TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አርሲ ዩኒቨርሲቲ⬆️የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ጥቅምት 7-8 እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወቂያ⬆️የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የነባር እና የአዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን እንደሚከተለው ነው፦

ነባር ተማሪዎች ጥቅምት 1 እና 2
አዲስ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6

© www.aastu.edu.et
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል⬇️

በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት ከመደገፍና ከማሳደግ ውጪ ሌላ #አማራጭ እንደሌለ የደኢህዴን ሊቀ መንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል ገለፁ።

ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል 10ኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ድርጅታዊ ጉባዔ #መጠናቀቅን ተከትሎ ለጉባኤተኛው የማጠቃለያ መልእክት አስተላልፈዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪያት በማጠቃለያ ንግግራቸው፥ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በለውጥ ሂደት ላይ መሆኗን ገልፀው፤ የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና ጉባዔተኛው ለውጡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስራት አንዳለባቸው ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ ለውጥ #ለማደናቀፍ ሌት ተቀን የሚሰሩ ሀይሎች እንዳሉ ሊቀመንበሯ ገልፀዋል።

እነዚህ ሀይሎች 10ኛው የደኢህዴን ጉባዔ እንዳይሳካም ሲንቀሳቀሱ ነበር ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪያት፤ ከሀዋሳ ውጪ በህዝቦች መካከል #ግጭት ለመፍጠር ገንዘብ ተመድቦላቸው #ሲንቀሳቀሱ እንደነበረ ከክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በተሰራ ስራ ለማወቅ መቻሉን አንስተዋል።

የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና ጉባዔተኛው ይህንን በመገንዘብ እነዚህን የጥፋት ሀይሎች በንቃት መጠበቅና ማጋለጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የለውጥ ሂደት ከመደገፍና ካማሳደግ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም ያሉት ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት፥ ከዚህ ውጨ ያለው አማራጭ #የጥፋት አማራጭ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ስለዚህ የለውጥ ጉዞውን በማሳከት ሂደት የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና የጉባኤተኛው ሚና አጅግ የላቀ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ከነገ ጀምሮ #በሀዋሳ ከተማ የሚካሄደው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በማድረግ እንዲሁም የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ርብርብ መቀጠል ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።

በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የደኢህዴን ጉባዔተኞች ልክ በደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ያደረጉትን የነቃ ተሳትፎ፣ ዴሞክራሲያዊ ሂደትና ሰላማዊ ሁኔታን እንዲያስቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት አክለውም፥ 10ኛው የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ በዚህ መልኩ የተሳካ ሆኖ በመጠናቀቁም እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።

ጉባዔው የተሳካ እንዲሆን የሀዋሳ ከተማ እና የሲዳማ ዞን እንዲሁም የልግ ባለሀብቶች ላደረጉልት አቀባበል እንዲሁም የኢህአዴግ ጉባዔን ለማስተናገድ እያደረጉ ላለው ዝግጅት ለአመራሩ እና ለህዝቦች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ መረጃ‼️

(ሼር ይደረግ)

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምዕራብ ወለጋ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ከ70 ሺህ የማያንሱ ዜጎቻችንን አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

ከብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር ባደረግነው ውይይት መሰረት ለኦሮሚያ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ በአፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታዎች ለማድረስ ተስማምተናል።

በዚህም መሰረት በአዲስ አበባና በአካባቢው የምትኖሩ ለሰብዓዊ እርዳታ ገር ልብ ያላችሁ ጽኑ ኢትዮጵያዊያን የተለመደው ርብርባችሁ ይጠበቃል።

#የማይበላሹ_ምግቦች

መኮረኒ
ሩዝ
ፉርኖ ዱቄት
ዘይት
ሴሪፋም /ፋፋ/
ብስኩት /ጋቤጣ/

#የንጽህና_ቁሳቁሶች

ሳሙና
ኦሞ
ሳኒታይዘር
የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

#አልባሳት

ብርድ ልብስ
ነጠላ ጫማ

የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን)
እነዚህን ቁሳቁሶች ብቻ ለግዜው የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ እኛ በምናዘጋጀው ግዜያዊ መረከቢያ ቦታ ታደርሱልን ዘንድ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

ቦታው #የሀገር_ፍቅር_ቴአትር ቅጥር ግቢ (ሰኞና ማክሰኞ መስከረም 28 እና 29 ብቻ) ጫካ ያደሩ ህፃናትና እናቶች አረጋውያንና ደካሞች ከምንም በላይ "የኢትዮጵያዊያን ያለህ!" እያሉ ነው።

#ሰብዓዊነት_ይቅደም !!
(ከአንድ ግዜ በላይ ሼር በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ)

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#updateሀዋሳ ዶ/ር ዐብይ⬇️

የኢህአዴግ ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ለተሳተፍ #ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል።

11ኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ድርጅታዊ ጉባዔ “ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ከነገ ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል።

በድርጅታዊ ጉባዔው ላይ ለመሳተፍም የኢህአዴግ ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል።

በተጨማሪም የኢህአዴግ ምክትል ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ድርጅታዊ ጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሀዋሳ ደርሰዋል።

እንዲሁም የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ተሳታፊዎችም ሃዋሳ ከተማ መድረሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።

11ኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ነገ ጠዋት ላይ በሀዋሳ ከተማ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት የባንክ ሂሳብ⬇️

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝና ከምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች #የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት የባንክ ሂሳብ ተከፈተ፡፡

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ ዞን እና በምስራቅ ወለጋ ዞን ስር በሚገኙ አጎራባች ወረዳዎች ውስጥ የፀጥታ ችግር መፈጠሩ ይታወሳል፡፡

በዚህም ምክንያት ከ20 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉና ከ70 ሺ በላይ ዜጎች ከንብረትና ቄያቸው መፈናቀላቸው ይነገራል፡፡

እነዚህን የተፈናቀሉ ዜጎች ለመርዳት የባንክ ሂሳብ መከፈቱን ኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በድረ ገፁ አስፍሯል፡፡

ድጋፍ ለማድረግም በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ 937719፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000259030138፣ በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000072131111 መጠቀም እንደሚቻል ተነግሯል፡፡

ከአራት ቀናት በላይ በእግራቸው በመጓዝ ነቀምቴ ከተማ የገቡት ተፈናቃዮች በአሁኑ ሰዓት በመምህራን፣ በቴክኒክና ሙያ፣ በነርሲንግ ኮሌጆችና በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠልለዋል፡፡

#የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች የምግብና አልባሳት #ድጋፍ እያደረጉላቸው እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር FM 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ መረጃ‼️

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝና ከምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች #የተፈናቀሉ ዜጎችን #በገንዘብ ለመርዳት የምትፈልጉ፦

በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ
937719

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000259030138

በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ
1000072131111

#ሼር

ምንጭ፦ ኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከነቀምት⬆️

"ፀግሽ የ07 እናቶች በዚህ መልኩ ለተፈናቀሉ ወንድምና እህቶቻቸው እንዲሁም ልጆቻቸው ምግብ ሲያዘጋጁ ነበር። #እውነተኛ እናትነታቸውን አሳይተዋል! ቦንሳ ከነቀምት"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም የነባር እና አዲስ ተማሪዎች መግቢያ ቀናት ይፋ ተደርጓል ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነገው እለት #በሀዋሳ ከተማ በሚጀመረው11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የሚጠበቁ ጉዳዮች፦

▪️በነሐሴ ወር 2007 በመቀሌ ከተማ ተደርጎ በነበረው 10ኛ የኢህአዴግ ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎችን መሠረት በማድረግ ባለፉት ሦስት ዓመታት የተሠሩ ሥራዎች ሪፖርት ቀርበው ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በጥልቀት ከገመገመ በኋላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያሳይ እና ለ12ተኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የሚሆን ሰነድ እንደሚያዘጋጅ ይጠበቃል፡፡

▪️ሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲዎችና ድርጅቶች በቅርቡ ባካሄዷቸው ጉባኤዎች የመረጧቸውን አዳዲስ የማዕከላዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎቻቸውን በዚህ ጉባኤ በማሳተፍ አዲስ የኢህአዴግ ምክር ቤት ይመሠርታሉ፡፡

▪️ወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ በጥልቀት ይገመገማል፤ ለውጡን ለማስቀጠል አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ፤ የቀጣይ አቅጣጫዎች ይመላከታሉ፡፡

▪️ባለፈው መጋቢት ወር ጥልቅ ተሐድሶውን ተከትሎ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና በተደረገውን የአመራር ለውጥ የተሠሩ ተግባራት ይገመገማሉ፡፡

▪️አዲስ የኢህአዴግ ምክር ቤት መመሥረቱን ተከትሎ የድርጅቱን ሊቀ-መንበርና ምክትል ሊቀ-መንበር #ይመረጣል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች ከአራቱም ብሔራዊ ድርጅቶች የተወከሉ ከእያንዳንዳቸው 250 በአጠቃላይ 1000 በቀጥታ በምርጫውና በውሳኔዎች ዙርያ በድምጽ የሚሳተፉ ይሆናሉ፡፡

በልዩ ሁኔታ የ11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ተሳታፊዎች በታዛቢነት የሚገኙ ግን ድምጽ (የማይሰጡ ተሳታፊዎች፡-

-ሴቶችና ወጣቶች
-አጋር ድርጅቶች
-የተለያዮ የኅብረተሰብ ክፍሎች
-ማኅበራት
-ፌዴሬሽኖች
-ዩኒቨርሲቲዎች
-የፌዴራል ተቋማት ኃላፊዎች
-ልማታዊ ባለሀብቶች

የ11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ መክፈቻ ላይ የሚሳተፉ፦

• የሠራዊት አመራሮች
• አርቲስቶች
• ስፖርተኞች
• ታዋቂ ግለሰቦች
• ተፎካከሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጥቅሉ አንድ ሺህ 900 ተሳታፊዎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ጌታቸው አሰፋ‼️

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ በሀዋሳ ያደርጋል። አራቱ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶችም ከድርጅታዊ ጉባኤው በፊት የፓርቲዎቻቸውን ሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀ መንበር፣ የማዕከላዊ እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን አካሂደዋል።

የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) መጠሪያውን ወደ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በተመሳሳይ መልኩ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ደግሞ ወደ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) መቀየራቸው ይታወሳል። ሁለቱ ፓርቲዎች ከስማቸው ባሻገር የአርማ ለውጥም አድርገዋል። በሌላ በኩል ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የቀድሞ ስማቸውን እና አርማቸውን ይዘው ቀጥለዋል።

ኦዴፓ፣ አዴፓ እና ዴኢህዴን በርካታ የቀድሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎቻቸውን በአዲስ እና ወጣት አባሎች ተክተዋል። ይህ በእንዲህ
እንዳለ ህውሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አድርጎ የመረጣቸው ግለሰቦች ነባር እና ከሞላ ጎደል የድርጅቱ ታጋዮች መሆናቸው አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል።

በተለይ ደግሞ የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ #ጌታቸው_አሰፋ ከዐሥራ አንዱ የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ ሆነው መመረጣቸው ብዙዎች ህወሓት #ከለውጡ ራሱን ገሽሽ እያደረገ ስለመሆኑ እንደ አንድ ማሳያ አድርገው ወስደውታል።

ለመኾኑ አቶ ጌታቸው አሰፋ ወደ ሥራ አስፈጻሚ መምጣታቸው አሁን ባለው የለውጥ አውድ ምን ፖለቲካዊ ትርጉም ይሰጣል?

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለቢቢሲ የሰጡት የህወሓት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የቀድሞ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን አቶ #ጌታቸው_ረዳን እንዲህ ብለዋል፦

''ጌታቸው አሰፋ #ጎበዝ መሪ መሆኑን አውቃለሁ። ጎበዝ #ኢህአዴግ መሆኑን አውቃለሁ። ጎበዝ #ህወሓት መሆኑን አውቃለሁ። ህወሓት ሲወስን በሚዲያ #ሃሜት ላይ ተመሥርቶ አይደለም የሚወስነው'' በማለት በቀድሞው የደኅንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ የሚቀርቡ ወቀሳዎችን አጣጥለዋል።

አቶ ጌታቸው ጨምረውም ''ይፋዊ መግለጫ ሳይኖር ሚዲያዎች ሃሜት ሲያወሩ ነበር። ሃሜት ላይ ተወስነን ውሳኔ የምናስተላልፍ ቢሆን ኖሮ ሃገር #ይጠፋል። ክስ ስለመመስረቱም የማውቀው ነገር የለም። አቶ ጌታቸው አሰፋን ፈልጎ ህውሓት ጋር የመጣ አካል የለም።'' በማለት አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ክስ አለመመሥረቱን አመላክተዋል።

አቶ ጌታቸው አያይዘው እንደሚሉት ከሆነ አቶ ጌታቸው አሰፋ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆኖ የመመረጥ ፍላጎት አልነበራቸውም።

''ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ መግባትም አልፈለገም፤ ሲሪየስሊ [አጥብቆ] ነው የተከራከረው። ጉባኤው ግን ከማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እንዲገባ ወሰነ። ማዕከላዊ ኮሚቴው ደግሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ውስጥ መግባት አለበት ብሎ ወሰነ።'' ይላሉ አቶ ጌታቸው ረዳ።

"አቶ ጌታቸው አሰፋ በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ወደ ሀዋሳ ይሄዳሉ ወይ?" ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ አቶ ጌታቸው ረዳ ሲመልሱ ''የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በጉባኤው እንዲሳተፍ ይጠበቃል። እንደማንኛው የኮሚቴ አባል ሀዋሳ ላይ ልታይዋቸው ትችላላችሁ።

እንደማንኛውም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ተሳትፎ ማድረግ ስላለብን አንዳንዶቻችን ያው መንገድ ላይ ነን። ለምሳሌ አውሮፕላን ካመለጠኝ ልቀር እችላለሁ'' ብለዋል።

ይህ አገላለጽ 'አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይገኙ ይችላሉ' የሚለውን ያመላክት እንደሆነ ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ፣"እኔ የእያንዳንዱ ሰው ስኬጁል አላወጣም። ሁላችንም ተበትነን ነው ወደ ሀዋሳ እየሄድን ያለነው፤ ጌታቸውም በራሱ ጊዜ ስኬጁሉን አሬንጅ ያደርጋል፤ ካገኘሁት እነግራችኋለሁ" ሲሉ በቀልድ የታጀበ ምላሽ ሰጥተዋል።

ነገ በሚጀመረው የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ማን ሊሆን ይችላል ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ''አሁን ያሉት ሊቀ መንበር ላለፉት 5 ወይም 6 ወራት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። እስካሁን የሠሩት ሥራ ተገምግሞ ለውጥ ማድረግ ያስፈልገናል ወይስ አያስፈልገንም የሚለው የጉባኤው ውሳኔ ነው የሚሆነው'' በማለት መልሰዋል።

ህወሓት ማንን በእጩነት ለማቅረብ እንደተሰናዳ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ፓርቲዎች እንደማይመርጡ አስረድተዋል። ''ህወሓት፣ ብአዴን
ወይም ኦህዴድ ዕጩዎችን አያቀርቡም። ፓርቲዎች አይደሉም ዕጩዎችን የሚጠቁሙት። ከ180ዎቹ የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ግለሰቦችን ለሊቀ መንበርነት ለጉባኤው ጥቆማዎችን ይሰጣሉ። ከዚያም ምርጫ ይካሄዳል። ድምጽ ያገኘ ያሸንፋል።'' ብለዋል።

በግንባሩ ጉባኤ ላይ ሊነሱ የሚችሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፤ ''የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አፈጻጸም ላይ መቀዛቀዝ ይታያል።

ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት እሱን እንዴት አድርገን ነው በፍጥነት የምናስቀጥለው የሚለው ትልቁ አጀንዳ ነው። ወደ ሃገር እንዲገቡ የተደረጉ ተፎካካሪ፣ ተቃዋሚ የሚባሉ ፓርቲዎች ወደ ሃገር ከገቡ በኋላ አንዳንዱ 'አሸንፌ ነው የመጣሁት' ይላል። ሌላኛው 'ወደሽ ሳይሆን ተገደሽ ነው የተቀበልሺኝ' ይላል። ይህ ዓይነት ስሜት የሚፈጥረው #የሰላም እና #የመረጋጋት ዝብርቅርቅ አለ። ይህን ለመሰሉ ጉዳዮች ጉባኤው #ምላሽ ይሰጣል። ይህ የሁላችንም አጀንዳ ነው'' ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንበተንም
አንጠፋም
አንጨራረስም
#ስሜታዊነት ረገብ ሲልልን ዳግም አንድ እንሆናለን!

አዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ETV ZENA Live! የኢህአዴግ 11ኛ ጉባኤ የመክፈቻ ስነስርዓት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia