10 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ተመረቁ።

ባሳለፍነው ሳምንት ኦርቢት የኢኖቬሽን ማጎልበቻ ማዕከል (OIH) ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን 10 አዳዲስ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን አስመርቋል።

የተመረቁት ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶቹ በጤና፣ በትምህርትና አገልግሎት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን የቴክኖሎጂ መፍትሄ መስጠት ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው።

ኦርቢት የኢኖቬሽን ማጎልበቻ ማዕከል አዳዲስ ጀማሪ ድርጅቶችን ሲያስመርቅ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም 5 ድርጅቶችን አስመርቋል።

እንዴት ነው ድርጅቶቹ የሚመረጡት ?

- ለአንድ ወር በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ዘመቻ ይካሄዳል ፤ ጥሪ ይቀርባል።
- ጥሪውን ተከትሎ የሚያመለክቱ ጀማሪ ድርጅቶች ይጠራሉ።
- የተወሰነ ቁጥር ተመርጠው የሶስት ቀን ስልጠና ይሰጣቸዋል።
- ከስልጠናው በኃላ በሚያቀርቡት ፕረዘንቴሽን እንዲሁም አዋጭነታቸው እና ችግርን የማፍታት አቅማቸው ተገግምግሞ የተመረጡ ወደ 4 ወር ስልጠና ይገባሉ።
- የ4 ወሩ ስልጠና ብራንዲንግ፣ ማርኬቲንግ ስትራቴጂ ፣ ቢዝነስ ስትራቴጂ ... ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ጥልቅ እውቀት እንዲያገኙ ይደረጋል።
- ከስጠናው በኃላ ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣቸዋል።
- በመጨረሻም የኢንቬስተሮች ጋር የሚገናኙበት መድረክ ይመቻችላቸዋል።

እስካሁን 15 ጀማሪ ድርጅት ከአዲስ አበባ የወጡ ሲሆን በቀጣይ ስራውን በስፋት ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ እንደ ጎንደር፣ ባህርዳር ፣አዳማ፣ ሀዋሳ፣ ደሴ በመሳሰሉ ከተሞች ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ኦርቢት የኢኖቬሽን አሳውቆናል።

* ባለፈው ሳምንት ስለተመረቁት ጀማሪ ድርጅቶች ዝርዝር መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia