በተከታታይ ለሁለት ዓመት አሜሪካ ውስጥ እንደነበር ማረጋገጥ ያልቻለ ግለሰብ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ይደረጋል። ፖሊሲው ዛሬ ይፋ ተደርጎ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች በአፋጣኝ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል ተብሏል።

አሜሪካን ሲቪል ሊበርቲስ ዩኒየን የተባለ የመብት ተሟጋች ቡድን ፖሊሲውን በመቃወም ፍርድ ቤት ወስዶ ለመሟገት ማሰቡን ተናግሯል። የአሜሪካ የስደተኞች ፖሊሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥብቅ እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል፡፡

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ደጋማው ክፍል በተነሳው የእሳት ቃጠሎ የደረሰውን ውድመት ለማካካስ ከ38 ሺህ በላይ ሀገር በቀል ችግኞች መተከላቸውን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አበባው አዛናው እንደገለፁት የችግኝ ተከላው በተያዘው ዓመት መጋቢትና ሚያዚያ ወር በፓርኩ ውስጥ በተነሳው የእሳት አደጋ የደረሰውን ጉዳት መልሶ ለመተካት ነው፡፡

ችግኞቹ የተተከሉትም ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ሁለት ሺህ የሚደርሱ ወጣቶችና የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አባላትን በማሳተፍ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

በፓርኩ ውስጥ በህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተተከሉ ያሉ ችግኞች በፍጥነት የሚያድጉና ለአካባቢው ስነ-ምህዳር ተስማሚ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከ60 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን እስካሁን በተካሄደ እንቅስቃሴ አብዛኛውን ማሳካት እንደተቻለ ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፡-ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮምቦልቻ

"እኛ የኢትዮጵያ መንገዶችን ባለስልጣን የኮምቦልቻ መንገድ አውታርና ደህንነት ማኔጅመንት ሰራተኞች በዶ/ር አብይ የተጀመረውን የችግኝ ተከላ ፕሮጀክት ጀምረናል።" ሀይሉወሰን በቀለ ከኮምቦልቻ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert አቶ አህመድ ቡህ #የድሬዳዋ_ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ አህመድ ቡህን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾመ።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ የስራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በዛሬው እለት አካሂዷል። ምክር ቤቱ በዛሬው እለት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው ካለፈው መጋቢት ወር 2011 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ በከንቲባነት ያገለገሉትን የአቶ መሐዲ ጊሬን መልቀቂያ ተቀብሏል። በምትካቸውም አቶ አህመድ ቡህን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሹሟል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባዔው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የአፈ ጉባኤ አብደላ አህመድን መልቀቂያ መቀበሉም ተገልጿል። በምትካቸውም ወይዘሮ ፈጡም ሙስጣፋን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የአፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰኔ_15 #ባህር_ዳር

የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ለተፈጠረውን ችግር የፀጥታ ተቋማት መደማመጥ አለመቻል እና ወጥ የሆነ የአመራር ሂደት አለመስጠታቸው እንደሆነ አመለከተ፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በጋራ የተስማማባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ አቅርቧል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የተፈጠረውን ችግር የተመለከተ ጉዳይ አቅርቧል፡፡ የጥፋት መንስኤው የፀጥታ ተቋማት አመራሮች መደማመጥ አለመቻል እና ወጥ የሆነ የአመራር ሂደት ባለመኖሩ መሆኑን ለምክር ቤት አባላቱ ግልጽ አድርጓል፡፡

በክልሉ መንግሥት የሠላም እና ደኅንነት ተቋም ላይ ችግሮች ከመከስቱ በፊት የፖለቲካ አመራሩ አስቀድሞ ዋነኛ መንስኤዎችን እየለዬ መፍታት ባለመቻሉ የተከሰተ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ሰኔ 15/2011ዓ.ም የተፈፀመው ድርጊት የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት በመቆጣጠር በወቅቱ ስብሰባ ላይ የነበሩ ከፍተኛ መሪዎችን በመክበብ ግድያ መፈጸሙ፤ በቡድን መሳሪያ ጭምር በመጠቀም ስልጣን ለመያዝ የተፈፀመ መሆኑን ነው ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበው፡፡ የክልሉ ሕዝብ፣ የክልሉ እና የፌዴራል ፀጥታ አካላት ችግሩን ለመፍታት ባስተዋይነት ለወሰዱት ፈጣን እርምጃ እና መሰዋዕትነት ለከፈሉት ወዳጅ ዘመዶቻቸው የክልሉ ምክር ቤት መፅናናትን እየተመኘ በማንኛውም ወቅት ከጎናቸው መሆኑን አረጋግጧል፡፡

አሁንም ቢሆን በወቅቱ የተፈጸመውን ድርጊት ለመሸፋፈን መሞከር እና የድርጊቱ ፈፃሚዎችን ከተጠያቂነት እንዲያመልጡ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው አስረድቷል፡፡

ተጨማሪ👇
https://telegra.ph/AM-07-23

@tikvahethiopia
#ትኩረት #አርባ_ምንጭ

"ከሁሉም በላይ የሰላም ተምሳሌት ወጣቶችና አባቶች በጋራ የሚኖሩባት ከተማ ተብላ ብትጠራ ማጋነን አይሆንም። በተለይ ቂምን በልቡም በሆዱም የማይዝ ለአባቶቹ የሚታዘዝ ወጣት የሚኖርባት ሁከትን አመፅን ጥላቻን የሚፀየፉ አባቶችን ያቆየች ለምለም ምድር ናት አርባምንጭ። በጣም መጥፎ የሚባሉ አስቸጋሪ ጊዜዎችን አሳልፈናል ገና በጋራ ሆነን እናሳልፋለን። ከጊዜ ወደ ጊዜ ችላ እየተባለ የመጣው የሞባይል የቦርሳ ንጥቅያና የቡድን ዝርፊያን መንግስት በትኩረት እንዲሰራበት ለመጠቆም እወዳለሁ። በተለይ ደግሞ በአንዳንድ ጉልበተኛና ነውጠኛ ወጣቶች የተደራጀው የቡድን ዝርፊያ ነገ መልኩን ቀይሮ ወደ ሌላ ግጭት ከማምራቱ በፊት በየ ጋራው በየተራራው ስር ተሸሸገው በሚገኙ ህገወጦች ላይ መንግስት እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።" የአርባምንጭ ወጣቶች/ለTIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፍሪካ

ከአጠቃላዩ የአለማችን ህዝብ 11 በመቶ ያህሉ ወይም 821.6 ሚሊዮን ሰዎች የረሃብ ተጠቂ መሆናቸውና በአፍሪካ ከአምስት ሰዎች አንዱ የችግሩ ሰለባ ሆኖ እንደሚገኝ አንድ አለም አቀፍ ሪፖርት አመልክቷል። ከሰሞኑን ይፋ የተደረገው የ2018 አለምአቀፍ የምግብ ዋስትናና የስነምግብ ሁኔታ አመላካች ሪፖርትን ጠቅሶ ቢቢሰ እንደዘገበው፤ ከአለማችን አገራት በረሃብ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቃችው አፍሪካ ስትሆን በአህጉሪቱ የረሃብ ተጠቂዎች ቁጥር ዘንድሮም ለሶስተኛ ተከታታይ አመት መጨመር አሳይቷል። በሁሉም የአለማችን አገራት ሴቶች ለረሃብ የመጋለጥ ዕድል ከወንዶች አንፃር ሲታይ ከፍ ያለ መሆኑን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ህፃናትም በከፍተኛ ሁኔታ የችግሩ ተጠቂ መሆናቸውን አመልክቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ልዩ ወረዳዎች የጸጥታ ሥራው በፌዴራልና በጸጥታ ሃይል ቁጥጥር ሥር ሆኖ በጊዜያዊ በኮማንድ ፖስት እንዲመራ ትላንት መወሰኑ ይታወቃል።

የክልሉ መንግስት ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በአንዳንድ አካባቢዎች በተከሰቱ የጸጥታ ችግሮች፤ የህግ የበላይነት በአግባቡ እንዳይከበር ንቅፋት መሆኑና የዜጎች ደህንነት ጥያቄ ላይ በመውደቁ የክልሉ መንግስት በጠየቀው መሰረት ከሐምሌ 15 2011 ዓ.ም ጀምሮ በኮማንድ ፖስት እንዲመራ የፌዴራል የፀጥታ ምክር ቤት ወስኗል።

በክልሉ በተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ ምክንያት በንብረትና በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑ፣ ያልተፈቀዱ ሰልፎችና የክልሉን ፀጥታ የሚያውኩ እንቅስቃሴዎች እንደሚስተዋሉም ነው በመግለጫው የተጠቀሰው።

ስለሆነም በክልሉ ሰላምና ደህንነት ለማስፈን እንዲሁም የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንዲቻልም ከሐምሌ 15/2011 ዓ.ም ጀምሮ ክልሉ በፌዴራልና በፀጥታ ሃይል ቁጥጥር ሥር ሆኖ በጊዜያዊ በኮማንድ ፖስት እንዲመራ ተወስኗል። ዝርዝሩ በቀጣይ ይፋ እንደሚሆንም ተገልጿል።

ምንጭ፦ የደቡብ መገናኛ ብዙሃን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ

ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በሚኒስቴሩ ስር የሚገኙ 15 ተጠሪ ተቋማት በቦሌ ለሚና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሐምሌ 15/2011 የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡

ከ3,800 በላይ ሠራተኞች በተሳተፉበት በዚህ የችግኝ ተከላ ከ22,000 በላይ ችግኞችን በቦሌ ለሚና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመትከል ተችሏል፡፡

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በነበረው የቸችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተሳተፉት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረየሱስ እንደገለፁት ይህ የችግኝ ተከላ መርሃግብር በዋናነት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ አቅም መፍጠሪያና በሐምሌ 22/2011 የሚካሄደው ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ቀን መንደርደሪያ ነው ብለዋል፡፡

ሐምሌ 22 ለሚካሄደው ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ሁሉንም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞችን ማሳተፍ እንዲቻል የቅድመዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን አውስተው በእለቱም በኦሮሚያ ክልል በፍቼ ከተማ አካባቢ 80,000 ችግኞች እንደሚተከሉ ገልፀዋል፡፡

በችግኝ ተከላው የተሳተፉ ሠራተኞች እንደገለፁት በዚህ ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ቀን ላይ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ በመቻላቸው የተሠማቸውን ደስታ ገልፀው በሀገራዊው የሠላም፣ የዴሞክራሲና የልማት እንቅስቃሴም ውስት ሁሉም በላፊነት የየግሉት አስተዋፅኦ በማድረግ የተጀመረውን ሀገራዊ መግባባት ማሳደግ እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ኢትዮ ቴሌኮም በኢንተርኔት #መቆራረጥ ምክንያት ብቻ 204 ሚሊዮን ብር ማጣቱን ገለጸ። ኢትዮ ቴሌኮም የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል። የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ፍሬህይወት በዚህ ጊዜ እንዳሉት በኢንተርኔት መቆራረጥ ምክንያት ብቻ 204 ሚሊዮን ብር አጥተናል ብለዋል።

ከዚህ በፊት በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ኢትዮጵያ በቀን 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች ተብሎ የወጣው ዘገባ ስህተት መሆኑን ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2011 በጀት ዓመት 36 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። የተገኘው ገቢ የእቅዱን 80 በመቶ ያሳካ ሲሆን ገቢው ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በ7 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ወይዘሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል።

ድርጅቱ የደንበኞቹን ቁጥር 43 ሚሊዮን ያደረሰ ሲሆን አገራዊ የቴሌኮም ስርጭቱ 44 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱም በመግለጫው ወቅት ተገልጿል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአገሪቱ የተወሰኑ አካባቢዎች የጸጥታ ሁኔታ አስጊ በመሆኑ የቴሌኮም አገልግሎቶች የግድ ማቋረጥ አስፈልጓል ይሄ ደግሞ በገቢው ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮብናል ሲሉ ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

Via #ኢትዮ_ቴሌኮም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የስልጤ ልማት ማህበር ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች የ500 ሺ ደብተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከስልጤ ልማት ማህበር ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የስልጤ ልማት ማህበር እና ተወላጆች ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች የሚሆን የ500 ሺ ደብተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የማህበሩ ተወካዩች የስልጤ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባህሉን እና ማንነቱን የሚያሳድግበት የባህል ማዕከል ለመገንባት ጥያቄያቸውን ለኢ/ር ታከለ ኡማ አቅርበዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ የስልጤ ልማት ማህበር ለተማሪዎች ላደረጉት የደብተር ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የማህበሩ ተወካዮች በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን እንደሚያደንቁ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይነትም በከተማዋ ውስጥ በሚከናወኑ ማንኛውም የልማት ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፉ አጋርነታቸውን በተግባር እንደሚያሳዩም ገልፀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮ ቴሌኮም የ2011 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም፦

https://telegra.ph/ETHIOTELECOM-07-23
አሜሪካ እና ኢራን ወዴት እያመሩ ነው

ኢራን ለሲአይኤ እየሠሩ ነበር ያለቻቸውን 17 ሰላዮች በቁጥጥር ሥር ማዋሏን ይፋ አደረገች። ከነዚህ ገሚሱ #ሞት ተፈርዶባቸዋል ተብሏል። የኢራን የደህንነት ሚንስትር እንዳለው፤ ተጠርጣሪዎቹ ስለ ኒውክሌር፣ መከላከያ እና ሌሎችም ዘርፎች መረጃ እየሰበሰቡ ነበር። የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን ክስ "ሀሰት ነው" ሲሉ አጣጥለዋል። በኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ሳቢያ ሁለቱ አገራት እንደተፋጠጡ ነው። ትራምፕ ከዓለም አቀፉ የኒውክሌር ስምምነት ባለፈው ዓመት ወጥተው ኢራን ላይ የንግድ ማእቀብ መጣላቸው ይታወሳል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አረንጓዴ አሻራ እናሳረፍ ፤ በአንድ ጀምበር 200 ሚልዮን ችግኝ እንትከል፤ ሐምሌ 22 በነቂስ እንዉጣ።" PMO
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከሐምሌ 19 -21ቀን 2011 ልዮ የበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች ፕሮግራም አዘጋጅቷል።
ቦታ:- መስቀል አደባባይ
ሰዓት:- 3:00-11:00
#አብዛን_ንግድ

20 ሺ ሠራተኞችን #ለመቅጠር ገንዘብ እያስከፈለ በመመዝገብ ላይ የነበረው ግለሰብ ከእነ ጓደኞቹ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀርቧል። አብዛን የተሰኘ የንግድ ሥራ ድርጅት ባለቤት መሆኑ የተገለጸ ግለሰብ 20 ሺሕ ሠራተኞችን ለመቅጠር በነፍስ ወከፍ 2,477 ብር በማስከፈል፣ በርካታ ወጣቶችን በመመዝገብ ላይ እያለ ከጓደኞቹ ጋር በቁጥጥር ሥር ውሎ ታሰረ፡፡ግለሰቡ አቶ አብርሃም ዘሪሁን የሚባል ሲሆን፣ የሥራ ማስታወቂያውን በቃና ቴሌቪዥንና በሌሎች ሚዲያዎች በማስተዋወቅ፣ ከሐምሌ 1 እስከ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ እያንዳንዱ ተመዘጋቢ የ2,477 ብር ሲፒኦ አሠርቶ እንዲመዘገብ ጥሪ ማድረጉ ታውቋል፡፡
.
.
ተጠርጣሪዎቹ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀምና በተለይ የ2011 ዓ.ም. ተመራቂ ወጣቶችን በማማለል ከሦስት ሺሕ ብር በላይ ደመወዝ እንደሚከፍል፣ #ሐሰተኛ ማስታወቂያ በማስነገር ከእያንዳንዱ ተመዝጋቢ 2,744 ብር መቀበላቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡ ስለማስታወቂያውና ስለሥራው የተጠራጠረው ፖሊስ ከአሥር ተመዝጋቢዎች ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ጥርጣሬውን ይበልጥ ስላጎላው፣ ግለሰቦቹን ሐምሌ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመረ መሆኑንና ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ABZAN-07-24

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዛን የንግድ ስራ ድርጅት በሚል 20 ሺ ሰራተኛ ለመቅጠር ገንዘብ ሲሰበስብ የነበረው ግለሰብ ከነጓደኞቹ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

#ጥንቃቄ: በተለይ ተመራቂዎች ለስራ ቅጥር ለማመልከት ስትሄዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የተለያዩ ሀገራት ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ‹‹ገንዘቡ የተያዘው ሐምሌ 14/2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ገዳማ ከጠገዴ ወረዳ ሾርካ ንዑስ ወረዳ መፈተሻ ኬላ ላይ ነው›› ብሏል ፖሊስ ለአብመድ በሰጠው መረጃ፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ምክትል ኮማንደር አስማማው ካሴ እንደገለጹት አቶ ገብረሕይወት አስማረ የተባለ ተጠርጣሪ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በቦርሳ ይዞ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥ ሥር ውሏል፡፡

የተጠርጣሪው መታወቂያ ‹‹ሥራ ፈላጊ›› የሚል መሆኑንም ነው ምክትል ኮማንደር አስማማው የተናገሩት፡፡ ግለሰቡም ከጎንደር ወደ ሁመራ ተጓዥ እንደነበር መናገሩም ተሰምቷል፡፡

ከ110 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በተጨማሪ የእንግሊዝ ፓውንድ መገኘቱንም ነው የወንጀል ምርመራ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤቱ ያመለከቱት፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ከሌሎች ሴክተር ተቋማት ጋር በመሆን በቅርቡ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የንግድ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መስፍን አሰፋ እንደገለጹት ከነጋዴው የኅብረተሰብ ክፍል ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር ውይይቶች ተደርገዋል፤ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ አካላት ላይም ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት መካከል የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ሱቆች፣ ዳቦ ቤቶች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ የእህል መነገጃ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች እንደሚገኙበት ኃላፊው መናገራውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

በተለይም ዋጋ የጨመሩ፣ ያለ ደረሰኝ ግብይት የፈጸሙ፣ ግራም ያጎደሉና በተለያዩ መንገዶች በኅብረተሰቡ ላይ ጫና ያደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ነው የተገለጸው፡፡

በተወሰደ እርምጃም መሻሻሎች እንደታዩና አልፎ አልፎም ከዚህ በፊት ከነበሩበት ዋጋ በታች የወረዱ ግብይቶች መኖራቸውን ጭምር ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

የቁጥጥር ሥራን ከማጠናከር በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ምርቱን በተሻለ ዋጋ የሚያገኝበትን አማራጮች በመፍጠር፣ በምርትና በሽያጭ ሂደት ውስጥ ምንም እሴት የማይጨምሩ ነገር ግን በሕገ ወጥ መልኩ በገበያ ስርዓት ውስጥ የተሰገሰጉ ደላሎችን በማስወገድ ኅብረተሰቡ በቀጥታ ከገበሬ ምርቱን ማግኘት እንዲችል ከተለያዩ ክልሎች በተለይም ከኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ ክልሎች ጋር እየሠራ መሆኑንም አቶ መስፍን ገልጸዋል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢቢኤስ(EBS) ቴሌቪዥን ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች 50ሺ ደብተር ድጋፍ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ አራት የመንግስት ት/ቤቶች እድሳት ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

Via @mayorofficezAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia