TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጊፋታ⬆️

የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታ!

የወላይታን ብሔር ከሀገራችንና ከደቡብ ክልል ብሔሮችና ብሔረሰቦች በተለየ መልኩ የሚገለጽባቸው በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ያሉት ሲሆን ከብሔሩ የማይዳስሱ #ሀብቶች መካከል የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል #ጊፋታ አንዱ ነው፡፡

ጊፋታ በብሄሩ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የብሔሩ ማንነት መገለጫ የሆነ #የአሮጌው ዓመት ማብቅያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡

ጊፋታ ማለት ባይራ(ታላቅ)፣ መጀመሪያ እንደ ማለት ሲሆን በሌላ በኩል ጊፋታ ማለት መሻገር ማለት ነው፡፡ ይህም ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ #ብርሃን መሻገር የሚለውን ይገልጻል፡፡ የወላይታ ብሔር የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ(ካሌንደር) ያለው ሲሆን በወላይታ የዘመን አቆጣጠር ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡

ወላይታዎች አስራ አንድ ወራት በስራ ካሳለፉ በኋላ የመጨረሻውን አንድ ወር ለበዓሉ ያውሉታል፡፡ 15 ቀን በበዓሉ ዝግጅት፣ አስራ አምስቱን ቀን ደግሞ በመዝናናትና በመጫወት ያሳልፋሉ፡፡

መስከረም ወር በገባ ከ14-20 መካከል በሚውለው እሁድ ዕለት አዲሱን ዓመት
ይቀበሉታል፡፡ በየዓመቱ ከመስከረም 14-20 ባሉት ቀናት መካከል የሚውለው እሁድ እለት የአዲስ ዓመት ቀን ይሆናል፡፡ ስሙም ሹሃ ወጋ /የእርድ እሁድ/ ይባላል፡፡
.
.
.
ጊፋታ የይቅርታ፤ የፍቅር እና የሰላም በዓል ነው!

ምንጭ፦ የወላይታ ዞን ባህል፣ ቱሪዝም እና መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በኦሮሚያ ክልል #አሰላ ከተማ ግጭት ሊፈጠር ነው በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሐሰት ነው ነዋሪዎች አትስጉ ሲል የአሰላ ከተማ ፖሊስ ተናግሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደብረ ታቦር❤️

"ሰላም ፀግሽ የደብረ ታቦር ከተማ የእስልምና እምነት ተከታዮች ነገ ለሚከበረው የመስቀል ደመራ በአል የሚከበርበትን ቴወድሮስ አደባባይን እንደምታየው አፅድተዋል። በጣም እናመሰግናለን! ሀይሌ ከደብረ ታቦር"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
📌የዩኒቨርሲቲ ምደባን በተመለከተ

የ2011 ዓ.ም የአዲስ ተማሪዎች ምደባ ይፋ የሚሆንበትን ቀን ለማወቅ ወደ ኤጀንሲው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ባደርግም ሊሳካልኝ አልቻለም። በጉዳዩ ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ለመውሰድ ብደውልም የተሰጠኝ መልስ"እኛ ትክክለኛውን ቀን አናውቀውም፥ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲን ጠይቅ" ብለውኛል።

ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረቴን ቀጥላለሁ። የኤጀንሲው ሰራተኞች በቻናላችን ውስጥ ካላችሁ ጥቆማ ልትሰጡን ትችላላችሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ⬆️

"ሀይ ፀግሽ የሀዋሳ ደ/ሰ/ቅ/ስላሴ ቤተክርስቲያን ዲያቆናት፣ መዘምራን እና ቀሳውስት በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ እየሄዱ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia