FBC (Fana Broadcasting Corporate)
198K subscribers
60.1K photos
737 videos
23 files
53.8K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
"ያለማሰለስ መሥራት ለስኬት ቁልፍ ነው" ይባላል። የኢትዮጵያ የደን ሽፋን የ#አረንጓዴዓሻራ ንቅናቄ ከተጀመረበት በ2011 ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማደግ የቻለው ባላሰለሰ ጽኑ ጥረት ነው።

በክረምቱ የችግኝ ሥራ መሪዎን ይከተሉ። አሻራዎን ይትከሉ።
ከ2011 እስከ 2016 ዓ.ም ምስሎች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
ባንኩ ዛሬ በልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ሸጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን አስታውቋል፡፡

ባንኩ ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም የተካሄደውን የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።

በዚህም ዛሬ በልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድን የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን አስታውቋል፡፡

በጨረታው 27 የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን÷ የዛሬው አማካይ ዋጋም የነገ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጠቋሚ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ መገለጹን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ÷ ተግባራዊ የተደረገው የባንክ ምንዛሪ ዋጋ ከትይዩ የገበያ ዋጋ ጋር ያለው ልዩነት መቀራረቡን የሚያሳይ ተጨባጭ ውጤት መገኘቱ አስደሳች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በክልሉ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 351 የንግድ ተቋማት ታሸጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉና ምርት በሸሸጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ እንዳሉት÷ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያን ተከትሎ በክልሉ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉና ምርት በሸሸጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ ተጀምሯል፡፡ ቢሮው ሰሞኑን ባደረገው…

https://www.fanabc.com/archives/256947
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ያለማሰለስ መሥራት ለስኬት ቁልፍ ነው"።

በክረምቱ የችግኝ ሥራ መሪዎን ይከተሉ። አሻራዎን ይትከሉ።

#አረንጓዴዓሻራ

#PMOEthiopia
ግለሰብን በማስፈራራትና በመደብደብ ንብረት ወስደዋል ተብለው የተጠረጠሩ የፖሊስ አባላት ፍ/ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሌሊት ለወንጀል መከላከል ሥራ በተሰማሩበት ቦታ ግለሰብን አግተው በሽጉጥ አስፈራርተው ንብረት ወስደዋል ተብለው ስልጣንን ያለ አግባብ መገልገል ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት የፖሊስ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት÷ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የሐርቡ…

https://www.fanabc.com/archives/256968
እሁድ ሊካሄድ የነበረው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊታችን እሁድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ሊደረግ የነበረው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ተራዘመ፡፡

ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሊከናወን ታስቦ የነበረ ቢሆንም ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
Live stream finished (1 hour)
ጃክ ሞተርስ በቅርቡ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መገጣጠም ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ (ጃክ ሞተርስ) በቅርቡ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የመገጣጠም ሥራ ለመጀመር የሚያስችለውን ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከጃክ ሞተርስ እና ሃዩጃን ኢንዱስትሪ ፓርክ አመራሮች ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/256986
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለማልማት የጀመረችውን ጥረት እደግፋለሁ - ቻይና

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከሰው ኃይል ልማት በመጀመር የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለማልማት የጀመረችውን ጥረት እንደሚደግፍ የቻይና የኒውክሌር ኃይል ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በቤጂንግ የሚገኘውን የኒውክሌር ምርመር እና ሪአክተር ማዕከል እንዲሁም የቻይና የኒውክሌር ኃይል ባለስልጣንን ጎብኝተዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/256989
በ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ በ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል  ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም፡፡

ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ከ43 ላይ በተካሄደው 3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያን የወከሉት አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ዋለ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ሳይገቡ ቀርተዋል።

በውድድሩ ሳሙኤል ፍሬው 6ኛ፣ ጌትነት ዋለ 9ኛ ደረጃ ይዘው ሲያጠናቅቁ፥ ለሜቻ ግርማ በመውደቁ ምክንያት ውድድሩን ሳያጠናቅቅ ቀርቷል።