TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ🔝

ከጅግጅጋ ከተማ የመጡ የከተማው ነዋሪዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ ከጥዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው ዋልታ ቴሌቪዥን ድምፃቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።

©Daw(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ለሼህ አላሙዲ #መፈታት የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር" አቶ ተካ
.
.
በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና የሳዑዲ ዜግነት ያላቸው ቢሊየነሩ ሼህ ሞሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ትናንት ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ከሪያድ ወደ ጅዳ በማቅናት ከቤተሰባቸው ጋር ተቀላቅለዋል።

የሳዑዲ መንግሥት ያካሄደውን የፀረ-ሙስና ዘመቻን ተከትሎ ከበርካታ ንጉሣዊ ቤተሰቦች እና ከበርቴዎች ጋር ተይዘው ከ14 ወራት በላይ በእስር ያሳለፉት አላሙዲ እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠበቃቸው አቶ ተካ አስፋው ለቢቢሲ ተናገረዋል።

አቶ ተካ ''ትናንት (እሁድ) በስልክ ተገናኝተናል። ጤናቸው በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተቀላቅለዋል'' ያሉ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ መቼ ሊመጡ ይችላሉ ተብለው ለተጠየቁት ''ወደ ኢትዮጵያ መምጣቸው አይቅርም፤ ነገር ግን መቼ እንደሚመጡ በእርግጠኝነት መናገር አልችልም'' ሲሉ የአላሙዲ ጠበቃ አቶ ተካ አስፋው ተናግረዋል።

ካለፈው ግንቦት 2009 ዓ.ም ጀምሮ አሊ-አላሙዲ ከእስር እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጥረቶችን ሲያደርጉ እንደቆዩ የሚናገሩት አቶ ተካ ''ጠቅላይ ሚንስትራችን ከአንዴም ሁለቴ ቦታው ድረስ ተገኝተው ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድረገዋል። ከዚያም በኋላ በነበራቸው ግንኙነት ከፍተኛ ጥረት እንዳደረጉ ነው የምናውቀው። ለመፈታታቸው የእሳቸው ጥረት እንዳለበት ነው የተረዳነው'' ብለዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት የፌስቡክ ገጽ የባላሃብቱን ከእስር መፈታት ይፋ ባደረገበት ጽሁፍ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ግንቦት 2010 ዓ.ም ሞሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ከእስር ለማስፈታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን እና በቅርቡም ወደ አገራቸው ይመለሳሉ በማለት በሚሊኒያም አደራሽ ያደረጉትን ንግግር አስታውሷል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ጨምሮም አሊ-አላሙዲ በሰላም እንዲመለሱ መልካም ምኞታችንን አንገልጻለን በማለት አስፍሯል።

ከ14 ወራት በፊት ከአላሙዲ ጋር በሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት መካከል ጥቂት የማይባሉ ከበርቴዎች መጠኑ በይፋ ያልተገለጸ ነገር ግን ካላቸው ሃብት ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ ለሳዑዲ መንግሥት ሰጥተው ከወራት በፊት ከእስር መውጣታቸው ይታወሳል።

ከዚህ አንጻር ሼህ አላሙዲንም ከእስር ለመፈታት #ከፍተኛ ገንዘብ #ከፍለዋል ወይ ተብለው የተጠየቁት ጠበቃቸው አቶ ተካ ''ከፍለዋል ብዬ ለመናገር ይከብደኛል። የተፈቱበትን አኳኋን ዝርዝር ሁኔታ ሰለማላውቅ ይሄ ነው ብዬ መናገር አልችልም። እኔ ግን ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለዋል ብዬ አላምንም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ግን ለመፈታታቸው የማይናቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል'' ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአንድ ፒካፕ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዙ የነበረ ሦስት መትረየስ፣ 1924 የስታር እና 1856 የማካሮቭ ሽጉጥ ጥይቶች ከ37 የጥይት መያዥ ጋር #መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጀርመኑ ግዙፍ የመኪና አምራች ኩባንያ ቮልስዋገን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱ ኩባንያው በኢትዮጵያ የመኪና #መገጣጠሚያ ፋብሪካ ለማቋቋም የሚያስችለው ነው ተብሏል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
እንኳን አደረሳችሁ!
የምስራች ለ ሳሙና አምራቾች!!

ለምታመርቱ ሳሙና የሽቶ ግብአት እጥረት አለብዎት? እንግጻውስ ይህን ችግር የሚቀርፍ የሳሙና ሽቶ ግብአት ህንጽ ከሚገኘው ሶናሮም በጥራት የተመረተ ግብአት በተለያዩ መአዛዎች አስመጥተናል:: ግብአቶቹ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጥራት ስለተመረቱ ለፈሳሸም ሆነ ለደረቅ ሳሙና በአስተማማኝ ሁኔታ መጠቀም ይችላል:: ግብአቶቹን መግዛት ለምትፈልጉ በአድራሻችን
በ ሞባይል :- 0911240726 ወይም
በ ቢሮ:- +251 11 558 5384
ኢሜል :-www.akmase.com ማግኘት ትችላላችሁ ::
ከአክማስ አስመጪና ላኪ::
#update የጀርመን የቴክኖሎጂ ድርጅቶች በኢትዮጵያ እንዲሰማሩ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑ ተነገረ። የጀርመን የቢዝነስ ልኡካን ቡድን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መስክ በሚሰማሩበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጀር ጄነራል ክንፈ‼️

የብረታብረትና ኢንጅነሪግ ኮርፖሬሽን ከተፈጸመ የመርከብ ሽያጭና የሆቴል ግዢ ጋር ተያይዞ የተከሰሱት እነ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በአቃቢ ህግ ክስ ላይ ከአምስት ገጽ በላይ መቃወሚያ አቀረቡ።

ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 14 ተከሳሾች ያለአግባብ በተፈጸመ በሆቴል ግዢና በመርከብ ሽያጭ በርካታ ብር እንዲባክን ሆኗል ሲል አቃቢ ህግ የመንግስት ስራን በማያመች አኳኋን መምራት ሙስና ወንጀል በሁለት መዝገብ ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

ይህን ክስ ተከትሎም ተከሳሾቹ ከአምስት እስከ 10 ገጽ የሚደርስ የክስ መወቃወሚያ አቅርበዋል።

ያቀረቡትን መቃወሚያ አቃቢ ህግ ተመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ለጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ከሆቴል ግዢ ጋር ተያይዞ ተከሰው ያልቀረቡ 2ኛ፣ 12ኛ እና 13ኛ ተከሳሾችን እንዲሁም ከመርከብ ግዢ ጋር ተያይዞ ያልተያዙ 2ኛ፣ 6ኛ፣ 7ኛ፣ 13ኛ እና 14ኛ ተከሳሾችን ፌደራል ፖሊስ አፈላልጎ እንዲያቀርብም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ምንጭ:- fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሚድሮክ ኢትዮጵያ የሼክ ሞሃመድ አላሙዲን መፈታት አስመልክቶ ለሠራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ አድርጓል፤ ዕዳ ላለባቸውም ዕዳ ሰርዟል፡፡ ለኢትዮጰያ ዐይን ባንክ ደሞ 250 ሺህ ብር መለገሱን የገለጸ ሲሆን የሚደሮክ ፕሮጄክቶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ የተመረጡ ትምህርት ቤቶችም እንዲሁ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡ የሚድሮክ ንብረት በሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎችም ላንድ ወሰነ ትምህርት #በነጻ እንዲማሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡

Via wazemaradio(walta)
@tsegabwolde @tikvahethiopia