#Update

ሶማሊ ክልል በሚገኙ 78 ወረዳዎች ላይ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በሁለት ወራት ተኩል ጊዜ ውስጥ ከ146 ሺ በላይ ከብት፣ ግመልና ፍየሎች መሞታቸውን የሶማሊ ክልል አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ አስታውቋል።

በክልሉ ከሚገኙት 11 ዞኖች ውስጥ በዘጠኙ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና በሲቲ ዞን ውስጥ በሚገኙ 5 ወረዳዎች ውስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዕርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር ወደ 3.4 ሚሊዮን ከፍ እንዳለ ቢሮው መግለፁን ሪፖርተር ዘግቧል።

በክልሉ ውስጥ ከሚገኙት 11 ዞኖች ውስጥ ዘጠኙ ዝናብ ያገኙ የነበሩት ከቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል በተለይ በመኸርና በበልግ ወራት ነው፡፡

ይሁንና በ2013 ዓ/ም ከሚያዝያ- ሰኔ የቆየው የበልግ ወቅት የዘነበው ዝናብ ዝቅተኛ በመሆኑና አሁን እየተጠናቀቀ ባለው የመኸር ወቅት ሙሉ በሙሉ ባለመዝነቡ በክልሉ ውስጥ የተከሰተው ድርቅ 6 ወራት ሆኖታል፡፡

እነዚህ ዞኖች እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮፓውያን ወር ድረስ ማግኘት የነበረባቸውን ዝናብ ባለማግኘታቸውና ደረቅ የሆነው የበጋ ወቅት እየገባ በመሆኑ ድርቁ ይቀጥላል የሚል ሥጋት እንዳለ ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክንያት አሁን በተከሰተው ድርቅ 3.4 ሚሊዮን የደረሰው የዕርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር በትንሹ አራት ሚሊዮን ይደርሳል የሚል ግምት ተቀምጧል።

አሁን ላይ ያለው ድርቅ በተለይ በዳዋ፣አፋሌር፣ ሸበሌና ኮራይ ዞኖች ተፅዕኖው እንደከፋ የተገለጸ ሲሆን ድርቁን መቋቋም ያቃታቸውና አቅም ያላቸው ነዋሪዎች እንስሳቶቻቸውን በመኪና እየጫኑ ከ600 ኪ.ሜ በላይ በመጓዝ ወደ ጅግጅጋ አቅራቢያ መምጣታቸው ታውቋል፡፡

ይሁንና እንስሳቶቻቸው በድርቁ እጅጉን በመጎዳታቸው በጉዞ ላይ እያሉና ከመኪና ሲወርዱ ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል: telegra.ph/RE-12-19

@tikvahethiopia