TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መሪዎቹ ተሸኙ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ለሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ መሀመድ ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን በመገኘት ሽኝት አደረጉላቸው፡፡ መሪዎቹን የአማራ ክልል ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን በመገኘት ሸኝተዋቸዋል፡፡

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቦንጋ⬆️

"ፀግሽ እንደምታየው በዞኑ ካሉ ወረዳዎች ህዝቡ እየመጣ ተቃውሞውን እያስተጋባ ነው። የከተማው ህዝብም ንፍሮ ቀቅሎ ለሰልፈኞች በማቅረብ ድጋፍ እያደረገ ነው። ደስ የሚለው ግን ከስራና ከሰው መጉላላት ውጪ እስካሁን በንብረትም ሆነ በሰው ላይ የደረሰ #አደጋ የለም። ጥያቄያቸው፦
1, የቡና መገኛነታችን ይከበር
2, ክልል የመሆን ጥያቄያችን ይመለስ
3, የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት ችላ ብሎናል
4, ዞኑን ወክለው በክልል እና በተወካዮች ም/ቤት ያሉት አመራሮች የህዝቡን ጥያቄ እያስተጋቡ አይደለምና....ሌሎችም ናቸው። መነሻው ግን አንደኛው ነው። esa ከቦንጋ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር❤️

ቆይታ ከቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር #አብይ_አህመድ ጋር ባህር ዳር!

ፎቶ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ፈረጃ ቶነር! የተለያዩ የኘሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ቀለምች በተሻለ ዋጋ አሉን። በ+251911276145 ይደውሉ
Forwarded from Abraham
🔊ከBLU trading
.
📲LGV10.....5,500ብር
.
እንዲሁም
💻 Laptops ከ 7500ብር ጀመሮ
📱ኦርጅናል SAMSUNG/IPHONE ስልኮች
🎸YAMAHA box Guitar ....4,000Br
.
🏢 አድራሻ ➠ Bole
.
☎️ ስልክ ➠ 0942180023
.
ለበለጠ መረጃ 👉 @Blumarket
ከፋ ዞን‼️

በካፋ ዞን ስለ ቡና መገኛነት በድረ-ገጽ በተላለፈ መረጃ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ወደ ነበረበት #ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በካፋ ዞን የተፈጠረው አለመረጋጋት ከቡና መገኛነት ጋር በተያያዘ በድረ-ገጾች በተላለፈ መረጃ አማካኝነት ነው።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፍረንስ በቅርቡ ለማዘጋጀት በሚያደርገው ሂደት በድረ-ገጹ የተላለፈው መረጃ የካፋን ወጣቶችና ህዝቡን አስቆጥቶ በአካባቢው አለመረጋጋት ተፈጥሯል።

“የቡና ባለቤትነት ጥያቄን በሚመለከትም የባለቤትን ጉዳይን የሚመራና እውቅና የሚሰጥ ራሱን የቻለ ተቋም በሃገር ደረጃ ያለ በመሆኑ ጥያቄው አሰራሩን ተከትሎ ምላሽ ያገኛል”ብለዋል፡፡

ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ያቀረበው የካፋ ህዝብና ወጣት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሲገታ የሚያሳድረውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና በመረዳት የተዘጉ መንገዶችን እንዲከፍት ጠይቀዋል፡፡

በአካባቢው ያሉ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ይህንን በማስተባበርና ወጣቱም ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመተባበር የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት እንዲመልስ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችም አሁን ላይ ወደ ሰላም እየተመለሱ መሆናቸውን ገልጸው የአብዛኛዎቹ መንስኤም ከመዋቅር ጋር የተያያዙ እንደነበሩ ጠቁመዋል።

በቅርቡ የክልሉ ምክር ቤት 44 ወረዳዎችንና 3 ዞኖችን በአዲስ መልክ ማዋቀሩን ተከትሎ አዳዲስ ፍላጎቶች የፈጠሩት ስሜትና የሚጠበቅ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

“ችግሮቹን በቀጣይ ከህዝቡ ጋር በሚደረግ ጥልቅ ውይይት መስመር የሚይዙ ናቸው” በማለት  በየደረጃው ያለ አመራር ከህዝቡ ጋር በሚያደርጋቸው ሰፊ የውይይት መድረኮች እንደሚኖሩ ገልጸው በዚህም የሰላም ግንባታ ስራው እንደሚጠናከር ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደብረ ማርቆስና ፍኖተ ሰላም ነገ #ሰላማዊ ሰልፎች ይካሄዳሉ፡፡ በደብረ ማርቆስ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች በሚካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች የጣና ሀይቅ እና ላሊበላ ጉዳዮች ዋነኛ መሪ ሀሳቦች ናቸው፡፡ ሰልፎቹ በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፈቃድ ያገኙ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvjethiopia
ባህር ዳር🔝የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሱማሊያ መሪዎች ዛሬ የአማራ ክልል ምክር ቤት ሕንፃን ጎብኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia