TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጊነር ወረዳ🔝ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ: ከእንግሊዝ የቀድሞ ጠ/ሚር ቶኒ ብሌር: ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ጊኒር ወረዳ አርዳ ቀብሶ ቀበሌ በ2350 ሄክታር መሬት ላይ በ133 ክላስተሮች የዱረም ስንዴ የሚያመርቱ ገበሬዎችን ጎበኙ።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አልበርከቴ‼️

የገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ አልበረከቴ በምትባል ከተማ ላይ 56 #ሽጉጦችን እንዲሁም ቶጎ ውጫሌ ላይ ደግሞ 64 ሺ ዶላር እና 300 ሞባይል መያዙን ተናግሯል፡፡ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል፡፡

የቁጥጥር ሥራውን በተጠናከረ መልኩ እያደረገ ያለው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉምሩክ ክፍል ከሕብረተሰቡ በሚደርሱት ጥቆማዎችና ሰራተኞቹ ሥራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ በመሆናቸው በፊት በቀላሉ ያልፉ የነበሩ ሕገወጥ ቁሶችን እየያዘ እንደሆነ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ #አዲሱ_ይርጋ ለሸገር ራድዮ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ከሕገወጦች የተወረሱ ገንዘቦችና ቁሶች በብሄራዊ ባንክ በኩል ለመንግሥት ገቢ እንደሚሆኑና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ከነማስረጃው ይፋ ይሆናል ሲሉ አቶ አዲሱ ለሸገር ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ🔝

"ፀጋ እኛ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የproduction engineering ተማሪዎች ባለፈው የነበረብን ችግር ተቀርፎልናል። ስለዚህ ድፓርትመንቱን በ ድግሪ ደረጃ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሰጥ ለማስተዋወቅ የተመረጡ መምህራን እና ተማሪዎች ወደ ተለያዩ የሀገራችን ፋብሪካዎች አምርተዋል። ስለዚህ አሁን ከሚገባው በላይ ደስተኛ ነኝ። ይህ የምታየው ፎቶ የተወከሉት ሰዎች የሚሄዱበት ሀገር እና production engineer ምን መስራት እንደሚችል ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከባህር ዳር🔝

"በባህርዳር ከፍተኛ የቤንዚን እጥረት አለ። ከጠዋት ጀምሮ የነበረ ሰልፍ ከዋና መንገድ አልፎ ሰፈር ውስጥ ደርሷል። ይህ ነገር ተደጋጋሚነቱ በዝቷል! ጃፒ ከባህር ዳር"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር🔝

በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ባለው #የሰላም_መድረክ የአማራ ክልል ሰላም ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ጄነራል #አሳምነው_ጽጌ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ጄኔራሉ ‹‹ከየትኛውም ወገን ያሉ አጥፊዎች #ዘርን_ሳያማክል በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡›› ቅማንት እና አማራን ሽፋን አድርጎ ግጭትን ሲያነሳሳ የነበረ ማንኛውም አካልም ስርዓት እንዲይዝ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጠው ህዝብ፤ አጥፊዎችን በመለየትና በማጋለጥ አንድነቱን ማጠናከር እንጂ መፍትሄውን ከሌላ አካል መሻት የለበትም ነው ያሉት፡፡

የአካባቢውን ሰላም የሚጠብቀው ህብረተሰቡ መሆኑን በመገንዝብ ይህን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ወጣቶች እና አርሶ አደሮችም ሰላምና አካባቢውን ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም እንዲያገኙ የክልሉ ሰላም ደህንነት ቢሮ ይሰራል፡፡

የተከሰቱ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈታሉ፡፡ ነገር ግን በየጊዜው ለሚፈጠሩ የብጥብጥ አጀንዳዎች መጠቀሚያ ላለመሆን ነቅቶ እና እየተናበቡ መንቀሳቀስ ይገባል ነው ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ፡፡

ውይይቱም በዕለቱ ምክክር ላይ የተነሱ ሀሳቦችን የሚያጠናክሩ ባለሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ረጲ ኃይል ማመንጫ‼️

አወዛጋቢው የረጲ ኃይል ማመንጫ ‹‹ቆሻሻ #ከማቃጠል የዘለለ ሚና የለውም›› ሲሉ የውጭ ባለሙያ አጣጣሉ...
.
.
ሥራ በጀመረ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ #እንዲያቆም የተደረገውና ሦስት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ የፈሰሰበት የረጲ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ ቆሻሻ ከማቃጠል የዘለለ ሚና የለውም ሲሉ የዘርፉ የውጭ ባለሙያ አጣጣሉ፡፡

የሲቪል ኤንድ ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ ባለሙያ የሆኑት ሰሃዳት ሁሴን (ዶ/ር) በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቴክሳስ ፕሮፌሰር፣ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የደረቅ ቆሻሻ ኢንስቲትዩትም ዳይሬክተር ናቸው፡፡ እንደ ባንግላዲሻዊው ባለሙያ ማብራሪያ በተለምዶ ‹ቆሼ› ተብሎ በሚጠራው ዘነበ ወርቅ አካባቢ የተገነባው የረጲ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ በኢትዮጵያ ከሚመነጨው የቆሻሻ ባህርይ አኳያ ኃይል ከማመንጨት ቆሻሻ ለማቃጠል ከፍተኛ ኃይል የሚያስፈልገው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

እንደ በባለሙያው ማብራሪያ ከሆነ፣ የረጲ ኃይል ማመንጫ ውጤታማነት ባደጉት አገሮች እንጂ እንደ ኢትዮጵያ ባሉት ውስጥ ብዙም የሚያዋጣ አይደለም፡፡ ምክንያታቸውን ሲጠቅሱም፣ በኢትዮጵያ የሚመነጨው አብዛኛው ቆሻሻ ተፈጥሯዊ (ኦርጋኒክ) በመሆኑ ከፍተኛ እርጥበት ያዘለ ነው፡፡ ይህንን እርጥበት ከቆሻሻው ለማውጣትና ለማድረቅ ብቻ የሚጠይቀው ኃይል ከፍተኛ በመሆኑ፣ ከቆሻሻው ይመነጫል የተባለው የኃይል መጠን ቆሻሻውን ለማድረቅ ከሚያስፈልገው አኳያ ሲታይ ‹‹ፕሮጀክቱን ዋጋ ቢስ›› ያሰኘዋል ብለውታል፡፡ በሩሲያም ሆነ በአፍሪካ በአብዛኛው የሚመነጨው ቆሻሻ ከፍተኛ እርጥት የሚታይበት ኦርጋኒክ በመሆኑ፣ ቆሻሻን በማቃጠል ኃይል ማመንጨት የሚለው አካሄድ አዋጭ አይደለም ብለዋል፡፡

የረጲ ኃይል ማመንጫ ከመነሻው 50 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭ ቢነገርም፣ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱ በተገለጸበት ወቅት ግን 25 ሜጋ ዋት ኃይል ብቻ ነበር የሚያመነጨው፡፡ ይህም በካምብሪጅ ኢንዱስትሪስና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከል አለመግባባት መፍጠሩ አይዘነጋም፡፡ ይሁን እንጂ 25 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ተስኖት ሥራ እንዲያቆም መደረጉን መዘገቡ ይታወሳል፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስተዳደር ጉዳዩን በድጋሚ በመመልከት ከተቋራጩ ካምብሪጅ ኢንዱስትሪስ ጋር ዳግም በመደራደር፣ ማመንጫው ወደ ሥራ እንዲገባ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኃይል ማመንጫው በትክክል ምን ያህል ያመነጫል በሚለው ላይም ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ከተገነባ ከሁለት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የሰንዳፋ የቆሻሻ ማከማቻና ማቀነባበሪያ ጣቢያ፣ በድጋሚ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር የሚችልበት እንቅስቃሴ መጀመሩም ታውቋል፡፡

በአሜሪካ ኤምባሲ ጋባዥነት ሰሞኑን አዲስ አበባ የሰነበቱት ሳሃዳት ሁሴን (ዶ/ር)፣ ከፖለቲካው ውጪ ባለው የቴክኒክ ጉዳይ ከታየ ሰንዳፋ የተገነባው የቆሻሻ ማቀነባበሪያ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ ሳያሳድር አገልግሎት መስጠት ይችላል ብለዋል፡፡ የሰንዳፋ ቆሻሻ ማጠራቀሚያና ማቀነባበሪያ ጣቢያ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የጠየቀና በ138 ሔክታር መሬት ላይ የተገነባ ነው፡፡ ይሁንና ሥራ በጀመረ በሦስት ወራት ውስጥ በፖለቲካ ምክንያት እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል፡፡ ይህ ይባል እንጂ ከአካባቢው የተፈናቀሉ ገበሬዎች ተመጣጣኝ ካሳ እንዳልተከፈላቸውም ሲገልጹ እንደነበር ይታወቃል፡፡ መንግሥት በበኩሉ ለተፈናቀሉት ገበሬዎች ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ መክፈሉን ሲናገር ነበር፡፡

የሰንዳፋን የቆሻሻ ማከማቻ ጣቢያን የቴክኒክ ይዘቶች የገመገሙትና ከአራት ዓመታት በፊትም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአማካሪነት የዲዛይንና የቦታ ዝግጅት ሥራዎች ላይ የተሳተፉት ባለሙያው፣ ጣቢያው በሰንዳፋ ነዋሪዎችና በአካባቢ ላይ ተፅዕኖ ሳያሳድር፣ ምንም ዓይነት ሽታም ሆነ የማቃጠል ሒደቱ ወደ ከባቢ አየር ሳይለቀቅ ታምቆ የሚቀነባበርበት ቴክኒካዊ አካሄዶች እንዳሉ አብራርተዋል፡፡

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተገኙት በቆሼና በሰንዳፋ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጣቢያዎች ላይ ጉብኝት ለማድረግና ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ የመሥራት ተግባራትን ለማስኬድ እንደሆነ የገለጹት ባለሙያው ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና ከሌሎች ኃላፊዎች ጋር መነጋገራቸውን፣ የከተማው አስተዳደርም በሰንዳፋ ጣቢያ የተጨበጠ ቴክኒካዊ ማስረጃ እንዲቀርብለት መጠየቁንና እሳቸውም ካካሄዱት ግምገማ በመነሳት ሪፖርት ለማቅረብ እየተዘጋጁ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ በተጓዳኝ የረጲ ቆሻሻ መጣያ አገልግሎት መስጠት ከማይችልበት ደረጃ ከማለፉም ባሻገር፣ የቆሻሻ መጣያው ላይ የመደርመስ አደጋ መጋረጡንና በማንኛውም ጊዜ ሊከሰት የሚችል አደጋ እንዳለም አስጠንቅቀዋል፡፡ ቆሻሻ መጣያውን በጎበኙበት ወቅት ሰፊ ስንጥቅ መመልከታቸውን ገልጸው፣ ከስንጥቁ በተጨማሪ የቆሻሻው እርጥበት ከፍተኛ መደርመስ ሊያስከትል እንደሚችል ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት በተከሰተው የቆሻሻ መደርስ 72 ሰዎች ለሕልፈት ሲዳረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩም ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️የሚመለከተው አካል #በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ያለውን ሁኔታ በትኩረት እንዲከታተለው የተቋሙ ተማሪዎች ጥሪ አስተላልፈዋል።

@tsegabwolde @tivahethiopia
ከሌላው መማር ይበጀናል!!

ስቃይ፣ ሞት፣ ሰቆቃ፣ ረሀብ፣ ስደት፣ መከራ እኛ ላይ እስኪደርስ አንጠብቅ። ከሌሎች መማር ብልህነት ነው። ዛሬ ሰላም በእጃችን ናት ዋጋ ሰጥተን እንጠብቃት ካልሆነ ግን የኛም መጨረሻ ወደማያባራው የእርስ በእርስ ግጭት መግባት ነው።

መስዳደቡን ትተን እንዋደድ፤ ተንኮሉን ትተን እንፋቀር፤ መጠላላቱን ትተን እንተሳሰብ! ያለችን ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ናት!

ሁሌም ቅድሚያ ለሰላም እንስጥ። ከልዩነቶቻችን ይልቅ አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ እናተኩር። መከራው ከመጣ ማናችንም #አናመልጥም። ዛሬ በሰላም ወጥተን መግባት ችለናል፤ ኔትዎርኩም አልተቋረጠም፤ ውሀውም አልጠፋም፤ መብራቱም አልተቆረጠም ያልኳቸው ነገሮች ዛሬ ላይ ሆነን ስናስባቸው ተራ ነገር ይመስሉናል፤ ነገ ሀገር ሲተራመስ ሁሉንም #ስናጣ ምነው ያን ጌዜ ስለሰላም አጥብቄ በሰበኩ፤ ምነው ስለፍቅር በሰበኩ እንላለን። ሀገሪቱ ስትተራመስ ፀፀቱ አያስተኛንም።

ሰላም ሰላም ብቻ በሉ!
ሰላም ሲኖር መለወጥ ይቻላል!
ዱላውን ጣሉት፤ ለስራ ተነሱ!
አትርሱ ዛሬም ኢትዮጵያ ብዙ ልጆቿ ተርበው ውለው፤ ተርበው የሚያድሩባት ምስኪን ሀገር ናት!

~ፀጋአብ ወልዴ ኢትዮጵያ~
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስሙኝማ!

እዚህች ሀገር ውስጥ የእርስ በእርስ ግጭት እሳት ቢለኮስ እሳቱ ቀድሞ አፈፍ የሚያደርገው ምስኪኑን ድሀውን ህዝብ ነው። ያለውማ ኮሽ ሲል የሚሄድበት አለው! ችግር ቢፈጠር መሸሺያ እና መጠጊያ አለው! ...የችግሩ ተጋፋጮች #እኛ ነን! ስለሆነም ጥዋት ማታ ስለሰላም፣ ስለፍቅር፣ ስለአንድነት እናስብ። ማንም እንዲያታልለን ልንፈቅድለት አይገባም። እኛ ከኢትዮጵያ ውጪ ምንም ሀብት የሌለን ሰዎች በሰላማችን ጉዳይ ከማንም ጋር ልንደራደር አይገባም። የምንወዳቸውን ሰዎች ስንከተልም ከምንም ነገር በፊት #ለሰላም የሚሰጡትን ቦታ ለይተን ልናውቅ ይገባል።

~ፀጋአብ ወልዴ ኢትዮጵያ~
@tsegabwolde @tikvahethiopia