TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፕሬዘዳንት ኢሳያስ ከAU ስብሰባ ለምን ቀሩ

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

የኤርትራው ፕሬዝደንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ ለምን ከአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ቀሩ? ይህን ጥያቄ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ለኤርትራው የተመድ እና አፍሪካ ህብረት ልኡክ ዋና ሀላፊ አምባሳደር አርአያ ደስታ አቅርቦላቸው ነበር። መልሳቸው፦
"የምፅዋ #የነፃነት_ቀን አሁን በኤርትራ እየተከበረ ነው። በአጋጣሚ የዚህ አመት የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ገፋ በመደረጉ ከቀኑ ጋር ተገጣጠመ። ያው ስንት ሰማእት ያለቀበት ማስታወሻ ፕሮግራም ሀገር ቤት ስላለ እዚህ አልተገኙም።"

ፎቶ፦ EP
@tsegabwolde @tikvahethiopia
250,000#TIKVAH_ETHIOPIA እዚህ ደረጃ እንዲደርስ እናተ የቤተሰቡ አባላት ላደረጋችሁት ከፍተኛ አስተዋፆ ከልብ ልትመሰገኑ ይገባል!

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምስራች🎊 ከረድኤት አስመጪ ቅናሽ አድርጓል!!

Konica minolta 451/550/650 በ 70 ሺብር ብቻ የምናቀርባቸውን ምርቶች ሲገዙ በተመጣጣ ዋጋ ከሙሉ የጥገና ዋስትና ጋር እናስረክባለን!!

ይምጡና ይጎብኙን አድራሻችን፦ አዲስ አበባ ሜክሲኮ #ኬኬር_ህንፃ ግራውንድ ስር እንገኛለን

ስልክ፦
+251904141404
+251902477474
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከሶማሊያና ከቦስትዋና ፕሬዝዳንቶች ጋር ውይይት አደረጉ። እየተካሔደ በሚገኘው 32ተኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በተመሳሳይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቦስትዋና ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት እያደረጉ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሰራተኞቹ ሽልማት ተበረከተ‼️

የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አበቤ የቶጎ ጫሌና ጅግጅጋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ሰራተኞች የኮንትሮባንድ ንግድን በመቆጣጠር ላበረከቱት አስተዋፅኦ የተለያዩ ሽልማቶችን አበርክተዋለ ።

ሚኒስትሯ በትናንትናው ዕለት በጂጂጋና ቶጎ ጫሌጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ለራሳቸው ጥቅም ሳይታለሉ ህገ ወጥ ንግድን በተገቢ ሁኔታ ለተፋለሙ በሁሉም የስራ መደብ ለሚገኙ ሰራተኞች የማበረታተች ሽልመት ሰጥተዋል ።

ሽልማቶችም ዘመናዊ ሳምሰንግ ሞባይል S9 (+) ቀፎዎች ፣ ዘመናዊ ላፐ ቶፕ፣ አንድ ኤፍ.ኤስ.አ እና ፒክ አፕ መኪናዎች መሆናቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወይዘሮ አዳነች በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ህገ ወጥ ንግድን መከላከልና መቆጣጠር ሀገርና ሕዝብን ከውድቀት ማዳን መሆኑን ተናግረዋል።

ሽልማቱ ሰራተኞች በስራቸው ላስመዘገቡት ስኬት የተበረከተ መሆኑን በመጥቀስ ለሀገርና ለወገን በጥቅማ ጥቅም ሳይንበረከክ ለሚሰራ ሽልማት ይገበዋል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ሀገራችን ካለችበት ዘርፈ ብዙ ችግር ውስት ለማውጣት ከዚህ በተሻለ በጋራ እና በቅንጅት ልንሰራ ይገባል ነው ያሉት።

በኮንትሮባንድ የሚገቡ የጦር መሳሪያዎች፣ ጊዜያቸዉ ያለፈባቸው መድሃኒቶችና መሰል ሸቀጦች ዜጎችን ለዘርፍ ብዙ ችግሮች ከመዳረጋቸው በሻገር የሀገርና የህዝብን ራዕይ የሚያጨልሙ መሆናቸውን አንስተዋል።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል የጉምሩክ ሰራተኞችና አጠቃላ ህብረተሰቡና የፀጥታ አካላት ከክልሉ መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰሩት ያለዉ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ሽልማቱን ባልጠበቁት ሰዓት ከሚንስትሯ እጅ የተቀበሉ ሰራተኞች በበኩላቸው ሽልማቱ የተሰጠንን ሀላፊነት በተገቢው ሁኔታ እየሰራን ነው የሚል ስሜት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።

በቀጣይም የኮንትሮባንድን ንግድ አመርቂ በመሆነ መልኩ ለመቆጣጠር የበኩላቸውን አስተወፅኦ የሚያበረክቱ መሆኑን ነው የገለፁት።

በቶጎ ጫሌና ጅግጅጋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ በተለያየ ጊዜ በርካታ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በሰራተኞች ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወሳል።

በቅርቡም በቶጎ ጫሌ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ 7 ኪሎ ግራም ወርቅን ጨምሮ 60 ሚሊየን የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

በርካታ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች እና ብዙ የሶሻል ሚድያ ተከታታይ ያላቸው ግለሰቦች የአፍሪካ ህብረት አማርኛን ስድስተኛ የስራ ቋንቋው አድርጎ እንደመረጠ ትናንት ሲፅፉ ነበር። እውን ሆኖ "እልል" ባስባሉን እያልኩ ነበር፣ ነገር ግን መረጃው #የሀሰት ነው።

ዛሬ በጠዋቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ቃል አቀባይ የሆነችው ኤባ ካሎንዶ ጋር ደወልኩ። በመልሷም፦

"የቋንቋ ምርጫ የመሪዎቹ አጀንዳ ላይ ጭራሽ አልነበረም። እርግጥ ጠ/ሚር አብይ ስለ አፍሪካ ሀገር በቀል ቋንቋዎች ጥቅም አውርተዋል። የኢኳቶርያል ጊኒው መሪም ቋንቋቸው የአፍሪካ ህብረት ቋንቋ እንዲሆን ይፈልጋሉ። ይህ ማለት ግን ሆኑ ማለት አይደለም። ስለዚህ ኤልያስ፣ አማርኛ የአፍሪካ ህብረት ኦፊሴላዊ ቋንቋ ሆነ የተባለው የሀሰት ዜና (fake news) ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማርኛ‼️
.
.
#የቋንቋ_ምርጫ የመሪዎቹ አጀንዳ ላይ #ጭራሽ_አልነበረም ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ተናገሩ። ሊቀመንበሩ ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት እንደተናገሩት ጠ/ሚር አብይ ስለ አፍሪካ ሀገር በቀል ቋንቋዎች ጥቅም አውርተዋል፤ የኢኳቶርያል ጊኒው መሪም ቋንቋቸው የአፍሪካ ህብረት ቋንቋ እንዲሆን ይፈልጋሉ፤ ይህ ማለት ግን ሆኑ ማለት አይደለም ብለዋል። ትላንት ምሽት በማህበራዊ ሚዲያ አማርኛ የአፍሪካ ህብረት ኦፊሴላዊ ቋንቋ ሆነ የተባለውም የሀሰት ዜና (fake news) ሲሉ ተናግረዋል።

#TIKVAHETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

"ከላይ የምታዩት ደብዳቤ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንደተላከ ተደርጎ የተሰራ ሃሰተኛና ከሃቅ የራቀ ደብዳቤ መሆኑን እንገልጻለን፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰተኛ መረጃ‼️

ለውድ መምህራን በሙሉ፦

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደመወዝ #የተጨመረ በማስመሰል #የተሣሣተ_መረጃ እየተሠራጨ ይገኛል። ስለዚህ መረጃው ከእውነት የራቀና ሀሠት መሆኑን የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የገለፀልን መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ‼️

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ችግር #የባከነውን የትምህርት ጊዜ #ለማካካስ የእረፍት ቀናት ጨምሮ እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡

በጸጥታ ችግር ምክንያት የባከነ የትምህርት ጊዜን በማካካስ የመጀመሪያውን መንፈቅ ዓመት በስኬት ለማጠናቀቅ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆናቸውን የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ለኢዜአ ገልጸዋል።

አሁን አንጻራዊ #ሰላም በመስፈኑ ተቋሙ ያመቻቸላቸውን የትምህርት ማራዘሚያ ጊዜ በመጠቀም የባከነውን ጊዜ ለማካካስ ከመምህራን ጋር እየሰሩ እንደሚገኙ ተማሪዎች ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዘላለም አብዲሳ በበኩላቸው በምዕራቡ ክፍል ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ለተወሰነ ጊዜ የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የሁለት ሳምንት ማራዘሚያ ተደርጓል።
በእረፍት ቀናትም ጭምር የማካካሻ ትምህርቱ እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይ ለሴት ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መዘጋጀቱን የገለፁት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራን ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በ1999 ዓ.ም 851 ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የጀመረው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት በመደበኛና ተከታታይ የትምህርት መርሀ ግብር በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ 38 ሺህ ተማሪዎች በማስተማር ላይ መሆኑ ታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቦሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ #ጥላሁን_ፍቃዱ በክፍለ ከተማው ወረዳ አንድ የነዋሪነት መታወቂያ ያላግባብ ተሰጥቷል መባሉን አስተባብለዋል፡፡ ሸገር ራዲዮ ቀደም ሲል ወረዳው ለ2 ሺህ ዜጎች ያላግባብ መታወቂያ መሰጠቱን ጠቅሶ ያሰራጨውን ዘገባ መሠረት በማድረግ ማጣራት ተደርጓል ብለዋል፡፡ ሆኖም ለጊዜያዊ ሥራ ፈጠራ ዕድል ሲባል በቀጠናው ነዋሪነታቸው ለተረጋገጠላቸው 597 ወጣቶች መታወቂያ ከመሰጠቱ በስተቀር ሌላ የተሰጠ መታወቂያ የለም፡፡ አንድ የወረዳው ሠራተኛ መረጃውን ለሸገር በማድረሳቸው ብቻ ከሥራ ስለመታገዳቸው መረጃ የለኝም ብለዋል፡፡

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከአልጄሪያ፣ ከሞሮኮ፣ ከቱኒሲያና ከኤስቶንያ መሪዎች ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ምንጭ፤ ጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia