TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ሶስት የሚኒስትርነት ሹመቶችን ሰጡ፦

- ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ [የትምህርት ሚኒስትር]

- አቶ መላኩ አለበል [የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር]

- ዶ/ር አብርሃም በላይ [የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር]

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለሦስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ወደ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች አቅንተዋል።

- ዶ/ር ዐቢይ በአቡዳቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼህ አብደላ ቢን ዛይድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

- ጠ/ሚ ዶ/ር በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ የተለያዩ አገራት ከተወጣጡ 300 የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በዱባይ ውይይት አካሂደዋል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድም ሰው የለም!

በአፍሪካ እስከ የካቲት 6 ቀን 2012 ከቀኑ 8 ሰዓት ድረስ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድም ሰው አለመኖሩን በአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማእከል (CDC) ዳይሬክተር ዶ/ር ጆን ንኬንጋሶንግ ተናግረዋል። ዳይሬክተሩ ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በአፍሪካ እስከ የካቲት 6 ቀን 2012 ከቀኑ 8 ሰዓት ድረስ በኮሮና ቫይረስ የተረጠሩ 51 ሰዎች እንደነበሩ ተናግረው፣ ሁሉም ከቫረሱ ነፃ መሆናቸው በምርመራ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ መንስኤ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ የውኃ ድብ ወይም የሌሊት ወፍ ሊሆን ይችላል ከማለት ውጭ በትክክል መንስኤው እስካሁን አለመታወቁን ጠቁመዋል፡፡

#EBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ህግን በተከተለ መልኩ እልባት እንዲያገኙ ይደረጋል" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

የኢህአዴግ የጥልቅ ተኃድሶ ግምገማ በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱ የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሉና አብዛኞቹ የትግራይ ክልል ተወላጆች መሆናቸውን በማስታወስ ጉዳያቸው በእርቅ እና በይቅርታ እንዲታይ የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ጠቅላይ ሚንስትሩም ከዚህ ቀደም በተለያየ ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ህግን በተከተለ መልኩ እልባት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ ወንጀለኝነትን ከብሄር ጋር ማያያዝ አይገባም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ማንኛውም ሰው በሰራው ወንጀል በህግ ይዳኛል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከስልጤ ዞን ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመወያየት ወራቤ ገብተዋል፡፡

ከሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ውይይቱ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በውይይቱም የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ትኩረት ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#PMOEthiopia #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢትዮጵያ መንግስት ለ60 ጉዳያቸውን በህግ ሲከታተሉ ለነበሩ ተጠርጣሪዎች ምህረት ማድረጉን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክረተሪ አቶ ንጉሱ፦

"መንግስት በቻይነት እና በሆደ ሰፊነት የተለያዩ ጥያቄዎች በመኖራቸው እና ትምህርት ስለተወሰደበት ለ60 ዜጎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ወስኗል።"

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምህረት የተደረገላቸው 60 ዜጎች ክሳቸው የተቋረጠበትን የሕግ አግባብ እና የስም ዝርዝራቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ነገ ዝርዝር መረጃን ይሰጣል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

"በጊንጪ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ካምፕ ላይ የቦንብ ጥቃት ደርሷል፤ የከፋ ጉዳት ግን አላደረሰም" - ፖሊስ

በትናንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ጊንጪ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ካምፕ ላይ የቦንብ ጥቃት ደርሷል።

በከተማው ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት በደረሰው በዚህ ጥቃት በወቅቱ በስራ ላይ በነበሩ ሁለት የፖሊስ አባላት ላይ በጭስ የመታፈን መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በቀር የከፋ አደጋ አለመድረሱን የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ገልፀዋል።

ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ ጌታቸው በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

በጥቃቱ ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ማንነት እስካሁን በተደረገው ምርመራ አለመታወቁን ተናግረዋል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በቢሾፍቱ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በዛሬው ዕለት 106 ለሚሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች ሹመት እንደሚሰጥ ታውቋል።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት ላለፉት 6 ወራት በስልጠና ላይ የቆዩ የአየር ኃይል ወታደራዊ ፖሊስ አባላት ምረቃ እንደሚኖር ተገልጿል። የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ሹመቱን እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ በስፍራው ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባለፉት 6 ወራት በተቋሙ ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞችም ሽልማት ይበረከታል ነው የተባለው።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GAMBELA

በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሄረሰብ ዞን በቀበሌ ሊቀመንበር መገደል ምክንያት የተቀሰቀሰ ግጭት ለ12 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ተነገረ።

ቀስ በቀስ ወደ ጎሳ ግጭት የቀየረው በዚህ ሁከት 21 ሰዎች ሲቆስሉ፣ 400 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከ300 በላይ የቤት እንስሳቶችም ተዘርፈዋል። በተጨማሪ የግጭቱ ሰለባ የሆኑ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች [7 ሺህ ሰዎች] ተፈናቅለዋል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia